ዕንባና የማስቲካ የፕሬስ ሴክራትርያት ውሎ። /ቅኝት/
እንኳን ደህና መጡልኝ።
ዕንባና የማስቲካ የፕሬስ
ሴክራትርያት ውሎ።
„ወደ ህይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው
በደጆችዋም ወደ ከተማይቱ እንዲገቡ ልብሳቸውን
የሚያጥቡ ብፁዕን ናቸው።“
የዮሖንስ ራዕይ ምዕራፍ ቁጥር ፳፪ ቁጥር ፲፬
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08.03.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።
· እንደ ቅድምያ …
ጤና ይስጥልኝ አዱኛዎቼ? እንዴት አላችሁልኝ? ደህና ናችሁ ወይ? አላዛሯ ኢትዮጵያስ እንዴት ይዞሻል ቋዬ ቀመስ ወጀቡ ገጀራና ሜጫውስ? ከዛሬው ጉዳዬ በፊት ግን እንዴት ነው አቶ አህመድ ሼዴ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ሆኑን? ይህ እንቆቅልሽ የዶር ገዱ አንዳርጋቸውን ፖለቲካዊ ውሳኔ መፍቻ ሹክ የሚለው ይኖራል … ዕለቱን ተወራራሽ የሆኑ የሀዘን ድባቦችን እኛ እኛን ይፈታተሻሉ …
· የጃዋርውያኑ የአቶ ንጉሱ ጥላሁን ልቦና በማስቲካ ተውኔት …
#EBC
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ጐበኙ፡፡
የገጀራ እና የሜንጫ ቤተኛ የሆኑት አቶ ንጉሡ ጥላሁን አለቃቸው አቶ አባ ዱላ ገመዳ በአዬር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢነታቸው የዛን የበረራ ነገር ስንብት ለማድረግ በማይፈልጉት ከቶውንም አጥብቅው በሚጸይፉት፤ በሚሳለቁበት ቤተ ቅዱሳና ቦታ ተገኝተው የእነዛን ሰማዕታት እዬቀፈፋቸውም ቢሆን ስንብት
https://www.youtube.com/watch?v=I-v5iQuFMW0
Addis ababa Ethiopia - የመጨረሻው ሽኝት አሳዛኙ ክስተት ነፍስ ይማር የወገኖቻችንን
https://www.youtube.com/watch?v=fN2lpu7womk
የዛሬ ሳምንት ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲጓዝ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ሟቾች የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈፀመ
እንግዲህ አቶ አባዱላ ገመዳ እዛ ጭራሽ ድርሽ እልበት አለሁኝ ብለው በማያስቡት ቦታ ሲገኙ የልብ ወዳጆች የፕሬስ ሴክሪታርይታቸው ደግሞ ወግ አይቀርም ወደ ጌዲኦ አብረው ተጉዘው አዬሁኝ።
ከዚህ ሜንጫ ይዘኽ ምድርን እያስናጥክ በልጆችህ ከዚያ ደግሞ ሂደህ ለራብ ደረስንላችሁ በዘገዬ ግብግብ በበዛ የመግለጫ መበራት በጥድፊያ የሆነው ሆነው .. መቼም ፍርድና ዳኝነቱን ለፈጣሪ ለልዑል እግዚአብሄር ብለናል።
