ከመጋቢት 24 ጀምሮ የተጠለፈው የሴራ ጉንጉኑ ሊፈታ ጥቂት ቀናት ቀርተውታል

የወለም ዘለም ዘለበት
የተስፋ መባቻ ክስመት።
„የማይታዬው፤ ከዚህ የሚበልጠው ፍጥረቱ ግን ጥቂት ብቻ ነው።“
መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፵፫ ቁጥር ፴፪

ከሥርጉተ©ሥላሴ 30.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


ዛሬም እዛው አቶ ጃዋር መሃመድ ሰሞነኛ መግለጫ ሁለቱን ብቻ አነሳለሁኝ። እርግጥ ተያያዥ ሁኔታዎችን ማንሳት ግድ ይላል። የተለመደው የጭንቅ ጊዜ ዓመት ድገሙ እያለን ስለሆነ። መጋቢት ደግሞ ተመልሶ በወርሃ መሰከረም ዱብ ብሎ ጭንቀትን ያስኮተኩተናል። 

ስለምን በሰሞናቱ ነገር ምነው ዝምታ ተብያለሁኝ። የኦሮሞ 5 ድርጅቶች ሚዲያቸው እና ተከሳሹ ኢሳት እስከ ግንቦት7 ያለውን ሙግት ሁለቱም በአካል መሬት ላይ ስላሉ ተከታዮቻቸውም ሙሉ ስለሆኑ እንደ ቀደመው ጊዜ ተጠቃ የምለውን ወገኜ ሙግቱ ይብቃኝ ስላልኩኝ ነው። አዬሁት እስኪበቃኝ።

ሁሉም ለወገኑ እንጂ እንደ እኔ ያለው ተማላ ገብቶ ከሳት መረመጥ ከምንም የማይቆጠር እንዲያውም በተደጋፊው አቅም ልክ ደጋፊውን በዘመቻ የሚያጠቃ ስለመሆኑ ተማርኩበት።

እንኳንስ ደጋፊን ዕውቅና ሰጥቶ ማገዝ ቀርቶበት ሌላ የማጥቃት ዘመቻው ቢቀር በስንት ጣዕሙ። ለዚህ ብልሁ ወያኔ ብቻ ነው። ደጋፊዎችን ጥሎ አይጥልም። ስለመሆኑም ዝምታ በስንት ጣዕሙ በሚል መነካካት አልሻም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ አምስግኑኝ እንጂ ውቀሰኙ ብሎ ፈቅዶ አያውቅም። ተመስግኖም አመስጋኙን ሲያጠቃ ነው የኖረው። ወደፊትም ጉዞው እንደዛው ነው።
  • ·       ሁለት ሀሳቦች ይነሱ።

በዚህ በሰሞናቱ የአቶ ጃዋር መሃመድ መግለጫ የዶር አብይ አህመድ ሙሉ ደጋፊ እንዲያውም ተሟጋች እና ተቆርቋሪ ሆኖ ቀርቧል። የለውጡም ሐዋርያ እና ለውጡን በማስቀጠል እንደሚታገም ገልፆልናልን። ለውጡ በማን ከተመራ ይሆን እሱ የሚደገፈው? 

አሁን ከዬካቲት 2010 እስከ ነሃሴ 2010 አቶ ጃዋርን ለተከታተል ሰው አይደለም የዶር አብይ አህመድ የቲም ለማ ደጋፊ ነበርን? ከቶ ሰውን የፈጠረ አማላክ ይህን እንዴት ያዬው ይሆን? ለዛውም ሃጅነቱ ታክሏል ይባላል? ሃጅነት እና ገሃዳዊ ዓለም?እም! የ ኢትዮያ ብልህ ኡሰታዞች ይፍረዱት። 

ቀድሞ ነገር ሚዲያቸው OMN ፎቷቸው እንዴት ይጸዬፈው እንደ ነበረ አያስታውሰውንም? ከጣና ኬኛ ወዲያ የምሥራች አልነበረም ለኢትዮጵያ ህዝብ። ሚዲያቸው ጣና ኬኛ የተሳተፉ ድንቅ የቄሮ ታሪካዊ ወጣቶችን ምስል ሚዲያቸው ላይ ለማቅረብ አቅም ነበራቸውን? ታዛቢዎች አኮ አለን። 

እዛስ የኦሮሞ ልጆች አልነበሩንም? እነዛስ የቄሮ መንፈስ ረቂቅ ሞገድ አልነበሩንም?ይህም ይሁን ኦቦ ለማ መገርሳ ለማለት ሚዲያቸው አቅም ነበረውን? የኦሮምያ ክልላዊ መስተዳድር ፕሬዚዳንት በማለት ብቻ ነበር ዜና ሲኖር የሚሠሩት። 

መንፈሳቸው እንዚህን ብርቅ ወገኖች እንዴት ባለ መልኩ ይጸዬፋቸው እንደ ነበር እኔ በሚገባ ተከታትያቸው ነበር። ያን ጊዜ ሁሉንም ሚዲያ ተዟዙሬ አይ እና እታዘብ ነበር። ምክንያቱም መልካምነትን ለማስተናገድ አቅማችን ምን ያህል እንደሆነ ማጥናት ስለፈለግኩኝ።

የሁለቱ ምስል እንደ ጠላት ነበር የሚታዬው። በስተመጨረሻ ላይም ቢሆን ቢለጠፉም በአሉታዊ ነው። እኔ ፎቷቸው ደምቆ በአዎንታዊነት የማዬው ሚዲያ ሳተናው እና ዘሃበሻ ላይ ብቻ ነበር።

