ኢትዮጵያስ እራሷስ እዬተፈናቀለች አይደል
እንኳን ደህና መጡልኝ።
ኢትዮጵያስ እራሷስ እዬተፈናቀለች አይደል።
"ይገባቸዋልና ስለዚህ ነገር ጣዖቶቻቸውን በሚመስሉ አጋንንት ጠፉ፤
በብዙ የሚሆኑ ትንኞች ክፉ የሚሆኑ እንዚህ ተጨነቁ።"
መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
20.03.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።
እንዴት ናችሁ ውዶቼ? ደህና ናችሁ ወይ? እኔ አምላኬ
ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ? አላዛሯ ኢትዮጵያ ታማለች። በሁለመናዋ እዬተጎሳቆለች ነው። እሷ እራሷ እተፈናቀለች ነው። በመንፈስ፤ በሥነ
- ልቡና በሁለመናዋ ነቀላ እዬተካሄደባት ነው። የዚህ ምንጩ ማነው? መሠረቱስ ምንድን ነው?
· ጋኔል።
ለዚህ ሁሉ ምንጩ እና መሰረቱ የሄሮድስ መለስ ዜናዊ
ጋኔል ማንፌስቶ ነው። የ አቶ ሌንጮ ለታ እና የሄሮድ መለስ ዜናዊ መግለጫም ነው ህገ መንግሥት
የተባለው። ሲቀመም በሻብያ ውሃ ልክ ነው።
ይህ ማንፌስቶ በኖረበት አራት አስር ዓመታት ሁሉ
በእያንዳንዱ ሰከንድ ማለት ይቻላል፤ ጣሊያን ወረስ የሆነውን ኢትዮጵያን ጨርሶ የማፍለስ ፍልስፍ ዶክተሪን ነው
የተከተለው።
ለጋኔሉ ሰነድ እውን ለማድረግ አጥፊ አረም ሲተክል ነው የኖረው የሄሮድስወሌንጮ
የሚባትት ክፉ መንፈስ።
አሁን ነው እኔ እዬታዬኝ ያለው ያ ሙት መንፈስ አሁንም እያመሰ ስለመሆኑ። ያ ሰይጣናዊ መንፈስ አሁንም
የዘራውን እያጨደ ሳይሆን እኛኑ ቀጥቅጦ ገዝቶ ደግሞ አሁንም አስደግድጎ እያሳጨደን ይገኛል። የሁለቱ የሙት መንፈስ አንዱ በአካል
ሌላው በደመንፈስ እንሆ ኢትዮጵያን እያፈናቀላት ነው ከባዕቷ። ኢትዮጵያዊነት ማለትም መሆንም በአደባባይ በአዋጅ እዬተራደ እዬተቃጠለ
እዬወደመ ነው የሚገኘው።
ሄሮድ መለስ ዜናዊ በያንዳንዱ የኢትዮጵያ ባዕት ገና
ከዚህ በኋዋላ ወደ 100 ዓመት የሚያስፈለገው ፈንጅ ቀብረው ነው የሄዱት። ያን ያጣውን 33 ቀሪ አመት የመከራ ያዋራርደዋል።
ምክንያቱም ችግሩ መነሻ ሳይሆን በሳቢያዎች ላይ ስለሆነ
አትኩሮቱ። ራሱ አዲሱ መንግሥት የቆመበት ምስሶ በቁሙ እዬተነቃቃለ ስለመሆኑ ሳይሆን ጉዳዩ ስለ ሥሙ መበከል ነው ጭንቅ ጥብብ የሚለው።
እንኳንስ የሰው ልጅ እግዚአብሄርም በፈጠራቸው ፍጥረቶቹ
መታማቱን ልብ አላለውም። ከችግሩ መንስኤ መነሳት ካልተቻለ ደግሞ ዛሬ ነገን እያበቀለ ሳይሆን ዛሬ ነገን እዬነቀለ
ስለመሆኑ ግልጥ ሊሆንልን አይችልም።
ሁሉም ፈንጅ ኢትዮጵያ በሚባለው አገር ሰው እንዳይኖርበት
በማድረግ ኢትዮጵያን ጠፍ መሬት ማድረግ ነው። ሰው መኖር የሚኖረው መኖሩ ዋስትና ሲኖረው ነው። ያን ዋስትና ደግሞ እርስ በእርሱ
