የተባባል አርምሞ!
ብራቦ! አቶ ተቀባ ተባባል።
ከሥርጉተ © ሥላሴ 22.06.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
"ማቅ ለብሼ በአመድ ላይ ሆኜ ስፆም እጸልይና እለምን ዘንድ ፊቴን ወደ ጌታ አምላክ አቀናሁ" (ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፫)
"ማቅ ለብሼ በአመድ ላይ ሆኜ ስፆም እጸልይና እለምን ዘንድ ፊቴን ወደ ጌታ አምላክ አቀናሁ" (ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፫)
- ተንደፋዳፊዎች።
የመሸባቸው ይንደፋደፉ። ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዋዜማ ላይም የታዬው ታይቷል። ሲነሳም የታዬው ታይቷል። አማራ ግን ደሙን ቀድሞ ስለገበረበት በሰላሙ ቀን ማገዶ መሆን ምርጫው ሊሆን አይገባም። ጥቅሙን ተጻሮ የሚቆም ተጠቃሚ የለም። እንደዛ እንደ ማበሻ ጨርቅ የተጠላው የአማራ የህልውና ተጋድሎ ከውሉ መንበር ላይ ነው። ዓለም ዓቀፍ እውቅናውን እና ተቀባይነቱን ማዬት ነው። የመንፈስ ዲታነቱ ልዕልናው ለሥነ - ልቦና ያጎረሰው ዘመን ጠገብ ትሩፋት እዮራዊ ነው። ታገድሎ እንዲህ ለአማረ እና ለሰመረ ድል ሲበቃ የመጀመሪያው ነው የኦሮሞ ንቅናቄ እና የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ። ፍሬውን ሰብሉን አይቷል።
የማያሰፍረው፤ ከቶውንም የማይሸማቀቅበት እጬጌውን ብቃት፤ ብልሃት፤ ማስተዋል፤ ትእግስት፤ ልቅና ጥበብ ዓለም እዬታደመበት ነው። እንኳንስ ለራሱ ለሌለውም ተርፏል የደሙ ዋጋ እና ዕሴት። ስለዚህ አሁን ለህውከት ለብጥብጥ ለልቅልቅ ሲያምስና ሲያተራምስ፤ በሚዲያው በብራነው በማይኩ የከራረመው ይውጣ ይውረድ … አልፏል ታሪክ፤ ታሪክ ሰሪውን ለድል አብቅቷል። ሌላው ደግሞ እንኳነስ አጀንዳ ለሙግት የሚሆን አቅም የለም። ባለቅኔው ጠ/ ሚር የሚያነሷቸው ነጥቦች ለስላሳ ግን የአንበሳ ግርማ ሞገስ ያላቸው ናቸው። ብትንትኑ እያወጡት ነው የ43 ዓመቱን የሴራ ጋድም ገደል ፖለቲካን።
- ፈቃድ ለሴራ ፖለቲካ መንሳት።
አማራ መሬት ምንም የሰላማዊ ሰለፍ ፍቃድ መስጠት አይኖርበትም። አማራ ጌጡን ማስከፋት የለበትም። አማራ የክብሩን የውስጥ ሰላም ማወክ አይገባውም። አማራ የሞተበት፤ የታራደበት፤ የተከፋበት ጎማም ዘመን አብቅቷል። ከእንግዲህ አማራ ተማግዶ ለድል አጥቢየ አርበኞች የብጥብጥ ማካካሻ፤ ማዋዣ፤ የብጥብጥ መፎካካሪ ሊሆን መፍቀድ የለበትም። ለአሳፋሪ ተግባር ራሱን ማጨት አማራ የለበትም። አማራ ራሱን ለማዋረድ መታተር የለበትም። በ አብሮነት ዝልቅ ዘይቤው በተለመደው ትእግስቱ እንደ ተለመደው መኖር ያስፈልጋል። ሰማይ እና መሬት የተገናኜ ያህል አሟራው በረረ ቅሉ ተሰበረን ለባለሠረገላ አርበኞች ...
