አማራነት ሌላውን አጥቂነት ሳይሆን ራሰን ጠበቂነት ነው።
ምን ስለሆነ?ምንስ ስለተገኘ?
„ደምን ለማፍሰስ የሚሹ ሰዎች ፍጹሙን ሰው ይጠላሉ።“
መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፱ ቁጥር ፲
ከሥርጉተ © ሥላሴ
06.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
ይህን የህዝብ ሙሉ የፍላጎት ድምጽ ጥሰህ እንዴት "የወጣት ብቻ" ትለላህ?
- · ጠብታ።
የግራሞት ሰሞናት ነው። አንድ የቪዲዮ ክሊፕ አዬሁኝ „አብይ አማራን ከሁለት ከፈለው“ ይላል።
ግን ቅናዊ ትህትናዊ ነው። አጀብ ነው። ምን አድርገው ነው ዶር አብይ አህመድ አማራን ከሁለት የሚከፍሉት? የሰበኩት ኢትዮጵያዊነትን ነው። አማራ ደግሞ
ሙሉ 27 ዓመት የተጨፈጨፈበት ዘሩ እንዲፈልስ የተደረገበት ዋናው አምክንዮ ይሄው ነው።
- · በመከራ የተወለደ የማንነት ተጋድሎ።
አማራ አማራ ነኝ ያለው እኮ በሀምሌ አምስቱ አብዮ ነው። ከዛ በፊት እኮ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ
በማለት ነው የቀራንዮንም፤ የጎለጎታም የመከራ ጽዋ ብቻው ዕጣ ነፍሱን
ሲጨልጥ 27 ዓመት ሙሉ የኖረው። አማራ ነኝ ሲል ደግሞ አሸባሪ ነህ ተባለ።
ስለዚህ ኢትዮጵያ ሚስጢር ናት
ስትባል ትናንት ያሳበዳቸው አሁን ሚኒ ጉባኤ ላይ ያሳኙን ባለተውኔቶ ሞደሬተሮች ይጨነቁበት፤ ለእኛማ የኖርንበት ማተባችን እኮ ነው።
እስኪ መቼ ነው አማራ ከዛ አፍሪካ የነፃነት ዓርማ ከሆነው አረንጓዴ
ቢጫ ቀይ አርማው ውጪ ለሰከንድ መንፈሱ ወጥቶ የሚያውቀው?
አሁን አንዳንድ የውጭ አገር ሚዲያዎች
አዲስ ዝግጅቶች አያለሁኝ በዛ ብሄራዊ ሰንድቅ ዓላማ ፊደሎችም ዝግጅቱም ተሽሞንሙኖ የሄዱበት ዥንጉርጉርነት ከንቱ መሆኑን አማራ
መሬት ላይ በተከተታይ ለሦስት ዓመታት ስላወጀላቸው አለን እያሉ ነው። እንደ ገናም ያው መናጆ አማራ ነገ ደግሞ እንደ አብራሃሙ
በግ ኮረጆ ሙላ አይቀሬ ስለሆነ … ግን አማራ ልብ የለውንም? ልቡን ማን ወሰደው?
የሆነ ሆኖ አማራ እኮ አይደለም ትናንት ዛሬ ከቤተክርስትያን እንደ ገባ ውሻ እኮ ነው እዬተንከከለ
ያለው። „የአማራ የማንነት የህልውና ታገድሎ“ ያሰገኘው በረከት ዕውቅና
ማግኘቱ ቀርቶ ስንኙን የሚደፈረው አይገኝም። ትናንት አቶ ጆዋር አህመድ ሲደግመው ሲሰልሰው ነበር በዬሚደያው፤ አዲስ አባባ በተደረገለት
ልዩ የሆነ ዘውዳዊ ንጉሳዊ መስንግዶ ላይ „ድሉ የተገኘው በእኛ ብቻ
ሳይሆን በሌሎችም ነው ብሎ የ66ቱ ዘመን አንሰቶ ሲያዝክር ነበር“ ጨዋታው ይሄው ነው።
ሌላው ከኦሮሞ ውጪ የተኛው ማህበረሰብ? ምነው ፈራው?
እያንዳንዱ ቀን ለአማራ የቀጣይ የህልውና መንፈስ አጅግ ብዙ መልዕክቶች አሉት። ነገር ግን ልንማርበት
እንጂ ዘራፍ ብለን ውድድር ልንገባት አይገባም። የአማራ ታገድሎው ሴሪሞንያዊ ጉዳዮች ተኮር መሆን የተገባ አይደለም። መንፈስን በበቃ
ህሊና በጽኑ ጥበብ፤ ዓላማን ባወቀ አጽህኖት ማጽደቅ ነው ዕለታዊ ተግባር ሊሆን የሚገባው።
- ኢትዮጵያዊነትን እኛን ለማስተማር? ህም …
እኛ፤ ትናንትም፤ ዛሬም ወደፊትም በአውራው ማንነታችን ውስጥ የነበርን የምንኖር ነን። የሚያስቀናውም
ይሄው ነው፤ በጥርስ እንደንያዝ ያደረግንም ይሄው የማይናወጽ አቋማች ነው።
በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮች ተትተው እኮ ሌላው ሞከረው፤ የተገኘ ትርፍ አልነበረም።
ወደፊትም እንዲሁ። ሌላው እኛ ኢትዮጵያዊ ሁኑ ስለተባልን ኢትዮጵያዊነትን የምንቀበለው፤ አትሁን ስንባል ደግሞ ኢትዮጵያዊነት የገፋን
ማህበረሰብ አይደለንም።
ኢትዮጵያዊነታችን የሰጠንን የምናውቀው ዛሬ ሳይሆን ገና ስንጸነስ
ነው። ከእሱም የሚለዬን የለም። የዘመነ ፋሽትም አልነጠለንም። ኢትዮጵያዊነትን
ሊሰጠንም ሊነሳንም የሚችልም አይኖርምም። በዛ ድቅድቅ ጨላማ እንኳን ያን የአሳር ዘመን ተወጥተነዋል እንኳንስ ዛሬ።
በዚያ ድንቅ ገናና የአማራ አብዮት
ቀንም ቢሆን አማራነቱን ብቻ ሳይሆን ሉዕላዊነቴ ይከበር፤ ደም መፍስስ ይቁም፤ የህዝባችን ነፃነት አይቃማ የሚሉ አንደኛውንም ሁለተኛውን
ዓለም ጦርነቶች ካስነሱት ሳቢያዎች የዘለሉ ምክንያታዊ ብሄራዊ እና ሉላዊ ጥያቄዎችን እጅግ በጎለበተ፤
በሰለጠነ እና እና ጥሞናው ዘመን አሻጋሪ የሆነውን ተጋድሎውን አድርጓል አማራው በጎንደር እና
በጎጃም።
- · ምንም ሃሳባችን ከሁለት የከፈሉት ነገር የለም ጠ/ሚሩ?
