"የሰው ልጅ ለአንድ ዓመት በማርስ ላይ መቆየት ምን ሊመስል ይችላል?" BBC

 

 https://www.bbc.com/amharic/articles/cp38kpn71n8o

 

"የሰው ልጅ ለአንድ ዓመት በማርስ ላይ መቆየት ምን ሊመስል ይችላል?"

 

"ከጥቂት አስርት ዓመታት በፊት ወደ ቀይዋ ፕላሌት ማርስ የሚደረግ ጉዞን በልቦለድ ፊልሞች ብቻ የምንመለከተው ነገር ነበር።

ዛሬ ላይ ቴክኖሎጂ ዘምኖ፤ የተመራማሪዎች እውቅት እና ፍላጎት ዳብሮ ወደ ማርስ የሚደረግ ጉዞ እውነት ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ አለ።

ለዚህም ቅድመ ዝግጅት በሚመመስል ሁኔታ የሰው ልጅ ወደ ማርስ ለመጓዝ ቢነሳ ረዥሙን ጉዞ እና ተስማሚ ባልሆነ ቦታ መኖርን ለማላመድ አራት ሰዎች በማርስ አምሳያ ወደተሠራ ቦታ ከዓመት በፊት ተልከው ነበር።

ከአሜሪካ የሆኑት ኬሊ ሃስተን፣ ሮስ ባሮክዌል፣ ናታን ጆነሰ እና አንካ ሴላሪዬ የአንድ ዓመት የማርስ ቆይታቸው ምን ይመስል ነበር?

የናሳ ሳይንቲስቶች በሂዩስተን ቴክሳስ በሚገኝ የጠፈር ምርምር ማዕከል ውስጥ ወደፊት ተመራማሪዎች ወደ ማርስ ሲጓዙ ሊገጥማቸው የሚችለውን እንዲሁም ኑሯቸው ምን ሊመስል እንደሚችል ለማሳየት የማርስን አምሳያ ፈጥረዋል።

በማርስ አምሳያ ወደ ተሠራው ስፍራ የተላኩት አራት ተመራማሪዎች ለአንድ ዓመት ያክል በስፍራው ቆይተዋል። በዚህ ወቅት ተመራማሪዎች የአራቱን ግለሰቦች አካላዊ እና አእምሯዊ ጤና በቅርበት በመከታተል የተለያዩ ግዳጆችን እንዲፈጽሙ ያዟቸው ነበር።

አራቱ ግለሰቦች ለመጨረሻ ጊዜ ሰማይ ከተመለከቱ ዓመት አልፏቸዋል። ከሚወዷቸው ወዳጅ ዘመዶችቻው ተለይተው 12 ወራቶችን አሳልፈዋል። ።

ለ370 ቀናት ከተቀረው ዓለም ተገልለው በማርስ ሊኖር በሚችል ሁኔታ ውስጥ ቆይተዋል። ይህ ቆይታቸው ናሳ ካካሄዳቸው የጠረፍ ጉዞ ቅድመ ዝግጅቶች ረዥሙ ነው።

የዚህ ጥናት ዋነኛ ዓላማ ረዥም ጊዜን በሚፈለግ የጠፈር ጉዞ እና በማርስ ላይ በሚኖረው ቆይታ ተመራማሪዎች የአእምሮ እና አካላዊ ጤናቸው ሳይጓደል ግዳጃቸውን መፈጸም ይችላሉ ወይ የሚለውን ጥያቄ መመለስ ነው።

አሁን ባለው የቴክኖሎጂ ውጤት የሰው ልጅ ወደ ማርስ ጉዞ ማድረግ ቢጀምር ቀይዋ ፕላኔት ጋር ለመድረስ 9 ወራት ይፈጃል።

አራቱ ግለሰቦች ለአንድ ዓመት ያክል የቆዩበት አጠቃላይ ስፍራ በባለ ሦስት አውታር ዕይታ (3ዲ) የተገነባ 160 ስኩዌር ሜትር ስፍት ያለው ነው።

ተመራማሪዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠር ኪሎ ሜትር ርቃ ወደምትገኘው ፕላኔት የግንባታ ቁሳቁሶችን ይዘው መጓዝ የሚታሰብ ባለመሆኑ አራቱ ግለሰቦች ማርስ ላይ በሚገኝ ግብዓት ግንባታ እንዲያከናውኑም ተደርገው ነበር።