እራሱ የአማራ መሬት የዚህም ዓመት የስፖርት ወድድር ሁሉ መዝጋት አለበት። አያስፈልገውም። መፈናቀሉም ቢሆን የተጠበቀ ታቅዶ የተከወነ ስለሆነ በልክ መያዝ ያስፈልጋል። "የረጋ ወተት ቅቤ" ይወጣዋል። ደግሞ በዚህ በግራ እና በቀኝ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ፋታ ባጡበት ጊዜ ተጨማሪ ሥራ መፍጠር አይኖርበትም። አቅል ላጣው ይባክኖ እሳቸው። ቢያንስ አማራ ይህን ጫና ሊቀንስላቸው ይገባል። ዶር አምባቸው መኮነንም አቶ ገዱ አንዳርጋቸውም የሠሩት ይህንኑ ነው። ልብም ከቦታው ህሊናም ከቦታው ስለመኖሩ ሚስጢሩን አማራ መቃኘት አለበት። አቶ ተቃባ ተባባል የወሰዱት እርምጃ ትክክል እና ተገቢ ነው። አማራ መቆስቆሻ፤ አማራ ማገዶ ከእንግዲህ አይሆንም፤ ለዛውም የአብይን ውስጥ ለማሳዘን፤ የለማን መንፈስ ለማጨማተር። አይደረግም አይሆንምም። አይገባም። የሚያጣድፍ ነገር ለሰላም፤ ቂምን ለመርሳት፤ ቁርሾን አሸቀንጥሮ ለመጣል እንጂ ለመበቀል ለጥል ለብጥብጥ መሆን አይገባም።
- ባድም እና እድምታው።
በጽሞና ቢመረመር የባድመ ውሳኔ ጉዳይ መቋጨት እኮ ለጎንደር ትልቅ የድል ርካብ ነው። ኤርትራ ይህን ያስመልስለኛል ያለችውን ሃይል አደረጅታ ስተዋጋ የኖረችው አማራ መሬት ላይ እንጂ አፋር፤ ሲዳማ፤ ጉራጌ፤ ትግራይ፤ ወላይታ አዋሳ መሬት ላይ አይደለም። የተማገደውም አማራ ነው። የተቃጠለው የአማራ ቀዬ ነው። በጥርስ የተያዘው የአማራ ታረክ እና ቅርስ ነው። ለወያኔ ብርንዶ ለዛውም የሰው የሆነውም ይሄው ባድማ ነው። ለ አውሮፓው ህብረት ክብር ልዕልና የዘመድ መወጣጫ የሆነውም ይሄው ባእት ነው። እና ምን ቀረብኝ ብሎ አሁን አመጸን ጥላቻን ቂም በቀለን ይተባበራል? ስለምን?
አማራ ምን ቀረብኝ ብሎ፤ ምን ጎደለብኝ ብሎ ነው አሁን በቅዱሰ መንፈስ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርገው? ጥያቄውን አቅርቧል፤ ጥያቄው ደግሞ በቱማታ እንዲመለስ አይጠብቅም። አደብ ጥሪታችን መሆኑን፤ እዮባዊነት መለያችን መሆኑን መተላለፍ ወንጀል ነው። እንደ አማራ መሆን ያስፈልጋል። ጸሎት፤ ሰጊድ፤ ሱባኤ፤ ድዋ፤ ምህላ የሚስፍልጋቸው የሰላም ሐዋርያችን እንዲጠብቅልን ነው መተጋት ያለበት። ሃሳቡን፤ ትልሙን፤ ራዕዩን ለማሳካት ቀን ከሌት መተኛት የለም። እኔ አልተኛም። ሦስት ሰዓት ብቻ ነው የምተኛው። በቃ። እጽፋለሁኝ። ዜና አዳምጣለሁኝ። አነባለሁኝ። ለዛ መልስ ለዛ ሙግት እጽፋለሁኝ። በተጻጸራሪ የቆሙ መንፈሶች በሬሳቸው ላይ ስላሉ ጊዜ አላጠፋም ለማድመጥ አሁን ለማዬት። ለሰድስት ወራት በላይ ተግቼበታለሁኝ። ዛሬ ቀንበጥ ላይ እምሠራው በዬሰ ዓቱ በመፊጠሩ ጉዳዮች ላይ እንደልቤ ሳልሳቀቅ መልዕክቴን ማስተለላፍ ስለፈልግኩኝ ነው።
- ቂም ሲፈጠር መሃን አይደለም።
ከእንግዲህም ቂም መሃን ባለመሆኑ ቂም መንታ ወላድ በመሆኑ በዚህ ዙሪያ ነው የምሠራው። የአሁኑ ሽርክና ፍለጋ ሌላ ምንም ሳይሆን የጥፋት ውድድር አብራችሁ ተደረቡልን ነው። አማራ አንብኝ ማለት አለበት። ማፈር አለበት እኮ ደቡብ 27 ዓመት ለሽ ብሎ ተኝቶ ከርሞ፤ ስንት ነፍስ አጥግቦ የሚያሳድረው የሀገር ጥሪት በገፍ እዬፈሰሰለት አሁን ከሞተው፤ ከደማው፤ ከተሸለተው ጋር ተጎድቻለሁኝ ይላል፤ ደቡብ ነበር እንዴ በግንቦት 7 ተከሳሹ? እንደገና አዎን እንደ ገና ደግሞ የእናቶችን እንባ ይናፍቃዋል። ውርዴት!
