ዴሞክራሲ ለምላስ ጣፋጭ ነው፤ ከማርም ይበልጣል።

ምን እንሁን? እንዴትስ እንሁን? የትስ እንቁም?
„የእግዚአብሄር አምላክ እንዲህ ይላል፣
---- መንገዳችሁንና እና ሥራችሁን አሳምሩ፤“
ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ  ፯ ቁጥር ፫
በዚህም ሥፍራ አሳድራችሁ አለሁ“
ከሥርጉተ©ሥላሴ
26.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

  • ·      ፍታ።

ትናንት የጨለማ ቀን ነበር ለእኔ። ሌላው ወገኔ ምን ዓይነት ቀን እንዳሳለፈ አላውቅም። የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች አንደ ሥርጉተ የአቋም መግለጫ ከምለው የውሳኔ ሃሳብ ውህደት ብለው ይሻለኛል በንባብ አቅርበዋል። ከመንግሥት ሚዲያ OBN አለበት። ውሳኔ እንዳልለው የኦሮሞ ህዝብ ተወያይቶ ማጽደቅ ስላለበት ነው።

አሁን እኔ በመንፈስ ኢትዮጵያም የማውቃቸውን ክ/ አገራትን ሳስብ አብሶ ነገረ ጢቾ ይመጣብኛል። ጤቾ ሥርጉተ ሥላሴ ተዛወረች ብለው ሳምንት ሙሉ ከመደበኛ ሥራቸው የቀሩት የኦሮሞ እህቶቼ ሽው ይሉኛል። 

በእኔ ኦሮምኛ ጅማሮ ከትከት ብለው ይሰቁ የነበሩበትን ጉዳይ ሳስበው ውስጤ ይፈወሳል። በዬከተሞች ስሄድ እሚያቅፉኝ ወገኖቼን ጠረን አስታውሳለሁኝ። ጢቾን ስለቅ መኪናው ሲንቀሳቀስ ያስቆሙት ይመስል ከመኪናው ጋር አብረው የሮጡ እነዛ ብርቅ ወገኖቼ ይመጡበኛል። 

መዛወሬን ስነግራቸው ቢሮ ውስጥ ድብልቅልቅ ያለ ጩኸት ማሰማታቸውን ዛሬም አስበዋለሁኝ። ሰው የተረዱ እስኪመስል ድርስ ነበር የጮኽቱ። የሚገርመው ብክን ብለው እንደዛም እንደሆኑ ጥለውኝ ወደ ቤታቸው እንዴት እየከነፉ እንደሄዱ ይታዬኛል። 

ስለዚህም ሁልጊዜ ወደ ጢቾ ያለትኬት እጓዛለሁኝ። ዛሬ በሃሳብ ለመጓዝ ይከብደኛል። ይፈቀድልኝ አይፈቀደልኝ አላውቅም። ልብሱም ያለውን ፎቶ ልጠቀምበት አልጠቀመብት እንዲሁ? ኤርትራ እና ኢትዮጵያ መለያዬታቸው ምን ያህል ውስጤን እንደ ጎዳኝ ያወቅኩት የኤርትራ ልዑክ ቦሌ ሲረግጥ ያለፈቃዴ በወረደው ዕንባ ነበር። ምን እንሁን? እንዴትስ አንሁን? የትስ እንቁም?

ትናንት የጨለማ ቀን ነበር ለእኔ አልኩኝ። ያው ዕድሜ „ለኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ሽልማት ተስፋ የሰነቅኩበት ዘመን ነው ብዬ አስብ ነበር። ስለምን አሁን ጨለመ? የውሳኔ ሃሳቡን አልነካካውም። ከእኔ ይልቅ የኦሮሞ ወገኖቼ ምን እንደተሰማቸው እንሱ ይግለጡት። ከዶር አብይ አህመድ ከዶር ለማ መገርሳ ጀምሮ በእነሱ ያማራል። ምን ያህል በመንፈሳቸው ውስጥ አመክንዮው ፍሬ ነገር ቅርበት እና ርቀት እንዳለው አላውቅም። ብቻ እኔ እንደ ሎሬት መንፈስ ፈቃጅነቴ ዝም ብዬ እም ብዬ ባምጠው ይሻለኛል። 

አብሶ ስለ  ወጣት ቡንቶ በቀለ ብዙ ርቄ እስባለሁኝ። ይህች ቀንበጥ ምን ትሁን? እንዴትስ ትሁን? የትስ ትቁም? ምክንያቱም ቡንቶሻ ለእኔ ልዕልቴ ናት እና።
ወደ ጨለመብኝ ጉዳይ ስመጣ፤ የውሳኔ ሃሳቡ ውስጥ ለእኔ ህሊና የሚፈትን ነገር ተገልጧል። ልጻፈው አልጻፋው እያልኩ ነው አሁን እራሱ ሙሉ ቃሉን። 

በአግድሞሽ ልጻፋው „የ6 ዓመት ህፃን ኢ- ሰብዕዊ“ አገዳደል ሁኔታ። ማን ይህን ሰምቶ ከምግብ ጋር ይገናኛል? ማን ከመጠጥ ጋር ይገናኛል? ማን አቅም ኑሮት የዕለቱን ሃላፊት ሊወጣ ይችላል? እኔ አልቻልኩም ነበር። የፈልግኩት ቤቴን ጥዬ ብን ብዬ ለቅቄ መውጣት ነበር። 

ለመጀመሪያ ጊዜ በህይወቴ ሙሉ አድርጌው የማላውቀውን ብቻዬን አንድ ካፌ ቤት ሄጄ ቡና ይዤ ቁጭ አልኩኝ። አልጠጣሁትም፤ ከፍዬ ጥዬው ነው የወጣሁት። ስመለስ የሌላ አገር የኦርቶዶክስ ልጆች የጸሎት ቤት አለ ወደዛ አምርቼ እባክህ አምላኬ መንፈሴን መልስልኝ ብዬ ተማጸንኩት? ግን እናንተ ሊሂቃን የምትባሉ ሁሉ፤ በሙሉ ምን ያህል በነፍስ ወከፍ መንፈስ አልባ እያደረጋችሁን እንደሆን ይታወቃችሁልን? ለዛውም እኔ ሥልጠናዬ ፈተናን ማስተናገድ ለሆንኩት ነው ይህን ያህል የከበደኝ።፡

የስደስት ዓመት ልጅ እንደዛ የክርስቶስን ስቃይ ሲቀበል፤ ለመሆኑ ፖሊስ የት ነበር? መንግሥት የት ነበር? እናት የት ደረሰች? የት ተቀበረ? በምን ሁኔታ ነበር የአቀባባር ሥርዓቱ የተፈጸመው? ሥሙ ማን ይባላል? በዬትኛው ቤት ይገኝ ነበር? ት/ ቤት ገብቶ ነበር ወይ? ጓደኞች አሉት ወይ? ጎረቤት የለም ወይ? ዛሬ ሁሉም ጋዜጠኛ ሆኗል አንድ ሰው እንኳን እንዴት ሳይዘግበው ቀረ? ስለምን እስከ አሁን ተዳፈነ? 