ብሄራዊ የነፃነት ዓርማውንም የሙጥኝ ብሎ አብሮ ሰማዕትነቱን ተቀብሏል አማራው። ስለዚህ ላልነበሩበት
የፖለቲካ ሊሂቃን ሁሉ፤ ላልኖሩበት የዘመነ ወያኔ ትውልድ አስተማሩ ዶር አብይ አህመድ ኢትዮጵያዊነት ጠቃሚ ነው ብለው። የሳቸውን
ያህል ክብር እና ሞገስ ያገኜ የለምና፤ በዚህ መንፈስ ውስጥ ስላሉ። ይህን ግርማ እንዲያገኙ ደግሞ አማራ ነው የተጋው።
ስለሆነም አማራማ አንጎሉ ኢትዮጵያዊነት ነው፤ ትናንትም፤ ዛሬም ወደፊትም። ኢትዮጵያ አታስፈልገነም
ላለው መንፈስ ቀስቅሰዋል ያም ሆኖ ጦርነት ላይ ነበሩ ሜኖሰፖታ ላይ፤ ሚኒያ ላይ።
እሳቸው ድሉን በረከቱን ጸጋውን ረድኤቱን ስለዩት ብቻ ሳይሆን እውነት ለመናገር በዛ ውስጥም
ስለነበሩ። ከሁሉም በላይ ዛሬ ጠ/ ሚር ስለሆኑ ሳይሆን ሰፋ ያለ መጠነ ሰፊ የሆነ የሰው ልጅን ተፈጥሮ የመቀበል አቅምም አላቸው።
ቅብ አይደለም ኢትዮጵያዊነታቸው ሆነ አፍሪካዊነታቸው ሆነ በተፈጥሮ ላይ ማተኮራቸው። እሳቸውን እኔ እማይበት መንፈስ ፍጹም የተለዬ ነው።
ስለሆነም የዶር አብይ አህመድ የብሄራዊነት ስብከት አማራን አይመለከተም። ተጋድሎው ዶር አብይ
አህመድ ጠ/ ሚር ቢሆኑልን ብሎ አልነበረም የታጋደለው። አማራነቴ
ይከበር ብሎ እንጂ። ስለዚህ እሳቸው ስለተሾሙ ተጋደሎው ጓዝ ጠቅላይ የሚያደርገው ምንም ነገር የለም።
ስለዚህ ዛሬም ወደፊትም የተጋድሎው መንፈስ ቀጣይ ነው። ምን ስለሆነ ነው አሁን እርግፍ አድርጎ
ትቶ ጓዳ የሚገባው? ተጋድሎው እኮ ቁልጭ ያለ መንፈስ ማንነት ያለው ነው። ከዬትኛውም አካል ችሮታ አይመኝም።
አማራ በሙሉ አቅሙ የተፈራበት ዘመን ተወግዶ አማራ በሙሉ አቅሙ
እና ሥነ - ልቦናው ልክ ራሱን ማስከበር ቢችል እንኳን ተጋድሎው ከዘላቂ ዓላማው ፈቅ ማለት አይኖርበትም።
ዶር አብይ አህመድ እኮ ሰው ናቸው። በመኖር ውስጥ ብዙ ነገሮች ይገጥማሉ። አርቆ ማሰብ ይገባል።
በብሄራዊነት ውስጥ አማራን ያገሉታል ተብሎ ባይታሰብም አማራነትን ማብቀል፤ ማጽደቅ፤ ማስበል ግድ የኛ የራሳችን የቤት ሥራ ነው።
እከሌ እንዲህ አደረገ፤ እከሌ እንዲህ ሊያደርግ ነው ከሚል ምሾ ወጥቶ የአማራ ልጅ ታጋድሎውን በሰከነ፤ በጨዋነት፤ በተሟላ ሞራል
እና በብቁ ሥነ - ልቦና መቀጠል አለበት።
ታዬ እኮ „ከጣና ኬኛ“ ወዲህ ለተደረገው መልካም ነገር መልሱን መመዘን ነው። ሥነ - ልቦናውን
በመጠበቅ፤ በመንከባከብ እረገድ ምንም ነው። የጉራጌ ወጣቶች ድል ላይ አለን ስላሉ እነሱ ናቸው ክብር ጸጋ ሆነው ሥነ - ልቦናቸው
በተደጋጋሚ ጥበቃ እና እንክብካቤ በማዕከላዊ መንግሥት ደረጃ ሲደረግላቸው የማዬው። ለምን ሆነ አይደለም ህሊና የሚባል ነገር ሙግት
ላይ ስለሚያሰቀምጥ እንጂ።
ስለምን ይህ ሆነ? ማስፈራሪያ ድርጁ መንፈስ ስላላቸው። በመንግሥትም በተቃዋሚ የፖለቲካ ደረጃ
አላቸውና። አማራ ድልድይ ይሁን፤ ያንግት ያደራጀውን ያስረክብ …
ክብሩን መስዋዕትነቱን ለዬዘመኑ የሥም ንጉሦሶች ፈቅዶ ይለግስ። እሱ ባባዶ ሜዳ ደመ ከልብ ይሁን።
