#ማካካሻ። ፲ አለቃ መሳፍንት

 

"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
#ምዕራፍ ፲፰።
 
 
፲ አለቃ መሳፍንት ይመስለኛል ሥሙ። የጄኒራል ሳህረ መኮነን ጠባቂ የነበረ ወጣት ነው። እኔ #ታቅዶ የተመደበ ይመስለኛል። ከእሱ ይልቅ ለመታመን ሌሎች ተመሳሳይ ማዕረግ ያላቸው ነበሩ የወንዝ ልጆች ነበሩና። ጄኒራሉን ለመቅደም #ገዳዩ #ጎንደሬ መሆኑ የትወናውን ሁነት ያብራራል።
 
በሌላ በኩል አገዳደሉን ማን ይምራው ማን? በፍጹም እርግጠኛ የሚያደርግ ነገር በሰውኛ #ስሌታዊ አመክንዮውን ስለማይደፈር። ወላጅ እናቱ ክፍትፍት ባለ #ጉሮኖ ይኖራሉ። አሁን በምን ሁኔታ እንደሚገኙ አላውቅም።
 
የፍርድ ውሳኔው ተሻሽሎለታል። እግሩ እና ዓይኑ ግን #በድብደባ ብዛት እንደተጎዳ ሰምቻለሁኝ። ደብዳቢወቹ ማን ሊሆኑ እንደሚችሉ የፋክት መረጃ ማቅረብ ባይቻልም፤ በቀልን የጸነሱ፤ መበቀልን በእጥፍ ለመተግረብ የጭካኔ ረሃብተኞች እንደሚሆኑ ግን መገመት ይቻላል። ለኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ ልኳ አይደለም፤ ለእኛም አንመጣጠንም የምለውም ለዚህም ነው።
 
ህወሃትን ያህል የሴራ #ጉድጓድ ተሸክመህ፤ ሌላውን ቤርሙዳ ትርያንግሉን የማህበረ ኦነግን #ትብትብ አቅፈህ ይህ ብላቴና ግርማቸው የሚያስፈራውን መኮነን ደፍሮ ገደለ ለእኔ ብዙም ቅርብ ያልሆነ ሎጅክ ነው።
 
መሪነት በግርግር ጊዜ ያላጠናቸውን፤ ግን የገደፋቸውን ስርክራኪ ሁነቶችን እንዲህ ቅንጡ ሆቴሎችን ለመመረቅ ሰፊ ጊዜ ሲሰጥ ደግሞ #ተግ ብሎ እንደነዚህ ዓይነቶችን እጅ እና እግር አልቦሽ የሆነ የበቀል መገበሪያ፤ #የቁርሾ ማካካሻ በሆኑ ዕውነቶች ላይ ጥርት ያለ የግንዛቤ ለውጥ አምጥቶ እራስን ማረመን - ይጠይቃል።
 
ለመሆኑ ይህ ወጣት አሁን በምን ሁኔታ ላይ ይገኝ ይሆን? ምህረት የሚደረግለት ቀን በእጅጉ #ይናፍቀኛል። እኒያ ኑሮሯቸውም ዓይናቸውም #ለላመ መነኩሴም ወላጅ እናቱ ማጽናኛ ምርኩዝ መስጠት #ምርቃትም ይመስለኛል።
 
ይህ ለውጥ እንዴት እንደተገኜ ፈጣሪ ያውቀዋል። የማይደፈር ተደፍሮ፤ እጅግ በሰመረ ጥበብ እና ጥንቃቄ በፈጣሪ መልካም ይሁንታ ለተከናወነ ዕድል እንዲህ ዓይነቶች እርምጃወች ፈጣሪ አምላክ #ዕንባ አውጥቶ የሚያነባባቸው ይመስለኛል። 
 
እኔ እማስተውለው ጥራት ያለው አመራር ለተጎዱ እናቶች ለመሆን አለመቻል፤ ለቀጣዩ ትውልድ #ዕዳ ማስቀመጥም ይመስለኛል። በፈጣሪ ዘንድ የትውልድ ቅጣት እንዳይኖር መጠንቀቅ ይገባል እንደማለት።
 
የቀንበጡ ፲ አለቃ መሳፍንት ጉዳይ እንደገና #ቢታይ መልካም ይመስለኛል። ቢያንስ የእስር ቤት ህይወቱ ቀላል እና #ወከባ የለሽ እንዲሆንም ቢደረግ ጥሩ ይመስለኛል። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን። 
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21/02/2026
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።