በመርዝ አንዲበቃቀል አድርጎታል የሄሮድስ መለስወሌንጮ ሰይጣናዊ ቀመር። ጋዜጠኛ እና ጸሐፊ አቶ ሙሉቀን አስፋው „የክፉ ሰው ሽንት“
የሚለውን ቅኔያዊ ቅኝት ከአባቶቹ ወርሶ እርስ ሰጥቶ የጻፈው በትክክል ይገልጸዋል።
በርከታችን ተከበረን ተፈርተን የኖርንበትን ሁለመና
ነው አሁን ተወሮ እዬተፈናቀለ ያለው። ሰው መሆናች እራሱ እዬተፈናቀለ ነው። የሰው ዘር ብዙ ተጎድቷል። ህልፈተ ለቅሶ ሆኗል። ተፈጥሮም
እዬተፈናቀለ ነው።
የቤት አንሰሳት ሳይቀር በግፍ ነደዋል። መስጊዶች
ቤተ እግዚአብሄሮች ነደዋል። ተቋማት ለቀጣዩ ትውልድ የሚበጁት ሁሉ እዬነደዱ ነው። ስለምን? የሄሮድስ መለስ ዜናዊ መንፈስ ከአደባበት ቀዬ በመፈናቀሉ ምክንያት። መበቀል ጨርሶ ኢትዮጵያን መሰረዝ ታቅዶ የተከወነ ነው። የዚህ መንፈስ ዋነኛ ባሎሟሎች
ይህ ፋሲካቸው ነው።
ይህ ዲያቢሎሳዊ መንፈስ ሰው የሆነውን፤ ህሊና አለኝ
የሚለውን ሁሉ ይፈትነዋል። ፈተናው በራሱ ውስጥ ራስንማጣት ነው። በራስውስጥ ራስንማፈረስ ነው። በራስውስጥ ራስንመደመሰስ
ነው።
እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ከዛ ክፉ መንፈስ ጋር ንክኪ
የለኝም ይበል እንጂ በአንድም በሌላም ቪክተም ነው። ቪክተምነቱ መሰረቱ ከክፉ ሥራ፤ ለክፉ ሥራ ማህበርተኛ መሆኑ ነው። ለእሱ ትክክል
የሚለው ነገር ለሌላው ትክክል አለመሆኑን ሊቀበል ከቶውንም አይፈቅድም።
በሁሉም ልቦና ውስጥ የኢጎ ቁልል አለ። ያ የኢጎ
ቁልል አገነባቡ ደግሞ ከሰው ተፈጥሮ ጋር የማይስማማ ነው። ኢጎ አውንታዊ አለ፤ የሄርድስ ውርስ ግን አሉታዊ ነው፤ አቅምን የመፍራት፤
ቡቃያን የመጥላት፤ ያፈራን የመንቀል እና የራስን ሰራዊት በዛ ዙሪያ ኮልኩሎ ከሌላው ጋር ቀን ከሌት ማታኳስ፤ በተዳከመለት ላይ
ራሱን ኮፍሶ ቆይቶ እንደገና ሌላ ሲነሳም በርብርብ ያን ማክስም;
እንዲህ ሰው ነው እንደ ሰው ተፈጥሯል ግን ሰው መሆን የሚጠይቀውን ዲስፕሊን
አቅምን ያደርቀዋል ይህ መሰል መንፈስ። ይህ ዶክተሪን የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ነው። ውርሰኛው ብዙ ነው። ውርስኛ ስለመሆኑ
እራሱ ተጠቂውም አጥቂውም ሳይተዋወቁ መኖራቸው ነው በዬዘመኑ እንዲህ ዕድል እዬፈሰሰ ነጥፎ የሚቀረው።
ሰውን በመንፈሱ ድርቅ አንዲመታው ማድረግ ዋና ስትራቴጅ
ግቡ ነው የሄሮድስ መለስ ዜናዊ የተጠመቀበት ሲኦላዊ መንገድ። ፋሽስት ከራሱ ውጪ ሌላ የማዬት አቅም የለውም። የፋሺስታዊ ተልዕኮም
ጠፍ ማድረግ የተፈጠረበት ነው። አሁን የምናዬው ይህንኑ ነው። ጠፍ ማድረግ። „እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል“
· ስክነት እና መኖር ምን እና ምን ናቸው?
