ለቀጣዩ ትውልድ ከልብ #ከውስጥነትም የማሰብ ጸጋ እንዲህም ይገለጣል።
• ለቀጣዩ ትውልድ ከልብ #ከውስጥነትም የማሰብ ጸጋ እንዲህም ይገለጣል።
«ትራምፕ ኦቲዝም ያስከትላል ያሉትን መድኃኒት ነብሰ-ጡር ሴቶች እንዳይወስዱ አሳሰቡ»
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ዶክተሮች ለነብሰ-ጡር ሴቶች ታይሌኖል የተባለውን ማስታገሻ መድኃኒት እንዳይሰጡ አሳስበዋል።»
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።

ይህ ለቀጣዩ ትውልድ ከልብ ከውስጥም የማሰብ ጸጋ በእጅጉ #መሰጠኝ። ስለሆነም ሼር አደረግኩት። በትውልድ ጉዳይ ላይ ጤነኛ ሃሳብ የሚያቀርቡ ሁሉ ለእኔ #ብጹዓን ናቸው። እንደ #ተራራው #ስብከትም ነው የማየው።
ዛሬ በዓለማችን ጎልተው ከወጡት ችግሮች ውስጥ እጅግም አሳሳቢው ጉዳይ፤ የህፃናት ተስፋ አብረው #በሚወለዱ መንፈሳዊ፤ አካላዊ ጉዳቶች መሰቃየታቸው ነው። ይህ አዌርነስ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም የሚገኙ ሴቶች ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ከውስጥ፤ ለውስጥ የተላከ #ቅዱስ #መልዕክት ነው።
በዘርፋ ላሉ ተመራማሪወችም፤ ፈላስፎች #አዲስ #በር የሚከፍት ይመስለኛል። በሉላዊ ደረጃ ከተደማጭ ሰብዕና የፈለቀ ሃሳብን #ባሊህ የሚሉ በርካታ ልባሞች ዓለማችን አላት እና።
ስለሆነም ኢትዮጵውያን ሃሳቡን #ከልብ #ቢያዳምጡት ጥሩ ይመስለኛል። "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።" ይላል አካል የሌለው የእግዚአብሄር ትጉህ አገልጋይ ቃለ ወንጌል።
በሁሉም ዘርፍ ከመውለድ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ጥንቃቄ የኢትዮጵያ ሴቶች እንዲያደርጉ ቤተሰብ፤ የትዳር አጋር፤ በዘርፋ ያሉ ባለሙያወች ሁሉ ሃሳቡን ሳያጣጥሉ ከውስጣቸው እንዲያደምጡት እመኛለሁኝ።
በተረፈ የተከበሩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንትን ፕሬዚዳንት ዶናል ትራንፕን ለዚህ የቀደመ፤ ንጹህ ሃሳባቸው ትሁት ምስጋና አቀርባለሁኝ። እንዲህ ከውስጥ፤ ለውስጥ፤ ስለውስጥ በሰውኛ ቃና ስለወደፊቱ ትውልድ የሚጨነቁ፤ የሚጠበቡ ሰብዕናወች #ያስደምሙኛል። ዘገባውን ሙሉውን ለጥፌዋለሁኝ ማንበብ ይቻላል። በዚህ መሰል ትውልዳዊ ጉዳይ ቸልተኛ ልንሆን አይገባም። #ነገ #የሚሠራው #በዛሬ ውስጥ ነውና።
ግን እንዴት ናችሁ ማህበረ ቅንነት? ደህና ናችሁ ወይ?
