ለጎንደሮች መርማሪ እና ሞጋች ጡሁፍ ከአቶ ለምለሙ ባይህ ፔጅ ያገኜሁትን እንሆ። የእኔንም ዕይታ አክያለሁኝ።

 

ለጎንደሮች መርማሪ እና ሞጋች ጡሁፍ ከአቶ ለምለሙ ባይህ ፔጅ ያገኜሁትን እንሆ። የእኔንም ዕይታ አክያለሁኝ።
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
 
 
……… እኔ ደግሞ እላለሁኝ።
 
"ጽድቁስ ቀርቶ በወጉ #በኮነነኝ" ይላል ጎንደሬ መንገድ ዘግቶ #ጉሮሮዋን መዝጋቱ፤ #ጢስ ጢንቢስ የሚሉ ተቋማት ተቀንቶባቸው #መንደዳቸው፤ እንደገና አወን #እንደገና የህወሃት ጠቀራማ #ህማማት ዘመን ተናፍቆ ለዛ ናፍቆት ብድግ ቁጭ ማለቱ በቀረባት።
 
መቸውንም በየትኛውም ሁኔታ ለጎንደር የተሻለ #ጤናማ ዕይታ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሊቅ ይመጣል ብዬ አላሳብም። በጋሜዬ እና ቁንጮዬ የተጀመረው #የፖለቲካ ህይወቴ ይሁን #በሰርዴታዬ የተዋህድኩት የራዲዮ ጋዜጠኝነት ህይወቴ ሂደቱን በጥሞና ስከታተለው፤ #ለናሙና የማነሳው ስለ ጎንደር ቀና የሚያስብ የፖለቲካ ሊቅ ለመሪነት በሌላው ወገን #የታጨ ወይንም ራሱን #ያጨ አላውቅም። ከሁሉም በዕት #ተገላዮች #በክፋ ዓይን የምንታይ እኛው ነን።
 
የሚገርመው #የእኛው ሰው የሚያጠቃው እኛኑ ነው። እኔን የሚታገሉኝ እኮ ጎንደሮች ናቸው። አሁን በቅርቡ ስለጠለምት ቅርብ ከሆነ ሰብዕ መረጃ ላይ ስፈልግ ብሎክ አድርጎኛል። ምን አድርጊ ብሎ ብሎክ እንዳደረገኝ አላውቅም። #እርግማን ይሁን ምን አላውቅም። በኪነጥበቡ ነው የሚኖረው። ሲያውቅህ ጥቃቱን አስቀድሞ ነው። የራስ ቤተሰብ ለአገር ሲዘራ ውሎ የሚያድረውን አቅም ከአንተ ሲደርስ ይቆልፈዋል።
 
ሼር፤ #ላይክ እና #ሰብስክራይብ ብርቅ ሆኖ ከእኔ ፔጅ አንድም እህት ወንድም የለም። ጨርሶ አያስቡትም። አንዳንዶቹ ምን እንደምሰራም ጭራሽ #አያውቁም፤ ቢያውቁም አጀንዳቸው አይደለም። #አብይዝም ውስጥን አርቆ ሌላውን ለመውቀስ የሚከብደውም ለዚህ ነው። ታዋቂ የሆነ ሰብ የራሱን ቤት አደራጅቶ አይቼ አላውቅም። ማዶ ማዶውን ነው የሚያሰኜው። በጣም ብዙ በትምህርት ዘርፍ የሚንቀሳቀሱ ወገኖች ከጎንደር የራቀ ተሳትፎ #ይቀርባቸዋል። ዕውነት ለመናገር በጥሞና ጥናት የሚፈልግ ጉዳይ ነው። 
 
የሚደንቀኝ ግን ቅኖችን የሚናገሩላት፤ የሚመሰክሩላት፤ የሚጽፋላት፤ አንደበት የሚሆኑላት #ኢትዮጵውያና አታጣም። የእኛን ነገር ተወት እናድርገው። 
 
ሥርጉትሻ 21/02/2026
 
ፎቶወቹ ሁለቱ ከአቶ ንጉሡ ዘመነ የተገኙ ናቸው። ሌላው ከእኔ ጨምሬ ነው። #የኮሪደር ልማቱ ይህንስ አይመለከተውምን የሚል ጥያቄ አለኝ። ሰሞኑን በኦሮምያ በጦርነት ውስጥም ተሁኖ ሜጋ ፕሮጀክትን ሁሉ ሳዳምጥ ነበር። የአውሮፕላን ማረፊያ እና የምግብ ማቀናበሪያ ፕሮጀክት ያንስ የሚያሰራው ሰላም፤ የሚያስቀጥለው #ክብሪት አይኖር ይሆንም ብያለሁኝ። #ማቃጠል ጀግንነት ስለሆነ በኢትዮጵያ ፖለቲካ።
========////======
የጎንደርን ክብር እና ልዕልና ከወሬ ባለፈ በተግባር ለማምጣት የማይጠቅም " እናትዋ ጎንደር፣ስስትዋ ጎንደር፣እኔስ ጎንደርን ሞቸ ነው ምወዳት---" ወዘተ የቃላት አጠቃቀሞች ለግለሰቦች የንግድ አገልግሎት ብቻ የዋለ የአስመሳይነት ካባ ነው!!!
---------------------////////----------------------
ጎንደርን ከልብ ከወደድክ የቃላት ማሽሞንሞኑን ለጊዜው ያዝ አድርገውና:-
*በምስሉ የሚታዩትን የጎንደር ት/ቤቶች ገጽታ ለመቀየር የድርሻህን በመወጣት የወደቀውን የጎንደሬነት ክብር አንሳው
*ጎንደርን ከልብ ከወደድክ በየጎዳናው የወደቁ ጧሪ ቀባሪ ያጡ የጎንደር አረጋውያንን ሰብስብ
*ጎንደርን ከልብ ከወደድክ ጎንደሬው የሚታከምባቸውን የጤና ተቋማት በቁጥር እና በጥራት ለማሻሻል ተባበር
የጎንደርን ክብር እና ልዕልና በተግባር ለመመለስ ምንም አይነት አስተዋጽኦ ሳታደርግ በምላስህ ብቻ እናትዋ፣ስስትዋ፣እህልዋ፣ሞቸ ነው ምወድሽ፣የጎንደር ወኪል ነኝ፣የጎንደር ምና*ምን ነኝ እያልክ ዝምብለህ እያቅ*ራራህ ከቀጠልክ ግን እውነቱን እልሃለሁ ጎንደርንና ጎንደሬነትን ለግል ጥቅምህ ያዋልክ አስመ*ሳይ የጎንደር ጠላ*ት ነህ!!
ንጉሱ Zemene Habtu

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።