ዋስትና የሌለው ህዝብ በመኖር ውስጥ ሰክኗል ለማለት
አይቻልም። መኖር ያልተፈቀደለት አሁን አንድ ሁለት ብለን የተወሰኑትን ብሄር እና ብሄረሰቦች መጥቀስ እንችላለን። በቀጣይ ግን በሁሉም
ደጅ የሚደርስ ቀጣይ እና ተከታታይ ማዕት ነው እኔ እያስተዋልኩት ያለሁኝ። ዛሬ አንድ መረጃ ደግሞ ወጥቷል። ወደ 6 ወር የሆናቸው
ተፈናቃይ ወገኖቻችን በሚመለከት።
የ37,000 የባስኬቶ ተፈናቃዮች የይድረሱልኝ ጥሪ | Ethiopia
ማፈናቀሉ መንግሥታዊ እንደሆነ ነው ቃለ ምልልሱ የሚጠቅሰው
ልክ እንደ ጌዲኦ ብሄረሰብ። ለገጣፎ ለጋደዲ፤ ቡራዩ እንዳዬነው ማለት ነው። የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ሙት
መንፈስ ወራሾች ናቸው አሁን ኢትዮጵያን እያፈናቀሉ ያሉት። ይህ መፈናቀል እከሌ ተከሌ
የለበትም ሁሉንም ነው የሚያፈናቅለው። የሚያፈናቅለውም አካል ብቻ አይደለም መንፈስን ነው።
አሁን የለማወአብይ መንፈስ ቅቡልነት እራሱ እኮ ተፈናቀለ።
አለኝ የምንለው፤ መተማመኛችን የምንለው መንፈስ ሁሉ ሲፈናቀል ሲወድቅ ሲነሳ ነው የባጀው ክራሞቱን ዘመናቱን። ሰው በዬመኖሪያው
ቁሞ ይሄዳል ግን የሌላ እብን መንፈስ ተሸክሞ ነው። ሁሉም ሰው በአካሉ ነው እንጂ በመንፈሱ የለም። ያ ስውር የዲያቢሎሳዊ የሄሮድስ
መንፈስ ህፃፅ እንዲህ ነው የህሊና ሪህ።
· የትውልድ መርዘን።
የሰው ዘር በምድር እንዳይኖር አድርጎ ነው መርዙን
የቀመመው የሄሮድስ መለስ ተባባሪ ትውልደ ዲያቢሎስ። እናም ይኸው አሁን ሁለመናው እዬተናደ ብቻ ሳይሆን እዬተነቀለ ነው። መኖር እዬተነቀለ ነው። ተስፋ እዬተነቀለ ነው። ራዕይ እዬተነቀለ ነው፤ ማግስትም እዬተነቀለ ነው።
ራሱ የሄርድስ መለስ ዜናዊ ዓርማ 666 ነው የሚባለው
መታዬት ያለበት ከዚህ አንፃር ነው። ያ የ666 ዲያቢሎስ መንፈስ መጥፊያችን ለጨርሶ ስለሆነ ነው መዳኛችን እንጅባራ ላይ ንጹሑ
አረንጓዴ ቤጫ ቀይ ብሄራዊ ሰንድቅዓላማ እዬር ምልክት የሰጠበት።
ቅድስት ቤተክርስትያናችን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የዚህ
የ666 መልክት የሆነውን የሙት መንፈሱን መለያ ምልክት ከቤተ መቅደሷ ማውጣት ይኖርበታል። ምክንያቱም ዲያቢሎሳዊ መንፈስ ነውና።
አገር ሲኖር ነው ዕምነትም ሃይማኖትም ቤተ አምልክም የሚኖረው። ለዲያቢሎሱ መንፈስም ልክ እንደ መስቀል ስለሚፈራው ይህ መድህኑ
ነው።
ከገባን አሁን ኢትዮጵያን እራሷን ለማፈናቀል እዬተጋ