እኒያ አንጀተ ሰፍሳፋው ዶር አብይ አህመድ፤ ዶር ለማ መገርሳ አስችሏቸው እንዴት ዝም አሉ? ስለምንስ ቀብሩ ላይ አልተገኙም ዶር ለማ መገርሳ? ዶር አብይ አህመድ ስለምንስ ለእናቱ አልደወሉም? ቢያንስ ቀብሩ ላይ የህግ ሙሁሩ አቶ ታዬ ደንኣ እና ወደ አገር የገቡት ሚዲያዎችስ ቤተሰባቸውን ለማጽናናት ቃለ ምልልስ ለማድረግ ስለምን አልደፈሩትም? ማለቴ የግዛት ክልሉ የእነሱ ስለሆነ።  
እርግጥ ነው ሻሽመኔ ላይ ሃፍረትን አዋራርደናል፤ ያን ግዜ ዶር ለማ መገርሳ ይሁን ዶር አብይ አህመድ የነበሩበት ሁኔታ ለእኔ የሚመች ሁኔታ ላይ እንዳልነበሩ አስብ ስለነበር ይት ሄዱ እያልኩ እጽፍ የነበረበት ወቅት ስለነበር አልፈረድም። 

ግን በወቅቱ አቅም የነበረው የኮሚኒኬሽን ሚ/ር ስለምን መግለጫ አልሰጠም? ያ ሰው ያ የሻሸመኔ ወጣት የማን ወገን ነው? ገማናውስ የማን ነው? ሃፍረቱስ የማነው? ይህ ኢትዮጵያዊነት የሚባለው ልጥፍ ካልሆነ የሚሆነው ነገር ሁሉ የሁላችንም የምናፍርበት ታሪካች ነው። ሃፍረትን እንደ ጌጥ ካላዬን በስተቀር በወገን ሰቆቃ ላይ ቆመን የተሻለ ተስፋ መጠበቅ አይቻልም እና።

የአሁን የ6 ዓመት ታዳጊ ወጣት በአገሩ መሬት ላይ ይህ ከደረሰበት ሊቢያ ላይ ወገኖቻችን ቢታረዱ ስለምን ይጨንቀናል? ስለምንስ ሻማ አብርትን ምሾ እንደረድራለን? እንደዛ ሳውዲ ላይ ሴት እህቶቻችን በአደባባይ ሲዋረዱ ስለምን ቀፎው እንደተነካበት ንብ ሆ ብለን ወጣን? 

ስለምን የዚህ ታዳጊ ወጣት አሰቃቂ ግድያ የአዲስ አባባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሩስ? የኢትዮጵያ መንግስት የኮምንኬሽን ሚሩ ትናንት  አቅም ስላልነበረኝ ዛሬ አዳምጫለሁኝ፤ ከዛም የለም። 

ከመግለጫው ጭብጥ ውስጥም የለም? ስለምን እንዲህ ዘግይቶ ወጣ? የትስ እንቁም? ማነው ምንድ ነው ስለምንድን ነውስ እዬታገልን ያለነው? ምንድ ነው ቅደመ ድርድሩ? አሁንም ወንበሩ ባዶ ነውን?

በወያኔ ሃርነት ትግራይ አውራ ፓርቲነት ዘመን በቀን ሦስት ዝብርቅርቅ ሙርቅርቅ መግለጫ የተለያዬ እንሰማ ነበር። አሁን መሰሉ ለዛውም በአብዩ ክህሎት ልክ ሊታሰብ የማልታገሳቸው የአምክንዮ ዝብርቆች እያዳምጥኩ ነው። 

የመረጃ ዝርክክርክነት እየታዬ ነው። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሸነሩ አዲስ አባባ ላይ የታሰሩት በፖለቲካ መስመር ሳይሆን ወንጀል አድርገው አቅርበወልናል „ሺሻ፤ ጫት፤ ቁማር“ የሚባል አዲስ ፓርቲ ተመሥርቷል ብለውናል ያውም ጣሪያ በነካ የበቀል ስሜት። 

የመንግሥት የመረጃ ምንጭ የሚባለው የመንግሥት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ ደግሞ „ጸረ ለውጥ ሃይሎች“ ነው የሚሉን። እራሱ አካሄዱ „ለውጥ“ የሚለውን ታላቁን የፍቅር ሞገድ ይሞግታል።

የአዲስ አባባ ፖሊስ ኮሞሽነሩ ሺሻ ቤት አሳዳጆች፤ ቁማርተኞች፤ ጫተኞች፤ ዘራፊዎች በጥቅሉ የደረቅ ወንጀል ዝንባሌ አለበት፤ አርባምንጭ፤ ጎንደር፤ እና ወሎ ተጠቅሰዋል። ሌላ ቦታ ወንጀል እና ወንጀለኛ የለምንስ? አሁንም እንደለመደብህ አማራ ጠብቅ! ዓይነት ነው።  

እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ድርብ አንጎል ካለው ከአብይ ሌጋሲ ይህን አልጠብቅም እንደዚህ ዝብርቅርቅ - ዝርክክር - መላ ቅጡ የጠፋ ውጥንቅጥ እና ሙርቅርቅ ጉድ እኔ ከአብዩ የብቃት ደረጃ ጋር ፈጽሞ ሊጠጋልኝ አልቻለም። ያ ብልህ ሰው የት ሄደ? 

እዚህ የቢሮ አደረጃጀቱን መመልከት ይቻላል። ለአገር ባለውለታዎች ያለው ጥልቅ አክብሮት ይታዬል። ሽልማቱን እንኳን እራሱ ወርሶ ነው የሚሰጠው።

Ethiopia - የመወድስ ግጥም ለዶ/ አብይ አህመድ

ይህ እኮ ነው አብዩ ማለት።

ውዶቼ ቀጣዩን ሊንክ ቃለ ምልልሱን ተውት የውጪውን ግቢ እንዴት ኢትዮጵያዊነት ጠረን እንዳለበት ብቻ ሳይሆን በምን መንፈስ እንደ ተደራጀ ተመለከቱት፤ ለታሪካችን አዲስ ምዕራፍ ነው።  እኔ እንደ ሌሰን ያጠናሁት አብዩ ይህ ነው … ከዚህ ውጥንቅጥ ጋኔል ከሠፈረበት የለውጥ መከራ እንዳ አናንያን፤ አዛርያን ሚሳዬል ከእሳት እንደ ተጣሉ ተቀቀልን ከመባሉ በፊት …

ጠቅላይ ሚንስትር / አብይ አህመድ በቀድሞ የስራ ባልደረቦች አንደበት ሲገለጹ


አብዩ እኮ የተለዬ ሰው ነው - ለእኔ። በፍጹም ልቤ የምሳሳለት። ታናሽ ወንድሜ በሆነልኝ የምለው። አዱኛዎቼ - ከልባችሁ ሆናችሁ። 

የኤርትራ እና የኢትዮጵያን ግንኙነት የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂን አቀባበል በቤተ መንግሥት የነበረውን የቡና ሥርዓትም በምልስት ቃኙት - እሰቡት። አደራጃጀቱ አወቃቀሩ ሃላፊነት የሚሰጣቸው ሰዎች ትጋት እና ስኬት። ታታሪዎች  የእናመሰግናለን ስርዓት ሁሉ። በመንፈሱ በአካሉ የተደረጃ ብቻ ሳይሆን የተረጋጋ ሰው ነው። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ባልተመደ ሁኔታ ቅን ሰው ነው። መንፈሱ ሰው አብዝቶ ያምናል።

እና በአፍሪካ መዲና፤ የአፍሪካ የመንፈስ አህታዊነት የመደመር ህልመኛ የአብይ ሌጋሲ መቀመጫውን በአዲስ አባባ መናህሪያው ያደረገውን እንዴት ይህን ቅጥ ማስያዝ ይሰናዋል? ለጸሐፊ ምስባዕከ ወርቁ ህመም የተጨነቀ ሰውኛ መንፈስ? 

ለአብይ አይደለም ይህቺ ጉዳይ በዓለም አቀፍም መድረክ ያላወጣቸው ቅምጥ ሃብቶች አንዳሉት፤ ያልተደመጡ ምርጥ ሃሳብም በህሊናው ማህጸን ለምተው እንደ ተቀመጡ፤ ለትልሙ የአፈጻጻም ስልት ምህንድስናም የማይዋስ፤ የክህሎት ፈጠራም ጥበብም የማያጣ ካለዘመኑ የተፈጠረ ሙሴ ነው። በዚህ ግንባሬን አላጥፍም። ግን አቅሙን ሥራ ላይ ለማዋል ምቹ የአዬር ጸባይ ነው አለው ወይ?

