የአብን መሥራች ጉባኤ ልዩ የምሥራች ነው - ለእኔ።
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ
መሥራች ጉባኤ
ታላቅ
የምሥራች ነው።
የምሥራች ነው።
ከሥርጉተ ሥላሴ ሲዊዘርላንድ 09.06.2018
(ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)
„ሁሉ በሥላሴ ፈቃድ ተፈጥሯልና፣ ይህ ለምንድን ነው
ያ ለምንድን ነው የሚል የለም።“
(መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፬ ቁጥር ፳፩)
- ብሥራት አባተ።
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ መሥራች ጉባኤ በባህርዳር
እዬተካሄደ ስለመሆኑ ዛሬ ግንቦት 09.06.2018 ከሚሊዮኖች ድምጽ ከጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሽፈራው እና ከዘሃበሻ ደስ የሚል ዜና አሁን
ተደምጧል። ይህ ትውልድ ከቶውንም ሊረሳቸው የማይችለውን የሰብዕዊ እና የሰላማዊ ትግል መብት ተሟጋቹን የፕ/ አስራት ወልደዬስን
ቅዱስ መንፈስ በባዕቱ ዳግም ትንሳኤውን ያወጀ እጅግ ታሪካዊ የምሥራች ነው።
አማራ ለ43 ዓመት በሥውር ህሊናው ሲመዘበርበት
የነበረውን ዘመን ማክተሚያሚ ላይ ይህ መረጃ ሲመጣ ታላቅ የሰናይ ቀን ነው። አማራ አቅሙን፤ ብልህነቱን፤ ችሎታውን፤ ተመክሮውን፤
ክህሎቱን፤ ሰብዕናውን፤ በራሱ አቅም ልክ ፖለቲካውን ዕውቅና
እና ተቀባይነትን አስጥቶ ትውልዱ የሚሻውን ማናቸውንም የዜግነት
ሙሉ መብት በእኩልነት ለማስከበር የሚያስችል ቁመና ላይ ለመገኘት ብዙ መጣር አለበት። ሥሙን ወድጀዋለሁኝ። አማራ አገሩ ኢትዮጵያ
ናት እና።
ገና ውጥን ስለሆነ ተጠልፎ እንዳይወድቅ ከኦህዴድ
ብልህ መሪዎች ሰፊ የሆነ ተመክሮ መውሰድ አለበት። ኦህዴድ በራሱ ላይ በቆመ ሃሳብ መምራት በመቻሉ ነው ዛሬ በዚህ መላቅጥ በጠፋው
ውጥንቅጥ ፖለቲካዊ ሁኔታ ኢትዮጵያን ለመታደግ አደራ ተረካቢ በመሆን የክፉ ቀን ቁርጠኛ ተጠሪ የሆነው። ይህ ተጋድሎ ባይሳካ እጅግ
የጎሹ ዕጣ ፈንታ ኢትዮጵያም እንደ አገር አፍሪካም እንደ አህጉር የመርዶ ዜና ይጠብቃቸው ነበር። የዓለምም ስጋት ከፍተኛ ነበር።
- · አቅምን ከሚበሉ ነገሮች መታቀብ።
ይህ ቀንበጥ ድርጅት አቅምን ከሚበሉ ነገሮች የሃሳብ፤
የፋይናንስ፤ የሥነ - ልቦና ጥገኝነት ተጠዋሪ ካልሆነ፤ ከዚህ የጸዳ ራዕይ ካለው በአጭር ጊዜ ውስጥ ራሱን ተወዳዳሪ አድርጎ ለመውጣት
አቅም - ብልህነትም - ችሎታም ያነሰዋል ብዬ አልገምትም። የውጭ ሃይል የፋይናንስ፤ የሥነ - ልቦና፤ የሃሳብ ተጠዋሪ ከሆነ ግን
