#ጊዜን የማድመጥ አቅም፣ ሊደመጥ ይገባል።
#ጊዜን የማድመጥ አቅም፣ ሊደመጥ ይገባል።
"እግዚአብሄር በአንድም በሌላም
ይናገራል፥ ሰው ግን አያስተውለውም።"
#ክፍል ፲፱።
ኢትዮጵያ ቦታዋ አሁን ያለችበት አይደለም | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ETV | EBC | EBCDOTSTREAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሰጡት ማብራሪያ
ሼር ባደረኩት ሊንክ ያዳመጥኩት ሲሆን፣ በጉዳይ ላይ ሦስት ጉልህ አመክንዮችን አስተውያለሁኝ። እና ሂደቱን በአራተኛ ደረጃ ላነሳ እሻለሁኝ።
1) ስለ ፕሮፌሰር ዶር. ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስተሩ የተነሳው በጎ ጉዳይ ነው። ገፊ ኃይሉ፣ ስለምን ጎልቶ እንደ ተነገረ ዛሬ ላይ ለእኔ ግልጽ ነው። ባለፈው በሰፊው ጽፌበታለሁ።
2) ስለ የጥበብ ቤተኞች የተሰጠው ማብራሪያ ነበር። "ዓዋቂወች ግን ……… " ጉዳዩን ባለቤቶቹ ይሂዱበት። እኔ በዚህ አገላለጽ የምሻውን ብቻ እገልፃለሁኝ።
3) ስለ "#የሠፈር' ዕሳቤ በተነሳው ጉዳይ ምልከታዬን አቀርባለሁ።
4) የፕረዘንቴሽኑ #ቶን፣ ጀስቸር እንዲሁ ብቃኜው ብያለሁኝ።
#አንከር ጉዳዮቼ።
ቁጥር 1) ስለ ፕሮፌሰር ከዚህ ቀደም ስለፃፍኩበት ሊንኩን አስቀምጣለሁኝ። ከእኔ ዕሳቤ ጋር አቻ የሆነ ዕይታ መራመዱን ወይንም አለመራመዱን የእናንተ ህሊና ይመዝነው ዘንድ እተወዋለሁኝ።
ቁጥር 2)
የጥበብ ቤተኞችን የህሊና አቅም ጎልቶ፣ የማህበራዊ ኑሮ ዘይቤያቸው ላይ ስስነት ተወስቷል። እራሳቸው ባለቤቶቹ ስላሉ እሱን ለእነሱ እሰጣለሁኝ። ተመቸንም፣ ጎረበጠንም የእነሱ ጉዳይ ነው።
ጉዳዩ የተነሳው በሰሞኑ የጥበብ #ጥምርወውህድ ልቅና በኢትዮጵያ ነው። በመጀመሪያው "የእዮሪካ" አልበም አርሲ ኢተያ ላይ የንፋስ የኃይል አጠቃቀም ከዴንማርክ በመጣ ሥልጣኔ ውጥኑን ለመጎብኜት በሄዱ ጊዜ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ በብስጭት ተናገሩ።
በሌላ መድረካቸው ንስር እና አሞራ ብለውም ምሳሌ አምጥተው፣ ጩኽቱን፣ ቆሻሻነቱን የአሞራን ገልጸው ንሥርቭሮችን አልቀው ገልጸውልናል።
" #አሞራ" የሚል ሥም ያላቸው ሰብዕናወች አሉ። ለዛውም በጥቁር አሞራ የሚጠሩ። ፍጥረትነቱ ደግሞ ከፈጣሪ፣ ሳይንስ ደግሞ በምርምር በባይወለጂ፣ ድምጹን ለሜድቴሽን ወዘተ ይጠቀሙበታል ዘረ ዓዕውፋትን።
የሆነ ሆኖ #ከ100 ሚሊዮን በላይ በፍጹም ጉጉት፣ በፍጹም አክብሮት፣ በፍጹም አድማጭነት፣ በፍጹም አድናቂነት በበዛ ፍቅር አቀባበል የተደረገለት " #እዮሪካ " የታምር ያህል ነበር። ደራሲው፣ አዜያሚው፣ ቲሙ ጠቅላላ ሆነ ጠባቂው፣ እንዲሁም የጠቅላይ ሚር ቢሮን ጨምሮ ይህን አልጠበቁም ነበር።
አጀንዳችን አይደለም ያሉት እንደምን እንደሚደጋግሙት እነሱው ያውቁታል።
#እኔ ባየሁት።