ያለው የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ክፉ መንፈስ ነው። ህፃናትን ሲጠላ በጥልቀት ሊታይ የሚገባው ትውልድን የማፍለስ ስለመሆኑ ነው።
ትውልድ ቀጣይ እንዳይሆን ነው አሁን በስፋት እየተከወነ
ያለው። ሚሊዮን ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ አይደሉም። ያሉትም ስጋት ላይ ናቸው ያሉት። ይህ ክፉ መንፈስ ሥልጣን ላይ እያለ
አንድ ሁለት ብሄር ብሄረስብ ተኮር ነበር። ኮንሶ እና አማራን ማጥፋት። ስለምን የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ዲያቢሎስ ዙፋኑ ላይ ስለነበር
በሁሉም አቅጣጫ ዘመቻ አልጀመረም ነበር።
አሁን ግን ከማዕካለዊ ባዕቱ ለጊዜው ስለተነቀለ ዙሪያ
ገባውን እያመሰው ነው። ለነገሩ ምስራቅ ላይ ዋዜማውን ጀምሮት የነበረው ዙፋኑ መነቃነቅ እንደጀመረ ነበር። ተስፋ ባጣ ቁጥር ብስጩው
የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ክፉ መንፈስ ገመናውን እንዲህ ዘርግፎ ኢትዮጵያን ከመሠረቷ የማፈናቀል ዘማቻውን ቀጥሏል። አለሁ የሚለው ሁሉ
እንዳለ አይቁጠረው። ለሥንቱ ህዝብ መንግሥት ሠራዊት ይቆማል? ይህን የሄሮድስ መለስ መንፈስ ውርሰኞች አሳምረው ያውቁታል።
· ሰውና መኖር።
በአላዛሯ ኢትዮጵያ የሰው ሁሉ ልብ ሽፍትነት ነው
ያለበት። ሽፍትነቱ ደግሞ ብር ብሎ የሚጣፈበት ቦታ እና ሁኔታን በማሰብ ነው። እኔ እንደማስበው ይህ አገርን ከባዕት የመንቀል መንፈስ
ምድር ያፈራችው ሳጥናኤል ቢኖሩ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ናቸው። ለዚህም ነው ልባቸውን ሞልተው 100 ዓመት እንገዛለን ይሉ የነበሩት።
ከመጋቢት 24ቀን 2010 ጀምሮ ስናዬው የነበረው
ያ አቅም፤ ያ ክህሎት፤ ያ ጥንድ እና ድርብ ብቃት ከሐምሌው ዝማታ ማግስት ይኸው ገና ዓመት ሳይሞላው ያን የሙት መንፈስ እንደገና
መማጸን ጀመረ ሁሉ እያለው፤ ሁሉ እዬተቻለው ልቦናውን ባርባር አለውና እንደ ገና ቀዶ ከወጣበት ነፃነት ጋር እዬተጣለፈ ይገኛል።
ራሱን በራሱ ላይ ያቆመበትን ባላ እራሱንበራሱ ላይ ያነጸበትን ዲታ መንፈስ
አሳልፎ ለመስጠት ጠናና መንገድ ጀመረ … ስለምን? ክፉው የሄሮድስ
መለስ መንፈስ ከውግዘት በስተቀር ተገንዞ እንዲቀበር አልተሰራበትም እና። ጸበል መጠመቅ የነበረበት ህንፃው ሳይቀር ነበር። ሳር
ቅጠሉ ሳይቀር ነበር። ሁሉም የባይረሱ ተጠቂ ነውና።
ገንዞ ለመቅረብ ወጪ አልነበረበትም የሄሮድስ መለስ
