#ማስተዋል። ዘለግ ያለ ዕይታ ስለ ባለቅኔው ቴዲ አፍሮ።
• #ማስተዋል።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
#ምዕራፍ ፲፱።
#አሜን።
እንዴት አድረን? እንደምንስ አረፈድን? ማስተዋል ተሰጥቶናል በጌታችን መዳህኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በአላህ፤ ያን እንጠቀምበት ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን። አሜን።
"እዮሪካ" አልበምን። በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉውን ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ ቀን መድቤ አዳምጨዋለሁኝ። ሥንኞችን እየመላለስኩ አንብቤያቸዋለሁኝ። ሥራው ሐዋርያ ነው። ለሁላችንም ራዲዮሎጂ ነው። የምሥራቹ ደግሞ የኢትዮጵያ የሥነ - ጹሁፍ አቅም ከፍ አድርጎታል። ቋንቋወች ዘምነዋል። የቅንብር ሥልጣኔ በጉልህ ታውጆበታል። የህዝብ ፍቅር እናቀና ተሳትፎ ዘመንን አናግሯል። እያንዳንዳችን መርምሯል። የዳኜ ብቁ አቅም ነው።
#ትውስታ በምልሰት። ተያያዥ ጉዳዮች ዘለግ ብለው ይነሳሉ።
እኔ ሙዚቃ አድማጭ አይደለሁም። በልጅነት ጊዜዬ በአጋጣሚ ራዲዮ አቨይ አባቴ ያደምጥ ስለነበር ከዛ ጊዜ ወስጄ ያዳመጥኳቸው ከ10 አይበልጡም። እኔ እምሳበው በሥነ - ግጥሙ ይዘት ነው። ዛሬም በሙሉ ዕድሜዬ ይኽው ነኝ። ቤተሰቦቼ አብሶ ክብርት እናቴ ትወዳለች። ከእኛ ቤት በመደበኛ ሙዚቃ ይደመጣል። ቤተሰቡም ሙሉ ነፃነት አለው። እናቴ የአርቲስት ይሁኔ በላይ አድናቂ ናት። እኔ ደግሞ የመጸሐፍት ቀበኛ ሆኜ ነው ያደግኩት።
የሆነ ሆኖ ሚዲያወቼ በተፈጥሮ ዜማ ነው የምሰራቸው። በጸጋዬ ራዲዮ ሦስት ዓመት ቢሞላው ነው፤ ሙዚቃወቻችንም ይደመጡ ብዬ የፈቀድኩት። ይህም ሆኖ ኖቱ፤ ቅኝቱ፤ ቅላፄው፤ የላይኛው፤ የታችኛው የሚባለውን ጥበብ አላውቀውም።
ፍሬ ሃሳቡ የገባኝ፤ ስክርቢቱን ማግኜት ከቻልኩ በራዲዮ ዝግጅቴ አጫውተዋለሁ። ባመዛኙ በመሳሪያ ቅንብር በጥቂቱ በሥንኛት ፍሰት፤ ሰፊው ጊዜ ክፋ ሃሳብን እንደምን ታግለን እናሸንፍ ላይ ነው ሚዲያወቼ የሚሠሩት። የፖለቲካ ሙግት ከዚህ ፌስቡኬ ላይ ብቻ ነው ያለው። አድካሚም ፈታኙን የፖለቲካ ህይወት ተኑሮበታል።
የሆነ ሆኖ የጥበብ ቤተኞች ፈተና ሲገጥማቸው ብዕሬም፤ መንፈሴም አብሮነቱን እናለመልማለን። ከሥር የለጠፍኳቸው ሊንኮች ጥቂቶቹ ናቸው። ልጅ ቴዲ አፍሮ ገና በመግቢያው ላይ ነበር ፈተና የገጠመው።
