#ከ2010 – 2024 አይቆጠርም። ኃላፊነት እና ተጠያቂነቱስ? • #ቦነሷ ዝቀሽ በሆነባት አገር አገረ ኢትዮጵያ።

 

#ከ2010 – 2024 አይቆጠርም። ኃላፊነት እና ተጠያቂነቱስ?
• #ቦነሷ ዝቀሽ በሆነባት አገር አገረ ኢትዮጵያ። 
 
«በኃይል ሳይሆን በሃሳብ የበላይነት በምክክር የምትጸና ኢትዮጵያ ETV | EBC | EBCDOTSTREAM»
«ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)አዲሱ የመደመር መንግሥት በይፋ ሲመሰረት ያስተላለፉት መልእክት» | Pm Abiy Ahmed
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።"
 
 
፩ኛ።
 
የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ መክፈቻ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ፤ በዛ በቀድሞው የኬኒያ መሪ አስደማሚ ንግግር በተደረገበት የምክክሩ የመዝጊያ ሥርዓት ላይ አልተገኙም። ጥፍት ብለው ነበር። 
 
እኔ በጥሩ ጎኑ ነው ያዬሁት። የጥሞና ጊዜ ከነበራቸው። ከሰሞኑ የራሳቸውን መንፈስ ለራሳቸው ርክክብ ሊፈጽሙ የአጀንዳ የውሳኔ ሃሳብ፤ ያሰቡት ሳይሳካ በቀረው በኢትዮጵያ፤ በአፍሪካ፤ በዓለም የዲፕሎማሲ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባን የኦሮምያ የማድረግ ህልማቸው በአሰቡት መስመር ከስሟል። የልጆች የዕቃ ዕቃ ጨዋታ በሚመስል በሚያስገምትም ሁኔታ ተለጣፊ ፈጥረው አንገዋለውታት ፋክት ዕውነት የ4000 ታዳሚን መንፈስም። 
 
ይህ ሃሳብ በምንያህል #እርቀት "ለታላቅ አገር ለታላቅ ህዝብ ለታላቅ ራዕይ" ለሚባለው የሚዲያ ሞቶ #እሩቅቅ በጣም እሩቅ እንደሆነ ላስታውሳቸው እፈልጋለሁ በትህትና እና በአክብሮት። እራሷ አዲስ አበባ በፌድራል ሥር ትሁን የተባለበት ምክንያት የንስኃ አባቷ መሆን ስለተፈለገ እንጂ ለራስ ገዝነት የማታንስ ትልቅ አስደማሚ ተናፋቂ ከተማ ናት። 
 
ያ ያአፈነገጠ ፍላጎት የህዝብ የውሳኔ ሃሳብ ያላረፈበትን የጎንዮሽ ጉዳይም ለመረከብ በአዳራሹ ሲገኙ #ደክሟቸው ነበር። #ዝለውም ነበር። እዛው ተቀምጠውም ገፃቸው የሚናገረው ነገር ነበር። ከውስጣችሁ እዩት። 
 
የአገራዊ የምክክር ኮሚሽን #የብልፄውን መንፈስ ለዛው ለብልፄው ፕሬዚዳንት በሚያደርግበት ዕለት ውስጣቸውን የሚያሳይ ሰውነታዊ ቋንቋ ነበረው። ያው ርክክቡ የሳቸውን መንፈስ እራሳቸው እንዲረከቡ ሁኗል። ሌላም ቢሆን ሊያደርገው ቢችልም ይህን ያህል መዋለ መንፈስ፤ መዋለ ንዋይ ለተመሳሳይ ፍላጎት እና ግብ ማፍሰስ ግን? ዶር አብይ አህመድ ሴሪሞኒ ነፍሳቸው ነው። ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሳሉም ይኽው ነበር። 
 
፪ኛ። 
 
የዘመኑ የፓርላማ ጉባኤ በቃለ ምህላ ተጀምሯል። #የህሊና ጸሎት አላየሁም። ሊሆን ግን ይገባ ነበር። ዕለቷ #በሞት የሚጠነዝልባት አገረ ኢትዮጵያ ጥቁር ልብስ አለቀቃትም እና።
 
አንዳንድ ሚዲያወች "#ስያሜ" ይሉታል፤ ሌሎቹ ደግሞ "#ለእጩነት" ቀረቡ ይላሉ። ይህንን ወጥ ግንዛቤ ማምጣት ብልፄው አይችልም። #ልል ዲስፕሊን ስላለውም፤ አደረጃጀቱም ጠንካራ አይደለም ከመሰረቱ። በወቅቱ እንዲያስተካክል ሃሳብ አቅርቤ ነበር።
 