ከቅንጅትም፤ ከአንድነትም፤ ከህብረትም ዕጣ ያለፈ ዕድል አይገጠመውም። ያለምንም ጥጥር ይወድቃል። ደጋፊ አካል ውጪ አገር ይህ ድርጅት
የመሠረተ ዕለት ደጋፊ አባላት ድርጅቱን ጥለው መውጣት ይኖርባቸዋል። አይዘልቅም። በጣም ዥንጉርጉር ነን። የተኖረበት ፖለቲካ የመጣጣል
ስለሆነ። ሰንጥቅ፣ ትርትር በመፍጠር ራስን ማጥፋት ብቻ ነው ትርፉ። ይህን እንደ ድርጅቱ አብን የሚፈቅድ ከሆነ ባይጀምረው ይሻለዋል።
ምክንያቱም የኢኮኖሚ ጥገኛ እስከ ተሆነ ድረስ
በሃሳብ ውስጥ ጠንቶ ጉዳይን ለማስፈጸም የሚጣልበት የተበተነ ቅደመ ሁኔታ እጅግ ሰፊ ነው። በዛ ላይ ሁሉም የራሱን አቅም አጎልብቶ
መውጣት ስለሚሻ በሂደትም መዋጥም ይኖራል። ሲፈርሱም ጥሪት
የላቸውም። ቢያንስ የፍቅር እና አብሮ የመኖር ዘይቤ እንኳን። በሌላ በኩል ይህ ድርጅት ውጪ አገር የሚኖረውን ማህበረሰብ ለመነጣጠል
ምክንያት መሆን በራሱ ሌላ ጠባሳ እና አሻራ ነው።
ቅንጅት ከመራራ ስንብቱ የገዘፈው በትኖን መክሰሙ ነው። ስለዚህ ውጭ ያሉት የአማራ
ድርጅቶች ሆኑ የተጋድሎው ታታሪዎች በጀመሩበት መልክ ተግባራቸውን መከወን፤ አገር ውስጥ ያሉት ደግሞ ሞቱንም፤ እንግልቱንም፤ እስራቱንም፤
መከራውን አይተውታል እና ወገባቸውን ጠበቅ አድርገው
ራሱን በቻለ ራዕይና አቅም ተግባራቸውን አህዱ ማለት ይገባቸዋል።
ይህ ለድርድር ሊቀርብ የሚገባው ጉዳይ አይደለም። ውጪ ያሉትም የ አማራ ተቆርቋሪ መንፈሶች ሰላማቸውን ሊያውኩት አይገባም። በምንም
ሁኔታ ጣልቃ ለመግባት ባይሞክሩ ጥሩ ነው።
ስለምን? ለሀዘኑ ዘመን ማለቂያ የሚጠቅም ስላልሆነ። ገና ሊመወለዱት ራፊ የመንፈስ
ጉልማ መሬት እንዳይኖራቸው ለተፈረደባቸው ዋቢ ለመሆን ስለማያስችለው። ላልተጸነሱትም ማሰብ አለበት። ባለቤት አልባ ጥለናቸው ነው
የምንሄደው። ዕውነቱ አማራ አገር የለውም። በመንፈስ መጠላት ብቻ አይደለም የተሰረዘ ማህበረሰብ ነው። በሌለንበት ነው አለን ብለን
አቅም ስናባክን ዕድሜያችን የሸኘነው። ስለዚህ የእኛ ይበቃል።
ዛሬ ማህበራዊ ሚዲያም ቢሆን እዛው ያሉት መጀመር ያስችላቸዋል። ሁኔታው የፈቀደለት አቅሙ ሁሉም አለው። አንድ ቴሎፎን
ብዙ ነገሮችን ይከውናል። አማራ እዬሞተ ለኖረበት መንፈሱ ራሱን ችሎ ለመውጣት በኤኮኖሚም ቢጠዬቅ ደም ሲገብር የኖረ ህዝብ ወርቁን እዬሸጠ እንደሚደግፍ ልብ ልክ ነው። ስለሆነም ይህ ድርጅት
የምንም ነገር ተጠማኝ መሆኑን በሩን ከዛጋ በትክክልም በራሱ ውስጥ
በቅሎ፤ ራሱን አስብሎ አስፈሪውን የነገ የትውልዱን ዕጣ ፈንታ የመግታት ሙሉ አቅምን አምጦ በመውለድ ታሪካዊ ድርሻውን ለመወጣት