ዜናዊን የተጠናወተውን የኔት ወርክ። ከዛ ጸላዬ ሰናይ መንፈስ ለመወጣት መቁረጥ መወሰን እና ራስን አሸንፎ ማደር ብቻ ነበር የሚያስፈልገው።
ራስ ማሸነፍ ማለት ኢትዮጵያዊ መሆነ መቻል። ሁሉም ሲሶ መንገድ ላይ ቆሞ ነው ዜግነት የሚለው …
በእራሱውስጥ ራሱየጠፋ ነውና።
ይህ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚታመስበት ሁነት ነው።
ስለሆነም አውራው ጋኔል ሁሉንም አንጥፎ ይገዛል፤
ይነዳል፤ ይኸው እያመሰ ያለው እሱው ነው። አምሳያዋቹ በዬቦታው ያሉ ግልገል ጋኔሎች አመራሮች እኮ ናቸው ይህን ኢትዮጵያን
የማፈናቀል ተግባርን በባለቤትነት እዬሰሩ የሚገኙት። የሄሮድስ መለስ ዜናዊ የመርዝ ክኒን የወሰደ ሁሉ ፈውሱ ዲያቢሎሳዊ የሆነውን አገርን የመንቀል
ተግባር ነው። እናም ይኸው ቀጥሏል።
እኔ ሳሰበው ኢትዮጵያ እራሷ እየተፈናቀለች መሆኑን
ነው ዛሬ የታዬኝ። ስለዚህ ቀጣይ 97ሺህ ህዝብም እንዲሁ የዚህ የተጣደ ቋያዊ ዕጣ ፈንታ ተረኛ ነው። ለነገሩ መንፈሱ ያልተፈናቀለ
እኮ የለም። ጽናት የጎደለው ሁሉ ቢሰላ ሁሉም ተጠቂ ነው። ተጠቂነቱን ማስላት ያለበት ለሄሮድስ መለስ ዜናዊ ጋኔላዊ ቤተኝነት ስለመሆኑ
አያሰላውም። በእያንዳንዷ ክፉ ነገር፤ በእያንዳንዷ መልካም ነገሮችን
በማደናቀፍ ውስጥ ያ ጋኔላዊ ዘማቻውን ያስኬደዋል። ጸረ አገር፤ ጸረ ሰው፤ ጸረ ተፈጥሮ።
· ምን ይደረግ?
ምን እናደርግ ዘንድ እኮ ነው በልደታ ማርያም እራሱ በሮ እራሱን መሬት ውስጥ የቀበረው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን እኮ ብንማርበት ከቀስት እንድን ዘንድ ነው
ያ ምልክትን እዮር የላከው። ራሳችን እዬቀበርን ያለነውም እኛው ነን። በሁሉም መንፈስ ውስጥ የሄሮድስ መለስ ዜናዊ
መርዝ ቢወደድም ባይወደውም ተጠናውቶታል።
በማፈረስ ውስጥ በማግለል ውስጥ፤ በመፃረር ውስጥ፤ እውነትን በመፍራት ውስጥ፤ ታማኝነትን
በመጫን ውስጥ አለን ሁላችንም ፈቅደን። ወቃሹም ተወቃሽ ነው። ተወቃሹም ወቃሽ ነው። የሚበጀው እውነትን ወግኖ መቆም ነው። ዕውነት
ደግሞ ንጽህና ያለው ያልባለቀ ኢትዮጵያዊነት ነው።
በውነቱ ከአዎንታዊነት ወጥተናል። መልካም አንሳብም።
ቅንነት የለንም። አናዝንም። አንራራም። እኛነታችን ክደነዋል። የእኛ የምንለው ወይ የፖለቲካ መሪ ወይንም
የራሳችን ዞግን፤ ወይንም የራሳችን የተፈጠርንባትን ባድማ ብቻ ነው።
ስለሆነም ወደ እግዚአብሄር ተመለስን ከሴራ ፖለቲካ
ወጥተን በዬዳጃችን ካለው የመፈረስ አደጋ እንድን ዘንድ ልባችን ህሊናችን እንጠበው። መወሰን ይጠይቃል። ሁሉም ልዩነትን ነው
