ማን ነው #የጠበቀው? #ዳታ ሠርታችሁልን?
"እግዚአብሄርን መፍራት ወደ ህይወት ያመራል።"
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፱ ቁጥር ፳፫።)
#ምዕራፍ ፳።
"የመንግስት ምስረታው ለምን ተጠባቂ ሆነ?"
በተለይ ሚዲያ። የራስን ሃሳብ ይሁን ፍላጎት ይሁን ምኞት ይሁን ራዕይ በፈለጉት ቃል
መግለጽ ይቻላል።
ቢያንስ አገር ውስጥ ያሉ ዕውነተኛ ሞጋች ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶችን
ማሰብ ይገባ ነበር።
#የሰላማዊ ታጋዮች እነሱ ተወዳድረው ውጤት ያላገኙበትን የምርጫ መቋጫ
መድረስ የተገባ አይደለም። #የታሠሩም አሉ እኮ።
ይህ ባለ ልዩ መክሊት የማህበረሰብ ክፍል የልቡን ሲያገኝ ብቻ ነው ግብረ መልስ
የሚሰጠው። ይህንን ጠቅላይ ሚር አብይ ወደ ሥልጣን ሲመጡ፤ #የቴዲ "ዳስ ጣል" ላይ
ታይቷል። ፖለቲከኞችን ወደ #ዘፈን የሳበ ሞገድ እኮ ይሄው የጭምቱ ማህበረሰብ ልዩ የአቅም
ክህሎት ነው።
የሰው ልጅ በኢትዮጵያ መኖሩ በምን ሁኔታ ይገኛል?
ሰላም በኢትዮጵያ?
ነፃነት በኢትዮጵያ?
የመፃፍ፤ የመናገር፤ የመደራጀት ነፃነት በኢትዮጵያ?
የመዘዋወር፤ ወጥቶ የመግባት ነፃነት በኢትዮጵያ?
ሃብት የማፍራት፤ የመጓዝ ነፃነት በኢትዮጵያ? ወዘተ ………
መሥፈሪያቸው ይህ ለሆኑት ደግሞ በእርግጥም የብልፄን መንበረ መንግሥት በጉጉት ይጠብቁታል ወይ?
የፖለቲከኛ እስረኞችም አሉ።
ዱር - ቤቴም ያሉ አሉ።
እርግጥ ነው ብልፄው ሚሊዮን አባሎች አሉት፤ ደጋፊወችም አገር ቤትም ውጭም ይኖራሉ።
እነሱን አስቦ ቢሆንም ይህን መሰል ሁሉን የጠቀለለ ጠንካራ #አቋም ደፍሮ ዕርዕስ ማድረግ ከባድ ይመስለኛል።
ለብልፄውም ከመዛናጋት ውጪ ሊያተርፈው አይችልም።
ኢትዮጵያ እኮ #ጦርነት ውስጥ ነው ያለችው። ሌላው ለፓርላማ እነዛው ፖለቲከኞች ተወዳድረው
አሸነፋ ከተባለ ዓመት ድገመኝ ካልሆነ እራሳቸው በነባር ባለሥልጣናት አዲስ ነገር የለም።
አውቀውታል። Surprise የለም እንደማለት። የፓርላማ አፈ ጉባኤን ወደ ፌድሬሽን አፈጉባኤ ማሸጋሸግ
ምኑ ይሆን አዲሱ????
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
06/10/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
See less
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