እኔ ፍተሻ አካሄድ ነበር። ምክንያቱ እግዚአብሄር ስለሰጠን መልካም ነገር የመቀበል አቅማችን መፈተሽ ግድ ይለኝ ስለነበር። እነሱ ለእኛ የሰጡን ነገር ቢኖር ትህትናን ነበር። ትናንሽ የሚባሉ ድጋፎች መጨረሻ ላይ ሲጠረቀሙ አቅም ጉልበት የመፍጠር ችሎታቸው የተቋም ያህል መሰረታዊ እና አስፈላጊ ስለነበር።
በጥቅሉ ቅባዕን ለመቀበል ዝግጁ አልነበርንም። አሁን ሌላ ቅብዕ ፍለጋ እዬመሳነ ነው አብሶ ኦዴፓ። 

እነዛን መልካም ድጋፎች የሚውጡ ሌላ ዲያቢሎሳዊ መንፈሶች ደግሞ እኛ ባዘጋጀንላቸው ማዳባሪያ ፋፉ። ነገ ግንባሩ ኢህአዴግ ምን ሊወስን እንደሚችል አይታወቅም። 

ለነገሩ አቅም ስለሚለው ፍልስፍና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዕውቀተ ቢስ ነው። የሆነ ሆኖ ለኦሮሞ ማህበረስብ በተለይም ወጣት ለሆነው ትውልድ መሪው አንድ ሰው ነው። አቶ ጃዋር መሃመድ። ለአውንታዊ ቢሆን መልካም ነበር። ጥንካሬው ብርቱ ነው። የሆነ ሆኖ የኦሮሞ ወጣቶችን ተጋድሎ ወደ ድል አደባባይ ያሸጋገሩት በረቀቀ ስልት እና ጥበብ ግን ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ ናቸው።

 እነሱም ብቻ አይደሉም የአማራ ሙሉ ህዝብ እና አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፤ አቶ ደመቀ መኮነን፤ ዶር አንባቸው መኮነን፤ ነፍሱን ቀድመን ያጣናት ቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው ፈቃድ የተከወነ ብልህ የተግባር ውጤት ነው።

ድል ለዛውም በድምጽ ለሚወራረድ ሂደት አንድ ብቻን የትም አያደርስም። ከሁሉ በላይ ለኦሮሞ ማህበረሰብ ታሪክ አንድ ልዩ የሰማይ ስጦታ ወንጌል/ ቁራን ነበር የተፈጸመው ገድል። ግን ግን ግን ዲያቢሎስ አይሆኑ እያደረገው ነው … ሌላው ቀርቶ ደግፎ የቆመው የአማራ መንፈስ ዕውቅናው ቀርቶበት ዘለፋው ቢቀርለት ምንኛ መልካም በሆነ ነበር። እፍረቱም የጋራ የወል ነው።

ታሪክ እኮ የሚበጀው እንዲህ መደጋገፍ ሲችል ብቻ ነው። የመተማ የሖንስ መሳዋት ዛሬን ሰጥቶናል አገር ማቆዬት ጨርቅ ማቆዬት ማለት አይደለም። አባቶቻችን ስለከበሩት እና ስላስቀጠሉት አገር አለን እንላለን። ታሪኩን መሳቀጠል የተሳነው የኦሮሞ ሊሂቃን፤ አክቲቢስቶች እና ጋዜጠኞች ናቸው።
የፈለገ ግድፈት ቢኖር እንኳን በዚህ ወቀት ይህን የመሰለ ትርምስ በራሱ በተጠቃሚው ማህበረሰብ መሪዎች መፈጠር እጅግ ያሳዝናል። ያንን ለማካካስ ምን ምህድስና እንዳለ ይገባኛል። ከግንባሩ ጉባኤ በፊት የተከወኑትም ባለቤት አልባ ህውከቶች ስለምን እንደተፈጸሙም ይገባኛል፤ ልብ አለኝ።  

ገዳ፤ ጉድፌቻ፤ ሞጋሳ በፍሬም የተሰሩ ፎቶውች በማድረግ የአባት/ እናት ቅርስን ቁሞ ቀር ያደረገ ሁኔታ ነው መሬት ላይ የሚታዬው። ሴራም ቢሆን ቅርስ አይደለም። የእነዛን ብርቅዬ መንትዮሽ አብርሃም ወ አጽብአሃም ድካምም ከንቱ በከንቱ … ጥቅሙን የሚጻረር ተጠቃሚ በምድር ያዬንበት ዘመን። ቢቀጥሉ በ አሃቲ መንፈስ የሚያካክስ ይሆን ነበር ... ግን ወፊቱ ? 

ወደ ቀደመው ምልስት ሲሆን የእነዚህ ብቻም ሳይሆን የብአዴን ምክር ቤት አባላት በሙሉ የሰጡት ሙሉ ድምጽ ነው ዛሬ የ ኦነጋውያን መንፈስን ለሚጋሩት ሁሉ ለሚፎከሩበት ድል የተደረሰው። 

ያንም ለመሸርሸር ብዙ ተደክሟል አሁንም በትጋት በአሉታዊነት እዬተሰራበት ነው። ብዙ ቅስም የሚሰብሩ ድርጊቶች ተፈጽማዋል። ቃለ ምልልሱ ለእኔ ፌክ ነው። ውስጥን ለመግለጥ የፈራ፤ ያልደፈረ ራሱን የሸሸ የግራጫ ገመና ነው።