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሆን።አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23/09/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
«ትራምፕ ይህን ያሉት መድኃኒቱ ከኦቲዝም ጋር ግንኙነት አለው ብለው ቢሆንም ይህ በሳይንስ የተረጋገጠ አይደለም።
ፕሬዝደንቱ ከጤና ሚኒስትራቸው ሮበርት ኤፍ ኬኔዲ ጁኒየር ጋር በመሆን ከዋይት ሐውስ በሰጡት መግለጫ ነው ይህን ያሉት።»
«የአሜሪካው ፕሬዝደንት የታይሌኖል ዋነኛ ግብዐት የሆነውን ፓራሴታሞል መውሰድ "ጥሩ አይደለም" ብለው ነብሰ-ጡሮች እጅግ የከፋ ትኩሳት ሲኖርባቸው ብቻ እንዲወስዱት መክረዋል።»
«አንዳንድ ጥናቶች ታይሌኖል በሚወስዱ ነብሰ-ጡር ሴቶች እና በኦቲዝም መካከል ግንኙነት እንዳለ ቢያሳዩም ጥናቶች ያልተጠናቀቁ እና ያልተሟሉ ናቸው።»
«ታይሌኖል የተባለው ክኒን አምራች የሆነው ኬንቩዌ ሴቶች መድኃኒቱን እንዳይወስዱት መባሉን አጣጥሏል።»
«ድርጅቱ ለቢቢሲ በላከው መግለጫ "ገለልተኛ እና ጠንካራ ሳይንስ ኤስታሚኖፊን በመውሰድ እና በኦቲዝም መካከል ግንኙነት እንደሌለ አሳይቷል ብለን እናምናለን። ከዚህ ውጭ የሚሰጥን አስተያየት አጥብቀን እንቃወማለን። ይህ ምክር ለነብሰ-ጡር ሴቶች የሚያስከተለው የጤና ቀውስም ያሳስበናል" ብሏል።
«ኤስታሚኖፊን የተባለው ታይሌኖል ውስጥ የሚገኝ ኬሚካል ለነብሰ-ጡር ሴቶች የተሻለው የሕመም ማስታገሻ ተደርጎ ይቆጠራል ያለው ድርጅቱ እርጉዝ ሴቶች ከዚህ ውጭ ያላቸው አማራጭ ስቃይ አሊያም ሌሎች ስጋት ያለባቸው መድኃኒቶችን መጠቀም ነው።»
«የጤና ሚኒስትሩ ኬኔዲ የሀገሪቱ የምግብ እና መድኃኒት አስተዳደር ለጤና ባለሙያዎች ማስታወቂያ እንደሚለቅ አስታውቀው ታይሌኖል ነብሰ-ጡር ሴቶችን አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል ብለዋል።»
«አክለው መድኃኒቶቹ ላይ የሚፃፈው ማስጠንቀቂያ እንደሚቀየር እና ለሕዝቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ እንደሚሰጥ ገልፀዋል።»
ኬኔዲ፤ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር ከዚህ በኋላ ሌውኮቮሪን የተባለውን መድኃኒት ኦቲዝም ላለባቸው ሕፃናት እንዲሰጥ እንደሚመክር አስታውቀዋል። ይህ መድኃኒት ላለፉት አስርታት የካንሰር ታካሚዎችን ኪሞቴራፒ ከሚያስከትለው ስቃይ ለማስታገስ ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ነው።»
«ኬኔዲ ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ነው በሚቀጥሉት አምስት ወራት የኦቲዝምን መንስኤ ለማወቅ "ሰፊ ሙከራ እና ጥናት ይካሄዳል" ሲሉ ያስታወቁት።»
«ትራምፕ ሰኞ በሰጡት መግለጫ በኦቲዝም የሚጠቁ ሕፃናት ቁጥር መጨመርን "ከፍተኛ ቀውስ" ሲሉ ገልፀውታል።
ነገር ግን ሙያተኞች ባለፉት አስርት ዓመታት ጥናት የተካሄደበትን ኦቲዝም መንስኤው ምንድነው የሚለውን በአጭር ጊዜ ማወቅ ቀላል አይደለም ይላሉ።»
«በጠቅላላው የኦቲዝም መንስኤ ተደርገው የሚወሰዱት ምክንያቶች በዘር የሚመጡ እና አካባቢያዊ አስተዋፅኦዎች ናቸው።@» ከBBC የአማርኛው ዜና የተገኜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