የዚህ ሁሉ ትርምስ ምንጩም ቅምጥ ያላዬናቸው አቅሞቹ ተደናቅፈው እንዲቀር ምቀኝነት፤ ሸር እና ተንኮል ሠራሽ የቅናት ገማና ነው። ያው እኛ በአካባቢያችን እንዴት ተቀብረን እንደ ቀረን እኛን የሚያውቁ ሰዎች የሚመሰክሩት ሃቅ ነው።

 እንኳንስ ለዛ ቦታ እና ደረጃ። ትቢያ ላይ እንኳን አንድ ሰው ስሌላው ቅንነት መናገርን አይደፍራትም። የሚፈለገው ለፈስፋሶች፤ አቅመ ቢሶች ፊት ለፊት ወጥተው አፍሪካ ተቀብራ እንድትቀር፤ ከኦሮሞ ማህበርሰብም እንዲህ ያለ ዕፁብ ድንቅ ፍጡር የኮከብ ኮብ የሆነ ፍጡር መኖሩን ያመማቸው ሴራ ስለመሆኑ ይገባኛል። በውነቱ የኦሮሞ ሊቃናት ኮራንብህ! አኮራን አብይ! ብላችሁ ደፍራችሁ መናገር ትችላላችሁን? ምነው በአቦ ዳውድ ኢብሳ አቀባባል ላይ ይህ የሚያኮራ ወገን ምስል ማዕቀብ ተጣለበት?

ይህ ሆኖ ነው አሁን በአዲስ አባባ የፖሊስ ኮሚሽነር እና የማእከላዊ መንግሥት ቃል ወጥ ሊሆን ያልቻለው ስለምን ይሆን? የደረቅ ወንጀል እስር እና የፖለቲካ እስር ይለያል። ሌላው ቀርቶ መኖሪያ ፈቃድ እዚህ ሲኖር በሰብዕዊነት የሚገኘው እና በፖለቲካ የሚገኘው እኩል ከፍታ የላቸውም። በህግ አግባብም፤  በአምክንዮ የጥራት አቅምም እንዲሁ። 

በችግሩ አፈታት ዘዴ እና በችግሩ ምንጭ አነሳስም ከመሰረቱ ልዩነት አለው። የአብይ ሌጋሲ ደራጃውን አልተጠበቀም ማለት እችላለሁኝ። ይህ የዘበጠ ነገር ዕሴቱን ያወርደዋል። ለኪናዊ አመራር ታሪኩም ጥሩ አይደለም። ሊንኮቹ መጨረሻ ላይ አሉ።

በድርጅታዊ ሥራ ፖለቲካ ውስኔ መስጠት እንዲህ ካስፈለገ የአዲስ አባባ ፖሊስ ኮሚሸንሩ መግለጫ አያስፈልግም ነበር። ይህ ከተሰጠ በኋዋላ ቢያንስ ዝም ማንን ገደለ። ተደጋገመ ይህ ነገር። ለዚህ ነው እኔ ቆሞስ ስመኛው በቀለን እራሱን ገደለ መግለጫ ምነው ቢቀር፤ ደረጃውን የጠበቀ ዝምታ መልካም ነበር ብዬ የጻፍኩት።

 ተስረክራኪ ጉዳይ ካለ፤ ከመንግሥት በላይ የሚፈራ ሌላ ቅጥያ አካል ካለ በቃ ዝም ማለት። እንደ ሻሸመኔው ገመና። የማንሸሸው ጥያቄ ምን እንሁን? እንዴትስ እንሁን? የትስ እንቁም? ዋዠቅን። ከሰመጠ መርከብ የመቀመጥ ያህል የራሳችን ህሊና እዬሞገተን ነው።
  • ·       ሞክራሲ ለምላስ ጣፋጭ ነው፤ ከማርም ይበልጣል።

ለዴሞክራሲ መታገላችን ራሱ የምናውቀው አይመስለኝም። ለመሆኑ ዴሞክራሲን በቤቱ ልምምድ ያደረገው ስንቱ ይሆን? እስኪ ቤት ውስጥ ሁላችንም ከሊቅ እስከ ደቂቅ ፊደል እንቁጠር። 

ለነገሩ አፍሪካን የድል ተቋም ከፍታ ነፃነትን የሳትማረች አገር ራሷን መምራት አቅቷት 50 የእልቂት መናህሪያ ናት። ለዜጎቿ የመኖር ነፃነት ነፍጋ በ ዓለም ዜጎቿን በማፈናቀል አንደኛ ደረጃ ወጥታለች።

እርግጥ ነው መባጃዋን የዓለም የዜና አምደኛ ሁና በአዎንታዊነት ወደ ፊት በመሪነት ስትመጣ አሁን ወደ ኋዋላ ደግሞ ተመልሳ እንደ ገና አንገቷን ደፋች። ራሳችን በፈበረክነው ችግር። 

ዕውነት ለመናገር የደቡብ እና የአሁኑ የአዲስ አባባ ችግር በእጅ የተሠራ ከነፃነት ፈላጊው እራስ የማያወርድ የጉድ ገደል ሲሆን፤ የኢትዮ ሱማሌ፤ የቤንሻንጉል የጋንቤላ፤ የቢሮ ሳቦታጅ ነክ ጉዳይ ደግሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ውስጣቸውን ባዶ ያደረገው የጸላዬሰናይ መንፈስ ያላቸው እነሱ የፈበረኩት ነው። 

ሲደመር ኢትዮጵያ አምጣ የወለደችው ልጅ ከምን ይመደብ ያሰኛል? አሁን „ ኢትዮጵያዊ ሰው“ ነኝ ለማለትም ይከብዳል። ወደ ቀደመው የዴሞክራሲ ጉዳይ ስመጣ „ሃሳብ መግለጽ“ መልካም ነገር ነው። ተፈላጊም ነው። እንናገር አልበረም ወይ ሙግቱ?  

„አይ“ ከእሺ በላይ አቅም አለው፤ ካልተፈራ። በለንደኑ ጉባኤ አቶ ሊበን የሚባሉ „ኢትዮጵያ ካልፈረሰች ኦሮምያ አትኖርም“ አሉ። ያን ጊዜ ከሁሉም ሚዲያ በጣም በጭንቀት በተደጋጋሚ ቃለ ምልልስ ህብር ራዲዮ ይሠራ ነበር። እናም ይህን መሰረት አድርጌ ከዚህ ስንኛ በኋዋላ ሌላ የሚነግሩን አዲስ አጀንዳ አይኖራቸውም እባካችሁ አትድከሙ ብዬ፤ ሃሳባቸው ቀጠለም ሃሳባቸው ወደቀም የመጨረሻ ቀኑ ነው ብዬ ጻፍኩኝ። ሌሎች ጸሐፍት ካዩበት የስጋት አንጻር አይደለም የእኔ ግንዛቤ። የማይቀጠሉ እዛው ከ አንደበት ሲወጡ ደርቀው ይቀራሉ። 

ፕ/ መስፍን ወልደማርያም „በባዶ ሜዳ“ የሚልም የጻፉት ነበር።  በአማራ እና በኦሮሞ የመሰብሰብ ጉዳይ አስመልክተው። ይናገሩት -- ያውጡት --- ይወያዩበት ብዬ ይህንም የፕሮፌስሩን ሃሳብ ሞግቼ ጽፌያለሁኝ። 

አሁን እኔ ሃሳቦች መውጣታቸው፤ መንገዳችን ቢያጠራው እንጂ አያደናቅፈውም ባይ ነኝ። ይህን እንደ ክብርም እንደ ውርዴት የሚያዩት ወገኖቼ ሊኖሩ ይቻላሉ። ሃሳቡ ቀጣይም ይሁን ኢቀጣይ መሬት ላይ ህዝበ ውሳኔ ይሆናል የሚዳኘው።
የተደበቀ ነገር ነው ክፋቱ። ሚዛን ያስጠብቃል። ያስተምራልም። እምናባክነውን ጊዜም ይቆጥባል።  