ያስችለዋል። አልፎ ተርፎም ዛሬ ኦህዴድ ኢትዮጵያን በመታደግ ላደረገው አስተዋፆ አቅም ሆኖ የመውጣት ዕድሉ ሰፊ ነው። ግን ጠንቃቃ
ከሆነ ብቻ ነው። በርን ከፍቶ የከፈለ ሁሉ ግባ ከሆነ ያ ገብያ እንጂ የፖለቲካ ድርጅት ሊሆን አይቻለውም ወይንም የሰርግ
ዳስ ደንበኛ።
- · ህብረትን፧
ከዚህ በተጨማሪ ህብረት፤ ውህደት፤ ጥምረት፤ የሚለውን መቀበል አይኖርበትም። ህዝቡ እና መሬቱ እንጂ የተጋድሎው መሠረታዊ
ጥያቄ በዓለም አደባባይ በግለት ታይቷል። የቅንጅት ምሥረታ እና ፍርሰቱም
አመክንዮው ይሄው ሃቅ ነው። ጠጣሩ ተከድኖ ተምስጥሮ የተያዘው ሥም ጠቀስ ሚስጥር ይህ ዕውቅ ፖለቲከኛ፤ ዓራት ዓይናማ ተንታኝ፤
የተዋጣለት ጋዜጠኛ፤ ብልህ መሪ አማራ ነው እንዲባል ፈጽሞ አይፈለግም። ለመሸጋገሪያ ድልድይነት ብቻ ነው አማራ የሚፈለገው እንደ
ቸረቸራ ውሃ ለመያዣነት። ስለሆነም ለጥያቄ ሊቀርብ የማይገባው ጉዳይ
አማራ እንደ አማራነቱ ራሱን ችሎ መውጣት ብቻ ነው የሚያስፈልገው። ሥነ - ልቦናውም፤ በደሉም፤ መገለሉም አይገናኝም ከሌላ
ድርጅት ጋር ተቀላቅዬ ልስራ ቢልም። ውሃ እና ዘይት ነው የሚሆነው። ስለዚህም አሁን ህዝቡን መናጆ ላለማድረግ፤ ተጨማሪ መስዋዕትንት
እንዲከፍል ላለማድረግ በትኩረት ራሱን ችሎ ለመውጣት ማናቸውንም የህብረት ጥሪዎች መንገዶችን ሁሉ መዝጋት አለበት። በዛ ላይ ገና ያረጋ ደም ነው - ጽንስ።
ህብረት ትብብር መልካም ቢሆን ለአማራ ግን የሚበጁት አይደሉም። ታይቷል። አማራ ከ አግልግሎት ውጪ ነው የሚሆነው ከተመጠመጠ
በኋላ። ይህ ደግሞ በህብረ ብሄር ተዳራጅተው የነበሩ የአማራ ልጆች የደረሰባቸውን መከራ ከእናንተ ሌላ እኔ ብናገረው ያስገምተኛል።
ከእስር ሲፈቱ እንኳን የነበረው የእስር ቤት አያያዝ ምን ያህል የሰፋ ልዩነት እንደ ነበረው ታሪክ ይናገረው። ዕውቅናውም የዛኑ
ያህል በምንም ደረጃ ነው የነበረው። የ አማራ ተጋድሎ አርበኞች መፈታታቸው ሁሉ አልተፈለገም ነበር። እንደ መያዣ፤ እንደ ፖለቲካ
ጫና መፍጠሪ እዛው ተከዝነው ፈተናው እንዲጋፈጡ ነበር የተበዬነው። ለዚህም ነው ሲፈቱ ደስታው የአማራ ብቻ ሆኖ የቀረው። ዘሃቸውም
ዘነዘናቸውም፤ ወጣትነታቸውን በልቶት ነው የታዬው - እስሩ። መከራው እና አሳሩ መጧቸዋል።
- · ጠብ ጠራኝን መጠዬፍ።
ሌላው ያልተገባ እሰጣ ገባም ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ጊዜን ከመብላት ውጪ የሚያመጣው ፋይዳ ስለማይኖር የፈለገ
የፈለገውን ቢል ተግባርን ብቻ መከወን፤ የተቀናቃኝን ሃይል ይቀንሳል፤ የሚባክን ጊዜንም ይታደጋል፤ የተቃርኖንም ሁኔታ ያረግባል።
ዕውን ይህ አዲስ ዕንቡጥ የአማራ ድርጅት ክልቡ ከሆነ ፍቅር ሰጥቶ ፍቅርን ከመቀበል ውጪ፤ ከሌሎች ቀደምት ድርጅቶች ጋር እሰጣ