በዚህ አጽማቸው የቀረ፤ አቧራ የለበሱ፤ ውስጣቸው እርር ኩምትር ያለ፤ ነፍሳቸው በሞት እና በህይወት መካከል የተጣበቀ ታላቅ ተጋድሎ በሚያድርግ ዜጎች ከቦታ ቦታ እንዲፈልሱ የተደረጉት ምንዱባን፤ በጉልበተኛ - ባለተረኛ - ዘመነኛ ባለጠበንጃ ከአንዱ ስደት ወደ ሌላው ክስመት መኖርን ሰቅለው እንዲኖሩ የተደረጉት ወገኖቻችን ማህል አንድ አንጀተ ቢስ፤ አንድ ህሊና ቢስ ነገር ደግሞ አስተዋልኩኝ።
ዜናው እራሱ ለእኔ እንደ ዜና አላዬሁትም። ምክንያቱም ለውጡ በተነሳበት ውስጥነት አብሰንት ሆኖ ነው የማዬው። ይህን ስጽፍ እራሱ እያዘንኩ ነው። እንደ ወትሮዬ ጉብኝቱም፤ መግለጫዎቹን መንፈሱን ልጋራ አልቻልኩም። ስለምን ለሚባለው ብዙ ነገሮችን ማንሳት ቢቻለኝም የኦሸቲዝም ሚስጥርን ፈልጎ ማንበቡ መልስ የሚሰጥ ይመስለኛል።
እስኪ ይህን ታሪክ እናስተውለው … ታሪኩን ተመልከቱት … ይህ ቃለ ምልልስ ነው እኔን የመሰጠኝ … የሰቀጠጠኝም …
https://www.youtube.com/watch?v=T0SUTVrMBdc
የኢትዮጵያ ዜጎች በቁጥርም እንዲሳሱ፤ በሥነ - ልቦናም እንዲቀደዱ እዬተደረገ ያለበት መንገድ ፋሽስታዊ በመሆኑ ታቅዶ እዬተከወነ ነው። ለማን ሲባል? የለንደኑ የኦነጉ ጉባኤ ህልም ይሳካ ዘንድ። „ኢትዮጵያ ካልጠፋች ኦሮምያ ዕውን አትሆንም“ እና።
የኦነግ ታጣቂ ቡድን ለማለት እንኳን ዝንቅ ፍላጎት ውስጥ እዬዳከረ ያለው ሰበነክ ጉዳይ እራሱ ቃር ነው የያዘኝ። ወደ ውስጥ የሚዘልቀው ነገር እዬተነነ ነው መስል።ጠቆር ያለ ልብስ የለበሱት „ለተባራከች አገር የተባረከ ትውልድን“
አንጋፋ ቅን እና ተስፋ ሰጪ ሞቶ የያዙት ቀዳማዊ እምቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ከጌጡም ቀነስ፤ ከልበስም ድብ ያለ ልብስ መልበሰቸው ብቻ የተሻለ ስሜት ሰጥቶተኛል ከቡድኑ ውስጥ አዬኔ ሞልቶ ያየኋዋቸው እሳቸውን ነው። ነገር ግን ከሳቸው በምጠብቀው ደረጃ ዝማታቸው ግን ውስጤን መጽናናትን አላከልኝም።
ቢዚህ ህሊናን በሚፈትን ወቅት ትግራይ ሄደው ለልጆች የወደፊት የተስፋ የህሊና ቤት የመሰረት ድንጋይ ሲያሰቀምጡ ሚዛናዊነት አይቸባቸው ስለነበረ በዛ በተረጋጋ መንፈስ ወስጥ ለገዳዲ ለገጣፎን ሄደው ማዬት ይጠበቅባቸው ነበር። ኢትዮጵያዊ እናትነት ግዴታ ፈቅደው ስለገቡ …
https://www.youtube.com/watch?v=bcRFG-LMcI8
"ስመለስ ወላጆቼን አጣቸዋለሁ ብዬ ስለምፈራ ትምህርት ቤት አልሄድም።" በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ያለ ህፃን
ይህ ልጅ ት/ቤት አልሄድም ስመለስ ወላጆቼን ላጣ እችላለሁ ሲል ህፃን በረከት ሃይለመስቀልም ልጃቸው ነውና። እሳቸው የሁሉም እናት ለመሆን በአደባባይ በግሎባል ደረጃ የገቡትን ቃል የሚፈትሽ ስለሆነ …
በሌላ በኩል እነሱ ጌዲኦ ሲሄዱም ሱልሉታ ደግሞ መንገድ በመኪና ተዝገቶ ለማምለጥ ከገደል ጋር ግብግብ የገጠሙ ሌላ መጠጊያ አንዲት ቅንጣት የተስፋ የሌላቸውም ዜጎች ጉዳይ አሉ በዛ ውስጥ ተማሪዎችም አሉና .. ልጆች አሉና።
https://www.youtube.com/watch?v=cHXaU9BLVyk
Ethiopia: የሱሉልታ ነዋሪዎች የድረሱልን ጥሪ ...