ይህም ብቻ አይደለም የውጪው የኦሮሞ አክትቢስት እና አጋሮቻቸው ሲታገሏቸው እኛ ወጥተን ሞግተን፤ በኔት መረብ ዘርግተን ደጋፊዎችን በማበራታት፤ በማመስገን በአደባባይ በኢሜልም የሚጣውን ወቀሳ ታግሰን ፊት ለፊት በትጋት ተጋፍጠን ነው። የት ነበሩ ለመሆኑ እነሱ? ሁከት ነበር የናፈቃቸው። ዛሬ እነሱ የሚነግሩን ድሉም ውጤቱም ስኬቱም የእኛ ብቻ ነው ይሉናል። ይበሉን ደስ ይለናል። እነሱም ወገኖቻችን ስለሆኑ።

ድሉ የእነሱ ከሆነ አሁን በዛው ክልል የሚፈጠረውን ግድፈትም፤ ጭካኔዎችንም፤ ህውከቶችንም የእኛ ነው ብሎ መቀበል ግድ ይላል። እውነትን ለመድፈር አቅም አንሷቸው እያዬን ነው። መንግሥታዊ አካሎቻቸው ጸጥታን የማስከብር ክህሎት አንሷቸው እዬታዬ ነው። በመጀመሪያ ነገር የእኔ ታሪክ ብሎ ለመቀበል አቅሙም ፍላጎቱም የላቸውም።

በዛ ላይ ልዑል እግዚአብሄር መሬት ላይ ወርዶ አግዞ፤ ደግፎ፤ ረድቶ ያጎናጸፋቸውነው የመንፈስ ልዕልናም አፍረሰውታል። ለዚህ ማን ይፈርላቸው? እኔው ጅሏ ደጋፊያቸው ሥርጉተ©ሥላሴ። ቀጣዩ የኢህዲግ ግንባር ደግሞ አዲስ ትይንት ይዞልን ይመጣል። 

ሁለት ሊንኮችን ልለጥፍ ዶር አብይ አህመድን እንዴት ባለ አኳሆን ቀደም ባለው ጊዜ አቶ ጃዋር መሃመድ እንዳቀረባቸው። የሚገርመው አሁን የሰኔ 16 ጥቃት በሚመለከት „በኦሮሞ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ይላል“ ተከሳሹ። ይህን ቀደም ብሎ መሪያቸው አቶ ጃዋር መሃምድ BBN ላይ የሰጠውን ቃለ ምልልስ ማድመጥ እና መመዘን ነው። ሌላም አቀናጇ ኬኒያ እንደሚገኙ ይጠቅሳል የክስ መዝገቡ፤ ኬኒያም ሄዶ ነበር። አሁንም ሚዲያውን ለመጀመር ዝግጅት ላይ ነው። 

ቀደም ባለው በቃለ ምልልሱ ውስጥ በዶር አብይ አህመድ እና በዶር ለማ መገርሳ ህሊና ውስጥ የመክፈል ተግባር ነው የፈጸመው። አቅማቸው በአሃቲነት ኢትዮጵያን መታደግ እንዳይችሉ ሁለቱ በጥርጣሬ እንዲታያዩ በጥምርት  በሃቲነት የሚደጋፋቸውንም ከሁለት ነው የተረተረው። አንዲስ የአጥንት ጽንስ ፈጠረ። ይህን ያስተዋለው የለም። ያ ጽንስ ተረገዞ ነው የከረመው፤ መጪው የኢህአዴግ ጉባኤ ያገላግለዋል። 

በዚህ ቃለ ምልልስ ለዶር ለማ መገርሳ ደጋፊ በማሰባሰብ ዶር አብይ አህመድን አቅመ ቢስ የማድረግ ተልዕኮ ሆኖ ነው የተነሳው። ሊከሰቱ ይቻላሉ ብሎ የተነበያቸው ጉዳዮች ሳይከሰቱ በአንድ የሹመት ንግግር ጸጥ ሲሉ ህመሙ ነበር። ስለዚህም ተግቶ ሰራበት ብቻውን ግን አልነበረም።
  • ·       ጠ/ሚር አብይ አህመድን ሲገልጻቸው።

ቃለ ምልልሱ እንዲህ ይላል „የለማን ያህል ታዊቂነት፤ ተቀባይነት፤ ክህሎት ተክለ ሰብዕን እንዲሁም በሴኩሪቲ ሆነ በፖለቲካ ረገድ ምንም ልምድ የሌለው ሰው የምታመጣ ከሆነ የመደራደሪያ አቅም ስሌለው በቀጥታ የወያኔ ሃርነት ሎሌ ይሆናል“ ይለናል። በሌላ በኩል መግቢያው ላይ ያሉት ስታዳምጡት ደግሞ አሁን የተፈጠሩት ሠው ሰራሽ ችግሮች ታቅደው ሰለመከወናቸው ግብረ ምላሽ ይሰጠናል።

ውዶቼ፤ --- በጥሞና ቃል በቃል አዳምጡት አዱኛዎቼ። ራሱ ቃለ ምልልሱ ዶር ለማ መገርስ በዶር አብይ አህመድ ላይ የህሊና አድማ እንዲመቱ የሚያደርግ ጉልበታም አመክንዮ ነው። ይህን እያዳመጠ ነው የኢትዮጵያ መንግሥት ከአቅም በላይ የሆነ በራስ መተማመን ፈጥሮ አቶ ጃዋር መሃመድ እንዲገባ በክብር የፈቀደው። አሁን መሬቱ ላይ ነው። እያንዳንዱ ሰከንድ ጦርነት ላይ ነው ያለው። ይህን ጉዳይ እንዳይታወቅበት ነው አሁን የመከላከያ የሚመስል ቃለ ምልልስ ሰሞኑን የሰጠው። ለነገሩ በቅርቡ ትልቅ ሃይል አለው። 
  • ·       የሁሉም መከራ መግለጫ ዓውድ።