ከ2008 እአአ ጀምሮ ሥምን መላዕክ ያወጣዋል መቅድምነት በጸጋዬ ድህረ ገጽ እና ራዲዮ እስከ ትናት ሌሊት እስከ ሠራሁት የኔታ ቋጠሮ ድረስ ቋሚ በሆነ አቋም ከቴዲ አፍሮ ጋር ነበርኩ ዛሬም አብሬው ነኝ። ለምን? #ዕውነት #ቦታውን ለቆ ስለማያውቅ። ጥበብ ነፃ ሆኖ የተፈጠረ አምላካዊ ሥጦታችንም ነው።
1) ቀንበጡ ባለ ቅኔ ሰበብ ተፈልጎ ታሰረ በዘመነ ህወሃት። ጽፌበት ነበር።
2) ዓለም ዓቀፍ ዕውቅና ሊያገኝ በሚችልባቸው ወሳኝ መድረኮች፤ የብራንድ አንባሳደርነቱም ታገድ። ያን ጊዜ ጃዋሪዝም ምድር አይባቅኝ ያለበት ጊዜ ስለነበር ሲጠየቅ "ደስታችን አጣጥመን አልጨረስንም" ብሎም ነበር። ሞግቼ ነበር።
ያን የሰማይ እና የምድር ልዩነት ለማርገብ ሰሞኑ ጥድፊያውንም፤ ቧልቱንም ታዝቤያለሁ። ሰውን በሆነበት ልኩ እንጂ ፌካዊ ጥገና ላይ አቅም ማፍሰስ ለማንም፤ ለምንም አይጠቅም። ብቻ ጊዜ ራዲዮሎጂ ነውና ዘንበል ቀናውን እያዬሁ ነው።
ይህ መንገድ አያድርም አይውልም። የሳሙና አረፋ አቅም የማጠራቀም ሂደት። ተፈጥሯዊም፤ ውስጣዊም ስላልሆነ። ልጥፍ ምርጊት አይሰነብትም። አያሰነበትም።
" ኢትዮጵያ ሱሴ ናት፤ ስንወለድ ኢትዮጵያ ስንሞት ኢትዮጵያዊ" በከነፍንላቸው ልክ እነኝህ አንከራዊ ሞቶወች ዛሬ አሉን? እእ። ግን ዕውነቷ ኢትዮጵያ ትናትም፤ ዛሬም ነገም ከዕውነት ማህለቋ ጋር ናት።
በውነት የአገራዊ ማንነት ጉዳይ የገበጣ ጨዋታ ባናደርገው መልካም ነው። በአንድ የወጣቶች ፖድካስት ሰሞኑን "ሴት ጠቅላይ ሚኒስተር ስትሆን ባለቤቷ ቀዳማዊ ማን?" ሊባል ነው የሚል ዋዘኛ ግን ማስተዋልን የሚጠይቅ ሃሳብ ተነስቶ ነበር። ኢትዮጵያን መምራት ከሱቅ ሻማ የመግዛት ያህል እንኳን አልታሰበበትም። አንድ ቦታ የሺወች ምኞት እና እሰጣ ገባው ይገርመኛል። ለዛ ቦታ እኔ ምን አቅም አለኝ እኮ ተብሎ አያውቅም።
3) "ኢትዮጵያ" በሚል አልበም ሲመጣም እንደ ተለመደው ወጀቡ አይሎ ነበር። "ጧፍ" ታግዶ ነበር።
3.1) የቀደምቱ አርቲስት ይርጋ ዱባለ ቃና በኮፒራይት ያነሱም ነበሩ።
3.2) ጎንደር ከተፈጠረበት ዕለት ጀምሮ በከፋ መከራ ውስጥ ስለነበረች፤ ጎንደርን ከፍ የሚያደርግ ዜማ ስለነበረበት አልበሙ፤ በዛ ላይም ጦሮ ተነስቶ ነበር።
3.3) ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን መጥተው ኢትዮኤርትራን መስመር መከተል ሲጀምሩ ከዚህም ጋር በተያያዘ ሁለት ነገር ተነስቷል፤ ቤተሰባዊ ሁነቱ የጎረበጣቸው ነበሩ። በሌላ በኩል በሚሊዬነም አዳራሽ በነበረው የክብር ዝግጅትም እንዲሁ ጠንከር ያሉ ሙግቶች ተነስተው ነበር።
3.4) ጎንደር በክፋ ቀን የተገኜላትን ልጇን አከበረች፤ ማዕረግ ሰጠች፤ መንገድ ሰየመች። ያን ጊዜም በቁጥብ ንግግሩ ኢትዮጵያን ላቅ አድርጎ አነሳ፤ በዚህም እንደ ቅናትም፤ ዕውቅናውን በማጣጣልም፤ አገርን አታንሳ ከማለትም፤ "ተደመረ በለጸገ" በሚልም ወጀብ ነበረ። ከዚህ አንፃር ዘለግ ያለ ጹሁፍም ጽፌ ነበር።