https://www.youtube.com/watch?v=b8JfkxjZ_zA
Ethiopia: ቤታቸው ምልክት የተደረገባቸው የሱሉልታ ከተማ ነዋሪዎች ለኢትዮታይምስ | Residents of Sululta | Addis Ababa
https://www.youtube.com/watch?v=wjZ0PzEKxec
Ethiopia: አረብ ሀገር ለፍታ ሱሉልታ የሰራችው ቤት ሊፈርስባት | Sululta Houses
ነፍሰጡር እናቶች አሉ … ይህን ስል ግን ክብርትነታቸው የፖለቲካ ድርጅት አባልተኛ ብቻ አለመሆናቸው ብቻ ሳይሆን ያላቸው አቅም ውስኑነትንም ከግምት ሳላስገባ አልቀርም። እስካሁን ባለው ሁኔታ ተስፋዬ ተንጥልጥላ ያለበት ቦታ ነው የቀዳማዊት እምቤት ቢሮ። ነገር ግን ከሰው ውጭ አገር የለም። ስለዚህ በሰብዕዊነት ዙሪያ መትጋት ከካህንነታቸው የሚጠበቅ ነው ብዬ አስባለሁኝ።
ሌላው በዚህ ጉባኤ ያዬሁት ድራማ ደግሞ የባለማስቲካው የጃውር የሴክራትርያት ሃለፊ የ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ጉዳይ ነው። ባለፉት ሰሞናት ስቸከችክ ጃዋርውያኑ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ስለ ሰብዕውነት ቅጭጭ የማይላቸው የራሰቸው ሰው እንደሆኑ ስገልጥ ባጅቻለሁኝ። እንዲያውም ደፈር ያለ ጹሑፍ አቶ ግርማ ካሳ መጻፋቸውን አመስግኜ ሁሉ ጽፌያለሁኝ።
በአቶ ንጉሱ ጥላሁን መንፈስ ውስጥ ያለው ድፍን መንፈስ በቅጡ ሊፈተሽ እና በቅጡ ሃይ ሊባል የሚገባው ለውደፊቱ እጅግ አደገኛ የሆነ የአገር ጠንቅ ስለመሆኑ ረዘም ላለ ጊዜ ጥፌያለሁኝ። ሰዋዊ መንፈስ የላቸውም።
ከዩንቨርስቲም ይሁን ከዬክልሎች የሚፈነቃለው የአማራ ጉዳይ ባህርዳር ላይ አትኩሮት የሚነሳውም ለዚህ ነው። በፖሊስ ነው የሚደበደቡት ቤተክርስትያን የተጠለሉት ሳይቀር። ቤተ እግዚአብሄርም ሲደፈር በ አደባባይ ተመልክተናል። ችግሩ ውጦን አንዱን ይዘን ሌላውን ስለምንጨብጥ ነው እንጂ …
የትም ቦታ የአማራ መንፈስ ሲታወክ እሳቸው ጃዋርውያኑ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ማለቴ ነው በተለጠጠ መታበይ ነው መግለጫ የሚሰጡት። ያን ጊዜ እኔ ተችቼ ስጽፍ ልብ የሚለው አልነበረም።
ሌላው ቀርቶ በኦነግ ዓርማ በተንቆጠቆጠው የሚሊዬንም አዳራሽ ያን ያህል እንደዛ መለ ቅጥ አሳጥቶ ሲፈነድቁ አንድም ሰው አንዲት ብጣቂ ነገር ያለው የለም። አልነበረም። ተኝተህ በለኝ ነገ አንድ ትውልድ ያስቀር ከሆነ የቆዬ ሰው ይዬው …
አሁን ጭንቅ እየያዛቸው በጠ/ሚር አብይ አህመድ ከተመራው ቡድን ጋር ወግ አይቅርም ሰንበት ላይ አብረው ተገኝተዋል። በሞት መንደር ሆነው ማስቲካ ያኝካሉ። የዳላቸው!
