ይህ ዜና የዘር ሐረጌ #ከኢትዮጵያ ነው ለሚል ሁሉ #የምሥራች ዜና ነውን?
«በግብፅ የተሰባሰቡት የኢትዮጵያ ጎረቤቶች በቀይ ባሕር እና በድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ላይ የጋራ መግለጫ አወጡ»
"ዕውቀትን ለማን ያስተምረዋል?
ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል?
ወተትን ለተወ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን?
ትእዛዝ በትእዛዝ፤ ሥርዓት በሥርዓት፤ ጥቂት
በዚህ ጥቂት በዚያ ነው?"
"ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፰ ከቁጥር - ፲፩።"
እንዴት አደርን ማህበረ ቅንነት ዛሬ ሁሉም በየፈርጁ ይሞገታል።
ሃሳቡ ነው የሚሞገተው።
#ምዕራፍ ፳።
ለምን ተወቀሱ? ለምን ተነቀሱም አለበት?
ኢትዮጵያ ሆይ! ስንት አሜኬላ፤ እሾህ፤ ኮሸሽሌ፤
ትሬኮላታ ሃሳብ አራማጅ በአንቺ ልጅነት ይጠራ?
ዘመን - ጊዜ - ራዲዮሎጂ ነው ማለቴ ትክክል ሆኖ አገኜሁት።
ሥርዓት ይመጣል ይሄዳል። ይደምቃል // ይከስላል
አገር ግን ከእኛ በፊትም፤ ከእኛም በኋላም ትቀጥላለች።
እኔ እምለው። ይሰቀጥጣል በውነት የምትሰሙት ትንታኔ
ይቀጠቅጣል። እናትን በዚህ ያህል ከውስጥ አግልሎ
በእሷ ሥም በተገኜ ተጨማሪ ዜግነት እየተኖረ??? ይገረምማል፤
ይኮሰኩሳል። ይገለማም።
የሚታገሉት በሚታገሉበት መሥመር፤ በብዕር እምንሞግተው
የምንሞግተው ኢትዮጵያ አገረ - መንግሥት ስላላት ነው። ዛሬ
እንዲያውም #ብልፄውን ልሞግት ነው የገባሁት። ቻል ብልፄው
ብዬ መጥቻለሁኝ። ስንቅ ቋጥሮ የሚያስተዳድራቸውንም
ሚዲያወች ጭምር። ዛሬ ርህራሄ የለም።
ግን ሁሉም ነገር ከፈጣሬየ በስተቀር ከአገሬ ከኢትዮጵያ መንፈስ
በላይ ሆኖ ክብሯን፤ ልዕልናዋን፤ ልቅናዋን፤ ገናናነቷን በገዛ ፍሬወቿ
ሌሎች ይድጡት ዘንድ፤ #ይጨፈላልቁት ዘንድ አልፈቅድም።
ከተፈጠሩባት መሃጸን ይልቅ የትውስት ማህጸን ለሚሹ ወገኖቼ
ይብላኝላቸው እንጂ ሁላችን ብንተዋት ዓለም ኢትዮጵያን አይተዋትም፤
ሁልጊዜ #ፓን ኢትዮጵውያን በዓለም መድረክ ብቅ ብለው ዓለምን
#የምሥራች ዜና ናት ኢትዮጵያ ብለው ያስደምማሉ።
የምክክሩ ኮሚሽን ሂደት የብልፄን መንፈስ ማፋፋት ነው።
ግን ስኬቱ የተከበሩ የቀድሞው የኬኒያ ፕሬዚዳንት ሁሩ ኬንያታ ኢትዮጵያን #ቀድሰዋታል።
በ2013 ዓም ላይም የጠቅላዩ ሹመት ላይ ያን የመሰለ የአፍሪካን ትውልድ በኢትዮጵያ
መንፈስ ውስጥ የተጸነሰ፤ የተወለደ፤ የአደገ፤ ያሰበለ መሆኑን ንባቡን፤ ትርጓሜውን፤
ማመሳጠሩን ተቃኝተውበት።
ቁጭ አድርገው ውስጣቸውን #የሳቱ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊቃናትን ፊደል አስቆጠሩ፤ አቡጊዳን
አስቀጠሉ፤ መልዕክተ የኋንስን አስቀጥለው ዳዊትን አስደገሟቸው። አገር ሳንሆን መለያ ሰንደቅ
ዓላማ ሳይኖረን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ተስፋችን፤ ብርሃናችን፤ ጎዳናችን
ካፒቴናችን፤ ጥጋችን ከለላችን ስለነበር ፓን አፊሪካዊው ወላጅ አባታቸው በስደት ቤታቸው
ውስጥ ኢትዮጵያ ነበረች።