4) በቅርብ ጊዜ ለንደን ኮንሰርት ነበረው። ያን ጊዜ ማት ነበር የፈሰሰው። ያጣጣሉ፤ የከሰሱ፤ የወነጀሉ ነበሩ። እኔ ደግሞ እዚኽው ፌስቡክ ላይ ሞግቼ ጽፌ ነበር። ያን ጊዜ ሁኔታውን የመከቱ አላየሁም። ቢኖሩም ኢሚንት ናቸው። ዛሬ ከ20 በላይ ፕሮግራም የሠሩ፤ ያለቀሱ፤ የእኛ ጀግና ያሉ ፋታ ያጡ ሰብዕናወችን አይቻለሁኝ። ከእኛ ፌስቡክ እኔ ብቻ ነበርኩኝ የሞገትኩኝ። ለምን? ዕውነት ቦታውን ለቆ ስለማያውቅ።
5) "ኢዮሪካ" ሱናሜ ነው። ኤርትራ ትቅደም ያሉትን ኢትዮጵውያንን ሳይቀር ገርቶ የጋራ ምዕታዊ ሽልማት መሆን ችሏል ማለት እችላለሁ። በአፍሪካውያን የሚዲያ ፎረም ሳይቀር "ኢትዮጵያ አጀንዳችን ከእንግዲህ አትሆንም።" ያሉት ሁሉ ማን ቀድሟቸው ሲያደንቁ፤ ሲከበክቡ፤ ሲያወድሱ፤ ሲቀድሱ። ፈጣሪ የሰጠን ማስተዋል ሊስተዋል የሚገባውም ከዚህ ላይ ነው።
6) ስለ እናት ኢትዮጵያ ማንሳት እንደ ወንጀል ይቆጠርበት የነበረበት የሚዲያ ፕላትፎርም ዛሬ ማዕከሉን ኢትዮጵያዊነት፤ አፍሪካዊነት፤ ሰውኛነት፤ ተፈጥሯዊነትን በቅኔ መግቦት ከሽኖ ያወጣው "የእዮሪካ" አልበም። ኢትዮጵያን በሚመለከት መሠረተ ጭብጡ አሳማኝ፤ ሳቢ፤ ተወዳጅ፤ ተደማጭ፤ ማዕከላዊ ፍላጎትን አደራጅ ሆኗል። ተመስገን።
ተግባሩ የሙዚቃ ቤተ - መፃህፍት መሆን የመቻል አቅም ያለው የከበረ ተግባርን ነው። ባለቤቱ ለመሆን የማየው ወረፋ ግን በእጅጉ ይገርመኛል። ሙዚቃ በተፈጥሮው የትግል #ማኒፌስቶ አይደለም። የፖለቲካ ፍላጎትን አማክሎ መምራት የሚችለው የአንድ የፖለቲካ ድርጅት አጭር፤ ግልጽ ዓላማና ተግባሩን በግልጽነት የቀመረ ማኒፌስቶ እንጂ #ቅኔ ሊሆን አይችልም።
*** ለምን?
ማኒፌስቶ ሲዘጋጅ ለተማረውም// ላልተማረውም ግልጽ በጣም ቀላል ቋንቋ ተጥቅሞ ነው ሊዘጋጅ የሚገባው። የአንድ የፖለቲካ ድርጅት ዓርማው እራሱ ውስብስብ ሊሆን አይገባም። ብሄራዊ መዝሙርም ከቅኔዊ ተፈጥሮ ጋር ሊገናኝ አይገባም። ለምን? ያልተረዳ ህዝብ አባልም፤ ደጋፊም መሆን አይችልም።
የቴዲ አፍሮ ሥነ - ግጥሞች ከባዶች ናቸው። ተልዕኳቸው ጥልቅ ነው። አማርኛ ቋንቋ መሆናቸው እራሱ የማናውቀው እስኪሆን። አይደለም ለምፍታት፤ ለማንበብ ይፈትናሉ።
ለትርጉም የሚደፈሩ አይደሉም። የዕድምታ ባለፀጋወች ብቻ ይሆናሉ መፍቻውን የሚያገኙት። ወይንም #ደራሲው እራሱ ብቻ። በቃ። የአንድ የፖለቲካ ማኒፌስቶ እንዲህ በጥልቀት፤ ተመስጥሮ፤ ለትርጉም ገዝፎ አይዘጋጅም። ፈጽሞ።