ዝምታ ነው ቦንብ እንጂ እንዲህ መወጣቱ የሚያስፈልግ ነው። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግሩ እኮ ግልጽነት አልቦሽ መሆኑ ነው። ይህ ስለሆነ አንድ ሰሞን ተጋብተው የጫጉላ ሽርሽር ላይ የባጁት ሲለያዩ ደግሞ ያ ያገናኛቸው፤ ያስተሳራቸው ነገር እንደ ገና ጥያቄ ወስጥ አስገብቶናል ይላሉ? ትናንት ለምን? ዛሬ ለምን? ሲባል ግልጽነት ስሌለ ነው። 

አንድ ወቅት "ኦቦ ሌንጮ ለታን አምነዋለሁ" ሲሉ ፕ/ ብራሃኑ ነጋ ነግረውናል። ይህን ያህል መተማመኑ ከኖረ ስለምን ሦስት ሊቀመንበርት ኖራችሁ ተብለው ግን ሞጋች አልገጠማቸውም፤ ለዛ ወቅት ብቻ … ነበር የልብ ልብ የመሆን መንፈስ መፍጠሪያ ነበር። በተደጋጋሚ የኦነግ  መሥራቾች እንኳን ወደ ኢትዮጵያዊነት መጥተው የሚሉ መግለጫዎች ይሰጡ ነበር፤ እያንጠለጠለን የተውናቸው ጉዳዮች ናቸው ዛሬ ተስፋን እያመሱ ያሉት። እዛው ላይ ፍርጥ ቢል መልካም ነበር። መከራችን አናራዝመውም። አብሶ ኦዴፓ ግልጽ ሆኖ መቅረብ ያለበት ይመስለኛል። 

የሚደንቀኝ ዛሬም ይኸውን ትውና አያለሁኝ። ሊሂቃኑ ግልጽ ሰለማይሆኑ ለህዝቡ ትናንት እንደግፋለን ዛሬ ደግሞ ወቃሽ እንሆናልን። ስለዚህ እኛ የምነለውን መደገፍ አለባችሁም ይላሉ። 

በግለሰብ ደረጃ ቢሆን ምንም አይደለም በተቋም ደረጃ። ከፍ አድርገህ አገር አስልፈህ አጅብኽ አጨብጭበህ የከበከብከውን፤ ስተወረወረው ስንት መዋለ መንፈስ ስንት የገንዘብ አቅም ከመፍሰሱ በፊት የሃሳብ ድርጁነት አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜም እንደምለው የለውጡን ፍላጎት ከፍ እና ዝቅ አድራጊው ወጀብ ንፋስ መሆኑን ያመሳጥርልናል። 

መውቀስ ያለብን እኛን እራሱን ነው። ላልተደራጀ፤ ላልበሰለ በቅጡ መሬት ላልያዘ መንፈስ ስለ አባከነው ማናቸውም ነገር እኔ ቀዳሚ ተጠያቂ ነኝ ማለት ይገባል። ትናንት ዕውቅና በገፍ እንሰጥ እና ዛሬ ደግሞ ነቃፊ እንሆናለን። 

የሚገርመው እውነቱን የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደው መባሉ ነው። አቅም ሳይኖር አገር እንመራለን ብሎ ትውልድን ማባከን አይገባም። አቅም ማለት ደግሞ ውጥኖች እርሾ መሆን እያቃታቸው በዬወቅቱ ሲንጠባጠቡ ችግሩ የእኔ ነው ማለት መቅደም አለበት። ስንት ጊዜ ይወደቃል? የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጅዋጅዊቱ ይኸው ነው።

ትናንት በአደባባይ መጸሐፍ ጽፈህ አማራ ይደራጅ ብለህ ዛሬ ደግሞ ህዝብ ብሄራዊ ሰንዴቄ ሞቴን ብሎ ሲመጣ ደግሞ የዛን ካባ ለብሰህ ደግሞ ሞቴን ከሰንደቄ፤ ሞቴን ከአንድነት ጋር ያደርገው ትላለህ። ትናንት እስከ መገንጠል ብለህ ዛሬ ደግሞ የመገንጠል አንቀጽ ይሰረዝልኝ ባይ ነህ፤ ትናንት የጎሳ ፖለቲካ ቢያራምዱም ለዚህ ጊዜ ያስፍለጉኛል ብለህ ከብክብህ እጬጌ አድርገህ እስከ ውጪ መንግሥታት ድረስ መስክረህ ዕውቅና አስጥተህ ዛሬ ደግሞ ትኮንናለህ። ግን አንተ ማነህ ማንስ ትሰኛለህ? 

በዚህ መከረኛው ትውልዱ ነው የሙከራ ጣቢያነት አክተሮቹ የሚተውኑት። ለዛውም ዘመኑ የአዲሱ ነው።  ለዚህ ነው „አፍንጫህን ላስ አቶ ሂደትን 2013/2014፤ እጬጌው ሂደትን በ2018“ እኔ የጻፍኩት። ውዶቼ ጹሁፎቹ እዚኸው ብሎግ ላይ ስለሚገኙ ደግማችሁ ውስጤን ታገኙት ዘንድ  በአክብሮት ልጋብዛችሁ። 

የባከነው ትውልድ ለሊሂቃኑ ጉዳይ አይደለም። ስለሞተው፤ ሰውንቱ በቤንዚን ስለነደደው፤ በአደባባይ በመትረዬስ ስለታጨደው፤ አካሉ ስለጎደለው፤ እግሩ ስለተቆረጣው፤ ወጥቶ ስላልተመለሰው፤ ዓይኑ ስለጠፋው፤ ዘር ማፍሪያው ስለተንኮላሸው አይደለም ጉዳያችን አሁንም ያ አራት እግር ስላለው እንጨት ብቻ ነው። ኦሮሞ እንደ ግዝፈቱ አገር ይምራ ተበላ። ተሰጠው ሞጋቾቹ ደግሞ እነሱው ሆነው አረፉት። ዕድሜ ለግርባው ብአዴን እና እድሜ ልጅል እኔን መሰል አማራዎች ማለት ይገባ ነበር። 

በመንፈስ የሚበተነው፤ እንደጠላት የሚተያዬውስ ሌላ ስደት እኮ ነው እዚህ ያለው። እክሌ ይደርስልኛል የሚባልበት ሁኔታ የለም። ያን ያህል ቀን እና ሌት ጠ/ ሚር አብይ አህመድ አገር ውስጥ እና ውጪ የደከሙበት የአብሮነት ሌጋሲ ሰሞኑን አፈር ድሜ ግጦ እንጦርጦስ ገባ። ሁሉም ወደራሱ ጎጆ ገባ። ደጋፊ የሚባለውም እንዲሁ መንፈሱ ሁሉንም በፍቅር የማቀፍ ተልዕኮው ጦርነት ታወጀለት። መንፈስ መሰብሰብ እኮ ከባድ ነገር ነው። 

ለነገሩ የአዲሱ ካቢኔ የተወሰነ ሹመት ጊዜ እኮ አገር ውስጥ የሚገኙ የተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ወጥተው እኛ ሳንሾም ቀርን ዓይነት ቃለ ምልልስ ነበር ያደረጉት፤ እኔ እንዲያውም ከትትክት ብዬ ሳቅኩኝ እና ስሜቴን ጻፍኩኝ። አስቸኳይ ጊዜ ሲታወጅ ኡኡታ ነበር። ሲለቀቅም ኡኡታው ወደ ተግባር ተቀይሮ መሬት ላያ የተሠራ ተግባር አልታዬም። 

ቢያንስ እንደ ተፎካካሪ ፓርቲ ያልተመዘገቡት ለመመዝገብ እና ሥራ ለመጀመር አልደፈሩትም። ነባሮችም ከመግለጫ፤ ከዘጋበነት ያለፈ ተግባር አልጀመሩም። መድረክ፤ አገራዊ ንቅናቄ፤ ሸንጎ ታላቆቹ የህብረት ተፎካካሪዎች ነበሩ አሁን አንዳቸውም የሉም። አቅም ጨምሮ መጎልበት ሲገባቸው ፈርሳዋል። እኛ እንዲህ ነን? 

