ልጥፎች

አዲስ አበባዬ የልዕልት ሉሲዬ ዬድንቅነሽም ናት!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  አዲስ አበባዬ የልዕልት  ሉሲዬ ዬድንቅነሽም ናት! „አንተን ማወቅ ፍጹም ክብር ናትና፤ አንተንም ማወቅ የነፍስ ክብር ናትና።“ መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ጠላትም ወዳጅም እንዲያውቀው አይለያዩም! ቅኖቹ ታዳሚዎቼ እንዴት ቆያችሁልኝ? ሰሞኑን የሉሲ ጉዞ የሚል አንድ ቡድን በመላ ኢትዮጵያ ይንቀሳቀሳል። የተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች በማይገኙበት ሁሉ ይለፍ ተስጥቶት ተልዕኮው ከተሳካ እዬሞከረ ነው … ለህሊና አጠባ ፕሮፖጋንዳ ሳይሆን መሬት የያዝ ተቋም ያስፈልገዋል። በዓዋጅ የሰው ህሊና አይታጠብም። በመሆን ውስጥ በተገኜ ቃል እና ተግባር ብቻ ነው ህሊና ሊጸዳ የሚችለው። የስሞታ ፖለቲካ በበቀል በሚጋገርበት በዚህ ወቅት አፍሶ መልቀም፤ ለቅሞ ማፍሰስ ከመሆን የዘለለ ነገር አይኖርም። በሳቢያ ላይ አትኩሮት ዘላቂ መፍትሄ አያስገኝም፤ በምክንያታዊ ችግሮች ከራስ የጀመረ ለውጥ ነው የውስጥ ሰላም ማምጣት የሚቻለው። መጀመሪያ የየትኛወም ሰላም የጉዞው አባልተኛው እራሱ በሰላሙ ውስጥ ስለመሆኑ ራሱን ያቻለ ሞጋች አመክንዮ ነው።  ኢትዮጵያዊነት ሳይቀበሉ በዕምነት ደረጃ፤ የኢትዮጵያን ሰላም ማስከበር አይቻልም። ልክ እንደ በዓዋጅ እንደተቋቋመው የእርቅና ኮሚሽን እና ማበርተኞቹ አይነት ማለት ነው። እነሱ እራሳቸው ከራሳቸው እና ከተልዕኮው እንብርት ከ ኢትዮጵያዊነት ጋር ምን ያህል እንደታረቁ ልብ እና ኩላሊት የሚመረምረው ፈጣሪ ያውቀዋል። ኢትዮጵያ በጎርፍ ፖለቲካ ስታታመስ ባጅታ አሁንም አዋጁም፤ ኮሚቴውም፤ ቡድኑም የሚመሰረተው በዛው በሸፈተ ልብ መንፈስ ነው። በዛ ላይ

ዕንባና የማስቲካ የፕሬስ ሴክራትርያት ውሎ። /ቅኝት/

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ዕንባና የማስቲካ የፕሬስ ሴክራትርያት ውሎ። „ወደ ህይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው  በደጆችዋም ወደ ከተማይቱ እንዲገቡ ልብሳቸውን  የሚያጥቡ ብፁዕን ናቸው።“ የዮሖንስ ራዕይ ምዕራፍ ቁጥር ፳፪ ቁጥር ፲፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ·        እንደ ቅድምያ … ጤና ይስጥልኝ አዱኛዎቼ? እንዴት አላችሁልኝ? ደህና ናችሁ ወይ? አላዛሯ ኢትዮጵያስ እንዴት ይዞሻል ቋዬ ቀመስ ወጀቡ ገጀራና ሜጫውስ? ከዛሬው ጉዳዬ በፊት ግን እንዴት ነው አቶ አህመድ ሼዴ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ሆኑን? ይህ እንቆቅልሽ የዶር ገዱ አንዳርጋቸውን ፖለቲካዊ ውሳኔ መፍቻ ሹክ የሚለው ይኖራል … ዕለቱን ተወራራሽ የሆኑ የሀዘን ድባቦችን እኛ እኛን ይፈታተሻሉ … ·        የጃዋርውያኑ የአቶ ንጉሱ ጥላሁን ልቦና በማስቲካ ተውኔት … https://www.youtube.com/watch?v=i-r7ACaC8Wk #EBC   ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ጐበኙ፡፡   የገጀራ እና የሜንጫ ቤተኛ የሆኑት አቶ ንጉሡ ጥላሁን አለቃቸው አቶ አባ ዱላ ገመዳ በአዬር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢነታቸው የዛን የበረራ ነገር ስንብት ለማድረግ በማይፈልጉት ከቶውንም አጥብቅው በሚጸይፉት፤ በሚሳለቁበት ቤተ ቅዱሳና ቦታ ተገኝተው  የእነዛን ሰማዕታት እዬቀፈፋቸውም ቢሆን ስንብት   https://www.youtube.com/watch?v=I-v5iQuFMW0 Addis ababa Ethiopia - የመጨረሻው ሽኝት አሳዛኙ ክስተት ነፍስ ይማር የወገኖቻችን