ይህ ቃለ ምልልስ በተለያዬ ጊዜ ጽፌበታለሁኝ። አሁን የሚሰጡ ትንተናዎች፤ ውይይቶች፤ ግምቶች ሁሉ ይህን ቃለ ምልልስ ልብ በሎ የ አብይ ካቢኔ ሊሂቃን ቢመረምረው መልሱን ያገኝበታል። ሌላውም አቅጣጫው ያልገባው ወገንም እንዲሁ አደብ ገዝቶ ሥራዬ ብሎ ቢከታተለው ይነገረዋል ቀድመው የተሰሩ ንድፎች ምን እንደነበሩ። ለነገሩ እኛ ወሳኝ በሆኑ የነፍስ ጉዳዮች ያለን ምልከታ ከጥፋት ማግስት እንዲ ከጥፋት መቅደም አይደለም።

ራሱ የአብይ ካቤኔ ይህም ቃለ መልልስ አንድ በ አንድ ቁጭ ብሎ ያዳመጠው፤ የገመገመው አይመስልም። ሌላው ቀርቶ አገር እንገባለን ብለው የወሰኑት ሊሂቃንም ይህን ቃለ ምልልስ ጉዳያቸው አልነበረም። እኔ ወደ ስድስ ሰባት ጊዜ ለጥፌዋለሁኝ።

ሕወሓት ለማ መገርሳን ለጠቅላይ ሚኒስተርነት ለምን አልፈለገችውም?
 – ጀዋር መሐመድ ያብራራል | ከሳዲቅ አህመድ ጋር ተወያይቷል

ይህን ቃለ ምልልስ ከሰማሁኝ በሆዋላ ነው በስትራጄዲና በኮሚዲ በብርሃን እና በጨለማ በሳቅ እና በዕንባ ማህል የተፈጠረ ፍጡር ፍለጋ ስማስን „ግራጫማ ሰብዕናን“ የሚል ዕሳቤ ያመጣሁት በዚህ ምክንያት ነው። ሰቆም አያውቅ አልቅሶም አያውቅ መንፈሱ። 

ከዚህም አልፌ አምላኬን ባገኘው አቶ ጃዋር መሃመድን ስለምን እንደ ፈጠረው እጠይቀው ነበር ያልኩትም ይህን ቃለ ምልልስ ካዳመጥኩኝ በሆዋለ ነበር። 
ገና ምኑ ታይቶ ጃዋርውያን መንፈሱ እስከዬት ሊሄድ እንደሚችል። ሁለተኛ እርእስ ከተማውን ሰሞኑን ኬኒያ ላይ አድርጓል። ለማን ለመቅረብ … አሜሪካን ራሱ አጥንቷታል። በዬሄደበት ቦታ ለጥናት ነው የሚሄደው። ጥናቱ ሥሙን  በአለም አደባባይ በአንድ ተግባር ማስጠራት። 

አንድ ጀርመናዊ ወጣት ህልሙ ይህ ነበር። ረዳት አውሮፕላን አብራሪ ነበር። ህልሙን ያሳካው እሱን ራሱን ጨመሮ ውደ 150 የሚጠጉ ነፍሶችን እሬሳቸው እንዳይገኝ አድርጎ አመድ በማድረግ ነው። ልብ ይስጠን። 

አቶ ጃዋር መሃመድን ያህልን የከይሲነት ዒላማ ተሸክማ ኢትዮጵያ ሰላማችን በእጃችን ነው ትለናለች። ቀልደኛ!ራሷን ማዳን አይደለም የዓለም ጠንቅ ተቋም መክፈቷን ልብ ያላለች።  

  • ·       አቶ ጀዋር መሸነፍ ስንቁ አይደለም። ሲያሸንፍ ደግሞ ተሸናፊ ላደርገው አምክንዮ በፈተነው አምክንዮ አቅም ልክ ጎልቶ መውጣት ነው። ይህንን እኔ ለረጅም ጊዜ አጥንቼ የደረስኩበት ጉዳይ ነው። የተፈጠረው በናዚዝም ፍልስፍና ውስጥ ነው። ተልዕኮውም ይኸው ነው። ለዚህ የሚመች ለም ሃብት አለው። አቅሙ ከኢትዮጵያ በላይ ነው። ይህን መቀበል ግድ ይላል። የሚያቃልሉት አሉ። እኔ ደግሞ የናቁት ይወርሳል ነው የምለው።

------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

ቀጣዩ ደግሞ ተቆርቋሪ ሆኖ ያቀረበበት የዛሬው ልብጥ ጢባ ጢቦሽ ነው፤ ለውጡን ደጋፊ ሆኖ ያቀረበብት ነው። አቶ ጃዋር መሃመድ ዕድሉን ካገኜ አይደለም ኢትዮጵያ አፍሪካም ወዮልሽ ነው።

እንዲህ ያሉ ሰብዕናዎች በተፈቀደላቸው ልክ የተፈጠሩበትን አፍራሽ ተልዕኮ ይፈጽማሉ። በመልካምነት ቢሆን እኔ ልሞገትለት በፈቀድኩኝ። ግን ለእኔ ግራጫማ ሰብዕናው ለአፍሪካም አስጊ ሆኖ ይታዬኛል። ሉላዊ ዓለምም ከአሁኑ ይህን ጉዳይ ባሊህ ካለለው የሱማሌ፤ የአፍጋን፤ የሶርያ ታሪክ ኢትዮጵያ ውስጥ ይፈጸማል። የሚታዬውም ይሄው ነው። ገና ቀጣይ ጉድም አለ። 
  • ·       ራስን ለጥቃት ላለማጋለጥ በመከላከያነት።

Ethiopia:በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አቶ ጀዋር መሀመድ የሰጡት ትንታኔ:OMN