የኢትዮጵያ ፖለቲካ አፍሶ መልቀም ለቅሞ መፋሰስ። የሰው ልጅ ህይወት ምኑ ያልሆነ ለውጥ ፈላጊ፤ ግን ለውጥ ፈሪ፤ ለውጥ ለሚያመጣቸው ጎርበጥባጣ ነገሮች ምቹ መንፈስ ያላሳናዳ ….  

ህብር ነን ያሉት ህብረቱን እዬተው በተናጠለ ሌላ ህብረት እዬፈጠሩ ነው። የሚያስዝነው ከዚህ አልበቃ ብሎ ለዛ መከረኛ ትውልድ የካቴና ራትነትም አሁን እስጠገባ ላይ ናቸው …
  
እነሱ ሲፈርሱ እና ሲሰሩ በመሃል ተጎጂው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። በተደሞ የባጀው የአዲስ አባባ ህዝብ በሚመለከት ብሄር አልቦ ነው። ብሄር አልቦ ነው ሲባል "ድህነት ዜግነቴ ነው" ከሚለው ጀምሮ አገሬ "አዲስ አባባ ነው"የተለያዩ እሳቤዎች ፍስፍናዎች የሚታዩበት የህብር ከተማ ናት አዲስሻ።

አሁን መከራን ታግሰው እንደ ኦሮምያ እና እንደ አማራ በተለይም እንደ ጎጃም እና እንደ ጎንደር በዚህ ሦስት አራት ዓመት በጥንቃቄ በዝምታ የቆዬው አዲስ አበቤ በአዲስ አባባ የከንቲባ ቢሮ  በሚመራው የፖሊስ ኮሚሸነር በጫትኛ፤ በሃሽሽኛ፤ በቁማርተኛ፤ በዘራፊኛ፤ መፈረጁ ሲገርመኝ አሁን ከመሼ ደግሞ በማዕከላዊ መንግሥት „በጸረ ለውጠኛ“ ተፈርጆ ለበለሃሰብ ተስጥቷል። 

መርማሪው አንድ ዓይነት ነው። የተቀዬረ ነገር የለም። ጉድጓድ ተቀብሮ ለኖረ አንበሳ ሥጋ እንደ መወርወር ማለት ነው …. ርቦታል እዬተስገበገበ ያሻውን ያደርጋል የስቃይ ቤተ ሙከራ የኢትዮጵያ ልጅ። ወዮ አዲስ አበባ ብዬ ነበር። የሆነውም ይኸው ነው። የደገፍህን ህዝብ ልጅ ወንድም ? ህም!

የአዲስ አባባ ህዝብ ንቅንቅ ብሎ ድጋፍ በሚመለከት ዶር አብይ አህመድን ደግፎ ወጥቷል። ሞቷል። ቆስሏል። አብይ የእኔ ነው ሲል ኦሮሞ ኬኛ! ኦህዴድ ኬኛ! ብሎ ነበር። ያን ጊዜ ሁሉም ይወክለኛል ያለውን ዓርማ፤ ይሁን ሰንደቅ ዓላማ ይዞ ወጥቷል። የኦነግም ዓርማ ወጥቷል፤ ባለኮከቡም ወጥቷል፤ ልሙጡም ወጥቷል። ያን ጊዜ ሁለም አብይ ነኝ ምልዕቱ፤ የተረፈውም ገዱ ነኝ፤ ለማ ነኝ ደመቀ ነኝ ነበር።

እርግጥ ነው አንድ የተረሳ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ደግሞ አለ። ለስላሳ እኔ ሁልጊዜ እምዘክረው ዶር አንባቸው መኮነን። እሱን ሥሙን  ከእኔ በስተቀር የሚያነሳ ሰምቼ አላውቅም። ግን ንጹህ ሰውነቱ ውስጤ የምለው ዓይነት ነው። ጎንደሬ ስለሆነ ነው እንዳትሉ ምን ጎንደሬ አክቲቢስት፤ ጋዜጠኛ፤ ተንታኝ፤ አስተዋዋዊ፤ የፖለቲካ መሪ እንዳሉም ታውቃላችሁ። ጓድ ገ/ መድህን በርጋ እንደ ነፍስ አባቴ እማነሳው ጎንደሬ አይደለም ይልቁንም ሽዌኛ ጉራጌ ነው።  

በዛ የ አብዩ የምስጋና እና የድጋፍ ስልፍ ላይ የዲያስፖራ ፖለቲካኞችን የያዙ ሁለት ፍሬ ፎቶ አይነተናል። አሁን ደግሞ ሌላ ዘፍን መጥቶ እያዬን ነው። እኔ እምወደው ከሆነ ስለምን አሁን ያን ጊዜም ለብሼው እወጣለሁኝ። በቃ!

የሆነ ሆኖ ሃሳብ እንደ ልብ እንዲገለጽ ከተፈለገ ይህን መሰል ሃርድ ቶክም መፍቀድ ግድ ይላል። ስንቱ ተፈርቶ ይዘለቃል? ሞጋች ሃሳቦችን ለመድፈር መሰናዳት ያስፈልጋል። ዴሞክራሲ የሰውን ተፈጥሮ ተጻሮ እስከ አልወጣ ድርስ የሃሳቦች ፍስት ቢጠቅሙ እንጂ አያጎዳም። አቅም ካልነበረው የአብይ ሌጋሲ ግቡ ብሎ መፍቀድ አልነበረበትም። አቅም ካልነበራቸው ተፎካካሪዎችም ለውድድር መሰናዳት የለባቸውም። ሁለት ሃሳቦች ጎልተው ወጥተዋል። አሁን ፊት ለፊት መሞገት ነው። ሽሽት ዘመኑ ቀብሮታል። ሚዛኑ ደግሞ ህዝብ አለበት። 

የታመቁ ያልፈነዱ ነገሮች አሁንም እንዳይኖሩ መንገዱ መከፈት አለበት። ከዚህ በኋዋላ የኦሮሞ ፖለቲካ መሪዎች ውስጣቸውን አሳይተውናል። የሚታገሉለትን የወል ፖሊሰያቸውን ዘርግፈውታል። የሃሳባቸውን ቀጣይነት ወይንም አይቀጣይነት ሂደት ይመለሰዋል፤ በአንሱም አቅምም ይወስናል። ማለት ሃሳባቸውን እንዲዘልቅ በሚሰሩት የሃሳብ ልዕልና ይወሰናል። ብሄራዊ መሪ ለመሆን ባለፈም አህጉራዊ መሪ ለመሆንም የውሳኔ ሃሳባቸው የስንኝ ፍሰት እና ጭብጥ ግዙፍ ስዕል ይሰጣል።

ለምሳሌ ግንቦት 7 ማዬት ይቻላል፤ የአማራ የህልውና ተጋድሎ ላለማለት የፈለገበት ዋንኛ እንኳር ጉዳይ  „አማራ“ ማለት ስለማይፈቅድ ነበር „የነጻነት ሃይል ያለው፤ ዘግዬት ብሎ ሲጠንክርበት ፋኖ“ ለማለት ተገደደ። አሁን የአማራ ልጆችን ደግፉኝ ልመና ላይ ነው ያለው ግንቦት 7። 

አውሮፓ ህብረት በነበረው የዕውቅና ዝና ግን አማራ ከመንፈሱ የተፋቀ ነበር። ወደፊትም ዕድሉን አግኝቶ መሬት ላይ ከተግባር ጋር በሚኖረው ፍትጊያ ይህ አፍቅሮተ አንድነት፤ አፍቅሮተ ብሄራዊ ሰንድቅዓላማ የሚታይ ይሆናል። አማራም ሰው ሆኖ በማዕቀፉ ከቁጥር ከገባም? ? ?

