ባለቤት #አልባወቹ ምንዱባን። የአዲስ አበባ #ከንቲባ ጽ/ቤት ባሊህ ሊለው የሚገባ በኽረ ጉዳይ።
ባለቤት #አልባወቹ ምንዱባን።
1) ቁጥር አንድ ቢጫ ለባሾች በመስከረም ወር በ2011ዓ.ም የታሠሩ ወለዮወች እና ጎንደሮች የደረቅ ወንጀል #ሽፍቶች ናቸው ሲሉ ነበር የጦር መኮንኖች የተናገሩት። የሆነው በቡራዩ በደረሰው ሰቆቃ ለልግሥና እና አክብሮት እጀ - ረጅሙ የአዲስ አበባ ህዝብ ተፈናቃዮችን #አጽናንቷል አንዱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ግንቦት 7 ሲገባ #ስቀህ ተቀብልኃል ዓይነትም ይመስላል። ይህም ብቻ አይደለም በውስጡ የተቋጠረው ቂም ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድንም #እልል ብላችሁ ተቀብላችኋል የሚል የውስጥ አርበኞች ጉዳይም ሊኖርበት ይችላል።
በተጨማሪም ኦነግ መስከረም ፭ ኢትዮጵያም ሲገባም በነበረው #ድባብ 1300 አዲስ አበባ ያፈራቸው ልጆች ጦላይ ተጣሉ። ፭ የአዲስ አበባ ነዋሪወች በአደባባይ #ተረሸኑ። ጠቅላይ ሚር አብይ እንደ ለለውጡ መስዋዕትነት እንደከፈሉ ይቆጠራል ብለው ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ውሹን ያነሳ የለም።
የሆነ ሆኖ እነኝህ የምታዮዋቸው የመጀመሪያወቹ ብጫ ለባሾች #ከ1300 የአዲስ አበባ ነዋሪወች የጦላይ እስረኞች እንግዲህ #በሃይማኖታቸው ይሁን፤ በዘር ሐረጋቸው በማንነታቸው እስር ቤት ነበሩ። በምን ሁኔታ ላይአሁን እንደሚገኙም አላውቅም። የታሠሩት ከባልደራስ ምሥረታ በፊት ቢሆንም ግን ስለአዲስ አበባ የተደራጀው ባልደራስ አጀንዳው አልነበሩም። እነኝህ ምንዱባን፤ ትናንትም ዛሬም #ለብልጽግናም ምናቸውም የሚያሰጋ አይደለም። ሰላማዊ እና ሩህሩህ ዜጎች ናቸው።
2) ሙሉ ዕድሜያቸውን እስከ ሰማዕትነት ለኢትዮጵያ የገበሩ #የኢህአፓ ሊቃናት ናቸው።
3) ሦስተኛ በርከት ብለው የሚታዩት ቢጫ ለባሾች ከአርቲስት ሃጮሉ መሰዋት ጋር ተያይዞ #የተበሳጩ ወጣቶች በቅድስት ቤተክርስትያን ላይ ጥቃት ለመፈጸም ሲያቀድ አናስደፍርም ብለው የታሠሩ ናቸው
በምልሰት ወደ ኋላ ሲታሰብ #የሚያረገርግ፤ ያልሰከነ፤ አዛዥ እና ታዛዡ የማይታወቅበት የፖለቲካ #የጎርፍ ሁነት የነበረበት ጊዜ ነበር። ጥቃቱን በሚመለከት ማን? እንዴት የሚለውን ማህበረ ኦነግ ምንም ፍሬ ሳያፈራ፤ በአስተዋዮች ልባም ተግባር ለተበቃው ድል፤ በዛ ልክ ክብር እና ሞገስ አግኝቶ ከፍ ባለበት ወቅት፤ ኦህዴድ ብዙም የፖለቲካ ስክነት ባላገኜበት ወቅት፤ ህወሃት ደግሞ መንበረ - ሥልጣኑን ከመልቀቅ ጋር ያደረበትን የውስጥ መከፋት #በቁርሾ ለማወራረድ ኔቱን እንደገና በሚዘረጋበት ሰዓት ብዙ፤ በጣም ብዙ የፖለቲካ ቀውስ ኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጠረ። ቃጠሎም በአዲስ አበባ እና በባህርዳር ከተማም ነበር። #ሞትም ነበር። ህውከትም ነበር።
ጥቃቅን እና አነስተኛ ቡድኖች መሬት አይብቃን ያሉበትም ወቅት ነበር። በዚህ መሃል የተጎዳ ተጎዳ። የሰበታ፤ የለገጣፎ ለገዳዲ፤ የጌዲኦ፤ የአማሮ፤ የወላይታ፤ የዶርዜ ህዝብ ችግሮችም ጎልተው ወጡ። ብቻ ብዙ ምስቅልቅሎች በተስተናገደበት ወቅት ለካቴና የተዳረጉ ወገኖች እንዲህ #ተረስተው ቀሩ።
በዛን ወቅት የታሠሩ ሁሉ በውነት #ከካሳ ጋር የኢትዮጵያ መንግሥት እራሱን #አሂሶ ከእስር መፍታት፤ የሚደራጁበትን ሁነት ማመቻቸት ይጠበቅበታል። በተለይ የወይዘሮ #አዳነችዝም የከንቲባ ጽህፈት ቤት እነኝህ ዜጎች ባላጠፋት፤ ባልጎዱት፤ ባልተገኙበት፤ ባላሰቡትም የፖለቲካ ትርምስ #ለመቀጣጫ ተብሎ ይህን ያህል አሳር ከፈሉ።
ለእነኝህ ንዑዳን እንዲህ ያለ የግፍግፍ - ግፍ ሊፈጸምባቸው ስለማይገባ፤ ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይቅርታ ተጠይቀው ከእስር ሊፈቱ ይገባል ባይ ነኝ። የከንቲባ ጽህፈት ቤት ከኮሪደር በላይ የነዋሪወችን መብት የማስከበር ጉዳይ አጀንዳ ይዞ፤ ተወያይቶ እና ወስኖ፤ ከሚመለከተው ጋርም ተነጋግሮ ከእስር ሊፈታቸው ይገባል።
በዛ ውቂ ደብልቂ ጊዜ ህዬወታቸውን ያለአግባብ ላጡ ወገኖችም ያሉበትን ሁኔታ ተከታትሎ የማጽናናት ኃላፊነት አለበት ባይ ነኝ። የተሰውም አሉ።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21/02/2026
#ፍትህ ለንጹኃን የአዲስ አበባ ልጆች እና ለቀደምት የኢህአፓ ሊቃናት።



አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