መከላከሉ ትጥቅ ለማስፈታት ነው። ለማዘናገት መረቡን መዘርጋት እንዲመቸው ነው። በዚህ ሁለት መሰረታዊ ነገሮችን ማንሳት እሻለሁኝ። የመጀመሪያው ቀደም ባላው ጊዜ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ኦቦ በቀለ ገርባን ጠ/ ሚር አድርጎ ቢሾም እንኳን አንቀበለም ብሎናል። ኦቨር ወያኔ ብሎ ነግሮናል።

ስለዚህ አሁን እንዴት ይህን ለውጥ ሊቀበል ይችላል? ለዛውም ጊዚያዊ ምርጫው የሆኑት ኦቦ በቀለ ገርባ ባልሆኑበት ሁኔታ። ሌላው አዲስ አባባ „በቀለበት ውስጥ ነበረች ብችል አሁን ማን ከልካይ አለኝ“ ያለውን ነገር ስናነሳ ደግሞ እና የቡራዩ ምክንያታዊ መንስኤ ስንመለከት የቀደመ መሰናዶ እንዳለ እናያለን።

ከዚህም በላይ ተጠቂዎች ካለፈው ዓምት ጀምሮ ጥቃት እንደ ተፈጸመባቸው እና በስጋት ዓመቱን ሁሉ እንደባጁ ነግረውናል። ሌላው ቀርቶ ለምን ተረዱ ተብለው ወጣቶችም ታስረዋል። በቀለበት ውስጥ ማለት ታዲያ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ይሆን እንዲህ ሻታ የሚዞረው። ከስሜን አሜሪካ መልስ ደጎስ ያለ እግታ እና የቅደመ ሁኔታ ጉዳይ እንዳለ ገልጬ ነበር። የአሁን የኢህአዲግ ጉባኤ ይገላግለዋል። ከመፈንቅለ መንግሥት የተሻለ ዕድል ይኖራዋል ለውጪው ማህበረሰብ። 

ወደ ቀደመው ስመለስ "በቀለበት ውስጥ" ቀድሞ ለተደራጀ መንፈስ ቀድሞ ለተሰናዳ መሰናዶ እራሱ እዬመሰከረ ከእውነት አደባባይ ጋር መጋፈጥ አስፈላጊ አይመስለኝም። ምክንያታዊ የሆኑ ተጨባጭ አመክንዮዎች እጅ ላይ ተቀምጠው።

 የያካባቢው ግጭቶች አገር መሪ አልባ ናትን የሚያሰኝ አመክንዮ አለው። የዛ የመነሻ የአቅጣጫ አመልካች ዕድምታ የጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ቃለ ምልልስ ሁሉንም ይመልሳል። ለማ ወደፊት ካልመጣ „ይፍረከረካል“ ነው ያለን? የምናያውም ይህንኑ ነው። ቀጣዩ ጠ/ ሚር እሳቸው ይሆኑ? ለጊዜያዊ ማስተዛዘኛ? አሱ ግን ይህም አያራካውም … ለጊዚያዊ ነው አጃቢዎቹን ከፍና ዝቅ የሚያደርጋቸው። የ እሱ ህልም ዓለምን ማመስ ነው። 
  • ·       ቀጣይነት በአጥቂነት መንፈስ።

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ
Ethiopia:በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አቶ ጀዋር መሀመድ የሰጡት ትንታኔ:OMN

ሊንኩ ደግሜ የለጥፉኩበት ምክንያታዊ ነው። ዶር ለማ መገርሳ እሬቻን ባዕል አከባበር በሚመለከት የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በትክክል ከአንድ ክልልዊ መንግሥት አካል የሚጠበቅ ነው።

እሳቸው ያላቸውን ያህል ሥልጣን ራሱ አቶ ጃዋር መሃመድ ሙሉ የመንግሥት ተቋማት እንዳለው ሁሉ እሱም መሰሉን ተግባር ሲያስከውን እንደቆዬ ነግሮናል።
በቀደመው ቃለ ምልልሱ በናሆ ቴሌቪዥን ስለ ስልጣን ሲጠዬቅ "አለኝ እኮ ከዚህ በላይ ምን ያስፈልጋኛል" ብሎን ነበር። አገር መሪነት ወይንስ የኢትዮጵያ የአገር መሪ ልዩ አማካሪ እንደ ኮነሬል መንግሥቱ ሃይለማሪያ የአሁኑ የዚንባሻ ሚና? ወይንስ የመጨረሻ ፊርማ አታሚ።  

ለመሆኑ ማነው መሪው? ሀምሌ 18.2010 ለሀምሌ 19.2010 ሌሊቱን ያዬሁት ህልም ወንበሩ ባዶ ሆኖ ነው? አንድ ሰው ግማሽ አካሉን አይቻለሁኝ። ያ ግምሽ አካል አሁን አገር ቤት ነው ግን አቶ ጃዋር አይደለም። ብቻ ወንበሩ ባዶነቱ እስከ አሁን ይምለሳል ብዬ ባስብም ባዶ እንደሆነ ነው። እኔ ደግሞ በህልሜ አምናለሁኝ። መጪው የግንባሩ ስብሰባ ላይ ሊኖር የሚችለው ሁኔታ ይወስነው ይሆን?

ቀጣዩ እጅግ አስጨናቂው ነገር ደግሞ ለጠፋው ጥፋት ሁሉ ተጠያቂ ዶር አብይ አህመድን የማድረግ ተከታይ መከራም አለ። ወንጀለኛ አድርጎ እንደ አቶ አብዲ ኢሌስ ዕጣ ቢሆንስ? ታሪካቸውን የማዋረድ ተግባር ነው እዬተሠራ ያለው። „መምራት ያልቻለ ራሱን ያውርድ“ መርህ ስለሚከተሉ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ እራሳቸውን እንዲያገሉ ልዩ ጫናስ ይኖር ይሆን? በዚህ ውስጥ ኦዴፓ ቲም ለማ ያለው ተመስጣሪነትስ?