በነገራችን ላይ እኔን ፕ/ አስራት ወ/ደዬስም፤ ሞረሽም፤ የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎም አማራ ነኝ አላሰኘኝም፤ እኔ አማራ ነኝ እንድል ያደረገኝ እራሱ ግንቦት 7 ነው። ለዚህ ነው እኔ ግንቦት 7 ኢትዮጵያዊነትን የመሸከም አቅም የለውም እምለው። 

እኔን ገፍትሮ አማራ አንድርጎኛል “ለኔስ ሰው መሆን ይበቃኛል“ መርሄን ተጭኖ አማራ አድርጎኛል። በአድሎ፤ በግለት፤ በክትር፤ በድብቅነት ዓላማ እና ግብ ይዞ መነሳቱ አላወጣውም ዛሬ ላይ።

የሽግግር መንግሥት መሪነትን ከነሰንዱ በምዕራባውያን ድጋፍ ተሳክቶለት ቢሆን ኖሮ፤ አማራ ክልል ብሎ ወያኔ በሠራው ክልል ብቅ አይልም ነበር።  ሁሉም አለቀ እና አሁን ጨዋታው ሌላ ሆነ። 

አሁን አማራ መሬት ላይ ፊት ለፊት የቀኝ እጅ የተደረጉት የትኛው መድረክ ከግንቦት 7 ጋር በድርድር፤ በውሉ በታላላቅ ስብሰባዎች ላይ መግለጫ ሲሰጡ፤ ትንተና ሲያቀርቡ ተስተውለው የማያውቁት ነው የማዬው፤  ብቻ ይህ ልብጣዊ ጉዞ በፍሬም ላይ ያለ ውብ መልክዕምድራዊ ምስል ነው - ሰንባች አይደለም።

ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆነ ግንቦት 7 እግረኛውን አማራ ጎልቶ የጫጉላ ጊዜ ከኦነጋውያን ጋር ነበረው። ያ አከተመ። „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው“ ሞገዱን ቁጭ ብሎ አዬ። አሁን የዛ አቀንቃኝ ሆኗል። 

አብሶ የጠ/ ሚር አብይ ድጋፋ በአማራ መሬት ሆነ ሌሎች ቦታዎች ላይ የነበረው የሰንደቅ  ሞገዳዊ ትዕይንት ልቡን ሳብ አደረገው እና ያን መንፈስ መዳፉ ውስጥ አስገብቶ እዬተጓዘ ይገኛል። ይህ እስከ ዬት ያስኬደዋል? እንደ ተለመደው ነው። ለዛውም በሁሉም ዘንድ በጥርስ የተያዘ ድርጅት ስለሆነ መድረኩ ከተገኜ ነው፤ ከተግባሩ ቀጣይነት እና ሾላኪነት ጋር የሚመዘነው። 

በተመሳሳይ ሁኔታ የኦሮሞ ድርጀቶች ሊሂቃን ደግሞ የሚሰማቸውን ግልጽ አድርገው ተናግረዋል። የቀራቸው አንድ አውራ ጉዳይ ቢኖርም? ብቻ ከአነጋገር ይፈረዳል፤ ከአያያዝ ይቀደዳል እንዲሉ …  ይህ ሃሳባቸው የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም በቀጣይነት ያስጠብቃል ወይ? በሥልጣን፤ በፕሮቶኮል ቅደምተከተል ነገ አያፋለሱንም? በቀጣይ የምናዬው ይሆናል። ለዚህ ወቅት ግን ወጥ አድርጓቸዋል። 

አብሶ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የመጡት ከኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅት ስለሆነ ፈተናውን እዬከመሩለት ነው። እንዳይታመን ተግተው እዬሠሩለት ነው። ጥቅሙን የሚጻረር ተጠቃሚ ቢኖር በተፎካካሪ ሥም የተዳራጁት የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ብቻ ናቸው።  

የአብይ ሌጋሲ አፍሪካዊ ነኝ ባይ ነው፤ አዲስ ፍልስፍና ይዢያለሁ ባይ ነው፤  ኦዴፓ ተመስጥሮ ያለበት ሁኔታ በዬትኛው ማህለቅ ይሆን ቀዛፋውን በቀጣይ የሚያስኬደው? 

ነገ ኦዴፓ አገር እመራለሁ ቢል ምን ፈተና ይገጥመዋል? ቢያንስ ምዕራብውያን አሁን ላይ ምን ያስባሉ ለሚለው ከህሊናው የሆነ ልብ ይሻል። ነገ ከእነዚህ አምስት የ ኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥስ ብሄራዊ ደረጃ የሚደርሱት በምን የመንፈስ አቅም ልዕልና ይሆን ያሰኛል? ይህም ሌላው ሞጋች ሁኔታ ነው።

ኦዴፓን በሚመለከት ከመረጃዎቹ ወጣ ገብነት አንጻር እንደ አውራ ፓርቲነት ነገ በነፃ ውደድር የማሸነፍ እና የመሸነፍ ሳይሆን፤ በመንፈስ አቅሙ ልቅና ልክ የታሪኩ ጅረት በምን መልኩ ጸሐፍት ይመለከቱታል ነው ትልቁ ጥያቄ። 

ሻሸመኔ፤ ቡራዮ መዲናው ላይ አዲስ አሉታዊ ስዕል አለ …. ያን የመሰለ የሚሊዮኖች የቸርነት ፍቅር የተሰጠው ኦህዴድ/ ኦዴፓ መቋጫው ምን ይሆን? መልሶ ያገኘው ይሆን ያን ፍቅር? የፍቅር ዳግሚያ ትንሳኤ ርችት ይኖረው ይሆን? ለመሆኑ አማካሪው ማን ነው? 

የትናንቱ ኦህዴድ/ የዛሬው ኦዴፓ ለማንስ ነው ልቡን፤ አንጀት ጉበቱን ፏ ፍንትው አድርጎ ከፍቶ የሰጠው? በመንፈስ አቅሙ ልክ ለመንቀሳቀስ ምን አገደው? ርህርህናውን፤ እውነት ፈላጊነቱን፤ ቃል አሳሪነቱን፤ ተስፋማነቱን ምን ዋጠው? ተገዶ፤ በተጽዕኖ ወይንስ ግርዶሽ አስፈልጎት ኖሮ?

ለመሆኑ አንድ ግልጽ ጥያቄ አለኝ። ኦዴፓ „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው“ በመንፈሱ አለን? አቶ አዲሱ ረጋሳ ስለ አዲስ አበባ ራሷ የመወስን መብት አይኖራትም ዛቻ ጉዳይ ለማውያን ለሆነችው ብቸኛዋ ሥርጉተ ሥላሴ መንፈስ ገዳይ አይሆንምን?

 የጋሙ አባቶች እና የጣና ኬኛ የገዳ አባቶች ቡራዩ፤ ሻሽመኔ ላይ አልነበሩንም? የጣና ኬኛ የአብቹ ልዑካንስ የት ገቡ? እኔስ እላለሁኝ እማትፈጽሙትን ነገር አትቸጀምሩት። 

አሁን አዋሳ የሚሄድ የወጣቶች ቡድን እንደ ተደራጁ አዳምጫለሁኝ። የሚያስፈልገው የሚዲያ ጋጋታ፤ የፕርፖጋንዳ ክምር ሳይሆን የውስጥ ለውጥ። የዕምሮ አጠባ ነው የሚያስፈለገው። 
  
ለመሆኑ አሁን ከተሰጠው የ5ቱ የኦሮሞ ፓርቲዎችን የውሳኔ ሃሳብ ኦዴፓ፤ ብአዴን እንዴት ያዩታል፤ ጊዜያዊ ማፈግፈግ፤ ስልታዊ ቅምረት፤ ስትራቴጃያዊ ንድፍ የት ይሆን አሸናፊው ሃሳብ ፌርማታው? 

ወያኔ ሃርነት ትግራይ ስለቱ ሰምሮለታል። ዘንድሮ አክሱም ጽዮንን ያዬ፤ ለነገሩ ለካንስ ድርጅቱ ዕምነት የለውም። ይቅርታ!

የውሳኔው ሃሳብ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ፋሽስታዊ ማንፌስቶ ይምራን ሲል፤ የራሱን ዓላማ እና ፕሮግራም ምን ላይ እንዳስቀመጠው ግራ ይገባል። ከሁሉ በላይ በጥብቆ የተቀመጠው መንፈስ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ለውጪው ዓለም  „ኦሮሞ አገር የመምራት አቅም የላቸውም“ ያለውን ግጥም አድርጎ ፈርሞበታል፤ አትሞታል ፈቅዶል፤ ቃል አስሮበታል - ወዶታል።
  • ·       ሞና!