ከዚህ ሃቅ ስንነሳ #ብልፄውም ይህን ያህል መደንገጥ፤ ፖለቲከኞችም ወህ! ከድካም ገላገለን ብለው ረፍት የሚወስዱበት፤ በሻሞ የእኔ፤ የእኔ የሚባባሉበት ሊሆን ፈጽሞ አይገባም ነበር። ለሦስተኛ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ፤ የደህንነት ሚኒስተራቸው ሲታከሉ አራት ብሄራዊ መድረኮች ላዬ አንስተውታል። ከውስጣቸው ገብቶ እያጠናቸው ወይም እየመረመራቸው ይመስላል።
ይህ ከስጋት መንጭቶ ነው። ግን ነገር ግን በሃቅ ፊት አንድ የሙዚቃ ክሊፕ ለአገራዊ የለውጥ ንቅናቄ አንከር ሊሆን ፈጽሞ አይችልም። ተፈጥሮው ስላልሆን። በትይዩ ኮመዲ፤ ተውኔት፤ ፊልም ብንወስድ እራሳቸውን ችለው እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ታግለው፤ አታግለው ለድል አያበቁም። ፈጽሞ። የፖለቲካ ታሪክዊ ሂደት እንዲህ አስተናግዶ አያውቅም። ፋክትም። ይህን ጉዳይ ሰከን ብሎ ማዬት ይገባል።
የብልጽግና መንግሥት የፖለቲካ አደረጃጀት መርሁ እንዲገባው ሊፈቅድ ይገባል። ስለዚህም የዘመኑን የኢትዮጵያ የሥነ - ጹሁፍ ደረጃ፤ የዜማ አቅም፤ የሥልጣኔ ሁነት ልዕለ ያደረገ ተግባር ለኢትዮጵያ ሽልማት ነው። ስለሆነም ከማወከባ መታገሥ ይገባል።
አገራዊ ዕሳቤ በየጊዜው በሚነሱ የበዬነ መረብ፤ የሰላም፤ የትጥቅ ትግሎች ሁነት በሚፈጥሩት ጫና አደጋ ውስጥ ይገባል። ይበተናል። መሰብሰቢያ ያጣል። ይህ ከፍተኛ አደጋ ኢትዮጵያ ገጥሟታል። ይህ "#የእዮሪካ" መንፈስ ይህን ችግር ግን ይፈታል፤ ፈቷልም።
ከኤርትራ ትቅደም በቀጥታ ጎዳናን ወደ ኢትዮጵያ ትቅደም ብዙወች አስገብቷል። እያንዳንዱን የፖለቲካ ተጽዕኖ ፈጣሪነቱን እና አቅሙንም እንዲለካ፤ ጉድለቱን እንዲይ ራዲዮሎጂ ሆኗል። ሚዲያወች እራሳቸውን እንዲያስተውሉ አስተምሧል።
በሌላ በኩል ጭምቱ ማህበረሰብም በተለምዶ ሳይለንት ማጆሪቲው ጥፍት ብሎ ከባጀበት ብቅ ብሎ የማድረግ አቅሙን ዕውን አድርጓል። ጭምቱ ማህበረሰብ ስለሰንደቁ፤ ስለ እናቱ ኢትዮጵያ ሙሽርነት፤ ዘመናይነት ይሁን ዕንባ በዝምታ፤ በማስተዋል ውስጥ ጊዜን አናግሯል። የኢትዮጵያ የማይናወጽ ዘባደሯ መሆኑን በዓለም አደባባይ እንደ ትናንቱ አስመስክሯል።
ይህ ሂደት ሁሉም እራሱን የገደፈበትን የማረሚያ ላፒስ ሲሆን፤ የውስጥ ጸጸትን አብቅሎ ወደ ቋሚ መስመር የሚያመጣ ልዩ ሐዲድ የዘረጋ ገጠመኝ ሐዋርያዊ ጉዞ ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያዊነት ውስጥነትን የሚጠይቅ ስለመሆኑ ተረጋግጧል። ኢትዮጵያዊነት ይካዳል። ገቢራዊ የማድረግ ግዴታ ከእያንዳንዳችን በግል፤ ከሁላችንም በጋራ ይጠበቃል ዕውነትን በመሆን ብቻ ማሳየት።
