!የተፈራ ~~~~ አምክንዮ!





!የተፈራ ~~~~ አምክንዮ!


ከሥርጉተ © ሥላሴ 01.05.2018 ((Sergute©Sselassie)
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)

እናንተ --- የከበርቴው ቤት የት ነው?“ (መጽሓፈ እዮብ ምዕራፍ ፳፩ቁጥር ፳፰)


ዕድሜ ይንሳውና ወያኔ የማይፈራውንም - አምክንዮ እያስፈራራ … ዘፈነብን 22 ዓመት … ድርብ አንጀት …. ልን ህሊና …. ልጥፍ ማንነት …. የወያኔ መግለጫ!
     አረቂ ሁና ተፈጥራ ~~~~
          በቅኔ ልታቀልም ስትጣራ ~~~
                ኑሮን በትግል ልታራ ~~~~
                   ትዕግስትን አልምታ ልትዘራ ~~~
                        ስትባትል ተግታ ሳባራ ~~~
                             ሕይወትን አሳምራ ልትጋራ ~~~~
                                  የጠራችው ማማ - እማ ወራ!
ይሏታል እናትና ዓናት። ይሏታል የማህበራዊ ኑሮ መስራች። ይሏታል የሥነ - ሕይወት ቤተ- መቅደስ። ይሏታል የፍቅር ዕልፍኝ። ይሏታል የርህርህና እመቤት። ይሏታል የብልህነት አስኳል። ይሏታል የፍሬ መዘክር ሴት - ምስክር ~~-- ሙቀት።

የዓውደ ተፈጥሮ - ምህረት
                                                        የሰናይ - መስታውት፤
የጥብብ ፍልቅ ቅኝት
       የነፍስ ማደሪያ ማዕዶት
      የእርቅ ድልድይ ማህሌት
                                         የእናትነት ጥንግ ድርብ፤ - ሴት!
ውበት መግለጫ አለው። የውበት ቀለም መግለጫው ደግሞ ሴት ናት። መኖር ጻዳል አለው። የመኖር ልከኛ ጸዳሉ  ጣዕማዊ ጠረኑ ደግሞ ሴት ናት። መሬት ማገር አላት። የመሬት እንዝርት ባላው ሴት ናት። ተስፋ ቤት አለው። የተስፋ መኖሪያ እልፍኙ ሴት ናት። ዓይን ሰርግ አለው። የዓይን የዘወትር ጫጉላው ሴት ናት። ኑሮ መስራች አለው። የኑሮ  እጬጌ ሴት ናት! መንፈስ ድንኳን አለው። የመንፈስ ስሜት እርገተ - አዳራሹም ሴት! ቁልፍ!

መካራ ተጋሪ ዓይነታ!
    ለችግር ደራሽ ያ’ቸለታ፣
         ለራህብ እናቱ ልዕልት!
                   ሁሉያላት መካር ንግስት!
                                   ሴት!
መሆንን በመቻል ሰፍታ፤ መሆንን በድርጊት አሰጊጣ፤ መሆነን በፍቅር ገርታ ትገኛለች ሁልጊዜ ተግታ - ሴት! ተፈጥሮ ሲፈጠር እንዲያምርበት ያደረገው ትልቁ ሚስጢር ያለው ከአንስትነት ማህለቅ ነው። ሐሴት ታላቅ ማሳ አለው - በማህፀነ - ሴት! የነገሮች ሁሉ በትረ መፈወሻ መዳራሻ የፍጥረተ - ሴት ቀመር ነው።
                                                                                   ይፈሩሻል … ገሉሻል
                                                                              ስለምን ሸሹሻል?
                                                                    ለጓዳ ግን ይመኙሻል
                                                                         ለአደባባይ - ይፉሻል፤
                                                                  መፍትሄ አምንነትሽን ይፈሩታል
                                               እኮ! ስለምን ይሸፍኑሻል?! --~~- ይጋርዱሻል
እኮ አንቺ ውብ የደም - ገንቦ፤ የማንነት ማርዳ - ዕንቁ፤ የእኛነት አልቮ - ጌጠ፤ የእናት ሀገር ማተብ - ጽናት፤ የሀገር ሩህ ደንበር። አንችን አልቦ ምን ያህል ስንዝር መራመድ ይችላል? እስኪ ጠይቂያቸው? ለነገሩ ክርኒው ይደልቅሻል። ሸሩ ይበጣጥስሻል፤ ትብትቡ ይጠልፍሻል። አደባባይ ለአንቺ ሳያምርብሽ ቀርቶ አይደለም። እኔ እውነቱን ልንገርሽ ስለሚፈሩሽ ነው፤ መሪነትማ የፍጥረተ ነገርሽ ረቂቅ አመክንዮ - ከአስተዳደራዊ ብቃት ጋር የሰመረ ነበር። ተምሳሌት!
ስሰንቀው
   ሳሳድገው
     ሳስመው
           በላው
            ይህው ላጠው
                  እህህን ቀለበው
                          እኩልነት - ቃል አባይ ነው!
 