የ43 ዓመቱን የጭነት መከራ ለማሰወገድ ተቋም ቢከፈትም እንኳ አይችለውም ጸረ አማረነት በታቆረ
ሁኔታ ከህሊና አጥቦ ለማስወገድ የ አዲሱ ለውጥ መንፈስ ይህን በመንትዮሹ የ ስሜን አሜሪካ ግዛቶች አይቶታል። ለዛውም በደል የተለዬ
አልደረሰበትም ነው አምክንዮው።
- · የሆነ ሆኖ …
ለውጡ ጥገናዊ ስለመሆኑ ልብ ማለት ይገባል። በዚህ አጋጣሚ ደግሞ በስልት እና በጥበብ እድሉን
ተጠቅሞ የራስን የቤተ ሥራ መስራት ነው። በዬጊዜው ምሾ ከማውረድ።
የሆነ ሆኖ በስሜን አሜሪካው ጉባኤ አማራነት ጓዙን ጠቅልሎ እንደ ተለመደው ተሸብልሎ አቅሙን
ይገበር ሲባል እኔ አላደመጥኩኝም። ስልቶችን አይቻለሁ፤ ይህን ዛሬ ማንሳት አልፈልግም። ጊዜው ስላልሆነ። መታገስም አብዝቶ ስለሚተርፍ።
ሁልጊዜም እኔ ሁሉን ነገር በቅን ነው የማዬው። አዎንታዊ ነኝኛና።
ተስፈኛም ነኝ …
ለሁሉም ጊዜ ሰጥቼ መፈተሽን እሻለሁኝ።
አብሶ የኦህዴድን መንፈስ አቅሜንም ፍቅሬንም እንደ ግንቦት 7 ሳልሰስት የሰጠሁበት፤ መከራንም ያሰተነገድኩበት ስለሆነ በትዕግስት
ላያቸው እምሻቸው ጉዳዮች አሉኝ። አሁን ጊዜው ልጅ ነው። ገና ነው የአብይን ካቢኔ እምወቅስበት። ይህ ማለት ግን ግድፈቶችን አልፋቸዋለሁ
ማለት አይደለም። አክብሮታዊ በሆነ ልስሉስ ሙግት እቀጥላለሁኝ። እምጠቀምባቸው ቃሎች ልስሉስ የሆነውም በዚህው ነው እንጂ እኔ ቃሎቼም
ቦንብ ናቸው …
የሆነ ሆነ ተመስጥሮ ቢያዝም የአስተዛሬው የአማራ መስዋዕትነት አገሩን መውደድን ብቻውን አማራውን
ዘሩን አስነቀለ፤ የማናቸውም መከራ ቤተ መኩራ አደረገው፤ ከማናቸውም መንግሥታዊ ፖለቲካዊ ደረጃ እንዳይደረስ በሃራም
አማራ ተባረረ እንጂ ያተረፈው አንዳችም ነገር የለም።
እኛ በማናውቀው፤ ፈጽሞም ባልተገለጠን ሁኔታ ራሳችን ያቀለጥንበት ሁኔታ አይደለም ትናንት ዛሬ
ላይም ያለውን ሁኔታ የምናዬውን እያዬነም ነው ያለነው።
አማራነትን የማይፈራ ሊሂቅ፤ አማራነት የማያርደው ፖለቲከኛ አይደለም ከሌላ ብሄር እና ብሄረሰብ
ከራሱም ከአማራው ሊሂቅ ለማግኘት የሚታሰብ አይደለም።
የአማራውም ሊሂቃን የሚሉን አማራነታችሁን ደብቃችሁ ግን ኢትዮጵያን ታደጓት፤ እሷን ስታተርፏት
ጽድቅ በሰማይ ደጅ ታገኛለችሁ ነው የሚሉን አደበባይ ወጥተው የሚሰብኩት ይህንኑ ነው። ሽግግር መንግሥት የሚሉትም
በዚኸው ዕሳቤ ነው።
ኢትዮጵያ ለአማራ ብቻ የተፈጠረች አገር አይደለችም። ኢትዮጵያ የሁሉም አገር ናት። እንዲያውም
እሷን እሷን ስላለ ብትን አፈር ለመኙ አማራ ነው። እንዲያውም በህሊና ተገላዩ አማራ ነው። ቅንነቱ ግምዱን ቢያጠነክረው እንጂ ያተረፈለት
ምንም ነገር የለውም። እናመሰግናለን እንኳን አላዳመጥነም። „በጨው
ደንደስ በርበሬ ተወደስ“ ሆኖ እያዬነው ነው …
ነገስ ለሚለው እንደ አባት አደሩ እዮባዊነት ያባት ስለሆነ እሱኑ ሰንቀን እንጠብቃለን … ምክንያቱም
ይህ የአሁኑ የለውጥ መንፈስ በአማራ ድጋፍ ቀጣይነት ነው ሊቆምም ሊራመድም የሚችለው … ለውጥ ተፈልጎ ለውጥ ተፈርቶ መሆን ስለማይገባው