1) ማፎካከር የሚቻለው ሊፎካከር ከሚችል ተጨባጭ የጊዜ ሁኔታ ጋር ብቻ ነው። አሁን በኢትዮጵያ #የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቃና የለም።። ስለሆነም ስለምን ይህ ሃሳብ እንደሚነሳ አላውቅም። ጥበበኛውን ከአገር መሪ ጋር በሌለ ህልም ማወዳደር ምን አድርጉ እንደሆን አይገባኝም።
2) በሌለ፤ ባልታሰበ የፖለቲካ ግዙፌ ክስተት ማፎካከርም የተገባ አይደለም። የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንታዊ የፖለቲካ ውሳኔን የሚጠይቅ እንጂ በፍላጎት ወይንም በምኞት የሚሆን አይደለም። ከማፎካከሩ ጋር እንዲፎካከሩ የሚደረጉ አካላት ይሁኑ ተቋማት፤ ግለሰቦችም ከሆኑ #አደጋ አለው። ይህ ሁሉ በዓለም የተካሄዱ፤ የሚካሄዱ ግጭቶች ይሁኑ ጦርነቶች፤ መገዳደሎች፤ መጨካከኖች ይሁኑ መበቃቃያወች ሥልጣን እኮ ነው። መሾምን፤ መደነቀን፤ መሻት እኮ ነው። በቃ። በዚህ ጉዳይ ላይ ማንኛውም የአገር መሪ #ቀናተኛ ነው።
3) ማፎካከር የሚቻለውም ከመሰል ጋር ሊሆን ይገባል። ኮመዲን // ከከሞዲ /// ተዋናይን ከተዋናይ// ባንድን ከባንድ ///የፖለቲካ ድርጅትን // ከፖለቲካ ድርጅት፤ ባለቅኔን /// ከባለቅኔ፤ ጸሐፊን /// ከጸሐፊ፤ እንጅ የአንድ አገር ጠቅላይ ሚኒስተርን ከባለቅኔ ጋር? ምን ይደረግልን ይሆን ይህ ዕሳቤ?
4) የብልህነት ቴርሞሜትር ማነስ። ይህ በግል ህይወታችንም የምናዬው፤ የሚገጥመንም በኽረ ጉዳይ ነው። አንድን ሰብ አግነን ሌላውን ዝቅ ስናደርግ፤ የአንድን ሙሉ አቅም ካለፈቃዱ ከግል ምኞት ጋር ማጋባት ለዛ ቅን ባለተጽዕኖ የሚፈጥረው አደጋ ሊታሰብበት ይገባል።
ማንኛችንም ተኪ የለንም። ልጃችንም ቢሆን እራሱን /// እራሱ ቢተካ እንጂ በፍጹም በአንድ ወቅት የተፈጠረ ማንነት በዘመናት ልውውጥ አይፈጠረም ደግሞ። #ጋሼ ወጋዬሁን እሰቡት። ተተካን? እእ። ለዚህ እኮ ነው አሻራችን የተለያዬው።
ስለዚህም ሰው #ለማትረፍ ብንተጋ ጥሩ ነው። ለአንድ ደግሞ ለማይገኝ ሰብዕና እራሳችን ቆጥበን፤ ስሜታችን ገርተን እንሳሳለት - እንዘንለት - መንፈሱን አናባክን - እረፍትም እንስጠው። በተለይ እናቶችን እንሰብ። የእኛ ባልሆነ ጥረት የተደከመበትን ስኬት ወደራስ ማጠጋጋት ለህሊና ዕዳ ነው። ነፃነትን መዝረፍም ነው። ሁላችንም ለጥሪያችን ዓይነታ ነን። ስለሆነም የየራሳችን ጸጋ በማስተዋል ብንቀምረው በቂ ነው።
3) በይፋ አንድ የጥበብ ሰብዕና በራሱ ጊዜ በፖለቲካ ተግባር መወሰኑን ካላረጋገጥ፤ ልጥፍ ማንነት አያስፈልገውም። እኔ እንደማስበው አርቲስት ቴወድሮስ ካሳሁን "ቢሆን" ብሎ የሚመኜው የኢትዮጵያዊነት ዘይቤ ያለው ይመስለኛል።
