#ብልጠት እና #ስልት።

 #ብልጠት እና #ስልት። 

 በ2014 እ.ኤ.አ በደጉ ሳተናው ድህረ ገጽ ከሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ነጥቡን አንስቼ ሞግቼበት ነበር። ጽፌበት ነበር። 

የሆነ ሆኖ ለመቆናጠጫ #ብልጠት ደራሽ፤ ቅጽበታዊ ሲሆን ለእኔ ሳላሞላቅቀው ቁልጭ ያለ #ማጭበርበር ነው። ታሪክም አልቦሽ።

 መስዋዕትነቱም የገዘፈ አስታዋሽ አልቦሽ የውሻ ደም ሆኖ ቀሪ። ስልት ግን በጠራ ዓላማ እና ፍላጎት የታነፀ፦ በቀነሰ መስዋዕትነት፤ እንዲሁም መስዋዕትነቱን #ዕውቅና #በሰጠ በተደራጀ የሃሳብ #ብቃት በስክነት የሚከወን የአቅም ልዕልና ከፍ ያለ ደረጃ ነው። 

ስልት የላቀ የሥራ ባህል ጥበብ ነው። የታወቅም // የተሰወረም ታክቲክ እና ስትራቴጂ በጊዜ፤ በሁኔታ፦ በአቅም የሚታሰቡ ትልሞች የሚቀመርበት። 

 አቅም መዋለ ንዋያዊ ብቻ ሳይሆን የሰውን የህሊና እና የጉልበት ችሎታን፦ በተጨማሪም ልምድን፦ ተመክሮን፦ ክህሎትንም ሁሉ ያካትታል። የነፃ አገልግሎትንም ይጨምራል ተመን የለሽ ቢሆንም።

 ሥርጉትሻ2024/07/20

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።