ቅናዊ እይታው ይቀጥላል አድካሚም አሰልቺም ቢሆንም …
- · ባለውለታ።
ዛሬ ለሚቀነቀንለት ኢትዮጵያዊነት ራሱ 27 ዓመት ቀንበሩ ተሸክሞ
የሞተለት አማራ እና አማራ ብቻ ነው። ለዚህ ቀን ያደረሰ ያ የተገፋ መንፈስ እና ማህበረሰብ ነው።
ለውጥ ለሚበላውም ለክልል ፍላጎት ሳይሆን በመጠነ ሰፊ ጥሞና የተዘከረ ተጋድሎ ነበር ያደረገው
- አማራ። አማራ ተጋድሎ ለማለት የኢትዮጵያ ሚዲያ ዛሬ ላይ ነፃ ወጣ የሚበላው ማለቴ ነው፤ ድንቅ ነው እዬተባለ የሚተረክለት የአማራ ብዙሃን ሚዲያም አፉን አውጥቶ አይመሰክራትም።
የእኛ አርበኛ በወለቃ ሲገባ ተቀባይም አክባሪም አለገኝም። በቦሌም ቢገባም አማራነቱ አለስከበረውም።
የሚጻፈው እኮ የትናንት ሳይሆን ዛሬ የምናዬው ሃቅ ነው። ታሪካችን ነው … ተጋድሏችን አቋጣሪ ማጣቱ አይከነክንም። ስለምን? የቀጣዩን
ቀጣይነት አሳምረን ስለምናውቀው …
ኦህዴድን ከፍ አድርገን ያነገስነው በንፅህና እና በቅድስና የደገፍነው እኛው ቅኖቹ ሞኞቹ
አማራዎች ነን። ያን የመከራ ጠቃራማ ዘመን እርግፍ
አድርገን እረስተን ትተን ወጥተን ሞግተን ራሳችን ረምጠን። ዛሬ በቀይ ምንጣፍ እልል ኩልል ብለው የተቀበሏቸው OMN ወይንም የራሳቸው ማህበረሰብ አልነበረም። የቄሮ ታጋድሎ ብቻውን የትም አያደርስም
ነበር፤
ዛሬ ግን እዚህ አደረስን አማራ ለማለት ደፍሮ የሚነገራት ሰው አልተገኘም። ሁሉንም ማዬት መልካም
ነው። እዬባዊነት የሐረግ ስለሆነ ወደፊትም የሚያከለፈልፍ ምንም ዓይነት መንፈስ ሊኖርብን አይገባም። ብዙ ቀናቶች አሉ ወደፊት።
ኢትዮጵያዊነት ፊደል ገበታ ሊገዛላቸው የሚገቡ ነፍሶች አውሮፓን ለፈጠረ የተደሞ ሚስጢረኛ ኢትዮጵያዊነትን
ሀሁ አስቆጥራለሁ ማለት የወንዝ ውሃ ከቁልቁል ወደ ላይ ይፈሳል የማለት ያህል ቧልት ነው።
ለዚህ ጊዜ ማባከንም ከፍና ዝቅ ማለትም አንባርጭቃነት ነው። ምንድነው የሰማሁት ባህርዳር …
የሆነ ነገር ከትከት ነው …
በሌላ በኩል አጋጣሚውን ተጠቅመውም የግንቦት 7 አውራ ካድሬዎች ስለ አማራነታችን እንሱ ሞጋች
ሆነው ትግራይ ውስጥ አማራ ተጎዳብን እያሉን ነው። አሁንም ከትከት ይቀጥል..
ጊዜ ጥሩ ነው ሁሉን እያሳዬን ነው … አጨብጫቢ፤ ሎሌ፤ ቀቃይ ሲጠፋ ምን ይደረግ? ስለሆነም
በድጋሚ የአማራ ፕሮፖጋንዲስት ሆነው የመንፈስ ጉዝጓዝ እና የማገዶ ድንኳን እንዲያደርጉንም መፍቀድ ያለብን አይመስለኝም። መናጆነት
መቆም አለበት።
መናከስ፤ መጋጨትን፤ ትርፍ ነገርን አቆሞ፤ ቂም በቀልን ተግ አድርጎ የራስን ተግባር መከወን
ልብ ላለው ኣመራ ጊዜው አሁን ነው። ግንቦት 7 የመታገያ መሬት የለውም። አዲስ አቤቤው አብያውያን ሆኗል።
ትግራይ፤ ኢትዮ ሱማሌ፤ አፋር፤ ቤንሻንጉል፤ ሐረሬ የሚደፈሩ አይደሉም። ኦቦ ሌንጮ ለታም፤ ዶር ኮንቴ ሙሳም የሉማ፤ የ አውሮፓው ህብረት ተስፋውም እንዲሁ ... በኗል። ስለዚህ ባጣ ቆዬኝ አማራው ...