የፖለቲካ ድርጅት የለውም። የየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ደጋፊ ሆኖ አያቀነቅንም። "ባደከሙን ጉዳዮች ላይ ሳይሆን ባጠነከሩን ጉዳዮች" ላይ እንሥራ ባይ ነው። ዝምታው እራሱ እኮ ዩንቨርስቲ ነው። ጸጥ ያለ ሰብዕናው ግርማማ ነው። ይደንቃል።
365 ቀናት ማይክ ላይ በሙያም ይሁን በመሪነት ያሉ ሰብዕናወች ከዚህ አንፃር እራሳቸውን ይገምግሙ። 365×8= 292 በቀን አንድ ጊዜ ማይክ ላይ ከህዝብ ጋር ብንገናኝ። 3/4/5 ጊዜ ከሆነም አስሉት።
ይህ ጭምት ደራሲ፤ ባለ ቅኔ፤ ባለ ሙሉዑ አደብ አብዝቶ የሰጠው #ለአድማጭነት ልዩ ሰብዕናው እራሱ ዘውድ ነው። ልጅ ቴወድሮስ ካሳሁን የአዘቦት ተናጋሪ አይደለም። የሚናፈቀውም ለዚህ ነው። የሚከበረውምም።
ብዕሩ ብሄራዊ ነክ ጉዳዮች ሲገጥሙ ተመጥና ከች ትላለች። በቃ! ዘመንን፤ ዕውቅናን፤ መከበርን ያስከበረለት ቁጥብነቱ ነው። በመናገር ብዛት ከሚመጡ የአፍ ወለምታወች የዳነውም በዚህ ነው።
ገና ለግላጋ ወጣት እያለ ነፍሱን ይማረው እና ከአለቤ ጋር ያደረገው ቃለምልልስ አዳምጡት። ይህ ፍጹማዊ እርጋታው ከእዮር ስለሆነ አዘለቀው። ምን ዓይነት ቤተሰብ ይሆን ያሳደገው? አሳዳጊውን ይባርከው። አሜን። ይህን እንደ ናሙና ወስዶ እራስን ለመግራት መሞከር ጥሩ ነው። ጠቃሚ ጎዳና ስለሆነ።
4) ተከባሪነት ከራስ አቅም ብቻ መንጭቶ በተደከመበት ማሳ ካልሆነ፤ አይሰነብትም። ይናዳል። ምራቅ ማለትም ነው። ካለ ገደብ ክሊፖችን እየተጠቀሙበት ነው። እሱም፤ ቲሙም በዝምታ ውስጥ ናቸው።
የቅርቦቹ ወዳጆቹ እስር ገጥሟቸዋል። እሱም አብዝት አትረፍርፎ በሰጠው በስክነቱ ውስጥ ነው። የጥበብ ዓውደ ምህረቱ ማዘጋጃው የህሊናው የአደራ ቤት ተሰብሮ ተዘርፏል የሚል ዜናም አለ።
እሱ ደግሞ ፈጣሪ በሰጠው ታጋሽነትን ወከባውን በፍጹም ኢትዮጵያዊ በትህትና እያስተናገደ ነው። ነገ ምን ሊገጥመው እንደሚችል አይታወቅም። ይህንንም አስፈሪ ገጠመኝ፤ በፈጣሪው ተማምኖ በበዛ ቁጥብነት ይዞታል። የቴዲ አፍሮ ኮቴው እራሱ ቀለሙ የፊደል ገበታ ነው። ትውልድ የሚታነጸው በመታገስ ውስጥ ባለ ጨዋነት ነው።
5) ምኞተኛው የኢትዮጵያ ፖለቲካ። ሁልጊዜ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የማዶን ናፋቂ ነው። አንዳንድ ጊዜ ጨምተው የከወኑት ባለቤቶች እያሉ እንደ ብልፄ እና ካቢኒወቹ ቶንቦላ ሊወጣላቸው ይችላል። እንዲህ ማሰቡ ያለ ነው እንደማለት። ይህ ግን ሁልጊዜ አይገኝም።
የጨመቱት ከውነውት ጸጥ እረጭ አሉ። ህወሃት መንበሩን ፈቅዶ ለቀቀ። ሞገደኛው ህወሃትን ዘመን ሰጥ ክንውኑ እያሳዬ ነው። እነኛ ተግባራት የዛሬው ዝምታቸውም ስኬቱ ምን እንዳከሰረም ይሁን ለማን እንዳተረፈ ስለመዘኑት ይመስላል።
