ዕድሜ ለዶር አብይ አህመድ ልበ ብርሃን መንፈስ!

ዕድሜ ለዶር አብይ አህመድ ልበ ብርሃን መንፈስ አቅሌን ወሰደው።

ከሥርጉተ © ሥላሴ 22.06.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)

"የህይውትን መንገድ አሳዬህኝ፡ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኽኝ፤ 
                 በቀኝህም የዘለ ዓለም ፍሰሃ አለ።" 
              (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፲፩)



መቼም እኔ በህይወቴ የምወዳቸው ሁለት ነገሮች ሥነ -ጥበብ እና እግር ኳስ ጨዋታ ናቸው። ያቺ ድንቡልቡል በተደሰቀች ቁጥር ከንበል ቀና፤ ከፍ  እና ዝቅ ባለች ጉናዊ ንጥረቷ ቁጥር ሚዜና እና ሙሽራዋን እዬለዋወጠች ወክ እንዲህ ባለች ቁጥር ነፍሴም ብን ትር ይልላታል። ለዚህም ይመስለኛል ጥቁር ነጭ በጣማራ የሁለመናዬ የቀለም ምርጫ የሆነው። ለሥጋዬ ማለት ነው። ለነፍስ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው።

ጀርመን በ2010 በድንቅ የመቻቻል ልቅናው፤ በ2014 ደግሞ በዋንጫ ባለቤትነቱ ውስጤ እንዲቀመጥ ሆኗል። ከሁሉ በላይ ግን የባስቲ እና የ የኡዚል ቅንንት የተለዬ ነው ለእኔ። ናሙናነታቸውን መጸሐፌ ውስጥ ሁሉ ጽፌዋለሁኝ። ከኢጎ ጋር የተፋቱ ናቸውና። የመንፈሱ ሃብት ደግሞ የመቻቻል ሉላዊ እናት የጠ/ ሚር አንጅላ ሜርክል ብቃት ልቅና እና  ለዓለም ግፉዕንን ለማድመጥ የሚሄዱበት መንገድ እና ትህትናቸው ጀርመን ልክ እንደ ጎጃም የልቤ ማህደር እንዲሆን ሆኗል።

ዘንድሮ የጀርመኑ ጨዋታ እጅግ በረዷማ ነበር። ጀርመን በቶማስ ሙለር አምልኮቱ በ2014 የአውሮፓ ዋንጫ ውደድር ዕድሉን አጥቷል። ቶማስ ሙለር የኮከቦች ኮከብ ተጫዋቻቸው ቢሆንም ከተገባው በላይ አምልኮው ግን ለእኔ የተገባ አልነበረም። እኔ ይህንኑ በ2014 ጽፌላቸው ነበር። የቶማስ ሙለር አቅም ኡዚል እና ባስቲ ናቸው። ለ2010 ለወርቅ ጫማ እና የኮከቦች ኮከብ ሽልማት ያበቃው የሁለቱ ከኢጎ ጋር መፋታት ነበር። እሱ ደግሞ ግለኛ ነው ማቀብል ሳይሆን ራሱ ዕድሉን መጠቀም ነው የሚሻው። የፈለገ የተሻለ ዕድል የቡድኑ አባል ይኑር ራሱ ነው የሚሞክረው።

በ2014 ላይ የዓለም እግር ኳስ ቡድን ሚናው ጉልህ አልነበረም። ሚናውም ዕድሉም እዬሸሸው መሄዱን በምን መልክ እንዳዬው አስተዳደሩ አይታወቅም። እኔ ግልጽ አድርጌ ጽፌላቸው ነበር። የ2016ቱ ፈርንሳይ ላይ የተካሄደው የአውሮፓውያኑ ጨዋታ ላይ ዕድሉን አጣ የጀርመን ቡድን። ዘንድሮም የሆነው ይኸው ነው።

ከእሱ ቀጥሎ ተሎ ተሎ በመውደቅ እና ለራሱ ጥንቃቄ ማድረግ ብዙም ግድ የማይሰጠው ከዲራም ቢሆን ብዙም ድርሻው የጎላ ሳይሆን ግን በቡድኑ ውስጥ ሁልጊዜም ይኖራል። ስለዚህም የእነ ኡዚል፤ የነቦቴ ትህትናዊ የረጋ እና የሰከነ ቅንነት የአዳዲሶቹ የጀርመን ሳተና ተጫዎች ዕድል እንደ ተጠበቀው ሳይሆን ቀረ።
ብቻ ዘንድሮ በጠ/ ሚር አብይ የካቢኔ ጉዞ ምርኮኛ ስለሆንኩኝ ሁሉን ነገር ስለምክታትል እንደዛ የሚናፍቀኝን ጨዋታ በሙሉ ቀልቤ ሁሉንም ለመከታትል እልቻልኩም። ሰብሩ ዝና ብዙ ስለሆነ።

ከሰበሩ በላይ የልግመኛውን ፖለቲካ ጉዞ እና ዕድሜ የሚገስጽ፤ የሚያርቅ የሚገራ ንግግር ስለማደማጥ ጤናዬን ያጣሁበትን መዳህኒት ስላገኘሁኝ ለዚህ መንፈስ ጋር በጽኑ ፍቅረኛ ሆኜ ሙሉን ማዳመጥ ባልችልም የተወሰነው ቀልቤን ሰጥቼ ለማዬት ሞክሬያለሁኝ። በሲዊዝዬ ከአርንጀንቲና ጋር በነበረው ጨዋታ እጅግ የተደስትኩበት ነበር። እረክቻለሁም።

ሌላው የፍፃሜ ጨዋታ ዓይነት አዎንታዊ የነበረው ድንቅ የጨዋታ ጥበብ በሙሉ ሞራል ያዬሁበት፤ ጀርመኖች ሄፍተግ ነው የሚሉት ዓይነት፤ እጅግ ፋታ እለቦሽ ደግሞ አግሬስብ ያልሆነ ግን ኢንቴነሲብ የሆነ ጨዋታ የራሺያ እና የእኛዋ የአፍሪካ የግብጽ ነበር።

የዓለም የኮከቦች ኮከብ የአፍሪካ ተስፋ የሊበርፑሉ አህመድ ሳልህም ስለነበርም እሱን በሙሉ አቅሌ አደብ ገዝቼ ተከታትዬዋለሁኝ። ግብፆች ከእግር ይልቅ የጭንቅላት ትርኢት ነበር ያሳዩት። እርግጥ ነው በሰፋ ልዩነት መጨረሻ ላይ 3 ለአንድ በሆነ ልዩነት ቢሸነፉም አቅማቸው ግን አንቱ ነበር። ኮርቸባቸዋለሁኝ። መኩራት ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ የዓለም ዋንጫን የምትወስድበት ማግሥታዊ ተስፋም ታይቶኛል።

ዛሬ የብራዚል እና የኮስተሪካ ጨዋታ እጅግ ማራኪ እና ልብ አንጠልጣይ የልቤም ሊባል የሚጋው ነበር። የኮከቦች ኮከብ ኒማር እና ማርሴሎን ጨምሮ ብራዚሎች ብዙ ደክመዋል ለማሸነፍ። 90 ደቂቃውን ገትሮ የያዘው የኮስቲ ጎል ጠባቂ በተጨማሪው 6 ደቂቃ ላይ ሁለት ጎል ደፈረችው እና ሪከርዱን ሳይወስድ ቀረ። ግን ጥንካሬው ከብረት ቁርጥራጭ የተሳራ ነበር ማለት ይቻለል።

77ኛው ደቂቃ ላይ ብራዚል የቅጣት ምት አግኝቶ የነበረ ሲሆን በ2014 የተጀመረው የሳይንስ መፍትሄ ኳስ ከመረብ ጋር ስትሞሸር የነበረውን ግድፈት የከላ ነበር፤ የዘንድሮው የሳይንስ ዕድምታ ደግሞ የቅጣት ምትን / ፔናሊቲን ህጋዊነት ችሎት ማን ደፍሮት ብሎ ኒማር ቁምጥ እንዳለ ቀርቷል፤ ነገር ግን ተጨማሪ ጊዜ ተጨማሪ ዕድል ሸለመው እና ብርዚል 2 ለምንም በሆነ ውጤት አሸንፈዋል። እርግጥ ነው ኒማር ቢጫ ካርዱንም ሰንቋል። 

የብራዚሉ አስልጣኝ ከደስታቸው ብዛት የተነሳ የመገመሪያዋ ጎል 91ኛው ደቂቃ ላይ ስትገባ አደናቅፏቸው ወደቁ። መቼም የ እግር ኳስ የጥበቡ ተሰምጦ አስልጣኞችንም ይጨመራል። የሚያሳዩት የመንገድ ላይ ትርዓት ሌላ ነው። ታውቃላችሁ የመንገድ ላይ ትርኢት ኮርስ እንዳለው እኔ ጀምሬው በክፎወች ምክንያት ኮርሱ ማታ ስለነበር አቀረጥኩት። የ የአስልጣኞች እንደዛ ነው በትከክል የመንገድ ላይ ቲያትር + ድምጽ አልባ ቲያትር ሁለቱም ራሳቸውን ያቻሉ የቲያታር ጥበብ ኮርሶች ናቸው።


