ልጥፎች

ጉደኛው መሪያችን።

ምስል
ጉደኛው መሪያችን ( ዶ / ር ዘላለም እሸቴ ) June 8, 2018 ምን እንላቸዋለን ? ከአሁን በፊት መሪዎቻችንን ለመግለፅ የተጠቀምንባቸውን ቃላት ሁሉ የሚያልፉ ሆኑብኝ። ጉደኛ የሚለውን ቃል የመረጥኩት፥ ያልተለመደና ያልታየ ነገርን ስለሚገልፅ ነው። በሌሎች ስንቀና የኛም ተራ ደርሶ ይሆንን ? ደቡብ አፍሪካ ማንዴላ ነበራት፤ ሕንድ ማህተመ ጋንዲ ነበራት፤ አሜሪካ ጆርጅ ዋሽንግተን ነበራት። ኢትዮጵያ ዶ / ር አብይ ደረሰውላት ይሆን ? ፋታ እንስጣቸው እያልን ስናወራ፤ እርሳቸው በድርጊታቸው አንዱን ሳናጣጥም ሌላ እየጨመሩ በመልካምነት ፋታ አሳጡን። ቀድመው ያሞገሱትን ማማት ይቸግራል ብለን፤ ተስፋን በስጋት ሰንቀን ዳር ቆመን በጥርጣሬ የምናይ ሁሉ ጉድ ፈላብን። ዛሬ ዛሬ ተስፋ ስጋትን እያሸነፈ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ለዶ / ር አብይ ድጋፍ እየጎረፈ ነው። ትላንት እንዳንጨራረስ እየፈራን ከዚህ አጣብቂኝ ማን ያወጣናል ስንል ነበር። የማይታለፍ የለም ያ ታለፈና፤ አሁን ዶ / ር አብይ በፍቅርና በይቅርታ ሁሉንም እየማረኩና እያስደመሙ፤ በደስታም እያሰከሩ በሚገርም አዲስ አካሄድ ኢትዮጵያን እያሻገሩ ይገኛሉ። ግን ቆም ብሎ ለሚያስተውል፤ ይህ ትዕይንት ከስጋና ደም ስራ በላይ ነው። የኢትዮጵያ አምላክ በምህረት እርሱ ራሱ ምድራችንን በፈውሱ እየጎበኘ እንደሆነ ለአስተዋይ ሰው ምንም ጥርጥር የለውም። አምላክ ደግሞ በስራ ላይ ሲሆን፤ ጠላት ለማሰናከል ሙከራ ያደርጋል እንጂ ፈጣሪን ያደናቅፈዋል ብሎ ማሰብ ሞኝነት