እህህህህ"በአሜሪካ የኢሚግሬሽን ባለሥልጣን ቁጥጥር ስር የነበረው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ሕይወቱ አለፈ" BBC

 

 

"በአሜሪካ የኢሚግሬሽን ባለሥልጣን ቁጥጥር ስር የነበረው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ሕይወቱ አለፈ"

 https://www.bbc.com/amharic/articles/cly7q2ee228o

 

 ስደተኛው ተይዞ የቆየበት የኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ ባለስልጣን (አይስ) ኢሎይ የማቆያ ማዕከል

በአሜሪካ የኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ ባለሥልጣን (አይስ) ቁጥጥር ስር የነበረ ሠራዊት ገዛኸኝ ደጀኔ የተባለ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ሕይወቱ ማለፉ ተገለጸ።

የ45 ዓመቱ ስደተኛ ፊኒክስ ግዛት በሚገኝ የባነር ዩኒቨርስቲ የህክምና ማዕከል ተኝቶ ህክምና ሲደረግለት እንደቆየ እና ጥር 21/2017 ዓ.ም. ዶክተሮች መሞቱን ማረጋገጣቸውን ባለሥልጣኑ ከቀና በፊት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ስደተኛው በህክምና ላይ የነበረ ቢሆንም ለሞት የዳረገው ትክክለኛ መንስዔ ምን እንደሆነ አለመታወቁን አንድ የህክምና ባለሙያ ሪፖርት አድርገዋል ተብሏል።

ሠራዊት ከታኅሣሥ 14/2017 ዓ.ም. ጀምሮ በአሪዞና በሚገኙት ባነር ካሳ ግራንዴ የህክምና ማዕከል በኋላ ደግሞ በባነር ዩኒቨርስቲ የህክምና ማዕከል ተኝቶ ሲታከም እንደነበር በምህጻሩ አይስ ከተሰኘው የአሜሪካ ኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

እንደ አይስ ከሆነ ሠራዊት ወደ አሜሪካ የገባው ባለፈው ዓመት ነሐሴ 13/ 2016 ዓ.ም. በሉክቪል አሪዞና አቅራቢያ በኩል ነው።

ወዲያውኑ በአሜሪካ የድንበር ጠባቂዎች ተይዞ በአስቸኳይ ከአገር እንዲወጣ የሚያዝ ማስጠንቀቂያ ሰጥተውት ነበር።

ሠራዊት አሜሪካ ከገባ ከሁለት ቀናት በኋላ በአሜሪካ የኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ ባለሥልጣን (አይስ) ኢሎይ የማቆያ ማዕከል እንዲዛወር ተደረገ።

 

ግለሰቡ መስከረም ወር ላይ በኢሚግሬሽን ችሎት ዳኛ ፊት ቀርቦ የነበረ ሲሆን፣ የጥገኝነት ማመልከቻውን እንዲሁም ከአገር እንዳይባረር የሚያግድ ጥያቄ እንዲያቀርብ መፍቀዳቸውን ከአይስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሠራዊት ከወራት በኋላ በማቆያ ማዕከሉ መዝናኛ ስፍራ ራሱን መሳቱን በማግስቱ ታኅሣሥ 11/2017 ዓ.ም. ለማዕከሉ አስታውቋል።

የልቡ ምት ከፍ ማለቱን እና በድካም ላይ የነበረ መሆኑን ተከትሎ ባነር ካሳ ግራንዱ ወደተሰኘው የህክምና ማዕከል ህክምና እንዲያገኝ መወሰዱን መግለጫው አመልክቷል።

ሠራዊት በህክምናው ወቅት ካንሰር (ሊምፎማ) ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሞ ከተቋሙ ከካንሰር ባለሙያ ጋር እንዲገናኝ ቀጠሮ ተሰጥቶት በማግስቱ ወደ ማቆያ ማዕከል እንዲመለስ መደረጉን መግለጫው አክሏል።

ሠራዊት ታኅሣሥ 14 እንደገና ወደ ማዕከሉ ተወስዶ ለቀናት እስከ ታኅሣሥ 22 በህክምና እንዲታገዝ መደረጉ ተገልጿል።

በኋላ ላይ ግን ለተጨማሪ ህክምና እና እንክብካቤ ሲባል በአየር አምቡላንስ ወደ ባነር ዩኒቨርስቲ የህክምና ማዕከል መዛወሩንም መግለጫው አስፍሯል።

ከዚያ በኋላ በበለጠ መተንፈስ እንዲችል ቱቦ ተተክሎለት እንደነበር የጠቆመው መግለጫው ጥር 21/2017 ዓ.ም. ሕይወቱ አልፏል ብሏል።

ባለሥልጣኑ በተጨማሪ ስለ ስደተኛው ሞት የሚመለከታቸው አካላት የአገር ውስጥ ደኅንነት መምሪያ ዋና ኢንስፔክተር፣ የአይስ ባለሥልጣናት ማሳወቃቸውን አመላክቷል።

መግለጫው በተጨማሪም ለስደተኛው ዘመድ ሞቱን ማሳወቁን አክሏል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?