ገባ የሚያስገባው ምንም ነገር አይኖርም። ጊዜም የለውም። በመንፈስም በአካልም በአረማመድም በፍጹም ሁኔታ ሰላማዊ መሆን አለበት። የሚያገኛቸውን ሰዎች መመጠን አለበት። እዬሄደ መላተም አይኖርበትም። የግንኙነት
መስመሮች ናቸው ጥርጣሬ እዬወለዱ ሳቢያ እዬሆኖ ያልሆነው ሆነ ለማለት ለቀባሪው ስንቅ አቀባይ ተሁኖ የተኖረው።
አፍ እላፊ ሁሉ የሚረዳ አይደለም። ይሄ ከድርጅቱ ውጪ ጹሑፍ መጻፍ፤ ተነጥሎ ቃለ ምልልስ ማድረግ ሁሉ በህግ ማሰር አለብ
አዲሱ ድርጅት ብዬ አምናለሁኝ። የሥራ ክፍፍል በወጉ የማድረግ። አንድ አመራር ሆኖ የተመረጠ ሰው ከድርጀቱ ህግ በታች እንጂ በላይ
መሄድ የለበትም። በዚህም ኦህዴድን ነው ለናሙና የምወስደው። የቀደሙትን ከኦህዴድ ጋር የተደረጉ ቃለ ምልልሶችን DW, OBN ላይ
አርኬቡ ላይ ስላለ ማዳመጥ ይጠቅማል። የኦህዴዱ አቶ ካሳሁን ኮፌ ለዚህ አብነት ናቸው። በጣም ጠንቃቅ፤ በጣም ብልህ ፖለቲካኛ ናቸው።
ኢትዮጵያ እንዲህ ያሉ ቁጥብ ፖለቲከኞች በእጅጉ ያስፈልጋታል።
- · መከራን ለመሻገር ጥሞና።
አሁንም በድጋሚ ለምሳሌ የማነሳው ኦህዴድ ነው። 700 ሺህ ያህል ህዝብ ተፈናቅሎ፤ ተጨማሪ 50 ሺህ ህዝብ ተፈናቅሎ፤
ህይወት እንደ ቅጠል ረግፎ የቻለውን ችሎ፤ በግራ በቀኝ የሚደርስበትን ግፊያ ችሎ አሁን ባለቀ ሰዓት ነው የተከናወነውን ተግባር
እንኳን ከቶውንም ዘመን የማይተካቸው የምዕቱ ቅኔ ኦቦ ለማ መግርሳ ስሜታቸውን የገለጹት። የልባቸውን ካደረሱ በኋዋላ። ትውልዱ ከእሳቸው
እጅግ በጣም ብዙ ብልህነትን በቅንነት መማር አለበት። የኦቦ ለማ መግርሳን ንግግሮችን በወል ቁጭ ብሎ ባጋራ በማዳመጥ መማር ይኖርበታል።
እጅግ ብልህ መሪ ናቸው። ሊጠኑም የሚገቡ። ዴሞክራሲን ዕውን ኢትዮጵያ ላይ በራሳቸው ሰብዕና የፈጸሙ የምዕት ቅኔ ናቸው።
“ለ40 ሺ ነፍሶች ይቅርታ ማድረግ በሰው ልጆችም ሆነ
በፈጣሪ ፊት ጥሩ ስራ ነው” - የሸገር ወሬዎች
- · ከልቅ ግንኙነት መታቀብ።
የታዬ ሁሉ አይበላም፤ የተዘራ ሁሉ እንደማይበቅለው ሁሉ። የፈለገ በሥሙ ገናና ይሁን የእናንተን የቤት ሥራም ሊሠራላችሁ
አይችልም። የውስጣችሁን የስብዕና አቅምም ሊተካ አይችልም። ስለሆነም ግንኙነትን በድንበር ማድረግ ብቻ ሳይሆን ከሥራ በፊት ማናቸውንም
ትልም ዘርግፎ ለዬትኛውም አካል ስንቅ ከመሆንም መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ቀዳዳን መድፈን። ከፈሰሰ በኋዋላ ለመጠገን ከመሯሯጥ ቀድሞ
በቀዳዳ ከረጢት ልባም አመክንዮችን አለማስቀመጥ።
- ብልጥነትን ከብልህነት ጋር እንዴት?