አማራ ይሙትለት ለእሱ። በሞቶ ያደራጀውን ሠራዊት ይሸልም፤ በድል ዋዜማ ላይ 27 ዓመት ተተኝቶ ዛሬ ነው ጥያቄው ሲዥጎደጎድ የሚታዬው ደቡብ ላይ። አማራ ይማገድ ድል ላይ ደግሞ ለቤተ መንግሥቶቹ ቀይ ምንጣፍ እንደ ተለመደው ይሰናዳ። ለዚህ ነበር እኮ ብጥብጡ ታቅዶ የተከወነው። የተበደለ፤ የተጨቆን ህዝብ የማንን ጎፈሬ ሲያበጥር ነበር። ስለምን እንደ ኦሮሞ እና እንደ አማራ ለማመገድ አልፈቀደም ቀድሞ። 50 ሺህ ኦሮሞ እና አማራ ሲታሰር፤ ሺዎች ሲደበደቡ ሲሞቱ ሲሳደዱ የት ነበር? በሁለት በሦስት አክተሮች ድል ላይ ከች ለማለት? አክተር አይሞትም ውጊያው ቃብቲያ የጦርነቱ ማዘዣ ጣቢያ አዋጊው ብራስልስ ፓርላማ ላይ … ጨዋታ … አሁን ጨዋታው ፈረስ ዳቦው ተቆረስ ሲሆን ደግሞ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰው ለቀማ … ሰው ይታዘበኛል አይባልም። ዓይን በጥሬጨው የታሸ ጉድ …
የሆነ ሆኖ ብራቦ ብያለሁኝ አቶ ተቀባ ተባባላን ጎበዝ! ወንታዳታ! ለአማራ አሁን ድልኑ፤ ተስፋውን፤ ፈርጡን ፈጣሪ እንዲጠብቀው መጸለይ ብቻ ነው ያለበት። ለመከራዊ ጊዜም መሞከሪያ፤ ለድሉ ጊዜም የሞሞከሪያ ጣቢያ አማራ መሆን የለበትም። አክቲቢስቶች ይህን በትጋት መሥራት አላባቸው። በውጭም በውስጥም ያሉ የአማራ ድርጅቶች ይህን መተግበር አለባቸው። መቼም ዘንድሮ የክብርት ወ/ሮ አና ጉምዝ ጉባኤ አዲስ አጀንዳ ፈጥሮ አያዋጋነም። ስለተደመደመ። እኛ አሸንፈናል የተሸነፈ ይንደፋደፍ።
አሁን ወሎም ቀረብኝ፤ ማርቆስም፤ ቀረብኝ፤ ዳንግላም ሰላሌለም፤ ምንጃርም ማለት የለበትም፤ ሰላሙ የወረደው ባህርዳር ላይ ጣና ኬኛ ላይ ነው። በቃ።
አማራ የመረጠው የወደደው ከቶውንም ብሩህ የሆነውን መንፈሱ፤ የተጋለት፤ ሙሉ ይሁንታውን የሸለመው የራሱ ድምጽ ባለቤት ሆኗል። በትግሉ የሚፈለገውን ቅድስና ፈጣሪ አክብሮለታል። አማራ ሙሉ አማራ ዘብ አደር ለዓይኑ ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ መሆን አለበት። እነሱ ቅማናት፤ አገው፤ እስራኤላዊ አማራ ይበሉ እኛ ግን ብለነውም አስበነውም አናውቅም። አንድነን ከምል ቀይ የደም ሴል ከቀለሙ መለዬት አይቻልም እና። አልኖርንበትም።