እያንዳንዳችሁ ሁላችሁም የፖለቲካ ሊሂቃን በሙሉ እናት አላችሁ እና እናታችሁን እሰቡ - በትህትና። የትም አይመጣም ልጅ። ልጅ በፋፍሪካ አይመረተውም። የሰው ልጅ እንደ እናንተ አሰተሳብ በማሽን እንደሚመረት ዶሮ ነው ያደረጋችሁት። ነገም የኢትዮጵያ እናት የሰው ብርንዶ ታቀርባለች። አሁንም እያቀረበች ነው።

አንዱ ጫተኛ፤ ሺሸኛ፤ ቁማርተኛ ሲለው ሌላው „ጸረ ለውጥ“ ይለዋል። ሌላው ቀርቶ የተገድል ውል ዕውቅና እንኳን መላ ቢስ ነው የሆነው። የተጋድሎ መልክ አድርሻ ቢስ ነው የሆነው። ለሰንደቃቸው ሲሉ ቢባል እንኳን ያስኬዳል።

የታሠሩት አዲስ አበቤዎች የብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ተጋድሎ ታታሪዎች ናቸው። ለዚህ ነው እንጅባራ ላይ ተንቀሳቃሽ የአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ከቀስት እናመልጥበት ዘንድ የላከው እዮር። 

በቀጣዩ ጊዜ የሰንደቅ ቀን እንሚከበር ተደምጧል። ምንም ውይይት አያስፈልግም እኮ ወይ የዲያቢሎስን መንፈስ ያለበትን ባለኮከቡን ወይንም ልሙጡን መቀበል። ከዛ ፍርዱ የእዮር ይሆናል። „ሰው የሚያጭደው የዘራውን ብቻ ነው።“  ለዚህ ብለው የታሰሩትም ሰማዕት ናቸው - ለእኔ። እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት የግድ የፖለቲካ ድርጅት አባል መሆን አያስፈልግም። አሁን ከውጭ የሚገቡት ሁሉም እንግዳ ናቸው። ምነው አገልግሎት ቅናሽ ሆኖ አልነበረንም? ስቃችሁ ተቀቡ ብላችሁ አልነበረምን?  

የሰይጣን ጆሮ ይደፍንና አሁን ኢትዮጵያን አንድ ሌላ አገር ቢወራት የቱ ሰንደቅ ይሆን ይዛችሁ የምትወጡት እንደ መንግሥት ኦዴፓዎች? ጥሞና የሚያስፍልግበት ወቅት ነው። እራቅ አድርጎ ቢሆን ብሎ ማሰብ ይገባል። የተሰበሰበው መንፈስ አሁን ደግሞ ጋሬጣ እዬተተከለበት፤ አረም እዬበቀለበት፤ መጠራጠር እዬሰፈነበት፤ ስጋት ጃሎ መገን እያለበት ነው ያለው። እንስከን!
  • ·       ርሻዬ።

ወንጀል የሚሠራ ልጅን ወላጆች ሃላፊነት አለባቸው፤ ወንጀል የምትሠራን ልጅ ወላጆች ሃላፊነት አለባቸው። ወንጀለኛ ልጅ ቢኖረኝ፤ አያድርግብኝ እንጂ፤ ኢሞራሊዊ ልጅ ቢኖረኝ ራሴ ነው አወጥቼ ለመንግሥት እጁን አንጠልጥዬ  የምሰጠው። ለእኔም አይጠቅምም፤ ለማህበረሰቡም አይጠቅምም፤ ለራሱም አይጠቅምም። 

ውስጡን እዬፈራ የሚኖር ልጅ ምን ያደርግልኛል? ማንኛውንም ሰውኛ ጉዳይ በጠላትንት የሚፈርጅ፤ ራሱን ውስጡን የሚፈራ ግለሰብ ብቻ ነው። ወይንም የበታችን ያለበት ነው። ወንጀለኛ ልጄን ብሸሽገው ወይንም ሽፋን ባደርግለት ራሱን ነው የምጎዳው። ትወልድ በዚህ መልክ አይቀረጸም። ፈጽሞ። ግድፈትን መሻገር፤ ጥፋትን ማውረስ ለማንም አይጠቅምም። ግድፈትን መገሰጽ እና የእኔ ብሎ መቅጣት ነው የሚበጀው። 
 
ሌላው ትወልዱ ማን ሮል ሞደሌ ነው ይበልለት? ሁልጊዜ መዋሸት። ሁልጊዜ መልቲነት። ሁልጊዜ ምቀኝነት። ሁልጊዜ የፖለቲካ ወገንተኝነት በአንድ ነገር እማንስማማ፤ የጋራ ጀግና የሌለን። ለእኔ ጀግና የሚባለው የሚሸለመው ካባ፤ የሚደረብለት በርኖስ፤ ወይንም ጋቢ ጀግናዬ ላይሆን ይችላል። 

ለሌላው ደግሞ ጀግናው ሊሆን ይችላል። ያ ጀግና ነህ ተብሎ ክብር የተሰጠውም ዕውን እኔ ጀግና የሆንኩበት መሥመሩ ምንድነው ብሎ ራሱን መጠዬቅ አለበት? በውስጥ የመኖር አቅም የለንም። በፍላጎታችን የመዝለቅ ዕሴትም የለንም።

 ለእኔን ንጹሃንን በዬተገኘው አጋጣሚ የሚያሳድዱ ብጹዕን አይደሉም። በንጹሃን ላይ የመሰከሩ፤ ያሳደሙ ብፁዑን አይደሉም። የተሰደዱት፤ የታደመባቸውም እናት አለቻቸው። ዕድሜዋን ሙሉ የምታነባ። ገባ ወጣ አያያዝ ስንቱን እንደሚያቆስል እዮር ይመስክረው።  
  • ·       ውነት ብቻ ነው ጀግና።

ለእኔ ጀግና የምለው ዕውነትን የደፈረ ብቻ ነው። ዕውነት እኛ ከመፈጠራችን በፊት የነበረ፤ ዛሬም ያለ፤ ወደፊትም የሚኖር ነው። ዕውነት ዘላቂ እንጂ ሟሻሽ አይደለም። ዕውነት ራሱን እንጂ ሌላን አካል አይወክልም፤ የእውነት ወገን እውነት ራሱ ብቻ ነው።  የእውነት ቤተሰብም እውነት ብቻ ነው። ዕውነት ቀለሙ ለራሱ ብቻ ነው የሚታዬው፤ ቅርጽ ሳይሆን ዕውነት ራሱን የሚገልጽ ይዘት ብቻ ነው ነው ያለው።

ዕውነት በእኛ ፕላኔት ሳይሆን በራሷ ፕላኔት ነው የሚኖረው። ችግሩም ይህ ነው። በአንድ ፕላኔት ለመኖር አለመቻላችን። ፍርድ እኮ የሙግት አቅም ባለው ተካራካሪ እንጂ በዕውነት አቅም ልክ አይደለም ፕላኔታችን እያስተናገደችው ያለችው። በፕላኔታችን አለ የሚበላው ፍትህ ጥሬ ቃሉ ብቻ ነው - ለእኔ። የሆነ ሆኖ አንድ ሰውም ሰው ነው፤ ቁጥሩ እራሱ የሞተው፤ የተፈናቀለው፤ የተጎዳው በትክክል አይገለጽም መንግሥት ባለበት አገር ለዛውም ዶር አብይ አህመድ እና ዶር ለማ መገርሳ በጥምረት በሚመሩት መንግሥት።
  • ·       ባለትራሱ የውሳኔ ሃሳብ።