ለፖለቲካ አመራር እና አስተዳደር ብልህነት እንጂ ብልጥነት የመሪነት የጥራት ደረጃ መለኪያ አይደለም። በራስ ሃሳብ ውስጥ
መብቀል እና በበቀለመው ሃሳብ ውስጥ ለመዝለቅ መወሰን። የወሰኑትን ሳያንጠራሩ በልኩ መተገብር። ቀጣዩ ቀን ሌላ አዲስ ስንቅ ሰለሚሻም
በብልህነት የተቀመመ አዲስ ሃሳብ ማማጥ እና አፍልቆ በዛ ውስጥ ለመቀጠል መፍቀድ። የራስ የሆነ ነገር ብቻ ነው አድሮ የሚገኘው።
ብልጥነት ዕለታዊ ዝና ቢያሰገኝ እንጂ ፖለቲካዊ ትርፉ ባዶ እያስቀረ የሚሄድ በሽታ ነው። ስለዚህ ከዝና ነጋዴነት መውጣት ያስፈልጋል።
የማይሰነብት ክብር እና ሞገስ በብልጥነት ከማጋፈፍ የሚሰነበት ድህነት ይበልጣል።
- · ብአዴን እና አብን።
ለብአዴን ትልቅ አቅሙ ነው አብን። ለአብንም ቢሆን አስፈላጊው ነው። ፖለቲካዊ ውድድሩ ለዛ ለተገፋ አማራ እስከ ሆነ
ደረስ ምን የሚያጋፋ ነገር የለውም። በሁለቱ የሃሳብ ልዩነት የሚጎዳው ያው ዘመኑን ሁሉ መከራ ሲገፋው የኖረው አማራው ነው። ስለዚህ
በመደጋገፍ ላይ፤ በመረዳዳት ላይ የተመሠረት ህዝብን የማገለገል መንፈስ መፍጠር ያስፈልጋል። ይህ አዲስ ድርጅት አለኝ ሊለው የሚገባው፤
ሃብቴ ሊለው የሚገባው ጉዳይ አዎንታዊነት እና ቅንነት መሆን
አለበት። አላስፈላጊ ቅራኔ ከብአዴን ጋር አለመግባት፤ አላስፈላጊ
ግብግብ ከጸጥታው ሃይል አለማድረግ ወሳኝ ጉዳዮች ሲሆን፤ ከ66ቱ የመጠላለፍ ፖለቲካ በፍጹም ሁኔታ መውጣት ያስፈልገዋል አብን።
መልካም መግባባት እና መገናኘት ነው ከብአዴን ጋር ሊኖር የሚገባው።
በዚህ ውስጥ የገዱ ቅዱስ መንፈስም እንዳለ መዘናጋት አይገባም።
በኮ/ ደመቀ መኮነን በዛ ክብር ውስጥ የእስሩ ጊዜ እንዲጠናቀቅ ማድረግ ታላቅ ተገድሎ ነው። የጠቢቡ ቴወድረስ ካሳሁን ጥቃት መመለሰም
ሰፊ ድል ነው። ይህ ዛሬ የተገኘው የመደራጀት ዕድል በራሱ የአማራ እና የኦሮሞ አብዮት ያመጡት ብቻ ሳይሆን ይህን አዳምጠው ለውጤት
ለማብቃት የተጉት የለማ፤ የአብይ፤ የገዱ የአንባቸው መንፈስን በህሊና አክብሮ መነሳት ይጠይቃል። እናመሰግናለንም ሊባሉ ይገባል።
ለስኬት ያበቁት የ እነዚህ ብልህ ስክነታዊ የተዋህደ የተግባር ተጋድሎ ነው።
ክብር የሚገኘው መከበር የሚገባወን ነገር አክብሮ ለመነሳት ቅንነት ሲኖር ብቻ ነው። አማራ ሰው ያከብራል ሲባል እራሱን ለማስከበር ሌላውን አክብሮ ይነሳል ማለት ነው።
እንደሚታወቀው በላፉት 43 ዓመታት አማራ የጽዋ ማህበርም አይፈቀድለትም እንኳንስ በሥሙ አማራ ነኝ ብሎ ለመደራጀት። ለዚህ ነው መአህድ እንዲከስም የተደረገው። መስዋዕትነት መክፈል በራሱ የድል ፍሬ