በጥቅሉ ልዑል እግዚአብሄር ውብ ዘመን ሰጥቶን ነበር። መቀበል ያቃተን እኛው ነን። በዚህ ዙሪያ አቅም ያላቸው ነፃነት ፈላጊዎች ፍላጎት ቅንነት ምን ያህሉ እንደ ሆነ የዓመቱን ሙሉ የሃሳብ ጉጉስ ለተመለከተው እሱ ይመልሰዋል። ግን ዴሞክራሲስ - ነፃነትስ - ፍቅርስ - ትህትናስ - ይቅር ባይነትስ ለእኛ ይገባን ይሆን?
  • ·       ውዶቼ ሆይ!

በታላቅ ትህትና እምጠይቃቻሁ እና እማሳስባችሁ ሁለቱንም ሊንኮች በትእግስት አዳምጧችሁ እንድትፈርዱ ነው። እውነት የዶር አብይ አህመድን ካቢኔ አቶ ጃዋር ወዶት ደግፎት ነው ወይንስ ገዝግዞ ለመጣል ከሴሮኞች ጋር ሆኖ እያረደው ነው? 

በነገራችን ላይ እትጌ ኤርትራስ የቱ ላይ ናት? ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ባይቀጥሉ ስምምነቱ እንዴት ይሆናል? ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ባይቀጥሉ  የአፍሪካ ዕጣ ምን ይሆናል? ጠ/ ሚሩ ባይቀጠሉ ዓለም በኢትዮጵያ ህዝብ የአስተሳሰብ ልቅና፤ ሥልጣኔ፤ ተራማጅነት ላይ የሚኖረው ዕድምታ ምን ይሆናል?አሁን አምደኛነቱ ገጹ ተለውጧል - ጃዋር ማለት እንዲህ ነው። ካላሸነፍ አይተኛም፤ አያንቀላፋም። 

ጠ/ ሚሩ ባይቀጠሉ ኦነጋውያን እና ወያኔ ሃርነት ትግራይ በምን ሁኔታ የጫጉላ ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ? ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ባይቀጥሉ አምነዋቸው ወደ አገር የገቡት ብፁዐን አባቶቻችን ምን ይሆናሉ? ለነገሩ አንድ ብጹዕ አባት ኦሮምኛ ተናጋሪ ናቸው ይህን ሁሉ መከራ እዬሰሙ አገር ገብተዋል። ሚስጢሩ ምን ይሆን? ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ባይቀጥሉ እሳቸውን አምነው የገቡት የተፎካካሪ ፓርቲ ሊሂቃን እና አባሎቻቸው ምን ይሆናሉ? አብሶ ግንቦት 7 እስከ ደጋፊዎቹ ምን ይሆናሉ?

ዶር ለማ መገርሳን በማምጣት ጉዳዩን ማቻቻል ይሞክሩን ይሆን? ለመሆኑ አሁን ያለው የሃይል አሰላለፍ ማን ከማን ጋር የወገነ ነው? ግልጽ ያለ የሃይል አሰላለፍ እኮ የለም። ያለው ወያኔ ሃርነት ትግራይ እና በብአዴን መካከል ያለው መፈታታ ብቻ ነው፤ በአይዲዎሎጂም እንለያለን ባዮች ናቸው ብአዴኖች። ሁለቱም ሊገናኝ የማይችል መስመር እዬተከተሉ ነው።

ብአዴን ባርነት በቃኝ መርሁም በቃኝ ባይ ነው። ወያኔ ሃርነት እንደ አንድ ብሄራዊ አገር የቻይናን ኮሚኒስት ፓርቲ ጉባኤው አሳታፊ ሆኗል። ይህ ደግሞ ቻይና ለርዕዮቷ እንደምትሟሟት ሰፊ ግብረ ምላሽ ሰጥቶናል።

ሰሞኑ ከብአዴን ተሰናባቾች ሳጅን በረከት ስምዖን እና አቶ ታደስ የአዲግራት መስቀል ባዕል ላይ የክብር እንግዳ ነበሩ፤ ሃይማኖት አልባዎቹ የሃይሞኖት ታላቅ ሚስጢር ተጋባዥ። በሌላ በኩል አቶ ጌታቸው ረዳ ባሉበት እንደ ኩሬ ውሃ መቆማቸውን በብአዴን ጉባኤ በንግግራቸው አስደምጠውናል።

የሆነ ሆኖ ብአዴን እንደ ግንባር ይቀጥላል ወይ? ሰላማችን በጃችን ነው ነው ብለዋል ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ግን የውነት ነውን? የኦዴፓ የምክር ቤት አባላት ድምጻቸውን በድጋሚ በቀጣይነት ለመሪያቸው የመፍቀድ አቅም አላቸውን?

በመጀመሪያ የግንባሩ ጠቅላላ ጉባኤ ዶር አብይ አህመድን የማዕከላዊ ምክር ቤት አባል አድርጎ ይመርጣቸው ይሆንስ? ቢመርጣቸውስ ማዕከላዊ ምክር ቤቱ ሊቀመንበርነታቸውን ያጸድቅላቸው ይሆን? መፍንቀል መንፈስ እርግጠኛ ያደረጋቸው ነገር እንዳለ ጃዋርውያን እና ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብርእግዚአብሄር የሰጡን ብልህነት ደግሞ አለ፤ ብቻ ዘመኑና ፖለቲካው አድራሻቸው ቋታቸው ምን ይሆን?