ከቻለ የህልሙ ማዕከል ደቡብ፤ ለአንጋችነት ደግሞ እዬጠላውም ቢሆን ቤተ አማራ ብቻ ነው። ለዚህ
ነው ሰማያዊ ፓርቲ እዛው ታድሞ የነበረው። ስለዚህ ይህን የእንቆቅልሽ
ጨዋታ አማራ በመከራው ወስጥ በኖረበት አመክንዮ ውስጥ ዘልቆ ራሱን ሆኖ በራሱ የፖለቲካ አቅም ጎልቶ እና ጎልብቶ በመውጣት የእኩል
አገራዊ ባልድርሻነቱን ከማስከበር ውጪ በሥማ በለው ግርግር መብቱን አሳልፎ ሊሰጥ አይገባም! ይሄ የሰው ሥም እና የድርጅት መንፌስቶቸን
አንግሶ አጎብድዶ መኖሩን በአስቸኳይ አማራ ማቆም አለበት።
የአማራ ልጅ ለመሪነት አይመጥንም ያለው ማነው? አማራ ቁልፍ ቦታዎችን፤ አስፈለጊ የሚባሉትን
ቦታዎችን ታምኖ መወጣት አይችልም ያለው ማነው? ራሱ አማራው ነው። መነጠፍ እንጂ በተነጠፈው ልሂድ ስለማይል።
ሌላው ህብረ ብሄር ፓርቲ የሚባል ጉድ ነው። ይህም ሌላው አማራን ተብትቦ አጋድሞ የሚያሳርደው ሰውር የሰይፍ እወጃ ነው። ለዚህም አማራ እጅ መስጠት የለበትም። ቲካ
ቲካ ማለት አያስፈልገውም።
ብዙ ጊዜ አማራ ከሁሉ ጋር ይጣላል ነው የሚባለው፤ እንገላብህ የሚባለው እሱ ስለሆነ
ብቻ ነው። ኦሮሞ መሬት ላይማ አራት ዓይናማዎች ፍንክች አይሉበትም። በሌላ በኩል ገረድ ሁነልን ሊቆም ስላልቻለም ነው። እኛን ሊረሱን አልቻሉም። መጡብን እንጂ አልሄድነባቸውም።
ሌላውም ቁምነገር ህብረ ብሄር ብሎም የራሱን
ወገን ከላይ እስከታች፤ በሲቢክስም ቢሆን የራሱን ወገን ደርድሮ ነው የሚስግር፤ ከአማራ ውጪ በዞግ የተደራጀው መፈንጫ አይደለም፤
የሌላ ብሄረስብ ከያኔውም በራሱ ውስጥ እንጂ የሌላው ሲሳይ ሞገስ
አይደለም። ልብ አለው ሌላው ዞግ።
እርግጥ ነው መጣላት አያስፈልግም። ሙያን በልብ መከተብ ነው። ስብሰባ ሲጠራ አለመሄድ በቃ።
የምርጫ ቅስቃሳ ሲሆን ባዶ አዳራሽን ማሳቀፍ። በዚህም ዘመን ሆነ
ለወደፊትም ለአማራ መተመማኛው አማራዊ ሥነ - ልቦናን በተከተታይ የመገንባቱን ሂደት አጠናክሮ መቀጠል ብቻ ሳይሆን ድርጁ አድርጎ፤ የሚመክት
አድርጎ፤ ወሳኝም አድርጎ የማውጣት ተግባር መከወን ነው።
- · ብአዴን እና ፈተናው፤
ብአዴን ለውጥ ከላመጣ፤ ብአዴን መዋቅራዊ ሥር- ነቀል እርምጃ ከልወሰደ ራሱ ብአዴን ቢሆን አማራ
ለእሱ መሆን አለመቻሉ የትናንቱ አልበቃ ብሎ አሁንም አማራን ለዳግም መከራ መናጆ ካደረገው፤ የሚከፈለውን መስዋዕትንት ከፍሎ ራሱን ማስከበር ግድ ይለዋል
አማራ።
እኔ ይቅርታ የማልጠይቀበት ሁኔታ አብን መንፈሴ አልተቀበለውም። ሰማያዊ ሲፈጠር የተሰማኝ ያህል
ነው የሚሰማኝ። በሰማያዊ ላይ ያልተፈለገ ውርጅብኝ ሲኖር ከማስተካክለው በስተቀር አንዲትም ቀን ከነፍሴ ጋር የተጣመረበት ወቅት
አልነበረም።
አብንም አሁንም እንደዛው ነው መንፈሴ የሚነግረኝ። አብሶ የአዲሱን አመራር አካላት ሥም ዝርዝር እና ሰከን ብዬ፤ የተመሠረተበትን ገፊ መንፈስ
እና ሁኔታ ወቅቱንም በማስተዋል ስቃኘው ግጥሜ ሊሆን አልቻለም። ከምንም ግን መሻሉን አሊ ልል አልችልም። ነገ ከፈቀደው ጋር እዋህዳለሁ
ቢልም ጉዳዬ አይደለም። አቅም አላብከንበትም፤ ተስፋም አልጥልበትም። ራሱን አጥርቶ እስከፍጻሜው ተግቶ ለአማራ መፍትሄ ከሆነም ጎሽ
ነው። ይቅናው! ግን በራሱ ገፊ ቁጭት የበቀለ አይደለም።
እስከ አሁን ባለው ግበረ ምላሽ አማራ የተደራጀ ባለቤት አለው ለማለት አልችልም። በዓላማ
ውስጥ ያለ ይዘልቃል ብዬ
እማስበው … የገዱ መንፈስ ጉዞው ወደ ብሄራዊ ማንነት እንጂ አማራ ተኮር ሊሆን አልቻለም። እንዲሁ ሳስተውለው፤ የትናንቱ
የአቶ ንጉሡ ጥላሁን የሚሊዬንም አዳራሽ የምልጃ ተማህጽኖም ይህንኑ የሚያጠናክር ነው። እኛማ አፈቀርን፤ ወደን ተጠጋን ግን ውጤቱ
መቸኮል የተገባ ስላልሆነ ለይደር ቢቀጠርም ሚኒ ላይ የታዬው ድራማ ግን ከበቂ በላይ ነው።
የሆነ ሆኖ ኦህዴድ ደግሞ ወደ ኦሮሞ ታላቅነት በብራዊ ማንነት መሰላልነት ነው መንፈሱ ያለው
ጭብጡ የሚነግረን። ኦህዴድ የሲብሉንም የፖለቲካ ድርጅቶችን የኦሮሞን መንፈስ አስከበሮ መንበር ላይ አውጥቶ፤ ሠርገላ አቅርቦ ሥነ