ሌላዋ የባርባዶሷ የደሴቷ መሪ በተመድ ጉባኤ በሙሉ የራስ መተማመን ማህለቅ
ኢትዮጵያ ቀደምት የሰብዕዊ መብት ተሟጋችነቷ ብቻ ሳይሆን፤ ቀድሞ የዘመን ፖለቲካዊ
ባህሬ በመተንበይም እረገድ ልቅናዋን #በቅኔ አስመስክረዋል። ስለአባይ ይሁን ስለ ዓድዋም
ታሪኩን ጽፈውታል። በተለያዬ ጊዜም። ተመስገን ነው።
እኛ ቅኝ ተገዝተን አናውቅም። አለማወቃችን የሰጠን ቢሊዮን ክስተት እያለን እርቃን
መቆም ይናፍቀናል። እኔ በየትኛውም አገር ፖሊሲ ሥር መሆን አይናፍቀንም። ለዛውም
የትኛው እና ምኑ ይሆን የሚናፈቀው። ጎንደሮች ባለቅኔ ናቸው ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ
ይቀራል ይላሉ። ዝምታው ለዚያ ነው።
የአንዲት ትንሽዬ አፍላ አገር ተገዢነት የኖፈቀው ካለ መንገዱን ጨርቅ ያድርግለት።
ዝም እምንለው ምላሳችን ተጠቁሮ አይደለም። ማረጋጋቱን በማስቀደም እንጂ።
በተባለው ቦታ ያልተገኜውን /// የማይገኜውን ብልፄን ቢሆን እስኪ ብለን የምናልፈውም
ሱዳን፤ ሱማሌ ወዘተ ስለማይናፍቁን ነው። ከሁሉ አስከፊው እና ሰቅጣጩ መከራ
#ሥርዓት አልበኝነት ነው።
ይህ አደጋ መላ ኢትዮጵያን ካጥለቀለቀ ጀምሮ ሳይሆን ሳይመጣ አስቀድሞ መመከት
የሚቻለው ሴሪሞኒያዊ ብቻ ቢሆንም ኢትዮጵያ፤
የኢትዮጵያ መንግሥት የሚባል ፍሬ ነገር መኖርን ግድ ይሆናል።
ምርጫ ላይ ተሳተፋ ስል የነበረው ለዛ ነው። ፍርስራሽ ቃርሚያ ለዛውም አፍሪካ ህብረት፤
ተመድን መንፈሷን ለቀለበች አገር እንዴት? ኧረ እንዴት???
ጭካኔ ካላሰከረን በስተቀር፤ ከሰብዕዊነት ካላፈነገጥን በስተቀር #አናርኪዝም
ሊናፍቀን ከቶም አይገባም። አሰፍስፈው ያሉ ክስተቶች ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት
ክስለት እንጂ ክብረት አይደለም። "አገር የለኝም ማለት" አያድርስ ነው።
በቅርበት የኩርድሽ ጋዜጠኛ ጓደኞቼን ውስጥ ስለማውቅ። ከጨለማ በላይ፤ ከእሳተ ጎመራ
#ላርባ በላይ እጅጉ አስፈሪው ገጠመኝ የአገር ነገር አይሆኑ ሲሆን ነው። "የሰይጣን
ጆሮ ይደፈን።" አሜን። የትኛውም ፍልሚያ፤ የፍልሚያ ዓይነት ግቡ ምንድን ነው? አገር
ለመምራት ከሆነ "የቤትህ ቅናት በላኝ" ማለትን መዋጥ ይገባል።
“Uhuru Kenyatta at Ethiopia’s National Dialogue: A Historic Message”
“Barbados - Prime Minister Addresses United Nations General Assembly 81st Session | #UNGA”
“Prime Minister Mia Mottley: Climate, Immigration, and the Power of Small Nations”
ጦርነት አሸናፊ ተሸናፊ ውስጥ የለሁም። ጉዳዬ በዛ ውስጥ ስለገበረው የኢትዮጵያ እናቶች ማህጸን ያሳዝነኛል። ከሁሉም ኢትዮጵያን ከውስጡ ያራቀ ሃሳብ ያስጨንቀኛል።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
06/10/026.
አገሬ ኢትዮጵያ ክፋ አይንካሽ። አሜን።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
See less
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