#መሻቀል ይታገት።
#መሻቀል ይታገት።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዘሃ ግራው መሻቀል ነው። ስለዚህም ደንጋጣ እና ያረገረገም ነው። ቱማታ እና "ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል" የሚሉትም ዓይነት ነው። ስለሆነም ውድቀቱ እንደ መድህን ቆጥሮ ቸበለው ይለዋል። የሚለው ግን አውሎ የሚያሳድር በቂ ኦክስጅን የለውም።
በጥቁር ቀን ተከቅልሎ ጢስን እዬመገበ በቀውስ በጀት የሚተዳደረው ኦነጋዊው የ፬ ኪሎ ቤተ መንግሥት ድል ቀንቶኛል ሲል ዓዋጅ ያስነግራል። ይህም ብቻ አይደለም ከሁሉም አለሁ በሚለው የዝልኝዲፕሎማሲያዊ ጉዞም ትርፋማ እንደሆነ ይዘባበታል።
በምንምመለበጥ፤ በምንምወጌሻ ሊጠገን የማይችለው የፋንታዚ ጉዞ ወፈፌ ነው። ዕለታት የሚሻቅሉት። መሻቀል ዬአለመርጋት ምልክት ነው። በሁለገብ የታቀደ ጥፋት የዳነም የተገነባም አገር የለም።
የማድመጥ አቅም የሚጠይቀው ብሄራዊ ብቻ ሳይሆን አህጉራዊዓለማቀፋዊምነው። አንድን ውድቀት ለማከምሌላ ውድቀት በማጨት የሚገኝ የተረጋጋ ሥርዓት አይኖርም።
በትንሽ የእፎዬታ አዬር ሚሊዮን ትእቢትን ፀንሶ መንጎድ እራስን አጉብጦ ከማሰናበት ውጪ ትርፋማ መንገድ አይደለም። ለኦነግ ፖለቲካ ኢንትሪግ፤ ማምታት ዶግማው ነው። ይህን ግን ለቀኑ ቀን ሲሰጠው የዶግአመድ ይሆናል።
እንኳንስ ተጠማኙ የኦነግ ፖለቲካ በራሱ ዛቢያ ተመሥርቶ እራሱን ለመራ ስኩን ፖለቲካ እና ፖለቲከኞችም ይህ ዲጅታል ዘመን ፈታኝ ነው። ሥርዓት የገነቡ አገሮች ምን ያህል ፈተና ውስጥ እንዳሉ እናያለን።
መከራውን ችሎ ያለው ከሊቅ እስከ ደቂቅ መቻል የሰጠው የኢትዮጵያ ህዝብ። ነው። ህዝቡ ያው መሻቀልን ገቶ ስኩን የሆነ አመራር ነው። እራቡ ይህ ነው። ይህ የሰከነ ህዝብ በልኩ መሪ ቢያገኝ ሙሉ 50 ዓመት እንዲህ አይነድም ነበር።
ያለው የዘመኑ የፖለቲካ ባህሪ አቋም ላይ አልተደረሰም። "ተረኛ" እያሉ የሚያሽሞነሙኑት አሁንም አሉ።
የሆነ ሆኖ አማራጭ መጥፋቱ ለጭካኔ ተጨማሪ ዕድል እንዲያገኝ አድርጎታል። ለዚህ ምንምዓይነት ቀመር ማውጣት አይቻልም። ይህም ቢሆን ግን የበለጠ እራስን አዳምጦ ያጎደሉንን፤ ያጓደልነውንም፤ አሟልቶ፤ እራስን አርሞ እና #ሰልቆ፤ እራስን ከጉድፍ አጽድቶ እና አዳምጦ #ከእኔ ምን? ከእያንዳንዳችን ምን ወደሚል የሃሳብ እድገት ሊያማትር ይገባል ጎዳናው።
ብቻችን እምንችለው ነገር የለም። ዛሬ ዓለም በትስስር ላይ ናት። ትስስሩን ለመልካም ተስፋ መጠቀም ይገባል። ይህም በጭፍጫፊ እክሎች ትጥቅ በመፍታት ሳይሆን፤ እራስን አዳምጦ በዲስፕሊን ገዝቶ በአቅም ልክ መንቀሳቀስን መቀበል ሲቻል ብቻ ነው ትውልድምአገርም መትረፍ የሚችሉት።
የሻቀለ ፖለቲካ አፍሶ ይለቅማል። ለቅሞ ያፈሳል። የረጉ፤ የሰከኑ ዬተግባር ዓውዶች ግን ግርዶሹን ገፈውተ ስፋ እንዲያሰብል የማድረግ አቅማቸው አንቱ ነው። መቼ ተጀመረ። ለመሆኑ ማን እና ምን እንታገል የሚለው አመክንዮ እራሱ እኮ ስምምነት ላይ አልተደረሰም።
ያለውን የኦነግ ፋንታዚ ብቻ ሳይሆን በዬራስ ተስጠው የተያዙ ቅምጥ መሻቶችም ትውልድን እያባከኑ ነውና እራስን አዳምጦ መነሳት ይገባል። ይህን አሳቻ ዘመን ከዬትኛውም ዘመን ጋር ለንጽጽር ማቅረብ አይቻልም። ጭካኔ የዘመነበት ዘመን ልንለው እንችላለን። አመድነት የተናፈቀበት ዘመን ልንለው እንችላለን።
ድህነት የተገፋበት፤ ግንድህነትምየተፈቀገበት ዘመን ልንለው እንችላለን። የተመሰጠረ ጥቁር ባዕድ መንፈስ አና ያለበት ዘመን ልንለው እንችላለን። ይህን ለመቋቋም ደግሞ ምን አጉድለን ለቅጣት ተዳረግን የሚለውን ወደ ውስጥነት አስገብቶ መድፈርን ይጠይቃል።በምንም ዓይነት መሥፈርት ኢትዮጵያ እናኢትዮጵያዊነን ድል ላይ አይደሉም።ቢያንስ በዚህ መስማማት ከቻልን ዕድለኞች ነን። ቢያንስ ብሎ አይዋቢያንስንም መቀበል ለቀጣይ ተስፋ ይረዳዋል። እንደ ባለ ፋንታዚወች ለለት አንሁን።
ጥድፊያው፤ ሩጫው፤ መሻቀሉ እና ማሻቀሉ ሳይሆን አደቡ፤ ስክነቱ በጀመሩት ጉዳይ ሳይዘናጉ ፀንቶ መቀጠሉ ለስኬት ያበቃል። ምንም ነገር አያውካችሁ። ምንም። ለቀኑ ቀን ሲሰጠው ኢትዮጵያ በቃሽ የሚል ሙሴ ይሰጣታል። አይዟችሁ። ስኬት የጀንበር ሰፌድ፤ የምሽት ሰበጥራ አይደለም።ስኬት የጥረት ጥራት የሂደት ዕንቁ ነው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ደህና ዋሉልኝ። አሜን።
ደህና አምሹልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
03/07/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