በማለት የለማ ነገር ቢኖር „አሉን ሴቶች - የሚሳተፉ“ ሲባል እንሰማለን። ምንአልባት ለግምጃ ቤትነት ወይንም ለኩሽና ተግባር ሊሆን ይችል ይሆናል። … በሀገር ውስጥና ውጪ ሀገር ያለው ፖለቲካ ድርጅት 92 ምናምን … ነው ይባላል። ያው የመንደሩንም አክሎ፤ የአንዱ መሪ ግን ለውርርድ ሴት አይደለችም። በዚህ ስሌት ነፃነት ይሰላ፣ ይደመር፤ ይባዛና ይታሰብ …. ነፃነት ከመምጣቱ በፊት ደርቆ ይታዬኛልለእኔ ነፃነት መለመላውን ቆሞ ካለከፍን ቀፎት ይታዬኛል። ቆፈን!
ግፊያው ጠንክሮ አያፈናፍን - ጠፍሮ - ማግሮ
    ኩርኮማው መሮ - ተደርሮ፣
              ተሰፋ አሮ - ተኮማትሮ - ተጫምትሮ
                ራዕይ እንዳይመትር አምርሮ፤
                   እሮ እሮሮ ሮሮ ሮሮ ሮሮ ሮሮ ሮሮ ሮሮ
                       የወንድ የበላይነት ተነባብሮ፤
                           የአንስትን አርነት
                              እሱ ግን ተደርድሮ ተከመሮ
                                   ዛሬ ሳይደርስ - ለከርሞ አቻነት ተርሮ
                                                 የተባዕት የበላይነት ተድሮ።
አዎን የሴቶች ትግል አድዮ አበባ ነው። ብቅ ብሎ የሚከስም። ለክስመታቸው መሰረቱ ግን የወንዶች የውስጥ ለውስጥ ተንኮልና የማያቋርጥ የማጥቃት ዘመቻ ነው። በህይወቴ ሙሉ ለሴቶች መብትና እኩልነት ፊት ለፊት ወጥቶ የተጋፈጠ የተግባር በኽረ ጀግና አልገጠመኝም። እርግጥ ፕ/ አላማዬሁ ገ/ ማርያም በብዕራቸው ዓይን ከሚቃኙት በስተቀር። ሴቶች በወጡ ቁጥር እዬተከታተሉ አረም የሚተክሉ፤ ከትግላቸው ለማደናቀፍ የሚያሴሩ፤ ባለፈም እድገታቸውን ትቢያ አልብሰው የሚቀጥፉ ወንጀሎኞች ግን እልፍ ናቸው። ለአፍ ብቻ ነው „ለሴቶች ቅድሚያ“ የሚባለው፤ ተግባር ላይ ግን የተመለመለ። ከሁሉም ቦታ እኛ አለን ነው … ሽሚያ! በለስ ቀንቷቸው ብቅ ያሉ ቡቃዬዎች ከወጡ የበቀሉበትን ቀን ሳያመሰግኑ ፍልሰት ይገጥማቸዋል። እርግጥ ነው በትናንሽ ትብትብ ሰንካላ መስመራዊ ግንኙነቶች አጥር ቅጥር የሚሰራላቸው፤ ጥግ ያገኙ ሊኖሩ ይችላሉ። ጥላ ከለላ የተረጋገጠላቸው። …. አብዛኞቹ የሚመጥኑ፤ የሚመክቱ፤ አቅም ያላቸው ውሳኔ የማመንጨት ኃይላቸው ሙሉዑ የሆኑት ግን ጦር ይታወጅባቸዋል። … ይህን ዛሬ ላይ ቁጭ ብዬ ነገን ሳስበው ነገ ሳይመጣ ተንጠልጥሎ ጠንዝሎ  ይታዬኛል። በጣምም ክው ብሎ ደርቆ።
ይሁን ብያለሁ እኔስ …
      ስለነገ ግንጣለሁ
በፅንስ - ብሌን አለቅሳለሁ፤
እስረኛ ሃሳብን እያያሁ ….
በመገፋት ይህው ዕንባን ጠገብሁ፤
                                              እኩልነት እንደራበኝ ባዶን ወልጄ - ወድጄ አልፋለሁ ….
                                       ነገም እንዳይማይመጣ አውቄያለሁ።

