ሃይማኖት ብሄር የለውም!

 የጅጅጋው ጥቃቱ ከብሄርሰብ ጋር መያያዝ አይገባውም።
„ድሀና ግፈኛ ተገናኙ እግዚአብሄር 
የሁለቱንም ዓይን ያበራል።“

 መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፱ ቁጥር ፲፫።
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 06.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።



ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት አመሻችሁ ዋላችሁ አደራችሁ። የጸና ደስታ የጸና ሃዘን ሁለቱም ሲያሰኛቸው በፈረቃ፤ ሲሻቸውም ደግሞ በአንድነት እዬሰላለቁን አመቱ ሊጠናቀቅ አንድ ወር ይቀረዋል። ባለፈው ዓመትም ይህን ሰሞን እስከ ፆመ ጽጌ መፍቻ ድረስ መሰሉ ፈተና ገጥሞን ነበር።

የዛሬው የታቀደው የቅድስት ተዋህዶ እና የእስልማና ሃይማኖትን ምክንያት ፈልጎ አጋጭቶ አገራዊ ብጥብጥ ለማስነሳት ነው። የቅዱስ ሲኖዶስ እርቀ ሰላሙ የውስጥ እሳት የሆነበት የመቀሌው መንግሥት አቅዶ የከወነው ነው።

ይህን ፍርድ ሰጪው መዳህኒዓለም ነው። ለዚህም ነው እኔ ግንቦት 7 ሆነ ኢሳት አገር ቤት መሄድ አይኖርባቸውም የምለውም። የአብይን መንፈስ መቀበል መልካም ነገር ነው፤ ይሄው ብራናው አርፏል። ህውከት የለውም። እናግዘው ይህን መንፈስ ከተባለ ሳሄዱ ውጭ እያሉ ብዙ ተግባራትን ሊከውኑ ይችላሉ ግንቦቶች እስከ ሚዲያዎቻቸው ድረስ።

ወያኔ ሃርነት ትግራይ ቂመኛ ነው። የፈለገ ይቅርታ ቢባል፤ ፍቅር ቢባል ልባችሁን አውልቃችሁ ብትሰጡ አይቀበለውም። ሌላውም እንዲሁ ነው። ይህን በሚኒ መንትዮሽ ጉባኤ አይተነዋል። ስለምን ልባችን ድፍን አድርጎ እንደ ፈጠረን ይጨንቀኛል።

ሌላው ይህ እልቂት የአማራ ጥቃት ብቻ አይደለም። ሃይማኖት ዘር እና ጎሳ የለውም። ቅደስት ተዋህዶ የመላው ኢትዮጵውያን ቤት ናት። የሁሉም ዓውደ ምህርት ናት እንጂ አንድን ዞግ ወይንም ብሄር ብቻ እምታሰባስብ አይደለችም። ጥቃቱ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው። የታቀጠሉት አብያተ ቤተክርስትያንት ደግሞ ሃብትነታቸው የኢትዮጵውያን ነው።

የተሰወቱ ሰማዕታት ደግሞ ኢትዮጵያዊ ዜጎች የሁላችንም ናቸው፤ ኢትዮጵውያን። ስለዚህ ቤተክርስትያንን ከጎሳ ጋር፤ ከብሄር ጋር አድርጎ ማዬት የተገባ አይደለም።

ጭብጡ ስደት ላይ የነበሩት አባቶች ስለምን አገር ገቡ ብቻ ሳይሆን ቅድስት ተዋህዶ አንድ ከሆነች ትጠንከር እና በኢትዮጵያዊነት ላይ የበረታ ጉልበታም ተግባር ትከውናለች፤ አቧራ ያለበሳናት ቤተክርስትያን ተነቃቅታ ብሄራዊ፤ አህጉራዊ እና ሉላዊ ሃላፊናቷን ከተወጣች ሰንደቅ ሆነ ትወጣለች፤ ይህ ከሆነ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንዴስቶ ዓላማ ይቃጠላል ነው።

በሌላ በኩል የአብይ መንግሥት እስልምናን እንጂ ቅደስት ተዋህዶን ጥበቃ አያደርግለትም ተብሎ እንዲሳጣም ነው፤ ኦህዴድ አገራዊ ሃላፊነት ለመወጣት አቅም የለውም። መንግሥታዊ መዋቅሩን ማዘዝ ማስተዳደር መቆጣጠር አልቻለም። በኢትዮጵያ የሃይማኖት ጦርነት ተነስቷል በማለት የተጀመረውን የለውጥ መንፈስ ምዕራቡ ዓለም በጥርጣሬ እንዲያዩት ለማድረግ ታቅዶ በደንብ ተደራጅቶ የተከናወነ ነው። ያለፈውን ሳምንት ሐሤታዊ ዜና ለማጥቆር ነው።