ታሪክ ያለፈበት የሾለከው ይንደፋደፍ ያው ሞቅ ደመቅ ካለው ፎቀቅ እያለ መቀራረብ የተለመደ ነው። ባዶ እጅ ሰማይ ጣሪያ የነከ ዝና። ለመሆኑ አማራ ምን ቀረብኝ ብሎ ነው ብጥብጥ የሚያነሳው። ድጋፍ ለአብይ ቢባልም እንዳት ወጡ። ኮሶ ጠንስሰው ነው የሚመጡት ለመከራው። ከጎጃም እና ከኦህዴድ በስተቀር ስለጎንደር አብሮት የቆመው የለም 10 ሺህ የመቱ ኗሪ አማራን እንዳትነኩ ብሎ ሲወጣ ያ ቀን አማራ እንደ ገና ተፈጥሯል።
የነገውን የአዲስ አበባው የምስጋና ቀን እራሱ እግዚአብሄር ይወቀው። አሁን ሁሉ አነኳሪ ሆኗል። ማንም እና ምን ሊቆጣጠረው እንደሚችል አይታወቅም። እኔ ወቅቱ አይደለም ብዬ ጽፌያለሁኝ። ስጋት ስላለብኝ እንጂ እኔ አብይ ኬኛ! ብዬ ስጽፍ ከሳተናው በስተቀር ያገዘኝ፤ የረዳኝ አንድም ሚደያ አልነበረም። ስለዚህ ምኞቴ ነው የኔ ነፍስ የፈቀደው ክብር እና ልዕልናው ግርማ ሞገስ ቢያገኝልኝ፤ ግን በዚህ መልክ ከባድ ነው። የሰው ብስጭት ንዴት ገና አልበረደም...ብዙ መንገድ አለው የሚታገዝበት።
የሆነ ሆኖ አሁን ምንም ጎንደር አብይን አልተቀበለችም፤ የአደባባዩን ስልፍን ረግጦ ህዝቡ ወጣ እያለ ለማሳጣት በጥርስ እንዲያዝ ለማድረግ ተጥሯል፤ አንድም ቀን የሚሊዮኖች ድምጽን ጋዜጠኛ የእስረኛ ዘገባ ለጥፎ የማያውቀው ሁሉ ሽሚያ ላይ ነበር፤ ከዛ በሀዋላም አብይን ነቅፎ ሲጽፍ ቀድመው ለጣፊዎች እነሱ ናቸው። ኤርትራ ላይ አርበኛ አንደርጋቸው ጽጌን ሊገለድ ነበር የተባለው ጎንደር ነበር። ለዛውም ዜናው በፋሲል ግንብ ታጅቦ ነበር የቀረበው።
ለዛሬው 27 ዓመት ተጨቆን የደቡብ የወል ጥያቄ ጎንደር ተማግዶ ግን እነሱ እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው ድሉ ላይ በዬቀጠናው ጠ/ሚሩን ሲያፋጥጡ አድምጠናል። ይህ የተለመደ ነው ብልጠት እና ፖለቲካ። "ነጋዴንት፤ ርካሽ ተዋዳጅነትም ነው" ብለውታል ባለቅኔው ጠ/ ሚር አብይ አህምድ። ይሄ ለሁሉም የሚሠራ ቋንቋ ነው። "የጊዜ ጉዳይ" ነውም ብለዋል። በቃላት ጋጋታ ማደራጀት እና መምራት እንደማይቻል አሳምረው ያውቁታል። ማደራጀት የተጽዕኖ ፈጣሪ ፍላጋ የኤጀንሲ ሸቀጥ ቤት መክፈት ሳይሆን ቂጥ ይፈልጋል። ቁጭ ብሎ ማሰብ።
ሌላው ጎንደር ሲባል ሁሉንም ይመለከታል። ሲከስል ሲቃጠል ሲነድ 43 ዓመት ኗሯል። ከእንግዲህ ማገዶነት መቆም አለበት። ታሪኩን በድጋሚ በሞቱ ጠልፎታል። የድል አጥቢ አርበኝነት ክፍሉ ስላልሆነ አደብ መግዛት አለበት።