ለዚህም ነው የነፃነት ትግሉ ከታቱ የማይወጣው፤ አሸናፊ መሆን የተሳነው። እጥረት አለበት የልዩ ቅመም፤ ተራቁቷል በለምለም ብልኃትተላልፎታል ሥልጣኔያዊ - ስልታዊ ጉዞ። ተነፍጓል የውበት ጣዝማውን። የነክላራ ትግል ያፈራል ሲባል እንደ ካሮት ወደ ታች ሆኗል። የሴቶች ብቃት ለኢትዮጵውያን ወንዶች ከግምት በታች ነው። ሴቶች ከእነሱ እኩል የሚያስቡበት ህሊና ጋር አቻ ስለመሆኑ ተሰውሮባቸዋል፤ ሴቶች የተፈጥሮ ሚዛን እንዳላቸው አልተከሰተላቸውም። የሴቶች ቀድሞ የመተንበይ ሰማያዊ ብቃት እንዳላቸው ፈጽሞ አይቀበሉም። ሴቶች የማይደክሙ ታታሪ መሆናቸው ሰሎባቸዋል። … የሴትን ሁለገብ የብቃት መክሊት ለማድመጥ አብዛኖቹ ወንዶች ፈቃደኛ አይደሉም። …. የፖለቲካ መሪዎችማ ይፈሯቸዋል። ሰራዊት አሰልፈው ነው የሚዋጓቸው። ይህን በጣም በርግጠኝነት ነው መናገር የምፈልገው።
ፍርኃት ሲሆን ከረባቴ
   ድፍረት ሲያመልጠው ቀበቶዬ
      ተብልቶ አዬሁት ፍሬዬ።
                መንገድ መሳቴ
                           ለፍሰቴ
                                ፍድሰቴ፤
                                    የሦስት ጉልቻ ተስፋ ስብራቴ።
ለዬትኛውም ቦታ ሴቶች ሲሆን የበለጠ በስተቀር የሚመክት አቅምና ብቃት አላቸው። ግን ማን ይድፈረው?! ወንድነትን ይጠይቃል?! እውነት ለመናገር የሀገራችን ችግር ብቸኛው የመፍትሄው ቁልፍ የሚገኘው ከሴቶች ዘንድ ነበር። ነገር ግን ተሰውሮባቸዋል መሪዎቻችን። ተጣፍቶባቸዋል የፖለቲካ ሳይንስ ሙሁሮቻችን …. አስበውት የሚያውቁም አይመስለኝም። „ተጋፍተው ይውጡ“ …. ይህ ነው መልሱ እኛ እኮ በረት ውስጥ አላደግነም። እንደ ከብት የምንጋፋው። …. በሚዘረጋው ሥርዓት ሁሉ፤ በሚቋቋመው ድርጅት ሁሉ፤ በሚፈጠረው መዋቅር ሁሉ ዝለቱ የሴት ነው። ታላቅ ስም ተሰጥቶናል በመንፈስ አቅመ ደካሞች በሆኑ „ኃይለኞች“ ናቸው በቃ! … ይህ የወረራ መርዝ ሀገር ምድሩን እያደረሰ ሴቶች አንገታቸውን ደፍተው በሀገራቸው ጉዳይ በእኩል መድረክ እኩል ድርሻ እንዳያበረክቱ ትልቁ በር ተከርችሟል። ከዚህም በተጨማሪ የሥነ ልቦና ጥቃት ሁሉ ይፈጸማል ብልኃት ያጣ ቅላት።

ነብዬ እግዚአብሄር ዳዊት በመዝሙሩ „ህግ ተላላፊዎችን ጠላሁ“ አለን። ወንዶቻችን ትሰማላችሁ?! እናንተም ተፈጥሮን እዬተላላፋችሁ ነውና ልብ ይስጣችሁ። የነፃነት አምሮት ካቃጠላችሁ። እንታገላለን ለነፃነት የምር ከልብ ከሆነ ቃላችሁ። እስከ አሁን የሴቶችን አቅም በሚኮረኩመው፤ በሚኮረኩደው መንገድ ፍሬያችሁን ቁጭ ብላችሁ ገምትቱት። የቁጥር ተማሪም ሁኑ። ትንሽ የማርኬቲንግ ኮርስም ውሰዱ። የነፃነት ትግሉን አትራፊ ለማደረግ ሥርነቀል እርምጃ ለመውሰድ አምላክ ይርዳችሁ። ሌላው ምቀኝነት ሞመከሪያ ጣቢያው ማዕከሉ በሴቶች የጭቆና ቤተ ሙከራ አርጓል

