ይድረስ ለአቶ ጌታቸው ረዳ! (ከጸሐፊ አቶ መስፍን ማሞ።)


እንኳን ደህና መጡልኝ።

ይድረስ ለአቶ ጌታቸው ረዳ!
“አውቃለሁ ለኅጣእ ግን ደህንነት የለውም፤
በእግዚአብሔር ፊት አይፈራምና፤
ዘመኑ እንደ ጥላ አትረዝምም።
መጽሓፈ መክብብ ፰ ቁጥር ፲፫

ከጸሐፊ አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ
ጥር 2011 ዓ/ም (ጃንዋሪ 2019)
ሲድኒ አውስትራሊያ


አቶ ጌታቸው ሆይ - ዕውን የነበረከት እስር ደንቆኃል? ወይንስ ነግ በኔ ታይቶህ ደብሮኃል? አዎ ባንተ ልኬት እነ በረከት በሙስናው ዝቅተኛ ወለል ላይ የሚገኙ ናቸውና የታሰሩበት ምክንያት ፖለቲካዊ ነው ብለሃል። (ይገርማል ደግሞ የዝርፊያቸውንም ልክ ታውቃለህ ማለት ነው?)

ለማንኛውም እስራቸው ፖለቲካዊ መሆኑን ለማን ነው የምትናገረው? ለራስህ ከሆነ ዕውነት ብለሃል። አንተና በረከት ሞክሼህ ጌታቸውና ሁላችሁ በህወሃት አቁማዳ ውስጥ ሆናችሁ ከኢኮኖሚው በባሰ በፖለቲካው የሰራችሁትን ሰቆቃ ታውቃለህና!


አዎ! እንኳን እኛ ዓለም በረከትን የሚያውቀው በዘር አጥፊነቱ <በናዚስት ጎብልስነቱ> ነው። ስለ በረከት <ናዚስታዊ ተግባር> (የኛን ዝርዝር ለጊዜው አቆይተን) የአውሮፓ ፓርላማን ስመ ጥር አባል ወ/ሮ አና ጎሜዝን ዋቢ እንሰጥሃለን። ክሱ ከምንጠበቀው ከፍታ ላይ እስኪወጣ <አይነኬው> በረከት <በኢኮኖሚም> ቢሆን መታሰሩ ወደ እናንተ መቅረባችን ነውና እኛ ደስ ብሎናል!



ደግሞምኮ መንግሥት ነኝ ብሎ ሀገር መዝረፍ፤ የድሃ ጥሪት መግፈፍ ያስቀፈድዳል - በተዘረፈ ሀብትና ንብረት ክምችት መለኪያችሁ ወለልም ላይ ሆንክ ጣራ ላይ!!
ዘንድሮ ከነዶችህ አይቀርላችሁም። ረስተኸው ከሆነ <እሳትና ጭድ> በሚለው የዘር ዕልቂት ፕሮፓጋንዳህ ትጠየቅበታለህ/ ትጠየቁበታላችሁ! ለሁሉም ጊዜ አለው - እንዲል መጽሐፉ።

በነገራችን ላይ የሚከተለውን አባባልህን አንተና ግብረ-አበሮችህ ተዋንያን ለነበራችሁበት ዘመነ ህወሃት የተናገርካት ስላቅ ነች ብዬ አምናለሁ። «አንድ ሰው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚያደርግ ወይም የክልል ወይም የፌዴራል መንግሥትን የሚተች በመሆኑ ለእስር የሚዳረግ ከሆነ ተገቢውን ፍትህ ያገኛል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው።»


“ጉድ ነሽ የአንኮበር ቅጠል ከማቃጠልሽ የመለብለብሽ” - አሉ! አይ የድሮው ኮሙኒኬሽን ኃላፊ¡ - የሃያ ሰባት ዓመት ስራችሁን እኮ ነው በቢቢሲ አማርኛ በኩል ያወጅከው!!! “ለቀባሪው አረዱት” - እንዲሉ።



ጉድኮ ነው ባካችሁ! «አፍ ሲያመልጥ ፀጉር ሲመለጥ አይታወቅም»  ደግሞ ሰነባብቶ ተረኛው ማናችሁ ትሆኑ? መቼም ዘንድሮ ዜናው ሁሉ ለእኛ ቸር ለእናንተ መርዶ ነው!!



ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይታደግ! አሜን!


https://www.youtube.com/watch?v=pGOaAWaswu0

Ethiopia: "አቶ በረከትና አቶ ታደሰ በሙስና መጠርጠራቸው አስደንቆኛል" አቶ ጌታቸው ረዳ

ፍትህ “ፍትህን” በረገጧት ሁሉ ላይ ትስፈን!

ይሁንልን፤ ይደረግልን! አሜን!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።