አስገኚ አይደለም። የፈለገው አይነት ህዝባዊ ሞገድ መሪ ከሌለው፤ አድማጭ አስፈጻሚ ህጋዊ አካል ከሌለው እንደ ግብጽ፤ እንደ ሊቢያ
ባክኖ ነው የሚቀረው። አመስግኖ አክብሮ መነሳት ያስፈልጋል ለተገኘው የመደራጀት ዕድል ራሱ።
- · ፈተና።
ፈተና የጽናት መለኪያ ነው። እያንዳንዱን የፈተና መስመር በትእግስት ለመወጣት መዘጋጀት ይገባል። በራስ ውስጥ ሆኖ እንጂ
የሌሎችን ተልዕኮ ለማስፈጸም በመትጋት ፈተናን ለመቀበል መዘጋጀት በፍጹም ሁኔታ የኪሳራ ወንጀል ነው። ይህ አዲስ ድርጅት ለተደራጀበት
ትልዕኮ ብቻ በነጠረ መንገድ ጉዞውን አህዱ ማለት ይኖርበታል። በፊትም በኋዋላም፤ በጀርባም፤ በሚታዘሉ ማናቸውም ጉዳዮች ላይ ዘው
ማለት አይኖርበትም። ለምሳሌ ከሌላ ብሄራዊ ፓርቲ የነበሩ ሰዎች አባልነት ቢጠይቁ፤ ቢመጡ ቢቀበል የአንድነት ፓርቲ የገጠመው ዕድል
ይገጥመዋል። እንደ እኔ እንደ ሥርጉተ ሥላሴ ከዚህ ቀደም ዬትኛውም ድርጅት አባል የልሆነ ንጹህ መንፈስ ያለው ለዛውም በአማራነቱ
መከራን በመቀበል፤ ኑሮው፤ ትዳሩ፤ ቤተሰቡ የተፈናቀለ ከአማራ ተጋድሎ ፍሬዎች ውስጥ መብቀል አለበት ባይ ነኝ። 20 ሺህ ወጣት
ታስሯል። በርካቶች ተሰውተዋል። ስለዚህ የመከራው ቤተኛ ለመከራው ጸንቶ ለመቆም ዋናው ማገር ሊሆን ይገባል ለድርጅቱ።
በዚህ ውስጥ የማይረሳው አውራው ማንነትም ኢትዮጵያዊነት አብሮ እንዲኖር ከልብ መፍቀድ ሌላው አደራዊ ተልዕኮ ነው። ድመቅትም፤
ክብረትም፤ ውበትም በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ነው ያለው እና። ከዚህ ከተወጣ አይቀናም። አላዟሯ ኢትዮጵያ ከነከብሯ፤ ከነማዕረጓ በውስጥ
እንደ ታቦት መታዬት አለባት።
- · እዮባዊነት።
በጥቁር ልብስ ጥቁሩን ዘመን በጥቁር ዕንባ ለመሻገር እዮባዊነትን
መሰነቅ ያስፈልጋል። ማናቸውንም የሃሳብ ልዩነት ከዛ መከረኛ ህዝብ በላይ ሰለማይሆን ለእሱ ከሆነ መደራጀቱ በርግጥም እንደ
ሥሙ ሁሉ አብን ፈላጊ ከሆነ የሰከነ፤ የበሰለ፤ የታገሰ፤ ያዳመጠ፤ ያሰተዋለ፤ ጥላቻን የተጸዬፈ፤ ቂምን ያገለለ፤ ቁርሾን የተጸዬፈ
ሁሉንም በፍቅሩ አሸንፎ ዓለማውን የሚያሳከ ብቁ ተልዕኮ ያለው ድርጅት አድርጎ ማውጣት ይጠበቀብታል። አንድ ነገር ሲመሠረት ከተበላሸ
አበቃ። አንድ ሥም አንድ ጊዜ ተገድፎ ከወጣ በዛው ነው የሚቀጥለው። ስለዚህ ሊያደርግ በሚችለው፤ በግልጽነት፤ በቀጥጠኝነት ዓላማውን
ግቡን፤ ፖሊሲውን ይፋ ማድረግ አለበት።
