#የከበደ ምስክርነት ለባለቤቱም ለተመስጋኙ ለአመስጋኙም።

 

#የከበደ ምስክርነት ለባለቤቱም ለተመስጋኙ ለአመስጋኙም።
 
"ልጄ ሆይ በክፋ ሰወች አትቅና፣
ከእነርሱ ጋርም መሆንን አትውደድ፣
ልባቸው ግፍን ታስባለችና፣ ከንፈራቸውም
ሽንገላን ትናገራለችና።"
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ከ፩ - ፪)
 
 
"ጭምት ናቸው" ሲባል እሰማለሁኝ። ለትዳራቸውም ታማኝ ናቸው" ሲሉ እሰማለሁኝ። ምክትል ጠቅላይ ሚር አቶ ተመስገን ጥሩነህ።
እኔ አየር ላይ ያዬኋቸው፣ ሥራ ላይ እንደነበሩ ያወቅሁት የአማራ ክልል ሊቃናት #ሰማዕታት ሲሆኑ ያን ጊዜ የአማራ ክልል መስተዳድር ፕሬዚዳንትነት ለአንድ ዓመት #በተመላላሽነት ሲሰሩ ነው ገፃቸውን ያዬሁት። 
 
አወንታዊ የሆነ ዕይታዋን የሰጠች የማከብራት አንስት ብዕረኛም ነበረች፣ ከእኔ ከእሩቋ ይልቅ እሷ ቅርብ ናት።
በጸረ ህወሃት የትግል ዘመን አላውቃቸውም ነበር። የሆነ ሆኖ በብልፄው ጉባኤ ላይ "ብልጽግናን መምረጥ ነገን መምረጥ" ነው ሲሉ ሙግት ቢጤ ጥፌ ነበር። ዕውነት ለመናገር ጽፌባቸውም፣ ሞግቻቸው አላውቅም።
 
ዛሬም #ልሞግታቸው አይደለም። ህዝብ የሚዬው የዕውነት - ዕውቀት አለና ለህዝብ የህሊና ዳኝነት ዕድሉን መስጠት ይገባል። እንደ እኔ ግን የሚከብድ ይመስለኛል ለቀጣይ ህይወታዊ ህሊናዊ ጉዳይ። 
 
በዚህ #የአዲስ #ፕላኔት ይሁን ሐዋርያ የአቶ ተመስገን ጥሩነህ ፍለጋ እና #ግኝት ውስጥ እንዴት የመንፈስ ቁመናቸው እራሱን ችሎ በጤነኝነት እንደሚቀጥል አላውቅም። ዶር አብይም አንገታቸውን ደፍተው አቀርቅረው ነው ያዬኋቸው። 
 
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ህዝብ #የትግዕስቱ መጠነ ሰፊነት #ቁሞ አስተምሮኛል። ንግግሩን ለማዳመጥ ልዩ የመቻል፣ #የመታገስ አቅም ይጠይቃል። ለ24 ሰዓት የቆዬ ንግግር ያህል ከባድ ነበር። #ይፈትናል። ዕውነት ቦታውን ለቆ ስለማያውቅ ያፋጥጣል። 
 
በሌላ በኩል እንደ ሰው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ በዘመናቸው የሠሩት ጠንካራም ይሁን ደካማ ጎን ይኖራል። "ልምድ የላቸውም" ሲሉ የምሰማቸው ፖለቲከኞች አሉ። ያንጊዜም በሚዲያ የሞገቱ ነበሩ። 
 
ሚኒስተር ነበሩ፣ የሠራዊቱ አካል ነበሩ፣ የቢሮ ኃላፊ ነበሩ በመንግሥት አስተዳደር፣ አመራር ውስጥ ማለፋቸው አሊ ሊባል አይቻልም። ችግሩ የአቶ ተመስገን ጥሩነህ ምስክርነት ያን ጨምሮ ነው ምስክርነቱ #ድምጥማጡን ያወጣው።
 
አንድ ኩባያ ወተት እየጠጣችሁ ሽቶ ቢረጭበት ሙሉው ኩባያ ሽቶ ሽቶ ይላልል። በተጉበት መስክ ሁሉ #ተጫኝ ሃሳብ ነው። ሩዋንዳ ሁሉ በሰላም ማስከበር #በተመድ ተሳትፈዋል። ያን ሁሉ አቀጨጨው።
 
መካሪ ቢኖር፣ መካሪን የማድመጥ ባህል ቢዳብር ከፕሮቶኮል አንፃርም ጹሁፋ ታርሞ ቢቀርብ ጥሩ ነበር። ቢያንስ ሰብዕናን የግል ማዳን ይቻል ነበር። ሰው ሰው እንጂ መላዕክ አይደለምና። 
 
ዶር አብይ አህመድ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚር እያሉ አዳምጣቸው ነበር። አብረዋቸው የሠሩ ሰወችም የነገሩኝ አወንታዊ ጉዳይ ነበር። የዛን ጊዜው "ከእርምጃ ወደ ሩጫ" አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚር የሰጡት ምስከርነት ያን ሁሉ አወደመው። 
 
ይከብዳል። በጣም ይከብዳል። በልክ በመጠን ሲሆን ሁሉም ነገር ያምርበታል። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ሳይፈተኑ #ተመሰገኑ። #ተደገፋ። ዓለም ዓቀፍ የኖቤል ሽልማት አገኙ። አገር እየመሩም ደግሞ ታዩ። ቃላቸው እና እሳቸው ተመዘኑ።
 
በዚህ ሂደት ጭምቱ ማህበረሰብ ምን ሚዛን ላይ እንደሚያስቀምጣቸው አቶ ተመስገን #ጥናት አልሰሩም። እሳቸው የጓደኝነታቸውን፣ የፍቅራቸውን ያህል ከባዱን ምስክርነት ሰጡ። 
 
ዛሬም፣ ነገም ምክትል ጠቅላይ ሚር አቶ ተመስገን ደስአለኝ በዚህ ሚዛን ውስጥ ይሆናል የሚሰፈሩት። በጣም የተደሰቱ ጹሁፎች አንብቤያለሁ። የታዘቡም አሉ። "ትዝብት ናት ትርፋ" ይሉ ነበር አባት አቶ ፍሰኃ ለምለም።
 
የሚሰነብት፣ አድሮ የሚገኝ በልኩ የሆነ ልከኛ ምስክርነት የተሻለ ነው ለተመስጋኙ። ይህን መሰል ግን ይጎዳል። ያሳቃልም።
 
ዛሬን የሚያውል፣ ነገን የሚያሳድር፣ ሥልጣኑ ቀጠለም ተነሳ ዘላቂ አሻራ ሊሆን በሚችል መልክ አደራጅቶ ማቅረብ ይገባል። ትውልድ ይቀጥላልና። 
 
ንጹህ ሃሳብን #በልኩ አደራጅቶ ማቅረብ አሻራም ነው። ለቀጣይ ትውልድም ካሪክለም ነው። የቃላት ኃይል ብዙ ነገር ያበጃል ወይንም #ይሰውራል።
 
“ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ደሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትርነት እጩ ሆነው ቀረቡ |» Prime minister | ETV | EBC | 
 
ቸር አስበን፣ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፣ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
06/10/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
See less

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።