#አናርኪዝምን አርቆ በህግ ሥር ለማዋል ያቃተውም ለዚህ ይመስለኛል። በምክትል ሚ/ር ደረጃ ያሉ አባሎች ምን እንደሚጽፋ እታዘባለሁኝ። የፖለቲካ ድርጅት ቲም ላይ በዲስፕሊን ነው የሚሠራው። ብዙ ነገር ይንዳል// ግለሰባዊ አቅጣጫ ሲከተል አንድ የፖለቲካ ድርጅት። ደጋፊ ሚዲያወች እራሱ ሊገሩ ይገባል። ይሄ ለብልፄው ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ፍላጎታቸውን ለማሳካት ዝንፍ የማይል የፖለቲካ ድርጅት አመራር እና ዲስፕሊን ይጠይቃል። 
 
የሆነ ሆኖ የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ንግግር #መሸበር አላየሁበትም። በአንድነት ለመቆም እንዲቻል ሃሳብ ቀርቦበታል። ንግግሩ ሰብሳቢ ይመስላል። ግን ከ2010 ዓም ንግግር ጋር ማወዳደር የሚቻል አይመስለኝም። 
 
ያ ድንቅ ንግግር የነበረው ህሊናን የመግዛት አቅም እና ንግግሩ በፖሊሲ ደረጃ ተቀርፆ ወደ ተግባር ይቀየራል የሚለው ያ የፋፋ ተስፋም አይሆኑ ሆኖ ነው የቀረ። በአብዛኛው ደጋፊውንም አጥቷል። ንግግሩ እራሱ ሞገደኛ #አብዮት ነው የነበረው። ደግሜ ላቅርበው፤ ላንብበው ቢሉ እንኳን ያን ቃና እና መዓዛ ማምጣት የሚችሉ አይመስለኝም።
 
ይህም የመስከረም 25/2019 ንግግር ከሦስቱ መደመር + የመደመር ትውልድ + የመደመር መንግሥት + የገዳ ሥርዓት እንዴት እና እንደምን ተጣጥሞ ሊቀጥል እንደሚችል ሂደት እና ጊዜ ይጨነቁበት። እኔ ስለምን ልልፋ????
#ነገረ ኢትዮጵያ ሁለት የምርጫ ጊዜ ተጠቅሜ፤ በቦነስ ትሰጥ እና አይቆጠረብኝ ይላል? ማን? 
 
ተጠቃሚው። ከ2910 - 2924 ድረስ ኦህዴድ የቆየበት የመንበረ - መንግሥት ጊዜ አይቆጠርም ተብሏል። ኃላፊነት እና ተጠያቂነቱስ ብሎ ለሚጠይቅ ቅን ዜጋ መልሱ ምን ይሆን ይሆን? የምክክር የውሳኔ ሃሳብ ይህን ጥንስስ ጸንሶ ነው የተጠናቀቀው።
 
አይቆጠርብኝ የሚባለው #አሻራው አይደለም። የአባይ ግድብ መጠናቀቅ፤ #ቀለጤ ሆቴሎች፤ የኮሪደር ልማት፤ ውጥኑ አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ ይመዝገብልኝ ባይ ነው የኦህዴዳዊ ብልጽግና። የማይፈልገው 13 ዓመቱ የሥልጣን ዘመኔ #አይቆጠር ነው። ስለዚህም የምክክር ኮሚሽኑ በብልጼ ፍላጎት ይሻሻል ለሚባለው የህገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን ጣጣውን አሸክሟል።
 
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ምርጫ በተርም ሊሆን ይገባል የሚል ንግግር አድርገዋል። ገዳዊ ሥርዓት ለ8 ዓመት ሁለት ተርም ነው ይባላል። ከዚህ ላይ ኦህዲዳዊው ብልጽግና ወገቤን ብሏል። 
 
የሚሻሻለው ህገ - መንግሥት ማዕከላዊ በሆነ ግምት ሁለት ተርም ቢሆን፤ አንድ ተርም ጊዜ እንደ ገዳ ሥርዓት 4 ዓመት ሲሆን ገዳን አሰልጥነው እነሱ ወደ 6 ዓመት ለማድረግ ሃሳብ አለ። ይህ ሃሳብ ባይሳካ እንኳን የገዳን 4 ዓመት ወደ ኢህአዴግ በ5 ዓመት ቢጸና አንድ ተብሎ የሚቆጠረው ከ2024 ዓ.ም የምርጫ ዘመን ይሆናል ማለት ነው። #ቀመሩ ይህ ነው።
 