 ያው እንደሚታወቀው ኦህዴድ ደግሞ የፈለገ መሰናክል ቢፈጠር ያቀደውን ከመከወን እንደማይታቀብ ጠንቅቀው ያውቁታል። ባለፉት ወራት ያ ሁሉ ህዝብ ተፈናቅሎ ኦህዴድ በትረ ሥልጣኑን ለማያዝ ያደረገው ጥርት እና ስኬቱን እዬተመለከተው ነው አቤቶ የመቀሌው ሥርዕዎ መንግሥት። የፈለገ ይፈጠር የተረጋጋ መንፈስ ነው ያላቸው ኦህዴዶች። ያቀዱትን እዬከወኑ ነው። 

የሚያሳዝነው የኢትዮጵያ ህዝብ ካለጠበንጃ ሰላማዊ ኑሮን መቀበል አለመቻሉ ነው። በዚህ ለስላሳ የሥርዓት ለውጥ በሚመስል ሂደት ላይ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ከመትጋት ይልቅ መታሰር፤ መገረፍ፤ መደብደብ ፈለገ። ፌድራል ሲገባ ደግሞ የሚመጣው ቀውስ ሌላ ይሆናል።

በሌላ በኩል ዘገምተኛ የመንግሥት እርምጃ ያመጣው ቀውስም ነው። ይህን አቶ አብዲን ለማስተካከል ብዙ ተሞክሯል፤ አልተቻለም። አለመቻሉ እዬታወቀ ምንም አርምጃ አለመወሰዱ ቀውሱን አባብሶታል።

እንደሚታወቀው እዛ ብቻ ሳይሆን በእያንንዱ የመንግሥት መሥርያ ቤት ነጥብ ጣቢያ ሁሉ በተጠንቀቅ የሚጠብቁ የተቀበሩ ፈንጆች አሉ። አጋጣሚ ከተፈጠረ የፍርሻ ማህበርተኞች አድፍጠው በዬጎሬው እንዳሉ ማወቅ ይገባል። ለዚህ ነው የኢትዮጵያ የመንግሥት ለውጥ ሁልጊዜ ነባሩን በሙሉ ሽሮ በአዲስ ለመገንባት የሚገደደው። አለመደብንም ቁልምጫ ... የት የምናወቀውን? 

ወያኔ ሃርነት ትግራይ 27 ዓመት የገነባውን የሴራ ግንብ በፍቅር ቃና ለመመለስ እጅግ ከባድ ከመሆኑም ባለይ ብዙ መስዋዕትነትን እያስከፈለ ነው። ወደፊትም ቢሆን በዚህ ከቀጠለ የአብይ መንፈስ እራሱ ሊቀለበስ ይችላል። ለዚህ ነው እኔ ጭንቁ ሌቦች ከሥር ተፈቱ ነው፤ ለውጡ ሊቀለበስ ሁሉ ይችላል ብዬ የጻፍኩት። ጤፍና ሰናፍጭ ምኑ ይለያል።

አሁን እኮ አዲሱ ለውጥ ያን ያህል በመዋቅር ደረጃ ልዩነት የለውም ከነባሩ።  አሰተሳሰቡ ብቻ ነው ለዛውም በሃሳብ ደረጃ የተለወጠው። ገና የፖሊሲ ድጋፍን የሚሹ መሰረታዊ አረጋጊ ጉዳዮች አሉበት።

 ይህን ለውጥ ማን ከልቡ ተቀበለ ለሚለው መስፈሪያ የለንም። ህዝቡ ተቀብሎታል አስፈፃሚ አካላት ግን ከላይ እስከታች ያለው መዋቅር በማን እና በምን ሁኔታ እንደ ተደራጃ ይታወቃል።  መመሪያም በቀጥታ የሚሰጧቸው ሰውር አካላት አሉ።

ከቀደመው የባሰ ከባድ ፈተና ፊት ለፊታችን ይኖራል ከተለመደው ውጪ። እንግዲህ ልዑል እግዚአብሄር ቤተ መቅደሱ እዬተደፈረ ስለሆነ እራሱ ቁጣውን በአጥፊው ላይ ማሰረፍ ካልቻለ በስተቀር አፋር እራሱ ተረኛ ነው።