- ልቦናውን ለመገንባት እዬተጣደፉ ነው። የሚያንቀላፈው ደግሞ ብአዴን እያንቀላፋ በአጃቢነት ተሰልፏል።
የራሱን ሥራ መሥራት እንኳን አልተቻለውም። አንድ ለወልዴ ከሁለት
ሰዎች ውጪ ሚዲያ ላይ ወጥቶ የሚናገር እንኳን የለውም …
- · ሌላው ልብ ሊባል የሚገባው አመክንዮ …
ቀድሞ ነገር አማራነት አልፈለግነውም። ፈልጉት ተብለን በጫና ተቀብለናዋል። ከተቀበልነው በኋዋላ
ደግሞ አሁን ደግሞ እኛ ኦሮሞነታችን ከፍ አድርገን ወደ ኢትዮጵያዊነት መጥተናል እና አማራነታችሁን እርሱት ኢትዮጵያዊነት ብቻ ተቀበሉ የሚል ፍልስፍና ከመጣ፤ ይህ የአስመጪው እና የላኪው ጉዳይ እንጂ
የእኛ ሊሆን አይገባም። አንዲት ስንዝር ከአማራ የማንነት የህልውና
ተጋድሎ ፈቅ ማለት አይገባም። ቄሮ እኮ ሌሰን ነው ዛሬ። ለቄሮ አጎንበሶ
ማደግደግ እለታዊ ስንቅ ሆኗል። ከሊቅ እሰከ ደቂቅ ሥራው ይኸው ሆኗል መደበኛ።
እኛ ቄሮን ከማንም በለይ አክብረነዋል፤ የከፈልንለትም መስዋዕትነት አንድ ቀን እሱ ባለው ቀን ይወጣል። የአማራን ተጋድሎን ግን አንድ አንድ ወልዴ ሰው መስካሪ ሊገኝለት አልተቻለም
„ፋኖ“ የተጋደሎው መንፈስ አይደለምና። ተጋድሏችን የህዝብን ድምጽ የማስከበር እንጂ ሌላ ሊሆንም አይገባም። አማራ ተጋድሎ ነኝ ብሎ የወጣው እራሱ አብዮቱ ነው። ይህ መብቱ ለዛውም በ አብይ መንፈስ ሊነፈገው አይገባም። ታሪኩ የጣፋበት ዝከረ
ታሪኩን አገላብጦ በይቅርታ ማስተካከል ይኖርበታል። የቸ እና የሸ ጉዳይ አይለደለም። የዓላማ እና የግብ እንጂ።
እነሱ በኦሮሞነት ልዕልና ኢትዮጵያዊነትን ያጣጥሙ፤ እኛ ደግሞ አማራነታችን በመገፋት መከራ በዕንባ
እናጣጥማለን። ኢትዮጵያዊነት ሚስጢር አይደለም ብለው ሲያብዱ የነበሩ መንፈሶች እንኳን ለዚህ አበቃቸው ክብር ለፈጣሪ እነሱ ብርቃቸው
ነው፤ በዛው ይታደሙ።
እኛ የተፈጠረንበት፤ የኖርንበት፤ ለደቂቃም ያለስከፋነው፤ መከራውን ሁሉ የተቀበልንበት፤ የቀለጥነበት፤
በመዶሻ መንፈሳችን የተቀጠቀጠንበት ስለሆነ ብርቃችን አይደለም።
ይልቁንም ለእኛ ብርቃችን አማራነት ነው፤ አማራነት በመንፈሳችን ውስጥ አዲስ ገብ ነው። ስለዚህ ቤት ለእንግዳ ብለነዋል።
ስለዚህም አማራነት ማለት ምን ማለት ነው? አማራነቴ ምን ሰጥቶኛል? ምን ነስቶኛል? አማራነቴ
ከእኔ ምን ይጠብቃል? ለመሆኑ አማራ ተጋድሎ ዳርቻ አለውን? የሚለውን በሚገባ መርምሮ አጢኖ የምርምር ማዕክል በማድረግ ዛሬም ላልቆመው
መገፋት እና የመጫን፤ የመገለለ መከራ አማራነት አሸንፎ ይወጣ ዘንድ መትጋት ይገባል። ቀጠሮም አያስፈልግም።
ይህን የነፈገን ዕለት የአብዩ ይሁን የለማ መንፈስ ጠቡ ከማንም ጋር ሳይሆን ከሥርጉተ ሥላሴ ጋር ይሆናል።
አማራነት እሸት ነው፤ እሸቱን አብስሎ መልክ አስይዞ ተፎካካሪ ሆኖ በሰከነ ብልሃት፤ በጥሞናዊ
ጥበብ እና በብልህነት አርቆ ማስተዋል የነገን ዘላቂነት መገንባት አለበት። አማራ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን ማስከበር ትውልዳዊ ድርሻችን
ነው።
ለአማራዎች በተለይ ጥግ ለለን
አማራነት አልተሰራበትም፤ አጀንዳችን ሆኖ አያውቅም፤ ስለዚህ 43 ዓመት በዞግ ፖለቲካ ከቆዬው መንፈስ ጋር ተወዳዳሪ ሆኖ መውጣት
ባይችልም፤ ግን በእሸት ዕድሜውም ክርስቶስ ለእሱ በሰጠው መክሊቱ ዙሪያ ድርጁ የሆኑ ተግባራትን ከትናንት በላይ ዛሬ በትጋት መሰረት
አለበት አማራዊ ትውልድ።
አማራነትን የሚጫኑ ረቂቅ ተውሳኮችን በጥበብ ታግሎ መርታት ያስፈልጋል። አማራነትን በስውር የሚያጠቁ
መንፈሶችን እያስተዋልኩኝ ስለሆነ። „አማራ ተነጥሎ ተጎድቷል“ የማትደፈር አመክንዮ ናት። እርግጥ ነው ቀደም
ባለው ጊዜ አኟክ እንደ እኛው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሁሉም ማህበረሰብ
ማለት ይቻላል፤ የጥቃት ሰለባ ሆኗል፤ የመሞከሪያ ጣቢያ ሆኗል። ግን ቢሆንም ግን ህሊና ውስጥ እንደ አማራ በር የተቀረቀረበት ምስኪን
ማህበረሰብ የለም።
ጥቂት ሊኖሩ ይችላሉ፤ ቅኖች ሰዋዊዎች ግን ይህም ቢሆን አስተማማኝ የሚያደርግ ፖለቲካዊ አቅም