በአማራ መሬት ላይ ወሎ ላይ፤ ባህርዳር ላይ ይህ ጥያቄ ሊነሳ ይችላል እንደ ዛሬው ጅማ ላይ በስፖርት ሰበብ እንደ ተነሳው ማለት ነው። አኩል እንሁን ፊፋን በአደባባይ የደበደበው፤ የሽንት ሽቶ በአደባባይ በህዝብ ሰብዕና ያርከፈከፈው፤ አደራ ተስጥቶት ያውም የሰው በአደራው ያልተገኘው ትዕቢተኛው ወያኔ ሃርነት ትግራይ እና ደጋፊው ጓደኛ ፍለጋ ነው ጅማ ላይ ያን ያደራጀው። ይህ ሁሉ ድራማ ሲያበቃ ፈንድተው ይሙቱ ነው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ። አፋርንም ጠብቁት።
- አፍርኩኝ ስለጅማ!
- ዘመነ ፈግግታ።
- ሥማኝ።
ኦቦ ሌንጮ ለታን በደቀሱበት ሚዲያ እነሱም ተሞሸረዋል። የውግዘቱ ፊርማ ሳይደርቅ። የፖለቲካው ብልህነቱ ይሄው ነው። „ዕለታዊ“ ናችሁ፤ ይህን ሥም የያዘው ውይይታችሁም ተመችቶኛል ብያለሁኝ። ቀድሞ ማሰብ የለም። ህልም እንጂ ውስጥ የለም። አሁንያልቻለው ለመቻል በፌስ ቡክ አርበኞቹ አለን ብሎ ከሰላም ማግስት ያውክ ሁለት በገጽ በመንታ ልብ ያንኩር ያተራምሥ … ለወያኔ ስንቅ ያቀበል። ነገም አይበጅም ያው ሾተላዩ ውጦ ወይ ደርሰምሶ መብቀል ነው እና ተልዕኮው … ጤና ቢሱ ጤና አይሰጥም መቼውንም፤ የትም፤ የተፈጠረው ለዚህ ስለሆነ … ያሃይማኖት ቅልቅልም ይኖራል ... ጥቅም፤ ትርፍ ከታፈሰ።
- ተደሞ!
የአማራ ክልላዊ መንግሥትም ማንኛውን ሰላማዊ ሰልፍ፤ ኮንሰርት፤ ስፖርታዊ ውድድር ሁሉ ዘግቶ መቀመጥ አለበት። የሱባኤ ጊዜ ነው። አሁን ዕንባ የናፈቀቸው ብቻ ሳይሆን የተጋድሎው አድማስ ዓለምዓቀፍ ዕውቅና ሲያተረፍ ተቀባይነቱ ሲጎላ ደግሞ አማራ በህውከት እንዲነሳ ይፈልጋሉ። አማራ ለኢህአፓ ሞቷል። ተዳደራዳረ ግን አንድ የለውም። ተደራዳሪ ለመሆን እኮ ሊቀመንበር መሆንን ይጠይቃል። ሌላው አይነሳ … ቴሌቪዥኑ ይመስክር … ሲንጎባለሉ ይታያሉ የሞተው የደማው የከፈለው ለእነሱው ነው ... መናጆነት ይቁም! ይቁም ሲባል ለሴራቸው አለመጋለጥም ጭምር ነው። ዕድሜ ለጎንደሩ የ አማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ የ43 ዓመቱን ቂልነት ቀብሮታል።
- አብይ ብዙ ሥራ አለበት።
- በሞኝ ደንደስ በርብሬ ተወደስ አማራ መሆን የለበትም።
አንድ ታሪክ ልንገራችሁ ውዶቼ። የጎንደር እና የወያኔ ሃርነት የ18 ቀን ጦርነት እኔም ስለነበርኩበት እኒያ የተከበሩ ጓድ ገዛህኝ ወርቄ የጦር ማዘዣ ማዕከሉን ኮማንድ ፖስቱን ቀጠነውን ወደ አርማጭሆ ትክልድንጋይ ያዛወሩት ጎንደርን የጦር ቀጣና አላደርጋትም ብለው በማስተዋል አጢነው ነበር። እርግጥ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር የመጀመሪያ አስኳል የአርበኛ አበጀ በለው አሟሟት ድንግተኛ እና አላግባብ ስለነበር ትኩስም ስለነበር፤ ህዝቡ ቁጭቱ ሳይበርድ የተከወነ ስለነበር፤ ይመስለኛል ታሪካዊ ትወልዳዊ ድርሻውን ሳይወጣ አርማጭሆ ተዋግቷቸው፤ ከልጃቸው ጋር ህይወታቸው እዛው ቀርቷል።