በድካማቸው ውስጥ የኮፒራይት ሻሞውን አስተውለዋል። አዲስ አቅመኛ ካለም ብለው ጸጥ ብለዋል። ይገባልም። የሆነ ሆኖ የስኬት ዕጣ ፈንታ #በኢንፖርት እና #ኤክስፖርት የሚሆን አይደለም።
ይልቁንም ገዢውም ብልፄ፤ ተባባሪወቹም እቅፍ ድግፍ አድርገው የያዙት፤ ተጣማኞችም፤ ዕውነተኛ ተፎካካሪወችም፤ ተቃዋሚወችም ምኞታቸውን በራሳቸው አቅም ልክ ብቻ ሊያሳኩ ስለመቻላቸው ቢቀበሉት ጥሩ ነው።
ይህ አጋጣሚ የማይገኝ ትምህርት ቤት ነው። ካለምንም የካድሬ በጀት፤ ካለምንም ፕሮፖጋንዳ፤ ካለምንም መፈክር ድርደራ አንድ የሙዚቃ አልበም በጉጉት እንደምን እንደ በክብር እንደተጠበቀ፤ ግብረ ምላሹ የሰማይ ታዕምር መሆኑ ትንግርታዊ ጉዳይ ነው።ለዚህ ነው እኔ ሳይለንት ማጆሪቲውን አትርሱ የምለው።
ሳይለንት ማጆሪቲው እንዲህ የልቡ ሲደርስ ብቻ የሚያረካ ተግባር ይፈጽማል። ነገር ግን በሌላ አካል በተፈጸመ ተግባር ላይ አንበሳነትም የውርንጫ ድካም ነው።
ይህ ሚሊዮኖችን አንድ መገናኛ ላይ ያዋህደ፤ ያገናኜ ክስተት ከላይ ነው። ከእዮር። በነገሮች ሁሉ አምላካችን፤ ፈጣሪያችን የማስቀደም ንባብ፤ ትርጉም ሚስጥር ነው የታዬው። ትዕይንቱን መገደብ፤ ማቀብ፤ ማስቆም ያልተቻለውም ለዚህም ነው።
ስለሆነም ከእልህ፤ ከብስጭት፤ ከቁጣ፤ ከኃይል እርምጃ፤ ከሽሚያም ወጥቶ መጠሞን ያስፈልጋል። ዝቅ ብሎ የህዝብ ነኝ የሚለው ሁሉ ይህን የልቅና ልዕልና ህዝባዊ ዕውቅና ሊያደምጠው ይገባል። መምህር፤ ሐዋርያም የሆነ ዕድል ነውና።
አካል የሌለው የእግዚአብሄር አገልጋይ ቃለ ወንጌል "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም" ይላል። እናስተውለው። ሂደት ሁልጊዜ መምህር ነው። ፍጽምና ከማንም የለም። በጥንካሬያችን ልክ ድክመት አለ። ስንጠነክር ማሸነፍ እንዳለ ሁሉ በደከምንበትም መሸነፍ መኖሩን መቀበል ያስፈልጋል። መሸነፍን መቀበል በራሱ አሸናፊነት ነው። ብልህነትም።
ከሁሉም ኢትዮጵያ በልብ በተሸፈተባት ቁጥር እንዲህም ትቀጣለች። እንዲህም እንዲያም ትመዝናለች፤ ታስመዝንማለች። ለዚህም ነው እኔ ኢትዮጵያ የከበደችን ለሁላችንም ነው የምለው።
ከ19 ዓመታት ላለነሰም ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው እላለሁኝ። ዕውነት ነው። ኢትዮጵያ ማለት ሁልጊዜ የሚያስፈራ፤ የሚያስደነግጥ፤ የሚያስጨንቅ፤ የሚያስቀና፤ የሚያስቀጣ፤ የሚያስወነጅል፤ የሚያስጠረጥር፤ የሚያሳስር፤ የሚያስገድል ለምን ይሆናል? ክብር - ግርማ - ሞገስ - ልዕልና - ልቅና ስለምን ይፈራል?