በመስጠት እረገድ የማይታሰብ ነው።
·
ጽኑ ተልዕኮ
የወጀብ ሲሳይ አይደለም።
ስለዚህ አማራ ተጋድሎ ተልዕኮ አለው። ተልዕኮው ወጀብ በመጣ ቁጥር
ምጥ ላይ መሆን የለበትም። ተልዕኮው ግቡ ገና ላልተፈጠሩት የአማራ ልጆች የብትን አፈር ብቻ ሳይሆን የነፃነት ዘላቂ ዋስትና ዕውቅና የማሰጠት ሰፊ እጅግ መጠነ ሰፊ ተግባር ፊት ለፊቱ ይጠብቀዋል።
ለነገሩ አንድ ተነባቢም፤ አንድም ተደማጭ ሚዲያ የለውም አማራ። ለዚህም ነው እዬጠቀጠቁት እንዲያልፉ
ሌሎች ምቹ ሁኔታ የተፈጠረው …
ብሄራዊነት ሊሰብክላቸው የሚገቡ ላለነበሩት አሳዛኝ ፍጡራን እንጂ ለአማራ ከሆነ ደረጃውን ያልጠበቀ
አመክንዮ ነው የሚሆነው። አማራ በነገረ ኢትዮጵያዊነት ሚስጢርነት ተጠማኝ የሚያደርገው ምንም ነገር የለም።
ሁሉም አለው።
አማራነት ከሌላውም አይበልጥም ከሌላውም አያንስም።
ስለዚህ
እኩል አድርገው ሊያሳትፉት በሚገባው ጉዳይ ላይ ዕውቅናውን ማስከበር የሚችለው በራሱ ውስጥ የሰከነ ድርጅት ሲኖረው ብቻ ነው። ድረጅት
ከሌለው አጃቢ አይሁን። ቤቱ ይቀመጥ። ሳይመርጥ ይቀር። ኮሮጆውን ባዶ ያደርገው።
እኔ የጀርመን የአማራ ድርጅትን እጅግ አድርጌ እወደው ነበር መንፈሱን። ባለቤት ልለው የምችለውም
ያን ነው። ሴራ የለበትም። ጥላቻም አልነበረበትም። ስድብ የለበትም። ቁርሾ እዬለቀመ አይተከዝም። አማራነትን ሌላውን
አጥቂነት ሳይሆን ራስን ጠበቂነት፤ ለሌለውም ደጅንነት ነው። በዚህ ውስጥ የተደራጀ መንፈስ ይናፍቅኛል። ገና አልተፈጠረም ለእኔ።
- · አማራ ከግንቦት 7 ምን ይማር?
አማራ አንድ ትልቅ ቁምነገር ከግንቦት 7 መማር አለበት። ግንቦት 7 መከላከያ አለኝ የሚለው
የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባርን ነው። ያም የአማራ አንጡራ ታሪኩ ነው።
ብዙም ገብሮበታል ከ35 ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው የአርበኛ አበጀ በለው፤ የጄኒራል ሃይሌ መለስ አንጡራ ትውፊት ነው፤
አባል አለኝ ደጋፊ አለኝ ውጪ አገር አለኝ ቢልም ግንቦት 7 አብዛኛው አማራ ነው፤ ሚዲያ ኢሳት
አለኝ ቢልም አብዛኛው ደጋፊ አባወራ/ እማወራ አማራ ነው።
ታገልኩበት የሚለው መሬት የአማራ
ባዕት ነው በዘመን አመጣሹ ቋንቋ ተወልጄው ያለበት፤ ዛሬ በዚህ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የተከበረው፤ ልዕልና የሆነው፤ የተፈራው፤
ራድ ያስያዘው ግን ግንቦት 7 እና ሚደያው ኢሳት ነው። አማራነት የማይፈልገበት ምክንያት ስለዚህ ነው። አቅሙን እንዲሸልም እንጂ በአቅሙ ልክ ዕውቅና እንዲኖረው አይፈለግም።
የሌሎችን ብሄረሰብ ሊሂቃን ዘብ ጠባቂ፤ ክብር አዳኝ፤ ፈዋሽ አማራ ነው። አሁንም ያለው የፖለቲካ ጨዋታ እሱ ተቀብሮ መኖር አለበት ነው
አምክንዮው። ይህ ለዛሬ ብቻ አይደለም ለወደፊትም ቀጣይ ነው…
- · ስጋት እና ምርጫ አልቦሽነት …
ኢህአዴግን ወደ ህብረ ብሄር እንዲሄድ፤ ምርጫ አልባ የሚያደረገውም እሸቱ እንቡጡ የአማራ ብሄርተኝነት ስጋት ነው። አማራ በአቅሙ ልክ ከወጣ ቻይ እንደሌለው በሚገባ
ይታወቃል። የሌላ ብሄረሰብ ሊሂቃኑ ቋንቋ ሲገናኙ ይሄው ነው። የሚገረመው ይህን ለማስፈጸም ነው ሌት እና ቀን የገዱ ሆነ የአንባቸው
መንፈስ የሚታገውም። አማራ አጓጓዥ እንዲሆን ብቻ ነው።
„ከዬት መጣ“ አትበሉን ነው የሚሉት ደፍረው እንዲህ ይናገራሉ። ይህ መቼም
አለማፈር ነው። ትናንት በነሳጅን በረከት ስምዖን፤ በእነ ሳጅን አዲሱ ለገሰ፤ በነሳጅን አለምነህ መኮነን ወኪል
አልቦሽ አማራ አሳሩን በላ፤ ዛሬ ደግሞ መንፈሴ የእኔ በሚላቸው በዶር ገዱ ገዱ አንዳርጋቸው መንፈስ ስብከቱ ይሄው ነው።
የሚገርመው
በደሉን አታንሱ፤ አጋር አልባ መሆናችሁን አታንሱ አማራነት ዕውቅና ይሰጠውም አትበሉ፤ ይህን ፍርደ ገምድልነት እዬር ይዳኛው። የት
ይደረስላቸው ይሆን አማራ? አማራ ነፃነቱን እስከ መቼ ይጠብቅ?