አዲስ ተስፋ አፋር ላይ እንዳለ ሰምቼለሁኝ፤ በጎ የሆነ በመንግሥት የታቀደለት። ስለዚህ ያን ደግሞ እምስ ማድርግ አይቀሬ ሲሆን ከባዱ ፈተና ግን አዲስ አባባ ነው። አዲስ አባባ ገና የሚፈነዳ ቦንብ በተከታታይ ይኖራል። ቦንብ ስል ቦንብ ብቻ ሳይሆን የጥፋት ተልዕኮ

ደግነቱ አሁን ት/ ቤት ዝግ መሆኑ ነው። በዚህ ማህል አስቸኳይ ጊዜ አዋጅም የወያኔ ሃርነት ትግራይ ታላቁ ህልሙ ነው። እዬከፋ ከሄደ ግድ ይሆናል።
ስለሆነም ሁሉም ራሱን መጠበቅ፤ በጊዜ ቤቱ መግባት። ያለተገቡ ፍጥጫዎችን ማቆም፤ ወደ እግዚአብሄር አብዝቶ መጸለይ በአጅጉ ያስፈልገናል። አብሶ ድል ያደረገው መንጠራራቱን ተግ ማድረግ ሲጠበቅበት፤ ሌሎች ደግሞ እንዳይገለሉ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠባቅባታል ጨዋው የኢትዮጵያ ህዝብ።

አሁን ቀጣናው በተለይ አዲስ አባባ እጅግ ከባድ ፈተና ውስጥ ነው። ሌላው የአማራ ክልልም የኦህዴድ ቀኝ እጅ ነውና እሱም በእጥፍ ዕዳውን እንደሚከፍል ልብ ሊለው ስለሚገባ በሩን ማጠባበቅ እና የክልሉን የጸጥታ ሃይል ህሊና በባለቤትነት ስሜት ማነፀ ግድ ይላል።

የተፈለገው ጁቡቲም መንገዱ ሲዘጋ፤ መተማም ቅማንትን በአዲስ አስነስቶ መንገዱ ሲዘጋ ድፍን ያለ ጥቅጥቅ ጨለማ ውሰጥ ብቻ ሳይሆን የኤኮኖሚ ድቀቱም ታሳቢ ነው። ኤሌትሪክም ሊጠፋ ይችላል። ውሃ ውሰጥም መርዝ ሊጨመር ይችላል። ለሰይጣናዊ ሥራ ምን ሲቸግር … ይህሊናም፤ የመንፈስም፤ የ አካልም መሰናዳት፤ ቢቻል ቀደም ብሎ የሚአስፈልጉ ነገሮን ለ ዕለት የሚሆኑትን ገዛዝቶ ማስቀመጥ ጥሩ ነው። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም። 

ለዚህ ደግሞ አንድ በድህንነት ሙያ ለኖረ መሪ የሚጣፋው አይሆንም። ስለዚህ ወሳኔ እና እርማጃ ግድ ይላሉ። በስተቀር ግን ከመርከቧ ጋር አብሮ መስመጥ እና 90 ደቂቃ በኢንተቤ ዕውን ይሆናል፤ ይህን የመሰለ የህዝብ ተቀባይነት እኮ እጅግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማንም አግኝቶት የማያውቀው መሰረታዊ ጉዳይ ነው። ስለዚህ ይህን ማደናቀፍ ግድ ይለዋል ነባሩ ዓውራ ድርጅት የወያኔ ሃርነት ትግራይ።

ብልህነቱ ግን በቅድስት ቤተክርስትያን የመጣው መከራ እራሱ ባለቤቱ ብድሩን ስለሚያስከፍል ዳኝነቱን ታግሶ መጠበቅ ነው። ከዚህ ሁሉ ሚሊዮን ህዝብ መፈናቀል፤ ሺዎች መርገፍ፤ አድባራት መቃጠል የቃዬል ዕንባ ከትውልድ ወደ ትውልድ ጩኸቱን አያቆምም።

አሁን መንግሥት ማድረግ ያለበት ጥሶ ገብቶ መቆጣጠር ነው። ዜጎቹን መታደግ ነው። ቃለ ምልልስ ሳዳምጥ የክልሉ ፖሊስ እያዬ ምንም ዓይነት እርምጃ እንዳልወሰደ ነው የተረዳሁት። እና አሁንም ያንኑ ፖሊስ አምኖ መቀመጥ ህዝብን ቀብሮ መዝፍን ይሆናል።

አቤቱ ልዑል ሆይ በቃችሁ በለን።
ለመከረኞች መጽናናትን ስጥልን።
እመቤቴ እባክሽን ልጆችሽን ከበላህሰቦች ታደጊያቸው። ፈጥነሽም ድረሸላቸው። እባክሽን?


የኔዎቹ ኑሩልኝ መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።