ትልቁ የምርምር ተግባር ለዛሬ፤ ለነገም፤ ለነገ ወዲያም ሊሆን የሚጋባውን የሴቶችን ተፈጥሯዊ ዕምቅና ቅምጥ ኃብት በምን መልኩ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚቻል መሆን አለበት። የወደፊቷ ኢትዮጵያ ንድፈ ኃሳብ ማሳው አምራች እንዲሆን ከተፈለገ መነሳት ያለበት ከዚህ በትረ ጉዳይ መሆን አለበት። ወረቀትን እንደ ፎቶ መርቅነዋል፤ እኛ የምንሻው በተግባር እንድታገቡ ነው ከምታረቋቸው በቄንጠኛ ቃላት በቅብ ቀለም ከምታሳምሯቸው ድንጋጌ አንቀፆቻችሁ ጋር። …. በስተቀር …. „የልጅ ነገር አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ“ እንዲሉ ነው ነገረ …. ሚስጢሩ የሚበልጧችሁን ሴቶች ለመቀበል ፍቀዱ። ከሁሉ በላይ የተፈጥሮን ሚስጢር አድምጡ። ቧልት ዓይደለም ዓይነታው የእኩልነት ማንነት ሥነ - ምግባርና ዶግማን ነው ላስተውሳችሁ የምፈልገው፤ ብቁ ሴቶችን ከመፋለም ቆጠብ ብሎ አቀራረብን በማሳመር ሚሊዮኖችን ማሰለፍ ብልህነት ነው። ነገን  በጠራ ሁኔታ ማዬት የሚቻለውም በእናትነት መክሊት ሆድ ዕቃ ውስጥ ነው።

ማሳረጊያ … ለመሆኑ በምትፈጥሯቸው ተቋማት የድርጅት መምሪያ የሚባል ነገር አላችሁን? ድርጅት የአንድ አካል የነፈሱ ዓይን እስትንፋስ ነው። የዚህ የነፍስ እስትንፋስ ሴሎች ደግሞ ሴቶች መሆን አለባቸው። በስተቀር ምድረበዳ ላይ ሆናችሁ ነው ተቋማችሁን የወጠናችሁት …. ለብዘንበልበለዝማረትፍርስ ዕጣ ፈንታው የተቋማችሁ። ስለምን? ዋናውን የደም ጋን ቧንቧ ስለምታፍኑት! ተዋፆውን ቀራኒዎ ስለምታውጁለት። ለነበረን ቆይታ እያመሰገንኩ በነካ እጄ በዚህ ነጥብ ዙሪያ እመለሳለሁ …. የተፈራ አምክንዮ ደፋር ቢያገኝ … እስኪ ይለካ በንብ አውራ ብዕረ - ክናድ …. እላለሁ። የተወሳሰበ ትግል የሚያመጣውን የኃይል አሰላለፍ

መፍቻ
  • ለችግር ደራሽ „ያ’ቸልታ“ ከሚለው ይህ ’ ምልክት አለ። ለንባብ እንዲያመች አንድ ፊደል ተውጧል ማለት ነው። ፊደሉን ነው ከትህትና ጋር።
  • የግጥሞቹ መስኖ እንደመንፈሴ የተገሩ ናቸው። እርእሶቹ የተሰመረባቸውና የጎሉት ናቸው። አመሰግናለሁ።


ሥጦታ … ይህን የኮቢዬን ትንፋሽ በመንፈሴ ሳታምም „መቻቻልን“ አስልቶ ነው። ስለሆነም ጹሑፉ በተለዬ የጻፍኩበት ምክንያት በዬአጋጣሚው ሁለመናቸው ለነፃነት ትግሉ ለሰጡ፤ የግል ህይወታቸውን ሆነ የልጅነት ጊዜያቸውን ምክንያታዊ ነው ብለው ሁለመናቸውን ለጎዱና ላጎሳቆሉ  ግን እዬታዩ ለሚዘለሉ፤ እያሉ ለሚረሱና አስታዋሽ ያጡ የድርጊት ጀግና እህቶቼን በአክብሮት በማሰብ ነው። የወንድ ወንድሞቼ …. ወጣ ገብ፤ ነቀል ተከል ጉዞ መንፈሴን አማርቶታልና። ተስፋዬን አጋድሞ ወቅቶታልና። ስለሆነም አቅሜ ብዕሬ! ጉልበቴ አምላኬ የሰጠኝ አቶ ቅንነት ነው። የመተንፈሻ ቧንቧዬ መስመር በጉልበተኛ ተባዕቶች ተጉሉና ጓጉሎ ነበር። ታዲያ አቶ ቅንነት ጥቃት አወጣ። ወጌሻ ሆኖም ጠግኖ ለወግ አበቃው! እግዚአብሄር ይስጥልኝ አቶ ቅንነት!


የሴቶችን እምቅ ተፈጥሯዊ ኃብት የዘለለ ማናቸውም የነፃነት ትግል ለድል ከመብቃቱ በፊት ይደርቃል!
ሴቶች የህሊና ዓይኖችየልብ ክናዶች ናቸው!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።   


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።