ብአዴን አሁን የያዘው መርህ ቢያውቀው ይህ ለአማራ አቅም ተሰብሮ -ጎብጦ - ዕውቅና ተነፍጎት፤ ተንበርካኪ ሆኖ እንዲቀጥል የሚደርግ እንጂ ፈዋሽ
መንገድ ሊሆን አይችልም። ኦህዴድ እሳት የላሱ የኦሮሞ ሊሂቃን ከላይ እስከታች በተተኪ ያቀርባል። ብአዴን ደግሞ በድርቅ
ምት ይተክዛል። አስደሳቹ ነገር ወጣቱ የአማራ ትውልድ ብቻ ሳይሆን መሬት ላይ ፆታም፤ ዕድሜም፤ እውቀትም፤ ሃይማኖትም
ሳይለይ በሚገርም ፍጥነት እና ጥንካሬ አማራነት አሽቷል። ውጪ አገር ደግሞ የሚገርም ነው።
ከእንግዲህ በኋዋላ ይህን አማራዊ መንፈስ እቀለብሳለሁ ቢባል ያልተለደሙ ነገሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ። እደግማዋለሁኝ ያልተለደሙ ነገሮች ይከሰታሉ። ሞቱን እንደሆን ለምዶታል አማራ፤ ስደቱንም እንዲሁ። መገለሉ ህይወቱ ነው፤
መጨፈልቁም ኑሮው ነው። ስለዚህ ለዛው መሰል ጉዳይ ጢሶ ወጥቶ ማሸነፍ ምርጫው ይሆናል። „ጢስ እና ልጅ መውጫው“ አይታወቅም እንደሚበላው።
አባ ዝምታ አማራ ዝምታውን ሰብሮ የወጣ ቀን ይከብዳል። ወያኔ ሃርነት ትግራይን እንኩትኩቱን
ያወጣውም ያ ገደለኛ አማራዊ አብዮት ነው፤ ከተለመደው ውጪ ደማቅ ድምፆችን ይዞ ስለወጣ። አሁን እራሱ የተጫነውን ሁሉ ለመሸከም
የሚፈቅደው እዮባዊነት ተፈጥሮው ስለሆነ ብቻ ነው። ሲከር ግን መበጠሱ፤ ሲሞላም መገንፈሉ
እና መፍሰሱ ግን አይቀሬ ነው። የትናንት ላይባቃ አሁን ደግሞ አዲስ ሸከም አንግተህ ዝለቅም ግፍ ነው?
እኔ ከአማራ ተጋድሎ ጋር የምጣለው ቅናዊ ሳይሆን፤ ሴራዊ መንገድ ከተከተለ፤ አሉታዊ ሆኖ ሁንም
ነገር ጸረ አማራ አድርጎ ከተመለከተ፤ ኢትዮጵያዊነት ምኔም አያደለም ካለ፤ አዲሱ ለውጥም አይመከተኝም ካለ ብቻ ነው። ከዚያ በመለስ
ያሉ ክብርን በአቅም ልክ ፖለቲካዊ ዕውቅናውን በማስመለስ እረገድ ሎሌው ነኝ። እተጋለታለሁኝ። ለብሄራዊነትማ አንደበተ ርቱው ጠ/
ሚር አብይ አህመድ ተደመውበታል። መደበኛ ሥራቸውም አድርገውታል። እኛም ሆነንበት ሞገትንበት ኖርን እኮ። ለዚህም ነው ጸጋዬ፤ ጸጋዬ፤
ብርቱካን ብርቱካን ስንል የባጀነው።
- · ክውና።
አማራነት ሰዋዊነት፤ ተፈጥሯዊነት፤ ፍቅራዊነት፤ ሰው አማኝነት፤ ሃይማኖታዊነት፤ ቅናዊነት፤ ቸርነት፤
ታጋሽነት፤ ቻይነት፤ ይሉኝታዊነት፤ ርህርህናዊነት፤ እኛዊነት፤ አብሮነት፤ አገር ወዳድነት… ወዘተ ስለሆነ ልገፋው ፈጽሞ አልፈቀድም።
ያሰጣኝ አንዳችም ነገር የለም። መከራው ነው የተለመደ ነው። አቅሙ መፈራቱ ያለ የነበረ ነው፤
ስለሆነም የፈለገ ቢሆን ከዚህ መንፈስ ውጪ የምትሳካ ቆራጣ ነገር እንደሌለ ሁሉም ያውቃዋል - አሳምሮ። ተፈሪነቱም ለዚህ ነው።
መንፈሱን አቅጭጮ እጓዛለሁም ከእንግዲህ አይሆንም፤ ወያኔ ሃርነት ትግራይ 27 ዓመት ተጠቅሞበታል
… ያ መንገድ እንደ ገደለው ብቻ ሳይሆን ተተኪ አልባ እንዳደረገው አሳምሮ አማራው ያውቀዋል። ልዑል እግዚአብሄርም፤ አላህም የማያሳጣውን
ነገር አይነሳውም፤ ታማኝ አገልጋዩ ነውና …
የኔዎቹ
ኑሩልኝ።
„አማረነት
ይከበር!“
„እንከባብር“
መሸቢያ
ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