እኔ እራሱ በቁስቋም በር ስለነበር ብቻዬን የወጣሁት መልዕክተኛ ልኬ ወደ እዛ ልቀላቀል ሳስብ የሆነውን ታሪክ መልዕክተኞች ሲነግሩኝ ነበር ያወቅኩት። ደጉ ጓድ ገዛህኝ ወርቄ ራሱ ጎንደርን ለማትረፍ የወሰዱት እርምጃ ሊቅ ነበር። ታሪክም ነው። በሌላ በኩል ጊዜ ሰጥቶ ይቅርታ እንዲጠይቁ ማድረግ ሲገባ ያን ክብርን የሚቀነስ ተግባር ፈጸመ አርማጭሀ። የአርበኛዬ ሞት በምህረት ሥም ገብቶ መገደሉ ቢያንገበግበኝም ግን አርምሞ --- ተደሞ እድምታ አንሶታል ውሳኔው።
ስለዚህ አርማጭሆ አደራ ባለማውጣት በዚህ ጉዳይ ያመኛል፡፤ አፍራለሁኝም። ታሪክ ጠቁሯል። ጓድ ገዛህኝ ወርቄ ማዕከላዊ ኮሜቴ ላይ ሁሉም ሹም ልጆቻችን ውጪ ሰደን እና እያስተማርን የሌላውን ልጅ እንማገዳለን በማለት የራሰቸውውን ልጅ የላኩ፤ በኋዋላም እንደ እኛ አቧራ ለብሶ ታጥቆ ጎንደርን ለማትረፍ በዬውጊያ ቀጠናው የተጋ፤ መኪና ውስጥ እንኳን ከጋቢና ተቀምጦ አይቼው አላውቅም፤ ከውጪ ነበር የሚሳፈረው … እጅግ ልዩ የነበሩ ሰው ነበሩ። ዘይት በብልቂጥ፤ ስኳር እህታቸው ከ እኛ ጋር ተስልፋ፤ ቡና እንደ እኛ ነበር የሚሸምቱ። መሬት ላይ እንደ እኛ ማትራሳ በ አዬር በተነፋ ፍራሽ ላይ ሰንበት የለ፤ ባዕል የለ የሚተጉ ንጹህ ታታሪ ነበሩ።
ጥዋት ወደ ሁለት ሰዓት ቆመው በረድንዳ ላይ አመልካቹን ሲያደምጡ፤ እዛው ዘበኞቹ ላይ ስልክ አለ እዬደዎሉ ለዬሚመለከተው ክፍል መመሪያ ይሰጡ ነበር። ጥበባቸው ፈግግታቸው ልዩ ነበር። ጎንደር ሊያመስግናቸው የሚገባ መሪ ነበሩት። ሽልማት ነበሩ። በጦርነቱ ወቅት ሁሉ እሳቸውን ለይቶ ነፍሳቸውን ለማዳን ኤሌኮፍተር ተልኮላቸው ጎንደርን በመከራው ዕለት ጥዬው አልሄድም አብሬው እሞታለሁ ብለው እዛው የቀሩ ለቃላቸው ያደሩ ቴወድሮሴ ናቸው። ትህትናቸው፤ አክብሮታቸው፤ ጎንደር በመመደባቸው መከራውን ለመጋራት ዕዱሉን ማገኘታቸው ሁሉ ያስደስታቸው ነበር። መንፈሳቸው ይንፍቀኛል። እነኝህን ሁሉ ነው 43 ዓመቱ የማሌ ርዕዮት ሴራ ያሳጣን።