ዛሬ ዓለም በኢትዮጵያ በደረሰው አደጋ በጥልቀት ሃዘኑን እዬገለጸ ባለበት ወቅት፤ ኢትዮጵያ መሬትም ገና ሽኝቱ ሳይጠናቀቅ በዕለተ ሰንበት፤ እሳቸው የደላቸው ናቸው ኦነጋቸው ያፈናቀለውን፤ መድረሻ ያሳጣውን ባለቤት አልባ ወገን ሲሳለቁበት፤ ሲመጻደቁበት በማስቲካ ተውኔት እነሆ ታዩ።
ዕውን በዛ መከራ ውስጥ ለዛች ደቂቃ አቅም አቅል አደብ አንሶ ማስቲካ የሚያላምጥ ምን ነገር መጣ። ይህን ባህል እማዬው በትግራይ ማዕከላዊ ምክር ቤት ውስጥ ነበር። ከዛም እንደ ባህል ወስደውት አንድ የአገር አንደበት የሚባል ቱባ ባለስልጣን ሬሳ ላይ ሆኖ ማስቲካ ጋር አሳይተውናል። አሳፋሪ!
እንግዲህ በዚህ ቅል ቋንቁራ ትውልድ ዕዳ ነው 27 ዓመት ሙሉ የጠፋው ትወልድ በገጀራ እና በዱላ በመዶሻ እና በድንጋይ ማህበር ወጥቶ ነፍስ ያለው ኢትዮጵያዊ ትውፊት ያለው ሞራል ይገነባል ሲባል አሁን ሃዘን ላይ፤ ሞት ላይ፤ ጭንቀት ላይ፤ ተስፋ ማጣት ላይ፤ ሰቆቃ ላይ፤ አፈር ላይ ትቢያ ላይ፤ መቃብር አፋፍ ላይ በቆመ ምልዕት ማህል ሆኖ ማስቲካ ማኘክ? ደመነፍስነት!
ኢትዮጵያዊ አቅምን እዬሰበሩ ዲሞግራፊ የመለወጥ ፍልስፍና መሰረቱ እና አካሄዱ እንዲህ ነው። አንዱን አፍልሰህ ሌላውን መገንባት። ቀስ እያለ ሰተት እያለ የገባው ዲያቢሎስ ድል ከማድረጉ በፊት ሁሉም ህሊናውን አሰርቶ ኢትዮጵያን የማዳን እንቅስቅሳውን የእኔ ማለት ይኖርበታል። ለ እኔ የሚሰጠኝ ምልክት ይህ ሁሉ በደል ኢትዮጵያዊነትን የመበደል ታላቅ ተልዕኮ ያለው ነው።
በሁለት ቀን በሦስት ቀን በአራት ቀን በጥድፊያ ሰምተን መጣን ነው የሚሉት ጠ/ሚር አብይ አህመድ … ችግሩ ግን ታፍኖ ወራትን አስቆጥሯል። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ህሊናቸውን ካልፈሩት ማለት ይችላሉ … ለዚህ ሙግት አያስፈልገውም … በሊቀመንበርነት በሚመሩት ድርጅት ስለሚከወነው ፋሽታዊ ተግባር አልሰማሁም፤ ከንቲባ አይደለሁም ሲሉስ አድምጠን የለም … ምን አዲስ ነገር ሲኖረው ነው?!
እኔ እንዲያውም ህሊናቸው የሚያፋጣቸውን ዕውነት ቸል ብለው መቀመጥ ስለማይችሉት በቅርብ ጊዜ የሚታመሙ ይመስለኛል። ህመሙ ደግሞ የሥነ - ልቦና ይሆናል ብዬም አስባለሁኝ።
ምክንያቱም ሸፍጥ እና መሆን እሳቸው ምን ያህል ልዩነት እንዳላቸው የኪነ ጥበብ ቤተኛ ስለሆኑ እሚጠፋቸው አይመስለኝም። በሌላ በኩል ባለቅኔነት ከሰባዕዊነት ውጭ በድን ነው።
ሰው ራሱ በእዮር የጥበብ ቃል የተበጀ ስለሆነ። በቃል ውስጥ ነው እግዚአብሄርም በ አምሳሉ የተፈጠረውም ሰው ያለው። ጃዋርውያኑ አቶ ንጉሡ ጥላሁን እና እሳቸው የሚያገናኛቸው መስመር ቢኖር የለሚ ምህንድስና ብቻ ነው እንጂ ሁለቱማ ሆድና ጀርባ መሆናቸው ይታወቃል። ከቻሉ ገዝግዘው ያስተኟቸዋል ጀዋርውያኑ አቶ ንጉሡ ጥላሁን።