ባዶ ወንበሩ እንደ ባዶ ይቀጥላል ወይንስ ፍትህን በተለዋጭ ቤተኛ ፊርማ ያገኛል?

  • ·       የጓንት መቆያ ቅኝት።

ኦነጋውያንን በመጨረሻ ላይ ደጋፊ የዶር ለማ መገረሳ ወደ ጠ/ ሚኒስተርነት ደጋፊ ያደረጋቸውን ሚስጢር ዶር መራራ ጉዲና ገልጸውልናል „ለማ ፊቱ ኦሮሞ ይመስላል“ ብለውናል። „አብይ ፊቱ ኦሮሞ“ አይለስልም ነው ቅኔው።
ስለዚህ ሁሎችንም የሚያስማማ መንፈስ ይፈልጋሉ ... 

ሌላው ቅደም ብዬ እንዳነሳሁት ዶር ለማ መገርሳን ቀድሞ ያወገዘው BBN የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ወደፊት መምጣትን ሲያውቅ ዶር ለማ መገርሳን ደግፎ ወጥቷል። ዋናው ነገር ግን የሳቸውን መንፈስ የቤት ሥራ መስጠት ነበር። ግፋ ከጎን ነን አይነት። ለእኛ ደግሞ ሁለቱንም እኩል እናይ ነበር። የተጋነውም ለዛ ነበር። 

የሆነ ሆኖ ያን ጊዜ የሆነው የመርህ ጉዳይ ስለነበር ኦህዴድ ቦታውን ይዞ የሚቆይለት ስላስፈልገው ነበር። ለምሳሌ ዶር ወርቅነህ ገበዬሁ ቢሆኑ አሁን ኦዴፓ ላቀደው ሰውም ልብ ላለው ጉዳይ መንገድ ጠራጊ አይሆንም ነበር። ጥርጣሬው ስለነበር። ቦታው የጠ/ ሚሩ ወንበር በኦዴፓ በሚያምኑት ሥር እንዲሆን ፈለጉ። በዚህ ማህል የአርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ሁነት እና ዕድምታም ሌላው ያልተዳደሰ አመክንዮ ነው። ይህ በራሱ በኦህዴድ/ በኦዴፓ ምን ያህል ተደጋፊ ነው? 

ያን ጊዜ ዶር ለማ መገርሳ በቀጥታ ለእጩ ጠ/ ሚር ለመወዳደር ከጉባኤ የመምጣት መርህ ግድ ይል ነበር። ያን የማቆያ ጊዜ እንደ ጓንት አብዩ ሸፍኖ ቆይቷል። ነገር ግን ትልቁ ችግር የሆነው አብይ በ100 ቀናት ያስመዘገበው ድንቅ ተግባር ከ10 – 30 ዓመት እንኳን ቢታሰብ የሃሳቡ ልቀት በራሱ ሚሊዮንን አሰለፈ።

በቀላሉ የአብይን የመንፈስ ዲታነት ለመናድ በሞትም፤ በምንም አልሳካ ሲል አገር የማወክ ተግባር ተጀመረ። 700ሺህ ወገን የተፈናቀለባት ኦሮምያ በክልሏ፡ለሚኖ ዜጎቿ ጥበቃ ለማድርግ አልችል አለች።

ስለምን? የአብይ ካቢኔ መሳጣት ስላለበት። የነበረውን ባለግርማ ታሪክ ጥላሽት መቀባት ስላለበት እንጂ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ኑሮ አይደለም አልነበረም። ምክንያቱም አቅማቸውን ብልህነታቸውን ስልታቸውን አይተናል የዶር ለማ መገርሳን። የኦሮሞ ድርጅቶችን ሆነ አክቲቢስቶችን በማሰባሰብ እና አቅም በመፍጠር ረገድ ዶር ለማ መገርሳ መደበኛ ሥራቸው ነበር። አቅም እና ሃይል በሚገባ ፈጥረዋል። የቀረው….?
  • ·       የቀረው።

የቀረው በየካቲት / መጋቢት እጩ የጠቅላይ ሚር ውድድር ስልት እና ስትራቴጂውን ባልታሰበ ፍጥነት ያስለወጠው የቲም ለማ መሰረታዊ አመክንዮ የድርጅቱ የዕጩ ተዋዳደሪዎች መርህ ነበር። ዶር አብይ አህመድ በምርጫ ውክልና፤ ዶር ለማ መገርሳ ደግሞ የምድባ ውክልና መሆኑ።

የአሁን ጉባኤ ይህን አሳምሮ ያስተካክለዋል። ከዚህ በፊት አቋራጭ ነገሮች ተሞካክረዋል። አልተሳኩም። አሁን ግን የሰላ መንገድ አለ። የፓርቲ አደረጃጀት የምርጫ መርህ ለከወን ችግር የለውም። ከዚህ ጋር ነው የሚታዬው የአቶ ታከለ ኡማ ጉዳይ ነው። ለዬትኛው መንፈስ የተገዢ ዝንባሌ  እንደሚሆን ብቻ ሳይሆን የቀጣዩን የፖለቲካ አቋም አመላካችም ነው።  … የሰሞናቱ የማዕከላዊ መንግሥት መረጃ ዝርክርክነትም ምንጩ ይኸው ነው። ተላልፎ እንዲሰጥ የማይፈለግ አካል ስላለ። ግን ህውከቱ ይፈለግ ስለነበረ። የአሜሪካ ኢንባሲ ተዝግቶ ሲውል እኮ እኔ ስሰማ የመጀመሪዬ ነው። ያ ለቀጣዩ የኢህአድግ ጉባኤ ጉዝጓዝ ነው።  