ስለዚህ አሁን ደግሞ እንደ ተለመደው ወያኔ ብቻ አይደለም ይሄን የሚፈልገው ጎንደር አለን ያለው ሁሉ እርቃኑን ስለቀረ የዛ ማበሻ እና መጠቅለያ እንዲሆንለት ጎንደርን ይፍለጋል። ለአረመኔ እኮ ነው ታልፈን የተሰጠነው። ትናንት የሃውዜ ሰምእታት ሲከበር አብሮ ወያኔ ሃርነት ትግራይም አክብሯል አብሮ አስደብድቦ በውስጥ አርበኞቹ፤ ቆሼም እልቂቱ ለዚህ የታሰበ ነበር።
ወልቃይት ወታደራዊ መሳልጠኛ አለኝ ተብሎ ስለነበር ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተቀብሎ ፈጽሞት ቢሆን ኖሮ ነገ ደግሞ አቤቶ ግንቦት 7 አብሮ አክባሪ እንዲያውም አሰናዳጅ ይሆን በነበረ። አሁን የወልድያው የራያው የቆቦ በኤሊኮፍተር መደብደብ የ50 ሺህ አማራ እና ኦሮሞ እልቂትን ከአቶ ሞላ አስገደሞ ጋር አድርጎ አይደለም ልክ ነው ያለው። ነገ ደግሞ ለሰማዕቱ አስተርዮ በኢትዮጵያ የጸሎት ቀን ሲከበር ዘገባውም ይደምጥ ይሆናል። የቂም ቀን ባይሆንም ሌላ ቂም ላለመጨመር ማስተዋልን መጸነስ ያሰፈልጋል። አይተኙልንም።
ወልቃይት ወታደራዊ መሳልጠኛ አለኝ ተብሎ ስለነበር ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተቀብሎ ፈጽሞት ቢሆን ኖሮ ነገ ደግሞ አቤቶ ግንቦት 7 አብሮ አክባሪ እንዲያውም አሰናዳጅ ይሆን በነበረ። አሁን የወልድያው የራያው የቆቦ በኤሊኮፍተር መደብደብ የ50 ሺህ አማራ እና ኦሮሞ እልቂትን ከአቶ ሞላ አስገደሞ ጋር አድርጎ አይደለም ልክ ነው ያለው። ነገ ደግሞ ለሰማዕቱ አስተርዮ በኢትዮጵያ የጸሎት ቀን ሲከበር ዘገባውም ይደምጥ ይሆናል። የቂም ቀን ባይሆንም ሌላ ቂም ላለመጨመር ማስተዋልን መጸነስ ያሰፈልጋል። አይተኙልንም።
ጎንደርም ግንቦት 7 ነበር ተብሎ የጎንደር አንድ ሰው ዓርማውን ይዞ እንዲወጣ ሊደረግ ይችል ሁሉ ነበር። ለወያኔ ሃርነትም፤ ለእነሱም ደልደል ያለ የምስክር ወረቀት። ወያኔም የበደልኩት በዚህ ምክንያት ነው የግንባሬን ሰላሙን ለማስጠበቅ እኔም ተጋድሎውን የመራሁት እኔ ነኝ ይሄው ህዝብ ወጥቶ አረጋገጠ ለማሰኘት የጎንደር ህብረት ምን ሥራ አለው። ይሄው ነው ተግባሩ …
ይህ ስለጎረበጣቸው እኮ ነው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የመሬት ወረራው በዛ ህዝባችን አስታጠቅን ያሉት። አሁን ይሄ አዱኛ ደግሞ ሌላ እንዲሸለም ይፈልጋል የጎንደር ህብረት። በነገራችን ላይ ሪፖርተር ዘጋቢው ሁሉ አሜሪካ የነበረ ነው የኢሳቱ ከጃናሞራ፤ ከጎንደር፤ ከጋይንት፤ ከማርቆስ ሲባል የነበረው … ይህ በራሱ በሚደያ ህግ የሚያስጠይቅ ነው… በሰለጠነው ዓለም የህግ ባለሙያ ጋዜጠኞች አሉ። እዚህ ሲዊዝ አሉ። እኔ አንድ የጋዜጠኞች መምህርም ገጥሞኛል። በህግ አጋግባብ ሙያውን የሚከታታሉ ማለት ነው። ስቲዲዮም እንደ እኛ ይሠራሉ ግን ከህግ አግባባነቱን ደግሞ ይከታተላሉ። ያን ጊዜ የወንጀል በጣም ጸያፍ ነገርም ነው ከሌብነትም በላይ … ነው የሚሉት። ተቸሎ ነው ሁሉ ነገር... ልጅ ተሜ ይሄ ናፈቀኝ ይለናል።
ይህ ስለጎረበጣቸው እኮ ነው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የመሬት ወረራው በዛ ህዝባችን አስታጠቅን ያሉት። አሁን ይሄ አዱኛ ደግሞ ሌላ እንዲሸለም ይፈልጋል የጎንደር ህብረት። በነገራችን ላይ ሪፖርተር ዘጋቢው ሁሉ አሜሪካ የነበረ ነው የኢሳቱ ከጃናሞራ፤ ከጎንደር፤ ከጋይንት፤ ከማርቆስ ሲባል የነበረው … ይህ በራሱ በሚደያ ህግ የሚያስጠይቅ ነው… በሰለጠነው ዓለም የህግ ባለሙያ ጋዜጠኞች አሉ። እዚህ ሲዊዝ አሉ። እኔ አንድ የጋዜጠኞች መምህርም ገጥሞኛል። በህግ አጋግባብ ሙያውን የሚከታታሉ ማለት ነው። ስቲዲዮም እንደ እኛ ይሠራሉ ግን ከህግ አግባባነቱን ደግሞ ይከታተላሉ። ያን ጊዜ የወንጀል በጣም ጸያፍ ነገርም ነው ከሌብነትም በላይ … ነው የሚሉት። ተቸሎ ነው ሁሉ ነገር... ልጅ ተሜ ይሄ ናፈቀኝ ይለናል።
እውነት ለመናገር ኦቦ ለማ መግረሳ እና አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአብይ መንፈስ ጋር እያንዳንዷን ደቂቃ መከታተል አለባቸው። ያልተጠበቀው የህዝብ ድጋፍ እና የሰላም መንገድ ያስደነጋጣቸው ሁሉ ፊት ለፊት በመደገፍ ውስጥ ለውስጥ ክብሪት ቤንዚን በማቀበል ማቀጣጠላቸው አይቀሬ ነው። ደቡብ የሆነው ይሄው ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ተደራዳሪ ናቸው። ሴራው እንዲህ በቀላል ቀመር ፍቺ አያገኝም። እፉኝትን ማሰቡ መልካም ነው።
- ምርኩዝ።
ህወሃት በቅማንት ተሸፍና ጎንደርን የጦር አውድማ ለማድረግ ያቀደችው ሙከራ ከሸፈ!!
የጎንደር ሰለማዊ ሰልፍ መከልለከሉ ተመስገን ብያለሁኝ። ደስ ብሎኛል። በርቱ!
ልብ እና ብልህነት የአባት ነው!
የአብይ መንፈስ እጬጌያችን ነው!
የ አብይ መንፈስ የጽድቅ ጉዟችን መባቻ ነው!
አብይ ኬኛ!
አብይ የእኔ ነው!
የ አብይ መንፈስ የጽድቅ ጉዟችን መባቻ ነው!
አብይ ኬኛ!
አብይ የእኔ ነው!
ቅኖቹ የኔዎቹ ተባሩኩ!
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