የሙሳ ወፍ ዕድል ቀናት። ተመስገን!
ጠይም ዕንቁ በጣምራ ድል የሙሳ ወፍ ዕድል ቀናት።
ከሥርጉተ © ሥላሴ 22.06.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዝዬ)
„አቤቱ በአንተ ታምኛለሁ እና ጠብቀኝ።“ አሜን!
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፩)
ዋው ዋው ዋውውውው! ለዛውም ሦስት አደገኛ የመረብ ዕድል አምልጧቸው እኮ ነው አረንጓዴ ዕንቡጦች ዛሬን በድል ያቀለሙት። ተመስገን።
ብዙ ጊዜ ናይጀሪያ ከጭዋታ ውጪ ሲሆን እኔን ጨምሮ የሙሳ ጉዳይ ብዙ ሰው የሚያዝንበት ነበር። የዛሬው ጨዋታ የሙሳ ወፍ ዕድል ቀናት። አይስላድንዶች ከእነታዳሚቸው እጅግ ተወዳጆች ናቸው።
የጋራ የወል ቃናዊ ድምጽ አላቸው፤ ሌሎች ቡድኖች ሲያሸንፉ የእነሱን ሲቀዱ ፈጽሞ አያማርባቸውም ባለቅኔው ጠ/ ሚር ዶር አብይ ሲዳማወችን "ፊትችሁ ያመራል፤ ደስ ትላላችሁ" ነበር ያሏቸው አዎ በአግር ኳስ ጨዋነት የአይስላንድ ቡድን ደጋፊ ሞራሊዊ ነው። የፍቅራዊነት ተፈጥሯዊ መርህ ናሙና ናቸው። መሸነፋቸውን በደስታ የሚቀበሉ ፍጥረቶችም ናቸው። ብስጭት የላቸወም። ለስላሶችም ናቸው።
80.50 ላይ ፔናሊቲ እድል አግኛቷል የአይስላንድ ቡድን። ፔናሊቱ ግን ተሳተ። ዛሬ ወፏ ለጠይም ዕንቁ ቡድን አዳላች ልብል ፈረደች። ፈረደች ይሻላል አይደል?
የአፍሪካ ቡድን ሁልጊዜ አጨራረስ ላይ ችግር ነበረበት። ይህ የወል ፈተና ነበር። ዘንድሮ ግን በጣም የተሻሻለ ሁኔታ ታይቷል። የሞሮኮ ቡድን ቢሸነፈም ጠንካራ ነበር። የግብጹ ወደር የለሽ ነበር። ያው ኳስ አንድንድ ጊዜ ዕድልም ነው። ሴኒጋሎች የጀርምንን ኤፍ ፋው ቤ አይነት ፈጣኖች ናቸው። እነሱም አሸንፈዋል። አሁን ናይጀርያ ከአፍሪካ ሁለተኛ መሆኑ ነው።
ደስ ያለኝ ሙሳን ለማዬት ቀጣይ ዕድል ስለገኘሁ አንዱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ተስፈኛ ስለሆንኩኝ አፍሪካዊ ቡድን ለፍጻሜ ውድድር ብሎም ለዓለም ዋንጫ ተስፋን ሰንቄ ማዬትን እምኛለሁ ለማግስት … አሁን ባለው ሁኔታ በተለይ ዘንድሮ እጅግ ደስ ብሎኛል። ጥቡብ ማሪኪ ነበር። አፍሪካዊ ጠረኑ ያውዳል። እንኳን ደስ አለህ የአፍሪካ የእግር ኳስ ቁንጮ የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ መንፈስ።
ምንም ከአውሮፓም ይሁን ከእስያ እግር ኳስ ተጫዎቾች አንሰው አላገኘኋዋቸውም።
ይህ ዕድል ከረፈት ማግስት ነው ያገኙት። አላዛሯም ኢትዮጵያም ከወል የዕንባ ማግስት ያጘኝቸውን ዕድል ላለማጣት ልጆቿን መምክር አልባት። አብሶ የኢትዮጵያ እናቶች ልጆቸቸው በዬተገኙበት ቦታ ሁሉ ሰላማዊ ይሆኑ ዘንድ መምከር አለባቸው። የአላዛሯ ኢትዮጵያ እናቶች የ43 ዓመቱ ዕንባ በቃኝ ማለት አለበቸው። ለዬትኛውም ሸር እና ተንኮል ልጆቻቸው አጋፋሪ እንዳይሆኑ አበክረው መምክር ይኖርባቸዋል።
ወደ ቀደመው ስመለስ ስድስት ደቂቃ የባከነ ጊዜ ስትጨመር ለብራዚል የቀናው ደግሞ ለአይሳላንድ ይቀናው ይሆን ብዬ ልቤ እንደ ቅል ተንጠልጥላ ነበር። ግን ጠይም ዕንቁ አሸነፈ በጣማራ ድል።
በጨዋታ ብልጫ፤ በማጥቃት እንቅስቃሴው በጎሏ የአገባብ ጥበብ እና ነፍስነት ዋዋው እንዴት ነፍሴ እንደዘፈነች … ተመስገን።
በተረፈ ጠይም ዕንቁ በብቃት ጨዋታውን አሸንፏል። ሁለት ለምንም፤ ሁለት ለባዶ። ሁለት ለዜሮ ዋውዋውዋውዋው … ተመስገን! ቀጣዩ 20.00 ሰዓት ላይ ጨዋታ የእኔዋ ገዳማዊቷ አገር ሲዊዝዬ ከሰርብያ ጋር ነው ደስ ካለኝ፤ ሲዊዝዬ ካሸነፈች እዘግበዋለሁኝ። ከተሸንፍን ግን እእ …
እሺ የኔዎቹ እያኮመኮምኳችሁ ነው አይደል … ኑሩልኝ!
እስፖርት የመቻቻል ሰንደቅዓላማ ነው።
ከአክብሪ ናፋቂያችሁ መሸቢያ ጊዜ ታትሟል...
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