Shaqiri und Xhaka, Stolz!

Shaqiri und Xhaka, Scholz!
ሻካና ሸኪሪ ኮራሁባችሁ!
              ከሥርጉተ© ሥላሴ 22.06.2018 
                   ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።


          "እግሮች እንዳይናወጡ አረማማዴን በመንገድህ አጽና።"
            (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፭)

ጭመቷ ሲዊዝ ዛሬ ጭምትነቷን ገፋ አድርጋ መኪኖች ሁሉ አደባባይ ወጥተው ሙሻረውን ድል እንኳን አገኘህን እያሉት ነው። ደግነቱ ቀኑ አርብ ነው። ህዝቡም በዬበረንዳው በዬመስኮቱ ሆኖ እያጀበ ነው።

 

ሲዊዝ ድብልቅልቅ ብላላች አልልታ በእልልታ እሰዬ …
የሲዊዝ ህዝብ የሞራል ልዕልና እኮ የተለዬ ነው። ሱቅ ላይ ቀላል ዕቃ ከያዛችሁ በርከት ያለ ዕቃ ለመግዛት የተሰለፈው ያሳልፋችሁዋል። ከዬትም አገር ቆይታችሁ ሲወዝ ስትገቡ ሻንጣ ማውረድ ካቃታችሁ ይረዱችኋዋል። ልዩነቱን በደንብ ታዩታላችሁ፤ ሌላ ቦታ እኮ ትዝ አትሏቸውም፤ ሲዊዝ ግን ጠረኑ የተቀደስ ነው።  


እናቶች ህፃናትን ጋሬ ይዘው ብቻቸውን ባቡር ላይ አያወጡም አያዋርዱም። ባልተፃፈው ህጋቸው የተከለከለ ነው።  መኪና ያላቸው ከሌላ አገር ወደ ሲዊዝ ሲገቡ ቀድመው እንዲሄዱ ይፈቅዱላቸዋል። ዲታውም ደሃውም ራሱን ዝቅ አድርጎ ምንም የሌለው መስሎ ይኖራል በልክ። ሁሉም ነገር በደንበር እና በዝምታ ውስጥ ነው … ለጠብ አይተጉም።  

ዛሬ የምር ከልቤ አለቀስኩኝ። እዚህ ከኖርኩበት ዘመን ሁሉ ለሲዊዝ ሰቅሰቅ ብዬ ያለቀስኩበት ቀን ነው። ለሲውዝ ይገባታል ከእናትም እናት ናት። ጨምሮ ጨማምሮ ህዝቧን የሚያስደስት ድል ፈጣሪ አምላኬ ይጨምርልኝ። አሜን! ብንታመም አስታማ፤ እናዳይርበኝ አብልታ፤ እናዳይጠማኝ ሁሉን ሰጥታኝ፤ መጠለያ እንዳላጣ ሁሉን ሸፍና ከብክባ አማካሪ በ ዓይነት መድባ ጠበቃ በነጻ ሰጥታ። ሲዊዝዬ እንኳን ደስ አለሽ!


በ2008 ካንፕ እያለሁኝ የወያኔ ሃርነት ማንፌሰቶ ባልደረቦች ርብሽ ሲያደርጉኝ 8 ወር ሆቴል ተከራይታ አስቀምጣኛለች። ዋ! አንቺ የቅድስና ተግባር እምቤት ሲዊዝዬ አንቺ ቤተ መቅደስ እንኳን ደስ አለሽ!

ዛሬ መላ ህዝብሽ ደስ ብሎ ፈገግታ እግኝቶ ያድራል። ወጣቶችም በዚህ የሥነ - ልቡና አቅም ነገን በተስፋ ይጠብቃሉ። ይጠንክራሉ። ይበረታሉ። በጣም ጠንቃቆች እና ቁጥቦች ስለሆኑ ሲዊዞች ይህ ድል በራስ የመታመመን አቅማቸውን ከፍ ያደርግላቸዋል።

ገዳማቷ ሲዊዝ ሰው ለመርዳት ደከመኝ፣ ሰለቸኝ የማትለዋ ርህርሂት - ፍቅሪት እንኳን ደስ አለሽ። ሲዊዝ ደጓ እናት፤ ሲዊዝ ምልካሟ እናት፤ ሲዊዝ አጉራሼ፤ ሲዊዝ አጽናኝዬ፤ ሲዊዝ የከፋኝ ዕለት ዋሻዬ - ሲዊዝዬ የእናት ጓዳያ፤ ሲዊዘዬ የዕንባዬ ዕለት እንኳን ደስ አለሽ! ነገን ፈጣሪ ያሳነዳው ዛሬ እንኳን ደስ አለሽ። እማዬ ሲዊዝ የእኔ መጠጌዬ፤ የእኔ ጠያቂዬ እንኳን ደስ አለሽ።

የእኔ ልዕልትዬ ሲዊዚዬ እንኳን ደስ አለሽ። እንዴት ብሩክ እና የተቀደሰ ቀን ነው። አንዴትስ ያመረበት ዕለት ነው።

ገዳመዊቷ ሲዊዘርላንድ ልጆች ዛሬ ለድል በቁ። ይህ ዕድል ለሲዊዝ ከምንም በላይ ታላቅ ድል ነው። የታላቅም ታላቅ ዋንጫ ነው።

ዋው ዋው ዋው ዋው ዋው ሲዊዘርላንድ ሰርብያን ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸነፈች። ተመስገን! የጀርመን የስፖርት ጋዜጠኞች በሲዊዝ አጨዋውት እና ውጤት ሁልጊዜ እንደ ቀለዱ ነበር። አሁን እነሱ የለሙ ሲዊዘርላንድ ለቀጣዩ ውድድር አለፈች። እልልልልልልልልልልልልልልል እለልልልልለልልልልልልልል...

ለካናስ ደስታ ሲኖር መጻፍም አይቻልም … አንዴት ደስ ይላል። ዛሬ ጎረቤቶቼ ምን እንደሚሉኝ ነው ጩኸቴ … በቃ ኳስ ላይ ምንኩስናው ሁሉ ጥፍት … ደስ አለኝ። ሐሴትም አደረኩኝ። ሲዊዝ አንኳን ደስ አለሽ። congratulation!

ስፖርት አክብሮት ነው!
ስፖርት ትውልድ ነው!

የኔዎቹ ሻማዬን አብርቻለሁኝ! የመኪናወን እልልታ እዬሰማሁኝ ነው። ዛሬ ጭምቷ፤ ዝምተኛዋ ሲዊዝ የሰርጓ ዕልት ነው … እንዴት ደስስስ ይላል፤ ያመረበት የተዋ ቀን ...
  

የኔዎቹ መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።