እሳቸውም ተገደው፤ እንያም ግድ ሆኖባቸው ነው እንዲህ በአንድ የኦሮሞ አገርነትን ምሥረታ ዓውደ ግንባርን ለማስፈጸም አብረው የታደሙት። በዚህ ውስጥ ምስኪኑ ብአዴን ተንጋሏል። አሁን ሌላው ጉዳይ ደግሞ ኦነጋውያን እና ህወሃታውያን በፍቅር ቅብጥ እና ቅልጥ እያሉ መሆኑን ነው … ህወሃት በታሪኩ ለጊዲኦ ወገኖች ሰብዕዊነኝ ሲል አውጇል። በተግባርም ተገኝቷል። ውሳኔው ሂደቱ ፖለቲካዊ ነው። በዚህ መሃል ያለው የፖለቲካ ድራማ እና እዮር ደግሞ ይጠበቃል …
የሆኖ ሆኖ ከልቤ ጠብ ሳይል የቀረው ጉዞ እና ዕድምታው እና የፎቶ ትዕይንቱ የማስቲካ ውሎ ደግሞ እጅጉን ገርሞኛል። ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ አይደል የሚባለው… ሞት ላይ ሆኖ የማስቲካ ነጋሪት … እግዚኦ? ግን ስንት ጊዜ እናምጥ!
በነገራችን ላይ የጎንደር የ100ሺህ ህዝብ መፈናቅል አውራው ጃዋርውያኑ የአቶ ንጉሡ ጥላሁን ምህንድስና መሆኑ ሊታወቅም፤ ልብ ሊባልም ይገባል። ለዚህ ነው የዶር አንባቸው ካቢኔ መጀመሪያ ሊሠራው የሚገባው ጉዳይ የጃዋርውያኑን የአቶ ንጉሡ ጥላሁን መረብ ማፈራረስ ሊሆን ይገባል። ጠንቅ ስለሆኑ።
እኔ በጎንደርም የበረታ ልዩ የሆነ ጥላቻ እንዳለባቸው ነው እኔ እማስበው። ጎንደርን በፋስ ከሁለት የተረተሩት የዘመን ሽንክ ናቸው። እኔ ጭልጋ መሬት ላይ አያንዳንዷን ነጥብ የገበሬ መንደር ስለማውቀው ፍቅር እሰከቻላችሁ ድረስ የሚቀናበት ባዕት ስለመሆኑ እመሰከርለታለሁኝ። ሰው በልቶ የጠገበ የማይመስለው የቅን ህዝብ ባዕት ነው። ስቀው ተቀብለው ኩርፊያ የሚመጣው ወደ ቤት እንሄዳለን ስንል ነበር። ውዶቼ ሌላ ቀን አጫውታችሁአለሁኝ። አሳምሬ እነግራችሁ አለሁኝ። ላዛ ላይ ነው አሁን ሰው የተፈናቀለው? ቅንጅቱ ግን ይህን ለማስፈጸም ነው።
Jawar Mohammed said "Ethiopia out of Oromia"
https://www.youtube.com/watch?v=2CB3k2gzFKs
Jawar Mohammed on Political Islam vs. Ethiopian Oromo [Amharic]
በዚህ ውስጥ ግራጫማ ሰብዕና ምን ያህል ጎንደርን እንደሚጠላ ታዩታላችሁ … የግራኝ ወረራ ግብዕቱ የተፈጸመው እዛ ነው። ግራኝ በር የሚባል ደንቢያ ውስጥ አለ …
በኢትዮጵያዊነት ክስመት ላይ ያለው ቃልኪዳን ...
የሆነ ሆኖ ለግራኙ ጃዋር ሚዲያ ቃለ ምልልስ ከቅማንት ሰው ያዘጋጁት እሳቸው ናቸው አቶ ንጉሱ ጥላሁን። እሳት ይፈልጉ ነበር ክብሪት። ይህ ሁሉ ትርምስ እንዲሆን የተደረገውም የብአዴን የስሜን አሜሪካ ወቅቱን ያልጠበቀ የቸለልተኝነት ጉዞ ነበር። ለማን ጥላችሁት ህዝቡን ሁሉ ብዬ ጽፌያለሁኝ በወቅቱ።
ለጃዋርውያን ተልዕኮ ምርጡ ...
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