የሚያበረታታው። ኢትዮጵያ የምትፈናቀለው እኛው ባቀድነው የተሳሰት መንገድ ነው። ህሊናችንም ልባችንም አልጸዳም።
ወስልተን የምንኖረው በራሳችን ተፈጥሮም ጭምር ነው።
አገር ለ እኛ የጅምላ እና የችርቻሮ የፖለቲካ መሸጫ መደበራችን እንጂ የነፍሳችን ድርና ማግ አይደለም። ውሸታሞች ነን። የ እኛ
ውሸታምነት ነው እነዚህን የነገ ተስፋዎች በመከራ እያገለበጠ እዬቀቀላቸው ያለው። ጭካኔያችን ልክም ወሰንም የለውም።
· ቀንና ትዝብት።
ስንቱ ቀን እኛን ይታዘበን? ስንቱ ደቂቃስ እኛን
ይታዘበን? ስንቱ ሰከንደስ እኛን ይታዘበን? ስንቱ አዬርስ እኛን ይታዘበን? ትናንት ስለ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሁሉ በአንድ ላይ
ጮኽ፤ ዛሬ እሱ እንኳን እንደ ጠላት ነው የሚታዬው።
ስለምን? መንፈሳችን ለሄሮድስ መለስ
ዜናዊ ክፉ መንፈስ ስላስገዛነው።
አቅም በማዋጣት ነው አገር ልትኖር የምትችለው። ትናንት ኮ/ደመቀ ዘውዱ ሲፈታ ለምን ተፈታ አካሉ ሳጣጉድሉ አሳራችሁት
ፈታችሁት ተባል፤ መፈታቱ የወል ደስታ ሳይሆን ቀረ፤ ዛሬ ደግሞ ሲሞግስ ይታያል?
ትናንት ስለ አቶ ነ ነዕምን ዘለቀ የዘመረ የተቀኜ ጀግናዬ ያለ፤ የቀደሰ ነፍስ፤
ሚዲያ ሁሉ ዛሬ ያን አይደፍረውም። ስለምን? የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ክፉ መንፈስ ሳናውቀው ስለተናወጠን። ደም ሥራችን ያ ክፉ ጸላዬ ሰናይ ስለተጠናወጠው፤
እንዲህ ነው የሚያናከስን ብናውቀው ያ እበዝተን የምንጸዬፈው ሙት መንፈስ አስረግዶ ቀጥቅጦ ራሳችን አዋርዶ ግን እሱ በቀዬሰልን
መንገድ መጪ እምንልለት። ክፉ ነገር አይቀዳም ሰው ብንሆን፤ ከህሊናችን ጋር ብንኖር ኖሮ …
በዚህ መንገዳችን የአንዱ መፍረስ ሌላው ተጠቃሚ ሊሆን
ከቶም አይችልም። ትግራይ ላይ ሰክኖ የሚታዬው ዲያቢሎሱ የተጠነሰሰውም፤ የተወለደውም የተኮተኮተውም ለወግ ለማዕረግ
የበቃውም ከዛው ባዕት ስለሆነ የጨረሻውን
ጽዋ የሚቀበለው እሱው ይሆናል።
ዲያቢሎሳዊ የሄሮድስ መለስ ዜናዊ መንፈስ እፉኝት
ነው። ሲረገዝ አባቱን፤ ሲወለድ እናቱን እንዲህ የሚገድል። በማጥፋት ማጣፋት ሁሉንም አስነጥፎ ጠፍ ማድረግ።
ቅኝቱ ስሪቱ በሙሉ ዲያቢሎሳዊ ነው የሄሮድስ መለስ።
ዘር አልባ ጠፍ መሬት የማድረግ ትልም ነበረው ያ ክፉ መንፈስ፤ አሁን ይህ ነው እዬተፈጸመ የሚገኘው። ግብግብ ላይ ነው ጤኛው መንፈስ
እና ያ ክፉ መንፈስ። ለጥቂቶች ሲል እንኳን ምህረቱን መዳህኒተ ዓለም ክርስቶስ ይላክልን። አሜን!