ኒማር ተንበርክኮ ነበር ያለቀሰው። ብዙ ዕድሎችን ስቷል፤ በዛ ላይ የኮስቲ ጎል ጠበቂ እጅግ ብርቱ በጣም ጠንካራ ነበር። በ2014 ብራዚል በተስፋው በኒማር ለዋንጮ እበቃለሁ ብሎ ነበር። ጨዋታው የተካሄደውም በህዝቡ ማህል ስለነበር ተስፋው እጅግ ከፍ ያለ ነበር። ነገር ግን ከእስፖርታዊ ጨዋነት ያፈነገጡ የሴራ ሸሮች በአካሉ ላይ ጉዳት አደረሱ እና ለዋንጫ ሳይበቃ ቀረ የብራዚል ቡድን። ዛሬ በተጨመረች 6 ደቂቃ ነው ይህ ድል የተገኘው። 

አትዮጵያ ለማ በሚባል ነብይ የሥልጣን ሽግሽግ አድርጎ አብይን እንደ ሰጠን ዓይነት ነው የዛሬዋ ድል። እንዲህ ያሉ ድሎች በአግባቡ ከተያዙ መጨረሻቸው ያማረ ይሆናል። ራሱ ነብዩ ላማም እዛው ኦህዴድ ላይ መቀመጡ የ ኦህዴድ አቅም የኢትዮጵያ አዲስ የፖለቲካ ባህል ተቋም ስለሆነ ለማስቀጠል ሰቅ ነው።

ፓርቲ አባል መሆን አልፈልግም፤ በዛ ላይ ብሄረሰቤ አሮሞ አይደለሁም ግን ብሆን ቀደም ባለው ጊዜ የድንቁን የኮ/ ጎሹ ወልዴን ፓርቲ መድህንን አሁን ደግሞ የልቤን ኦህዴድን ነበር እምቀላለቀለው። መቀላቀል ብቻ ሳይሆን ህይወቴንም ልሰጥለት የምፈቀድለት። የምፈልገው ዓይነት ፓርቲ ነው። ጓድ ገብረመድህን በርጋ የተፈጠረው እንዲህ ላላ የፓርቲ ድርጅታዊ ጥንካሬ ስለነበር።

ወደ ቀደመው ስለመስ ዛሬ የኮስቲ ቡድን ሲሸነፍ ሲዊዝዬ ደረጃዋ ከፍ ብሎ እንዲታይ ያደርገዋል። ምክንያቱም የኮስቲ በር ጠባቂው በራሱ የጠንካሮች ሁሉ አንበል ስለነበር …

ዛሬ እንዲህ ሆኖ አልፏል … ብራዚል ዛሬ ተጨማሪ ደቂቃ በሰጠው ዕድል የበለጠ ፈጣሪውን አምስግኖ ለቀጣይ በረከቱ የሚያበቃ የመንፈስ አቅም ይኖረው ይሆን? አዎን እግዚብሄር የሚሰጠውን ዕድል አክብሮ አመስግኖ በጸሎት የማይቀብል ማንኛውም አጋጣሚ ይሾልካል … ስለዚህ „ልብ ያለው ሸብ“ እንላለን ልግማኛው ሴረኛው ሸረኛው የ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህልም ፈጣሪ መርቆ የሰጠውን የ ለማ የገዱ የ አብይ የ አንባቸውን መንፈስ አክብሮ የ108ቱን ተደሞ ተመስገን ብሎ ዘሃ እና ፈትል ሆኖ ዕንቁውን ትውልድ ለመግነባት መጣር አለበት። 

እድሎች ታቅደው ከመጡ ውጤታቸው እንብዛም ነው እንዲህ በድንገቴ ከሆነ ግን ትርፋቸው አልፋ ኦሜጋ ነው። አሁን ቅጽበታው የ ዓይን ለ ዓይን ግብታ ስንት ህይወትን ለናሙና ያበቃ ምርምር ያልተደረገበት መስክ መሰላችሁ። በቃ ድንገቴ የሚሰጣችሁ ዕድል በጥንቃቄ መያዝ ያስፈልጋል ወርቅ ከቀለጠ ይፈሳል።
እስፖርት የፍቅራዊነት አንባሳድር ነው!

አሁን በ2016 የአውሮፓ አግር ኳስ ውድድር ዳኛውም፤ ጋዜጠኛውም፤ ተጫዋቾችም በፍጹም የፍቅር ሥነ ጥበብ የዓለምን ቀልብ የሳበው ISL ከ NGA ሜዳ ላይ ናቸው ጨረፍ እያደርኩኝ እያየሁኝ ነው ይህን ዘገባ እምጽፈው። 

የኔዎቹ ለትሁቱ ትእግስታችሁ ቸርነትን ሸልሜ ኑሩልኝን መርቄ ልሰናበት።

ስለ ፍቅራዊነት Seregut Selassie YouTube እስቲ ይምጡለት።


ተባረኩ ቅኖቹ! መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።