ልጥፎች

የእኔ ትእግስት።

ምስል
                    የእኔ ትእግስት ስናፍቅሽ ወይንስ ስመኝሽ                      እሙዬ የትኛው ሥም ይሻልሽ ይሆን?                                      ከሥርጉተ ሥላሴ 05.06.2018 (ከጋዳማዊቷ - ሲዊዘርላንድ።)             „እግዚአብሄር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከአፉም እውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤ እርሱ ለቅኖች ደህንነትን ያከማቻል፤                 የፍርድን ጎዳና ይጠብቃል፤ የቅዱሳኑንም መንገድ ያጸናልና። ( መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፪ ቁጥር ከ፮ እስከ ፰ ) ·          በር። አቶ ዛሬ እምር ብሎበት ነበር የዋለው በገበርዲን በከረባት ሽቅርቅር ብሎ ወሸቤም የቆዬ መስሏል። ንግሥቲቱም ፏ ብላ በሠረገላ ተኮፍሳ አገር ምድሩን እያፍነከነከችው ነው። እልፍኟ ኑብኝ ይላል። አልባብ ባልባብ፤ ታዲያንላችሁ ሥርጉትሻ ምኗ ሞኝ። እሷም የአቶ ዛሬን ግምጃ ቤት ለመታደም በልክ በሆነ ዝነጣ ወጣ አለች። ግን ምን አለ ሁልጊዜ እንዲህ ብትሆን ይህቺ የአውሮፓ ቅምጥል። ሰዉ ይስቀላ። ቀሎታል። ደስ ብሎታል። ታውቃላችሁ አይደለም? የሆነ አውሮፓ የሚጫን ደመመን ነገር አለው። ክብድ የሚል። ግን ዛሬ፤ ዛሬማ የእምዬን ያህል አምሮበታል። አድባሩ። ውይ ሳልነግራችሁ እነዛ ጥፍት ብለው የከረሙት ባለክንፎቹ ባንዳቸውን ይዘው ከች ለበጋ እረፍት። በጥዋት የቀሰቀሰኝ የእነሱ የንጋት ማህሌት ነበረ። ተዛንላችሁ ትንሺ ዘወርወር ብዬ መለስ አለኩኝ እና ወዜን አሳርፌ ማለት ነው፤ ያው የዘወትር የሀገር ቤት የዜና ኬወስክ እናቱ ይባል አባቱ ይባል ብቻ የአንጀት አድርሱ አይዋ ዩቱብን ከፈት ሳደርግ የምወድሽን ግኝት። ዛሬ ወግ በወግ ሆንኩኝ አይደለ … ብርሃን ደስ ይላል። በጠሐይ ጥንቢዝ ብሎ መስከር

ፍቅር ቁጥር አይደለም።

ምስል
           የፍቅር ተፈጥሯዊ መርህ                 ቁጥር አይደለም።                                          ከሥርጉተ ሥላሴ 03.06.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)                        „የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው። ሰነፎች ግን ጥበብን ተግሳጽን ይንቃሉ።“                                         (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፯) ፍቅር ቁጥር አይደለም፤ አንድ ሁለት ሦስት እዬተባለ በጥቁር ሰሌዳ ላይ በጠመኔ የሚጻፍ። ፍቅር መስፈሪያ የለውም። ፍቅር ዳርቻ ዲካ የለውም። ፍቅር ስፋት እና ቁመት የለውም። ፍቅር ቅርጽም ፎርምም ሊወጣለት አይችልም። ፍቅር አልፋ እና ኦሜጋ ነው። ፍቅር ነፍስ ነው። ፍቅር ደም ነው አብሮ የተፈጠረ። አብሮ የሚኖር። ልባም ከሆንክ ለትውልድ የምታወርሰው ቋሚ ቅርስ ነው። ትውልድንም የምታስቀጥልጥበት የህሊና ርስት ነው። ፍቅር ደም ነው። ቀዝቃዛም ለብ ያለም ሳይሆን ሙቀቱንም ቅዝቃዜውንም ለመለካት መሳሪያ ያልተሰራለት አንተም እራስህ የማታውቀው፤ ደረጃውን መመዘን መስፈር መመትር የማትችለው። ነገር ግን ፍቅር ተቀብሮ የኖረ የሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን ሳንጠቀምበት በመቅርታችን፤   እራሳችን ስናጠፋበት የኖርንበት የረቂቅ ሚስጢራት ቅምር ውጤት ሆኖ በተቃራኒው፤ ባልሆነ መንገድ ነው እትጌ ዓለም መጪ ስትል  የኖረችው። ወደ ሰው ሰብዕና ስንመጣ አንድ ሰው በልቡ ያለውን፤ ከደሙ ውስጥ ያለውን የፍቅር ተፈጥሮ የማያውቅ ፍጡር ከሆነ፤ አውጥቶ ለመጠቀም የማይተጋ ሰው ከሆነ የነቃው ህሊና ድፍን የሆነበት ሰው ነው። ይ