እኔ አዲስ ፓርቲ ሲፈጠር ለመጀመሪያ ጊዜ ነው እንዲህ ተሎ አስተያዬት የሰጠሁት። አድርጌ አላውቅም እንደዚህ። ምን አልባት
ራህበተኛ ስለሆንኩ ሊሆን ይቻል ይሆናል። አላውቅም። ይህ ለእኔ ደፋር እርምጃ ነው። ስለምን? እጅግ ዘግይቼ ስለሆነ አስተያዬት
የምሰጠው። አሁን ግን ለክቡር ጠ/ሚር አብይ አህመድም አብይ ሆይን! ስጽፍ ያስገነዘብኩት ስለሆነ በማግስቱ ይህ ሲመጣ መንፈሴ የሚያርፍበት
እራፊ ስላገኘሁ ይሆናል።
- የቁርሾ ራህብተኛ አለመሆን።
የነበረውን፤ ያለፈውን ነገር በማንሳት በመጣል ለድል አይበቃም። በፍጹም። መከራው ዕውን ከአንጀት ገብቶ ከሆነ በተግባር
ለዛ ባላቤት ለሌለው ባይታዋር ህዝብ ዕውነተኛው የድምጽ ማዕከሉ፤ የውስጥ ልሳኑ፤ የነፍሱ አንደበቱ፤ የኑሮ ድምጹ ሆኖ መገኘት ነው
ጠቃሚው ነገር። የራስን ተግባር መሥራት። የመንግሥትን በሚመለከት ወኪሎች አሉበት፤ የሚዲያውን ሥራም በሚመለከት ተንታኞች ጋዜጠኞች
አሉበት የሚከፈላቸው። የእናንተ ሥራ ማደራጀት እና መደራጀት ነው። ቀጣዩ ጹሑፌ በማደራጀት ዙሪያ የምለው ይኖረኛል።
- የስለት ልጅነት።
ሰፊ ማሳ ለመሆን በሰፊ ልቦና ለዛሬ ሳይሆን ለቀጣዩም የአማራ ተጋድሎ ተከታታይ መስመር የሚያስዝ በነፍስ የደረሰ ድርጅት
ስለሆነ አብን እጅግ ስክነትን ከእያንዳንዳችሁ በግል ከሁላችሁም በጋራ ሁላችንም እንናፍቃለን።
- አደራ
ድርጅቱን የብሶት፤ የራሮት፤ የዋይታ፤ የምሾ፤ የብሶት አደባባይ እንዳታደርጉት - አደራ። ለዚህ ለተጋፋ ህዝብ ቅርበት
በሌላቸው አጀንዳዎችም ላይ ቆራጣ ቀልብ መስጠት አይገባችሁም። ያን አንጋፋዎቹ ተፎካካሪዎች ይትጉበት። አማራ አገር እንዲኖረው ያሰፈልጋል፤
አማራ እኩል ዜጋ ስለመሆኑ የተግባር ማህተም ህጋዊ ዕውቅና ያስፈለገዋል - የለበጣ ያልሆነ፤ አማራ በቁመናው ልክ የፖለቲካዊ፤ የማህበራዊ፤
የኤኮኖሚያ ተጠቃሚነት እንዲዲሆን ከሰብዕናው መነሳት ያስፈልገዋል።
አማራዊ ሞራል ማለት ነው። ለዚህ ሁሉ ሃላፊነት ደግሞ በሌሎች
አጀንዳ እዬገቡ አቅም በመሸለም ሳይሆን መከራ ተኮር በሆኑት አብይ አጀንዳዎች ዙሪያ መሆን አለበት ተጋድሎውን
መታለም ያለበት። አቅሙ ገና ጮርቃ ስለሆነ ሁሉም ላይ አለሁኝ ቢል ይዘብጣል ዋንኛው ትልዕኮውም ይከስማል። አብን … አቅሙን ለክቶ
መነሳት ይኖርበታል።
- ጊዜው ከኖረ እነኝህን ይምጡልን ይላሉ …
Kebete (ቀንበጥ)
Seregute Selassie YouTube
- ደስ ብሎኛል መልካም የሥራ ዘመን!
"አማራነት ይከበር!"
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