የእናትነት #የእናታዊነት ነገር ህብር።
የእናትነት #የእናታዊነት ነገር ህብር።
ፆመ ጽጌ ልዩ ፍጹም ልዩ ድንቅ ጊዜ።
ዘለግ ያለ፤ ዝልቅ፤ ፍልቅ፤ ብርኃናማ ጊዜ።
#ጎንደር ገጠር የጽጌ ፆምን አስመልክቶ
መላው የገበሬ ማህበር የመታሰቢያ
የመገናኛ ጊዜ በየሳምንቱ አላቸው።
"አቤቱ አንተ አምላኬ ነህ ድንቅን ነገር
የዱሮ ምክርን በታማኝነትና በዕውነት
አድርገኃልና ከፍ ከፍ አደርግኃለሁ
ስምህንም አመሰግንሃለሁ።"
(ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፭ ቁጥር ፩- ፪።)
ለፆመ ጽጌ ቤተኞች እንኳን አደረሳችሁ።
ፆመ ጽጌ #የመሰባሰብ ይሁንልን። አሜን።
ሥርጉትሻ 6/10/026.
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