ጠቅላይ ሚር አብይ የተበሳጩበትን ማንኛውም ክስተት ተልዕኮውን ለሌላ ከእነ #ሙቀቱ ካወረሱ በኋላ፣ ቋሚ የጉዳዩ አስፈፃሚ መገኜቱን ካረጋገጡም በኋላ፣ እሳቸው የዛ ጉዳይ #አስታራቂ፣ #አስማሚ ሆነው ይቀርባሉ።
ጉዳዩ በሚኒስተር ደረጃ #ተረካቢ ተገኝቶለታል። ለዛውም ትርፍ ንግግር ታክሎበት። እሳቸው ተመልሰው ይህን ጉዳይ ያነሱታል ብዬ አላስብም።
3) "#ከሰፈር ውጡ" አዬ የእርስወ ነገር። ኢትዮጵያ ከሰፈር ዕሳቤ የወጡ ሚሊዮን ልጆች አሏት።
ይህ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ስለመጡ አይደለም። ውስጣችን የተቀረጸው #ኢትዮጵያ በሚል #የፊደል ገበታ ስለሆነ ሥምወት የማያውቁ፣ ምግባረወትን ያላዩ ሚሊወኖች እልል ብለው ነበር የተቀበሉወት።እኔ እንኳን ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር እያሉ መደበኛ አድማጨወት ነበርኩኝ።
ያን ጊዜ ብዙወቹ የእርስወን ድምጽ ሳይሰሙ ማደር ህመም ነበር። በተለይ #የአማራ እናት። ሥመወት በየቤቱ #ማዕደኛ ነበር። 05 ሳንቲም አልከፈሉም። የካድሬ ወጪም አልነበረበወትም። በነፃ ሙሉ አቅም፣ ሙሉ መንፈስ፣ ንጽህና፣ ፍቅር፣ የሚያሳሳ ናፍቆት ተፈቅዶ ፈሰሰለወት። #አቅም ያጡት እርሰወ ነወት።
ምክንያት ያፈሱትን ዕንቁ አልደከሙበትም። የፕሮፌሰር ብርሃኑ ዕድልን ሳያፈሱ ለክብር መብቃት ሚስጢሩ፣ ዝቅ ብለው ለመታዘዝ መፍቀዳቸው ነው። ይመስጠኛል ይህ ሰብዕናቸው። የምር። ሁለት ጊዜ ጫካ፣ ሁለት ጊዜ የሞት ፍርድ ተደጋጋሚ እስር፣ ስደት ወዘተ …
ዶር አብይ አህመድ ግን ከባድ የሚባል የገዘፈ ዋጋ አልከፈሉበትም። የህወሃትን ዲሞሽን ዘንግቼው አይደለም። ግን ለህዝብ ፍቅር የታደሉበትን ወጪ አላወጡበትም። የምልዓትን ፍቅር በቅጡ ማስተዳደር አቅቶ ዛሬ ያለንበትን ሁኔታ ያውቁታል።
ከዚህ ቀደም በሄዱባቸው ቦታወች፣ በጎበኟቸው ቦታወች "ሠፈረኛ" ሥንኞችን እንደምን እንደተጠቀሙ ከእኔ ይልቅ ሚዲያውን የመንግሥትን በምልሰት ይቃኙት።
ህዝብ #ተከፋ። ህዝብ ተጠራጠረ። ህዝብ ተገለልኩ አለ። ተስፋ ነኝ አሉ፣ ያገኜውን ተስፋ መሬት ላይ ያለው ማህበረሰብ ይለካው። በርቀት ስላለሁ በዳታ ላቀርብ አልችልም። ከመስማት ውጪ አላየሁም።
ሥምንት ዓመት ሁለት የምርጫ ጊዜ ነው። ውስጥ #ለቃሉ ቢያድር የተረከቧት ደሃ አገር መሆኗን ሁሉም ያውቃል።
ግን ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመፍታት ከመዳፈው ሁሉም ነገር ነበር። በዛ ላይ ዓለም ዓቀፍ ሙሉዑ #ተቀባይነቱን ያስሉት።
ያን እርስወ #አላበጁትም ነበር። የአማራ ልጆች የተጉበት ጉዳይ ነበር። ሥልጣን ከያዙም በኋላ ህወሃት ስለሚታወቅ ችግሮች በትዕግሥት ተይዘው፣ ይደገፋ ነበር።
ቢያንስ አቅምን ለማን? ከዛስ አገር ለሚለው? በህሊና ችሎት መቻልን ያስቻለ ጥበብ ነበር። ይህን ዕድል እንኳን ለመጠቀም አልደፈሩም።