ሌላው ወደ መርህ አፈጻጻም ስንመጣ የግንባሩ ጠቅላላ ጉባኤ የግንባሩን ማዕከላዊ ምክር ቤት እና ኦዲት ይበሉት ቁጥጥሩን ይመርጣል። የግንባሩ ማዕላዊ ምክር ቤት ደግሞ አዲስ የግንባሩ ሥ/ አ/ ይመርጣል። ስለዚህ በቀጥታ ዶር ለማ መገርሳን ወደ ፊት ለማምጣት የጃውርውያን ትልም ለማሳከካት ምቹ ሁኔታ ይኖራል ። በሁለቱ መካካል ያለው ትዕይንትም ያልተገለጠው ተከድኖ የባጀው ሚሰጥርም ይቋጫል። በተገላገልን። 

እርግጥ ነው በዚህ ውስጥ አዲሱ የማዕከላዊ ምክር ቤት አባላት ድምጽ ወሳኝ ቢሆንም ድምጹን የሚከፍሉ ድርጅታዊ ሥራዎች ተባጅቶበታል። ለዚህ ነበር ዶር አብይ አህመድን ለመደገፍ አቅሙን ለማወቅ የሚያስችል ግብረ መልስ አስፈላጊ አለመሆኑ ብቻ ሳያሆን አደጋው ታይቶኝ የድጋፍ ሰልፍ የሚባለውን ሙሉውን የተቃወምኩት። 

ሰው ሰው ነው። ሚዛን ለማስጠበቅ ብዙ ሰርቻለሁኝ። ሞራላዊ የሆኑ አቅሞች አንድ ዓይን ብቻ ሳይሆን የሁለቱን መንፈስ በእኩልነት የተጋሁበት ምክንያት ያ ነበር። ያልተጠበቁ ህልም የሚመስሉ ክስተቶች ነበሩ። ያ እንደ ሰው  ሊከብድ ይችላል። 

በጠቅላላ የሰራሁት ሥራ ለስልት አልነበረም። ለኖርንበት የሴራ ፖለቲካም ይረዳል በማለት። ምቀኝነትን ቢያስታግስ በማለት ነበር። ቢያንስ ያደባባይ ሰልፎች ሁለቱንም ዘክሮ መነሳት ግድ ነበር። የሰኔ 16ቱ ከውኖታል ከዛ በመለስ ያለው ግን ብዙም አልነበረም። ብዙ ሰው አልሰራበትም። 

ለመሆኑ ማቆያ ጓንቱ የተሰጠው ገደብ እስከ መቼ? አብሶ የብጹዕን አባቶቻችን ጉዳይ ወሳኙ ነው። ኦዴፓ እንደ ድርጅት በብጹዕን አባቶቻችን ላይ ያለውን ርቀት ሳስበው ይጨንቀኛል። ንክኪ እንዳይኖር የጠ/ ሚር ቢሮ ብቻ ጉዳይ አድርጎ ነው የያዘው። ፎቶዎችን ንግግሮችን ገለጣዎችን መረመርኩኝ መንፈሱ የለም።  

የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የአንድነቱ ጉባኤ በሚሊዬንም አዳራሽም የነበረው ዕድምታ ብዙ ሚስጢሮችን ይገልጣል። የሆነ ሆኖ የተሻለ ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኬኤል ቅርብ ለመሆን ጥረት እንዳደረጉ አይቻለሁኝ። የቀድሞው ፕ/ አቶ ግርማ ብሩም እንዲሁ። 

ብቻ ዥንጉርጉሩ መርከብ ታጉረናል። ወይ ያስምጠናል ወይ ደግሞ ይማለደናል። ከጥቂቶቹ በስተቀር ብፁዕን አባቶቻችን ከፈቀዱላቸው ወደ ነበሩበት ወደ አሜሪካ ቢመለሱ ደስ ይለኛል። አንድነቱ ግን ቢቀጥል። 

ዱላ ተነግሮናል“ ሬሳችሁም አይመጣም ነበር ተብሎ። በሌላ በኩል የሚኒያ ንግግር ቶንም የቅርብ እና የሩቅ ዕድምታ ነበረው። እነሱ ጨርሳዋል እኛ ደግሞ የሃቅ ውልብሊቢቶችን ተከትለን በምናብ ተጉዞን ያ ባዶ ወንበር ለማን እንደ ተሰናዳ በስልት እና በስትራቴጂ በሚገባ ታቅዶ እንደሚከውን መላመቱን እንኮልማለን … ይልቅ ሬቻ በሰላም ተጠናቀቀ ይሆን? ለነገሩ ችግር ሠራሹ ራሱን የመጠበቅ አቅም ያንሰዋል ብዬ አላስብም።

በመጨረሻ "በኦነግ ሥም" የሚባለው ቀልድ ቢቆም ጥሩ ነው። በጸረ አብይ ካቢኔ የተደራጁ እኩይ መንፈሶች ወይንም ግልጽ ያለውን ድርጅት መግለጽ ነው። እዛው አፍንጫችሁ ነው ያለው። ዕውነቱ። ነገም ይታያል። ጉንጉኑ ሊፈታ ጥቂት ቀናት ቀርቶታል፤ በማን የኢጎ ምህንድስና እና ቅየሳ አላዛሯ ኢትዮጵያ ስትታመስ እንደ ባጀች ጊዜ ያነጥራዋል።

ለቅኖች መንገዳቸውን እግዚብሄር ይጠርግላቸዋል።
ለቅኖችም ማንም ባይኖር እግዚአብሄር አላቸው። 

ልዑል እግዚአብሄር የሬቻን ባዕል በሰላም እንዲጠናቀቅ ይርዳን። አሜን!
የኔዎቹ ኑሩልኝ

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።