የባድሜ ፖለቲካ እና ወልቃይት!!

የባድሜ ፖለቲካ እና ወልቃይት!! 
(የሺሀሳብ አበራ)
June 9, 2018
ሻዕቢያ የትህነግ የበላይ ሆኖ በሰላም መኖርን ይመርጥ ነበር፡፡ ነገር ግን ተመሳሳይ ፋብሪካዎች በመቀሌ እና በአዲግራት፣ በአስመራ ስለተከፈተ ሁለቱም ሻጭ ሲሆኑ ገበያ ጠፋ፡፡ ሻዕቢያ ትህነግ ካልተመችኝ የምኒሊክን ቤተመንግስት ለኦነግ እሰጣለሁ እያለም ዛተ፡፡ ኢሳያስ አፈወርቂ በህይዎቴ የሚቆጨኝ ነገር የምኒሊክን ቤተመንግስት ለኦነግ መስጠት እየተገባኝ ለትህነግ መስጠቴ ነው ሲል ከርሟል፡፡
ትህነግ እና ሻዕቢያ ወዳጆች ነበሩ፡፡ 1972 ጀብሃን አስመራ ላይ በጋራ ቀብረውታል፡፡ ትህነግ 1968 በፃፈችው ማንፊስቶ የኤርትራን መገንጠል አውጃለች፣ ተቀብላለች፡፡
ሻዕቢያ በሽግግር መንግስቱ ወቅት ትህነግን እንደ ቅንጣት እየቆጠረ ለመኮርኮም ሲሯሯጥ፣ አስመራን ይዞ የበላይነቱን እንዲያነሳ ተወሰነ፡፡ እስከ 1989 ግንኙነቱ መልካም ነበር፡፡

