መቼ ነው ወደ ጎልማሳነት የምትሸጋገሩት? ምን አለ #ከእጩ ወጣትነት እራሳችሁን ብትታደጉ?
መቼ ነው ወደ ጎልማሳነት የምትሸጋገሩት? ምን አለ #ከእጩ ወጣትነት እራሳችሁን ብትታደጉ?
«በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአብረሃም በላይ (ዶ/ር) ጋር የተደረገ ቆይታ | ETV | EBC | EBCDOTSTREAM»
"ዋይታ ለማነው? ኀዘን ለማን ነው? ጠብ ለማን ነው?
ጩኽት ለማን ነው? ያለምክንያት መቁሰል ለማን ነው?
የዓይን ቅላት ለማን ነው?"
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፫ ቁጥር ፳፱)
#ምዕራፍ ፳።
ጉዳዬ የዶር አብርኃም በላይ ቃለ ምልልስ አይደለም። ለነገሩ እሳቸውም የመለሲዝም ትውልድ ናቸው። ይህ × ይመቻቸዋል
ብዬ አላስብም።
#ነገረ ሚዲያ እና የቲን ኤጀርነት ናፍቆት።
ሚዲያ መሠረቱም፤ ራዕዩም፤ ግቡም ህዝብ እና ትውልድ፤ ማግስት እና ተስፋ፤ ሞራል እና ኤቲክስ፤ ህግ እና ሥርዓት፤ ነፃነት እና "ፍትሃዊነት" ወዘተ በመሆኑ ትውልድን አስቦ መሥራት ቀዳሚ #ዶግማው ሊያደርገው ይገባል።
ወጣትነት፤ እጩ ወጣትነት በራሱ ጊዜ የሚኖር የባህሬ ዓይነት ቁጣ፤ ግንፍልነት፤ ብስጭት፤ ገረጭራጫነት፤ ችኩልነት፤ አኩራፊነት፤ ልቅ ነፃነትን መሻት፤ ፈጣንነት፤ #አቅማዊነት፤ ብሩህነት ወዘተ ማነሳሳት ይቻላል። ሁላችንም ያለፍንበት ነው። እናውቀዋለን።
ልጆች ላለውም፤ የልጅ ልጅ ላለውም አብሮ ይኖራል። ሳይኮንበት ግን እያዩት ለመኖር ዕድል ይፈቅዳል እንደማለት። ግን የራስን ዘመን፤ የተቋምን ዘመን ለክቶ በልኩ መጥኖ መንቀሳቀስ የተገባ ነው። ወጣት ሆነው ወጣትነታቸውን ተላልፈው እንደ ጎልማሳ የሚያስቡ ርጉ ሰብዕናወች እኮ አሉ። በተለይ ህግ ያጠኑ ሰብዕናወች፤ በሃይማኖት ቀኖና እና ዶግማ የተመሰጡ ወጣቶች ህይወታቸው የማስተዋል መምህር ሆነው የሚገኙ አሉ።
ከሥርጉትሻ ቤት የእግዜአብሄር ፍጡር የሰው ልጅ ቀንድ፤ ጅራት ተሰርቶለት፤ በምስሉ ላይ #ኤክስ ሆኖበት፤ ወይንም ተዘቅዝቆ፤ ነውረኛ ቃላትም ታክሎበት አይፈቀድም። ፌስቡክ ስጀምር በጣም ብዙ ችግር ነበር። በትጋት ነው የሠራሁበት። ጊዜ መስጠቴ ካልቀረ የታረመ አንደበት፤ የተቀጣ ብራና እና ብዕር እንዲኖር ተግቻለሁኝ።
እንዲህ ዓይነት ገጠመኝ አልፎ አልፎ ሲገጥም፤ ለረጅም ጊዜ በቤታችን የቆዩ ከሆነ በጓዳ ሄጄ አሳስባለሁኝ፤ ወይንም ለ30 ቀን ሚዩት አደርጋለሁኝ። ከተደጋገመ ግን ሥልጡኑ ፌቡ በሰጠኝ ዕድል መሠረት መራራ ስንብት ይሆናል። እንኳንስ አንጋፋወቹ የሚሊዮኖች ቤት የኢትዮጵያ የመንግሥት ሚዲያወች ቀርቶ።
በይፋ ነው #በደጺዝም ፎቶ ላይ ኤክስ አድርጎ ለጥፎ ከች ያለው። እጩ ወጣትነት ይህን መሰል ግድፈት ያሠራል። ኤዲተር የላችሁምን? የህግ ክፍልስ? ለሃሳብ የተፈጠረ ተቋም በሃሳብ መሞገት ሲሳነው #በቁጫን መበቀል እንደ ኮበሌ???? አይጠቅምም። ፈጽሞ አይጠቅምም።
እነዚህ ሰወች እኮ #አራጠው 27 ዓመት መርተዋችኋል። አሁን ያሉ መሪወችም #የመለሲዝም ትውልድ ናቸው። ሌላ ከሌላ ፕላኔት የመጣ የለም እኮ። #እሱበእሱ እኮ ነው። የገበርዲን እና የከረባት ለውጥ ነው። የሰሞኑን ሹመቱን ተመልከቱት? #ኢህአዲጋዊ ነው። ይህ ዕውነት ነው። ፍልሚያው ለመንበረ መንግሥት ይገባኛል ብቻ ነው። #ረጋ ብላችሁ እሰቡት።
እባካችሁ የኢትዮጵያ ሚዲያወች ሆይ! ለሰው ልጅ የተሰጠውን #ተፈጥሯዊ #ሚዛናዊነት እና #ማስተዋልን አትግፉት ወይ እንደ በርሚል አታንከባልሉት። ህወሃትን በሃሳብ በሰላ የሃሳብ አቅም ነው በሰላም እራሱን ድምጽ ሰጥቶ ነበር መንበረ መንግሥቱን ያስረከበረው። አማርኛ ቋንቋ ዲታ ነው። ጉልበታም ነው።
አይደለም ወጣ ገቡን የኢትዮጵያ ፖለቲካ የዳበሩትን ሥልጡን አገር ፖለቲካ የማሳመን ጥንቅቅ ያለ አቅም ያለው ቋንቋ ነው። የሚቀናቀኑት እኮ አቅም ስለላቸው ነው። ግን ያሸንፋል በውስጡ ኦርጋኒኳን ኢትዮጵያ ስለአመሳጠረ። ዕርዕሱን አጎልብታችሁ ማውጣት ትችሉ ነበር። #የልጆች ሥራ ከምትሠሩ።
ስለምን የታዳጊ ወጣትነት ናፍቆት ይዟችሁ በዘመን የከበረ፤ በዘመን #የሰላ፤ የበሰለ ወይንም የደረጄ ተቋም ለምን እንደ ዕድሜው ማሰብ እንደተሳነው አልገባኝም። እንደ ታዳጊ ወጣት ፎቶ ላይ ኤክስ አድርጋችሁ ለሚሊዮኖች ዕይታ በአደባባይ ትቀርባላችሁ? #ሃይ ባይ የላችሁንም? #ሃግ የሚል የለምን? ለነገሩ በቦርድ አባላቱ እነማን ቢሆኑ #ስክነት መጠራት ተሳነው ይሆን?
#አደብ በብዙ ያስፈልጋል።
"ቤት በጥበብ ይሠራል፤
በማስተዋል ይጸናል።"
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ፫)
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
06/10/026.
ትዕግሥት ሲያልቅ #ፍቅር ይሰደዳል።
ፍቅር ሲያልቅም ትዕግሥት ይሰደዳል።
See less
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