ያ ልስሉስ ዕድል አመለጠ። ዕድሉ ዕንቁም። አልማዝም ነበር። ለኢትዮጵያም ለእርሰወም ሌጋሲ የማይገኝ ዕድል ተጣለ።
ሁሉም ነገር ለስኬት የሚበቃው #ከራስ ሲጀመር ነው። "#ሠፈርተኝነትን" ለመመከት ከካፒቴኑ ቢጀመር፣ ብስጭተወትን እንደሚጋሩት የብልጽግና አካላት እና አባላት፣ አዲሱን እርምጃወትንም መከተል፣ በመከተል ውስጥ መሆን ይገኝ ነበር።
4) የስብሰው ሂደት ከወትሮው የተለዬ ለስላሳ ነበር። ምንጊዜም ጊዜን የማድመጥ አቅም ሊደመጥ ይገባል።ብዙም ባልተፈለገ ቦታ ላይ ሐረጉ ሳይጠናቀቅ #ጭብጨባው ባይመችም።
እንዳየሁት ተግባራችን፣ ሥራችን፣ ድካማችን እዩልን የሚል ጸጸት ይሁን ይቅርታ፣ ይቅርታ ይሁን ምህረታዊ ጉዳይ ብዬ መፃፍ ባልችልም፣ በስሱ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ሳሉ የነበረው ቶን ዓይነት ከአካለወት እንቅስቃሴ የታዘብኩት አለ።
ከሰሞናቱ ያሰቡት እና ያለሙት፣ ያቀዱት እና የፈጸሙት ግብረ መልሱን የመዘኑት ይመስለኛል። የገባኝ ያ ነው።
#ምርጫ። እንደ መከወኛ።
ምርጫው ልክ የዛሬ ወር ይመስለኛል። በመንግሥት በጀት እና መዋቅር ስብሰባወችን እያካሄዳችሁ የብልፄው መሪወች። የምረጡኝ ቅስቀሳ።
ምርጫ በሚካሄድባቸው ቦታወች ተመዝጋቢው በሚሰጠው የድምጽ አቅም በአንፃራዊነት ይወሰናል ውጤቱ። ብዙም የከፋ ዕድል ይገጥመዋል ብዬ አላስብም ብልፄው፣ 50+ ኃይል ሳይጠቀም ያገኛል።
ያ ባይሆን ከተመጋጋቢው ኢዜማ ጋር እንደ ጀርመኖች ኮኦሌሽን ፈጥሮ መንበሩን ሊያስቀጥል ይችላል። እኔ ምርጫው ላይ ህዝብ እንዲሳተፍ እሻለሁኝ። የሚጎዳው እራሱ ነው። ወኪል አልቦሽ ይሆናል። ግን ህዝብ ፈርቶ ሊሆን አይገባም፣ ፈቅዶ እንጂ።
የሞት ዜናም #ንፋስ መውጫ ሊደረስ ሲል ባለች ታዋቂ መንደር፣ በሥራ አውቃታለሁ እኔ ችግር ተፈጥሯል። ሰላማዊ ነው የነበረችው እኔ ሳውቃት የጨመተች።
ከምርጫ መሰናዶ ጋር በተያያዘ ከቢቢሲ ዜና የሞት ዜና ለዛውም በቤተ እግዚአብሄር አዳምጫለሁ። ስጋት አለኝ። ምርጫውን እግዚአብሄር አምላክ በሰላም እንዲያሳልፈው ምኞቴ ነው። በሁሉም ተግባር ይሁን አካል፣ በመንግሥትም ይሁን በታጣቂወች #ሞት ሊታቀድ አይገባም። ሰው አልባ ፖለቲካ ከባህር የወጣ አሳ ነው።
ምርጫ መሳተፍም // አለመሳተፍም፣ ድምጽ መስጠትም /// አለመስጠትም መብትነቱ ቢከበር ጥሩ ነው። ምርጫ የሃቀኛ የፖለቲካ ፋክክር እንጂ መበቀያ፣ ጉልበት ማሳያ ሊሆን አይገባም። መንግሥት ከፋኝ ካሉ ተቃዋሚ ታጣቂወች ተሽሎ፣ ታጋሽ ሆኖ መገኜት ይኖርበታል። ትዕዛዝ አይደለም፣ ትህትናዊ ዕይታዬ ነው።
ቸር አስበን፥ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ማህበረ ቅንነት ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
01/05/026
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