በዚህም ብቻ አይቆምም ዕድሉ ከተሰጠ አዲስ ሌላ #ተለጣፊ ህግ ወጥቶ ደግሞ የምርጫ ዘመን ፈረቃው #ለ3 ወይንም ለ4 ጊዜ ይሁን ሊባል ይችላል። መንሹ በብልፄ ከኖረ። ይህ እንግዲህ የ፬ኪሎ ፍልሚያ እንደዚህ ዘመን አይቼ አላውቅምና ብልፄ ተረጋግቶ የመግዛት ዘመን ካገኜ ነው።
 
ዛሬ ዛሬ ሳይ እኔስ ከማን አንሳለሁ ሁኗል ጉዳዩ። ሁሉ ነው የሚመኜው ፬ኪሎን። ለቀዳማዊ #እመቤትነትም እራሳቸውን ያጩም አስተውያለሁኝ። ብቻ ዕድሉን ብልጼ ከተሳካለት 50በ60 ትልሙ ማቆሚያ የለውም። 
 
የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት አስተባባሪወች ይሁኑ ዱር ቤቴ ያሉት "ይህን መስከረም፤ ይህን ልደት፤ ይህን ዓመት፤ ይህን መንፈቅ አያልፋትም ብልጽግና" ይላሉ ሂደቱ ግን ቀጥሏል። እንደ ትንበያው ሳይሆን ጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ #ሸብረክ ሳይሉ፤ በአቀዱት፤ በአለሙት ሁኔታ ህልማቸውን እየኖሩት ነው። 
 
ሁሉም አይቅርብኝ ነው የሚሉት። የኦነግ መንፈስም - ፍላጎትም ተጠሪው እኔ ነኝ ባይ ናቸው፤ የኢህዴግ መንፈስም ፍላጎትም አሻራ አስቀጣይ እኔው ባይ ናቸው፤ የኦህዴድ መንፈስም ፍላጎትም ካፒቴኑ እኔ ነኝ ባይ ናቸው። በዚህ ውስጥ ቅንጥብጣቢ ሳትቀር ልቅም ብላ ፍላጎታቸውን እያሳኩ ይገኛሉ። 
 
ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትን ከሳቸው በላይ እንዲወጣ አይፈልጉም። ይታገሉታልም - ቀደምት ንጥረ ነገሩን። ያንኳስሱታል። ያጣጥሉታል። ነገር ግን ኢትዮጵያዊነት ቀደምት ማንነት ስለሆነ ህሊናቸው ያደረጉ #ሐዋርያት የሌላ አገር መሪወች ግን ኢትዮጵያን #የትንግርት የፊደል ገበታ አድርገው በዓለም አደባባይ የሚሰጡትን ምስክርነት ሊያስቆሙት አልቻሉም። ኢትዮጵያ ረቂቅ መንፈስ ናት ብዬ በ2014 እኤአ የፃፍኩት ታምሩን እያሳዬ ነው። 
 
ወደ ቀደመ ሃሳቤ ስመለስ ከዛ ዘመን ቀድሞም በ2008 እኤአ ጀምሮ ኢትዮጵያዊነት #ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነውም የምለው ቋሚ ሞቶዬም ገድል እና ታማርቱን አንደበት ከፍቶ እያናገረ ነው። ለዛውም በዚህ ዘመን እነ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ሚኒስተር፤ አማካሪ የፓርላማ ተመራጭ ሆነው ያሻቸውን በአሻቸው ጊዜ እንደ ልባቸው በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ላይ #ጥቅጠቃ እየፈጸሙ፤ በተቋማት ላይ፤ በምሰሶወች ላይ ይፋዊ ጥቃት እየተፈጸም፤ በዓለም አደባባይ አንደበትን ከፍቶ የሚያናግር ማግኔታዊ ስበት ኢትዮጵያዊነት ከፍታው ልዕልና በልቅናው ልክ ሆኗል። ተመስገን ነው። 
 
"እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል። ሰው ግን አያስተውለውም።"
 
#ዕለቱ በዚህ የወግ ገበታ ይጠናቀቅ።
 
ፈተናው ይቀጥላል፤ ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል። እኛ ሳንሆን የተመሠረተበት ዓላማ እና ቁምነገር ግሎባል አቅሙ ዓራት ዓይናማ ነው እና። ቀላል ጊዜ አልነበረም ከ2010 - 2019 ኢትዮጵያዊነትን አጉልቶ፤ በአፍሪካ የመሪነት መድረክ የበለጠ ጉልላት ማድረግ ይቻል ነበር። ጊዜም ነበር። በቂ ጊዜ። ግን ተላለፋ። እነ አቶ ቀጀላ መርዳሳ የባህል ሚር ያደረገች አገር? ለፍርሰቷ ሹማ ሸልማ እምታዘባንን አገር???
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ደህና እደሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
06/10/926.
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
See less

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።