በማርስ ያለው የመሬት ስበት መጠን በጣም አነሳ መሆኑን እንዲሁም የጨረራ መጠኑ እጅግ ከፍ ያለ መሆኑን በማስታወስ በምድር ላይ የማርስን ትክክለኛ አምሳያ መፍጥር ጨርሶ የሚታሰብ አይደለም የሚሉት የናሳ ተመራማሪዋ ሱዛን ቤል ናቸው።

“ይሁን እንጂ” ይላሉ ተማራማሪዋ፤ “ይሁን እንጂ ወደ ማርስ ብንጓዝ ሊገጥመን የሚችለውን ሁኔታ መገመት የሚያስችል ተቀራራቢ ነገር ለመፍጠር ተሞክሯል” ይላሉ።

አንድ ዓመት ሙሉ አራቱ ግለሰቦች ወደ ጠፈር ቢጓዙ ሊመገቡ የሚችሉትን የታሸገ ምግብ ብቻ ሲመገቡ ቆይተዋል። በተዘጋጀላቸው አነስተኛ ስፍራ እራሳቸው የሚመገቡትን ተክል እንዲያበቅሉም ተደርገዋል።

በዚህ ቆይታቸው ወቅት ከባዱ ፈተና የነበረው መረጃ ልውውጥ ነበር። በምድር እና በማርስ መካከል ካለው ረዥም ርቀት የተነሳ ከምድር የተላከ መልዕክት ማርስ ለመድረስ 24 ደቂቃ ይወስዳል። አራቱ ግለሰቦች ጥያቄ ልከው ምላሽ እስኪያገኙ ድረስ 48 ደቂቃ መጠበቅ ነበረባቸው።

ይህ ማለት ደግሞ ጠፍርተኞች አስቸኳይ ምላሽ የሚፈልግ ችግር ቢገጥማቸው ምድር ላይ ካሉ ባለሙያዎች ድጋፍ ውጪ በራሳቸው ለገጠማቸው ፈተና መፍትሄ መስጠት ይኖርባቸዋል።

ተመራማሪዎች አራቱ ግለሰቦች ለአንድ ዓመት የቆዩበትን ሁኔታ ዲዛይን ያደረጉት የቴክኒክ ችግሮች እንዲገጥሙ እና ያልታሰቡ ፈተናዎች እንዲከሰቱ አድርገው ነው።

ሱሳን ቤል እንደሚሉት አራቱ ግለሰቦች ያልጠበቁት ፈተና እንዲገጥማቸው የተደረገበት ምክንያት ጠፈርተኞች በትክከለኛው ዓለም ወደ ማርስ ሲጓዙ የሌሎች እርዳታ በሌለበት እና ጫና በበዛበት ሁኔታ ትክክለኛ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ምን ዓይነት ውሳኔ ይወስናሉ የሚለውን ለማወቅ ነው ብለዋል።

የአራቱ ግለሰቦች የአንድ ዓመት ቆይታ ወደፊት ወደ ማርስ ለሚደረገው ጉዞ ግብዓት ይሆናል ተብሎ ቢታመንም ሙከራውን የተቹ ሰዎችም አሉ።

አንዳንዶች ደግሞ ጨርሶ ሰዎችን ወደ ማርስ መላኩ ከፍተኛ ወጪ ከማስወጣቱ በተጨማሪ ደኅንነትን ማረጋገጥ አይቻልም ይላሉ።

በዚህም ከሰዎች ይልቅ ሮቦቶችን ወደ ማርስ ለመላክ ማቀዱ ወጪ ቆጣቢ እና ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወትን አደጋ ላይ አይጥልም ይላሉ።

የሩሲያ አካዳሚ ኦፍ ሳይንስ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ሌቭ ዜሌኒ ግን ይህ ልምምድ ዋነኛውን ፈተና የዘነጋ ነው ሲሉ ይተቻሉ።

እኒህ ሩሲያዊ የጠፈር ተመራማሪ የናሳው ፕሮጀክት የሰው ልጆችን ወደ ማርስ መላክ የሚቻልበት አስተማማኝ መንገድ ሳይመቻች ማርስ ላይ እንዴት መቆየት ይቻላል የሚለውን ለመመለስ የሚጥር ነው ይላሉ።

“ሰዎችን ደኅንነቱ በተረጋገጠ ሁኔታ ወደ ማርስ መላክ እንደሚቻል አይታወቅም” የሚሉት ሌቪ በማርስ ካለው ጠንካራ ጨረራ ሰዎችን መከላከል የሚያስችል ቴክኖሎጂ እንደሌለም ጨምር አስረድተዋል።"

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?