ጤነኛው መንፈስ ሁሉ ወደ ክፉ መንፈስ የተለወጠበት
መንገዱ የዛ ጸበል ተጠማቂነት የፈጠረው ተጽዕኖ ነው። የቀረ የለም። የሚቀረም የለም። ጠቅላላ መንፈሱ ሆነ ተልዕኮው እኮ ሰውነቱ
ኢትዮጵያን የማፈናቀል ስለሆነ የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ክፉ መንፈስ መከራው ቀጣይ ነው የሚሆነው።
· ልልነት።
እራስን በማሸነፍ ብቻ ነው ከዚህ ፈተና መውጣት የሚቻለው። ዛሬ አፋናቃዮች ነገ ደግሞ እነሱው ተፈናቃዮች ይሆናሉ። አፈናቅሎ በማፈናቀል፤ ተፈናቅሎ
በማፈናቀል ዙሪያ ገብ ኡደት ውስጥ አገር ለመጨረሻ ጊዜ ለዘር ሳትበቃ ትፈናቀላለች። በነፍስ ወከፍ ስናዬው የዚህ የዚያ አካባቢ
ሰው እንላለን። ዕውነት ብንናገር ግን የተበደለው የተጎዳው ኢትዮጵያዊነት ነው። የሚፈናቀለውም እሱው ነው።
ግፋችን ብዙ ነው። እውነት ውስጥ መኖር አንችልበትም።
በሥም ኢትዮጵያዊ የሚለውም በሩብ እና በሲሶ ነው። የአብሲኒያ ወይንም የስሜን ፖለቲካ የሚለውም ቢሆን በዛ ውስጥ ዜግነት አለመኖሩም
ኢትዮጵያዊነትም የለለ መሆኑን አያስተውለውም። ዘሃ እና ፈትል አልባ ሸማ የለም፤ መሬት አልባ ሰማይ የለም፤ ቀን አልባ ሌሊት የለም።
መሬት በሬ ቢኖር ገበሬ እና ተፈጥሮ ጸጋ ከሌላ ሰብል የለም።
የአብስንያ ሰው አገር አብጅቶ ዛሬን የሰጠ ነው።
ዘመኑ የፈቀደለትን ሠርቶ ትውልድን ያበረከተ ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያዊነት እንደ ነዶ ጨርቅ በመቀስ ተሸንሽኖ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነትን
ጎንደሮች እንደሚሉት „ሲወዱ እስከ ንፍጥ ልጋጉ“ መሆን ይኖርበታል። በስተቀር ቀን ኢትዮጵያ ተፈናቅላ የሚቀር አንድም ሽራፊ ነገር
አይቀርም። ድንጋዩ እራሱ እርስበርሱ ይፈነካከታል።
· ጥሪት የሄርድስ መለስ ዜናዊ …
ክፉ ጊዜ እንዲህ ነው። የሄሮድ መሰለስ ዜናዊ ጥሪት
ክፉ ጊዜን ማበርከት ነው። ይኸው ነው … ልብ ይስጠን። አልጀመርነውም አላታዬነም መከራው … ቢታዬንማ ኖሮ ማዳፍ ላይ ያለውን ራስን
ማሸነፍ በቀደመ ነበር … እንደ ወትሮው ሁሉ እኩል ሁሉንም በማስተናገድ ሳተናው ድህረ ገጽን ከልብ አመሰግናለሁኝ። ራስን ማሸነፍ
ማለት መራራውን ጣፋጭ ለማድረግ ከራስ ጀምሮ ሁሉን በ እኩል አይን ማዬት ማለት ነው …
አቤቱ እንደበለዳላችን ሳይሆን እንደ ምህረትህ ይቅር
በለን! አሜን!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸብያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