ለኢትዮጵያ ነኝ የሚል መንግሥት ይሁን እምታገለው ለኢትዮጵያ ነው የሚለው ተፎካካሪ ለምን የኢትዮጵያ ሥም ሲጠራ፤ ሰንደቋ ንጹሁ ከፍ ሲል፤ አገናኛችን ስልጡኑ አማርኛ ቋንቋ ሲነሳ ለምን ይጎረብጠናል? እራሳችን በቅንነት እንመርምር። ፈጣሪም አላህም ይርዳን አሜን።
#ዳስ።
ገበሬ አደራጅ ስለነበርኩ ትንሽ ስለዳስ ልግለጥ። ዳስ ገበሬው ለሠርግ፤ ለአውጫጭኝ፤ ለሰንበቴ፤ ለደመር (የለቅሶ የቀጠሮ ቀን)፤ ለለቅሶ፤ ለመልስ፤ ለግጥግጥ፤ ለተዝካር፤ ለድል ወዘተ የሚሠራ ጊዚያዊ መጠለያ ነው። አብዛኛው የገጠር ትምህርት ቤትም እኮ ዳስ ነው።
#ዕንባ።
በደስታ እና በሃዘን መሃል ባለው ሲቃም ይከሰታል። ደስ ሲልም ይለቀሳል። ዳሱ የዓይናችን ሽፋሽፍት ሊሆኑ ይችላሉ።
በጽኑ ህመም ይመጣል። ሰው በሥጋ ሲለይም ይመጣል።
በተመሰጠ ሐይማኖታዊ ዝማሬም ስብከትም ይመጣል። ዕድል ሲወድቅም ይመጣል።
ተማሪወች ከፈታና ሲወድቁ፤ ህፃናት ሲርባቸው፤ ልጆች አጥፍተው ሲገረፋ ወይንም በእንቅፋት ሲወድቁም፤
የምንወደውን ስናጣ መራራ ስንብት፤ ወይንም የአካል ጉድለት ሲኖር፤
በውስጥ ደዌ ህመምም፤
ዕድል በቸልታ ሲሾልክም፤
ድል ሲደረግም፤
ዙሪያው በእሾኽ ሲታጠር፤
ስደት ሲያንገላታን፤ ብቸኝነት ሲነጠን የውስጥ ማስታገሻ ዕንባ ነው።
አንድን የቅኔ ፍሰት እንዳሻው ተርጉሞ ባለቤቶች ላይ ጭንቀት መጫን የተገባ አይደለም። ለመሳቅም ለማልቀስም ነፃነት ያስፈልጋቸዋል። የመኖራችን አካልም ናቸው።
#ክወና።
ኢትዮጵያዊነት የጨመተ፤ ጨዋ፤ ቅን፤ ተፈሪ፤ አሰባሳቢ፤ እናታዊ ጸጋ የተሰጠው ማንነት ነው። ብንታደልታ ዩንቨርስቲ ከፍተን እንደ አንድ የመመረቂያ የዕውቀት ዘርፍ ልናደርገው የሚገባ ባለተስጥኦ ነው።
ኢትዮጵያ ሳይንስ፤ ፍልስፍና፤ ዩንቨርስ፤ ህግ፤ ይሉኝታ ናት። እሷን ከፍ ስናደርግ ከውስጣችን ምርቃት አለ። ስናጣጥላት ደግሞ ሊጠገን ዬማይችል ውድቀትን እናስተናግዳለን። ከሊቅ እስከ ደቂቅ ባሟላነው ሳይሆን ባጓደልነው ድካማችን ላይ ብናተኩር ጥሩ ነው። ወቀሳን አንፍራ። እርማትን አንሸሽ። በድክመታችን ላይ እናተኩር።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
30/05/026.
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
#ሊንኮች የቀደሙ ሃሳቦቼ በጥቂቱ።
• የቅኔ ቃና ሊያቃና።
መባቻው አባተ ለመሰንበቻው … ተመስገን አሜኑ!
- ጁላይ 16, 2018
የቅኔው ዕንቡጥ ቴወድሮስ ካሳሁን፤
- ሜይ 02, 2018
የቅኔው ዕንቡጥ ቴወድሮስ ካሳሁን
ስለእኛ በጣና ዘገሊላ ፍቅራዊነትን
ተሰናዳ ሊመግበን።
የቅኔው ዕንቡጥ ቴወድሮስ ካሳሁን ስለእኛ በጣና ዘገሊላ ፍቅራዊነትን ሊመግበን ተሰናዳ (ሥርጉተ – ሥላሴ). ከሥርጉተ - ሥላሴ 13.01.2018 (ከጭምቷ - ሲዊዘርላንድ)„
ቴዲ አፍሮ የቅኔ ዕንቡጥ – ለእናቱ ልዩ ዓርማ ነው!
Monday, February 4, 2013
ታማኝነት ለህዝባዊ ፍቅር ሲሰግድ። ታማኝ ትናንትም ዛሬም! ሥርጉተ ሥላሴ
02.02.2013
ጥበበኛው ቴወድሮስ ካሳሁን የዘመን ነባቢት። 01.07.2010 EC. (09.16.2017)

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