1990 ጀምሮ የኢኮኖሚ ጦርነት በድንበር ሰበብ ተቀሰቀሰ፡፡
ባድሜም የሁለቱ ሃገራት የፉክክር ሜዳ ሆነች፡፡ 1993 አቶ መለስ እና አቶ ኢሳያስ በአልጀሪያ ባድሜ የኤርትራ እንደሆነች ተስማሙ፡፡ የዛኔው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዮም መስፍን ባድሜ የኛ ናት፡፡ አልሰጠንም ብለው መላው ኢትዮጵያን በደስታ አሰለፉ፡፡ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ ህዝቡ ደስታውን ገለፀ፡፡
70 በላይ ዜጎች ቢገደሉም መሬታችን ተመልሷል የሚለው ዘፈን ሾላ በድፍን 17 ዓመት ቀጠለ፡፡
ዘንድሮ 17 ዓመት በኃላ ኤርትራ መሬትሽን ውሰጅ ተባለች፡፡ በዚህ ውሳኔ ውስጥ የህወሓት የአንበሳውን ሚና ይጫዋታል፡፡ እንደተጫዎተም የሰጠው መግለጫ ያሳያል፡፡
ህወኃት በምዕራብ በወልቃይት፣ በሰሜን በባድሜ፣ በምስራቅ በኩል ከወሎ እና ከአፋር የእኔነት ጥያቂዎች ተነስተውበታል፡፡ የአፋር ወጣቶች ወረዳችን ያላግባብ ተካሏል ብለው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ናቸው፡፡
ባድሜም 1989 ጀምሮ የኤርትራ ጦር አዳምኖባት ቆይቷል፡፡ ወልቃይት እና ራያ በተለያየ አቅጣጫ 1972 ጀምሮ የማንነት ጥያቄዎች ተነስተውበታል፡፡
ባድሜ በአልጀርስ ቀድሞ 17 ዓመት በፊት ተሰጥቷል፡፡ በባድሜ 3500 ያልበለጡ ዜጎች ይኖራሉ፡፡ ቦታውም የወልቃይትን ያህል ጠቃሚ አይደለም፡፡ ስለዚህ ባድሜን ለኤርትራ በመደርጎት በሰሜን ጫፍ የሰላም እርግብ ለመልቀቅ ትህነግ የከጀለች ይመስላል፡፡ ኢሳያስ አፈወርቂ ግን ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ፀጥ አለ፡፡ ስልክም አያነሳም፡፡ በትህነግ በኩል የባድሜ ስጋትን ቀርፎ ወደ ወልቃይት ለማተኮር ቢሞከርም የሚሳካ አይመስልም፡፡
የግንቦት 20 በዓል ሲከበር አቶ ስዮም መስፍን የስነ ልቦና ጦርነት ተከፍቶብናል እንመክተዋለን ብለው ነበር፡፡ ጦርነቱ ከአስመራ ጋር አይደለም፡፡ ከጨቋኟ ብሄር እና ከትምክህተኞች ጋር ነው፡፡ የትህነግ መሰረት የአማራ ጭቆናን ማቆም የሚል ነው፡፡ ሻዕቢያማ ወዳጁ ነበረ፡፡ ዛሬም ሁነኛ ጠላቱ አይደለም፡፡
በአንድ ሃገር እየተኖረ፣ ተቀራራቢ ባህል ያላቸው የሁለቱ ወዳጅ ህዝቦችን ጉዳይ ሳያጤነው የትግራይን ህዝብ ከአማራ ህዝብ እንዳይገናኝም እያደረገ ነው፡፡ በአማርኛ የቀደሰ ካህን፣ በአማርኛ ያንጎራጎረ ብሶተኛ፣ የአማራ ክለቦችን መለያ የለበሰ ወልቃይቴ ሁሉ በበጎ ካለመታየት አልፎ እየተቀጣ እንደሆነም እየተሰማ ነው፡፡
ትህነግ ባድሜን ለአስመራ ሸልሞ የኢሮብ ብሄረሰቦችን የማንነት ጥያቄ ወደ ሚነሳባቸው አካባቢዎች ላስፍር ማለቱም አይቀርም፡፡ በማስፈር የአካባቢን ማህበራዊ ሁናቴ ለመቀየር ያስብ ይሆናል፡፡
በግንቦት 20 ክብረ በዓል ወቅት በመድረኩ የተፀባረቁት ነገሮች በብዛት የአማራን ጉዳይ የተመለከቱ ነበሩ፡፡ ስለ ብአዴን መርህ አልባነት፣ ስለ ትምክህተኝነት፣ ስለ ድሮ ስራዓት መናፈቅ ወዘተ አጀንዳዎች ነበሩ፡፡
የእነዚህ የሻገቱ ጥያቄዎች መነሳት ቀስቱ ዛሬም እንደ ትናንቱ አማራው ጠላቴ ነው ከሚለው ፍረጃ የሚመነጭ ይመስላል፡፡ ባድሜም ትንሽ መጥፎን አልፈህ፣ ትልቁን መጥፎ መክት ለሚለው የፖለቲካ ስልት መፍትሄ ናት፡፡ ለትህነግ ትልቁ መጥፎ ወልቃይት ናት፡፡ የባድሜ መሄድ ብዙ አይጎዳም፡፡ ጥቅሙ የበረከተ ነው፡፡ አካባቢውን ያረጋጋልና፡፡ የወልቃይት ጉዳይ ግን ይጠጥራል፡፡
የአማራ እና የትግራይ ህዝቦች የሰመረ የባህል እና የታሪክ ትስስር ያላቸው ተዋዳጅ ህዝቦች ናቸው፡፡ ህዝብ ፍቅር ነው፡፡ ህዝብ አንድነትን ይወዳል፡፡ ሁለቱ ህዝቦች የጋርዮሽ እሴት አላቸው፡፡

ይህን እሴት ግን ትህነግ እያጠፋው ነው፡፡ በወልቃይት የሚደርሰው ግፉ፣ በእስር ቤት የሚደርሱ የማንነት እርግማኖች፣ በማንፊስቶ ህዝብን ጠልቶ በመጀመር የሁለቱን ህዝቦች ግንኙነት ጥቁር መጋረጃ ጥሎበታል፡፡ ህዝብ አይሻርም፡፡ ዘላለማዊ ነው፡፡ የአማራም የሆነ የትግራይ ህዝቦች የህወሓት ሆነ የብአዴን ስልጣን ሲያልፍ ተዋደው ይቀጥላሉ፡፡ እውነቱም ይረጋገጣል፡፡

ነገር ግን ማንነት በሴራ ላይፋቅ የማይሆነውን ለማድረግ መሞከር የታሪክ ኪሳራ ከማስከተል ያለፈ ሚና አይኖረውም፡፡ ወልቃይቴው አማራ ነኝ ካለ አለ ነው፡፡ ልክ ለባድሜ ምላሽ እንደተፈለገው ሁሉ ለወልቃይትም በአፋጣኝ መፍትሄ ካልተፈለገ የሁለቱን ተዋዳጅ ህዝቦች ግንኙነት ማጥቆሩ አይቀርም፡

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።