የኦሮሞ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች የሰጡት የውሳኔ ሃሳብ ትራስ፤ ድልዳል የለውም ማለት አይቻልም። ህጋዊ ዕውቅና ሳይኖር አሁን፤ ለዛውም በዚህ የሽግግር ወቅት ይህን የውሳኔ ሃሳብ አያቀርቡም ነበር። እነሱን ወደፊት በማውጣት ጫና ስላለብን፤ ሌላም ሃስብ ያለው ከሳሽ፤ ተባዳይ ወገን አለም ለማለት ታስቦ የተከወነ ነው -  ለእኔ። ኪኖ ነው። ጉዳቱ የወል ነው። ውርዴቱም እያንዳንዳችን ቤት አንገት አስደፈቷል። መልካሞቹም የጋራ ኩራቶች የትውፊትም ዕሴቶች ናቸው እትዮጵያ አገሬ ለምንል ወገኖች። 

የሆነ ሆኖ ቡራዩ ችግር እናት አልባ ነው ሆኖ የሚታዬኝ። ያ የመከራ ማዕልት ጎዳና ተዳደሪ ሆኖ ነው የሚታዬኝ - ለእኔ። ጉዳቱን ባለቤት እኔ ነኝ የሚል ጠፋበት። ሃላፊነት የሚወስድ የለም። ልክ እንደ ዘመነ ቅንጅት ክስመት።  

ይህ የተናፈቀ፤ የተከበረ ተስፋ የተደረገ ለውጥ ሃላፊነት እና ተጠያቂነትን እዬሸሸ እያዬሁ ነው። ለዚህ ነው የመረጃው ዝግምት እና ዝገት፤ ወጣ ገብ እና ውይብነት እዬታዬ ያለው።

ምን እንሁን? እንዴትስ እንሁን? የትስ እንቁም?!

ብቻ ውዶቼ እኔ እንደ ማስበው እሰቡ እያልኩ አይደለም፤ ሌላው ቀርቶ አገር እስኪገባ የሚጠበቀው ግንቦት 7 ነው ስላችሁ ነበር። ባይሄዱ ስልም ተማጽኛለሁኝ፤ በእነሱ ምክንያት ከ97 ጀምሮ ያለውን መከራ እሰቡት። ዛሬ አባይ ሚዲያ ላይ አንድ ዜና አገኘሁ ሊንኩን ይኸውና።
  
„የግንቦት 7 ስልክ ይጠለፍ“ ነበር ይላል መረጃው። 

ኢትዮጵያ በታሪኳ የደህንነት ጣምራ ሙያ ያላቸው ፕሮፌሽናል የሆኑ የአገር መሪዎች ፊት ለፊት ሲወጡ የመጀመሪያዋ ነው። ወርቃማ ዘመኗ ነው ብዬ ከዚህ በፊት የኢትዮ ኤርትራን አቻዊ ግንኙነት ስጽፍ አንስቼው ነው። በትክክል ለውስጥም ለውጭም ደህንነቷ ከተጠቀመችበት። 

መረጃዎች እዬደረሱ ግን መቅደም አለመቻሉ አገረ ውስጥ ችግሩን መጨመሩ፤ የውጭ ጠላትን የደህንነት ሁኔታ እንዴት ልትመክተው ነው የሚልም ስጋትን አስባለሁኝ? ማሸፈን እኮ የተመሰጠረን ፈልፍሎ መቅደም ነው። 
  
ከዚህ ሊንክ ጭብጥ ስነሳ እኔ የፖለቲካ ድርጅት የሌለኝ፤ የትኛውንም የፖለቲካ ድርጅት ሃሳብ ደጋፊ ያልሆንኩት በሃሳቦች ዙሪያ ብቻ እምሞገተው ሥርጉተ ሥላሴ "ፍቅር፤ ምህረት፤ ይቅርታ ስለታወጀ" ሳት ብሎኝ፤ ምርቃን ይዞኝ ስልክ ለእናቴ አልደወልኩኝም። ለዛውም የዓመቱ የዘመን መለወጫ ዕለት። 

አብሶ ዋዜማው ለጎንደር ከተማ ልጅ ልዩ ነው። እናቴ በህይወት መኖሯን፤ መመንኮሷን የሰማሁት ዶር አብይ አህመድ ጎንደር አደባባይ ላይ ንግግራቸውን ላይፍ እያዳመጠች አክስቴ ደውላ ነው የነገረችኝ።

ደስታ ስለነበረኝ እንጂ ውጪ ለሚኖሩት ቤተሰቦቼ ስልክ ራሱ አላነሳላቸውም፤ እንሱ እግዚአብሄር ሁሉንም ይፈታዋል ባዮች ናቸው። አክስቴ የደወለችው ምክንያት ከቤተሰብ ጋር መገናኛሽ ጊዜ መጣ፤ እኔ ራሴ አንጠልጥዬ ይዤሽ እሄዳለሁኝ ብላ ነው። ከሲዩዝ እስከ ኢትዮጵያ መልስ አሜሪካ አቅዳ ነው የደወለችልኝ።

እርግጥ ነው የድንጋጤም ቀን ነበር። ደንጋጣ ነኝ። እናቴ መዋብ ስለምትወድ እዚህ ምንኩስና ደረጃ ምን አደረሳት ብዬ በድንጋጤ ስጮኽ አክስቴ ፖለቲካ ብትተይ ይህ ሁሉ አይመጣም ነበር ብላኛለች። ብቻ ዛሬ ላይ ሆኜ ሳዬው ለእኔ  በአብዩ መንፈስ ደስታ ሰክሬ አለመደወሌ ብርታትን ሰጠኝ። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም። መጠንቀቅ ምንግዜም - ለሁልግዜም።

አንድ ሰው የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ሲገባ የሰራ አካላቱ ሁሉ ዓይን መሆን አለበት። መጠንቀቅ። ራስን መግታት፤ ራስን መቆጠብ፤ ማድመጥ ያስፈልጋል። „ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ ሁሉ ግን አይጠቀመኝም“

 የሰው ልጅ ብዙ ፍላጎት ይኖረዋል። ነገር ግን ፍላጎቱን የሚፈጽመበት ጊዜ መለዬት ይኖርበታል። አብሶ እዛ ለሚኖረው አዲስ ትውልድ ማሰብ፤ መጨነቅ ይገባል። በእኔ ምክንያት ስንት ወላድ አልቅሳ ቀረች ብሎ ማሰብ ይገባል። 

አሁን እኮ የጽሞና ጊዜ እንጂ የፉክክር ጊዜ አልነበረም፤ አሁን የሱባኤ ጊዜ እንጂ የአሸናፊነት እና የተሸናፊነት ጊዜ አልነበረም። አሁን የተደሞ ጊዜ እንጂ የከሳሽና የተከሳሽ ግዜ አልነበረም። 

አሁን ሃሳብን ፍላጎትን፤ ምኞትን፤ ሁሉንም በግልጽነት ጠረጴዛ ላይ አቅርቦ ፍርዱን ለእውነት የማስረከቢያ ጊዜ ነው። ለዛውም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖቻችን እንዲህ ተስፋ አልባ ናቸው…. ከትግራይ በስተቀር በመላው የአገራችን ክፍል ይህን ሰቆቃ ይጋፈጣሉ ወገኖቻችን። የፖለቲካ ሊሂቃኖቻችን ይህ አያስጨንቃቸውም። 

https://www.youtube.com/watch?v=7BHtWjl4EQ8

Ethiopian today - በኢትዮጵያ በሚደርሰው የህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ላይ ያጠነጠነ ፕሮግራም ይማሩበታል


አሁን ምርጫ በሌለበት ሁኔታ ይህን ከተሆነ፤ ምርጫ ሲመጣ ምን ሊኮን ነው። የሆነ ሆኖ የዲያስፖራ ሊሂቃን አገር ሲገቡ ይገጥማል ብዬ ያሰብኩት ሁሉ ችግር እዬታዬ ነው። እዚህ ያለውን ችግር የመሸከም፤ የመፍታትም አቅም የለም፤ እንደተዝረከረኩ ነው አገር የገቡት። 

ብዙ የአማራ ድርጅቶች ውጪ አገር አሉ። የት እንደ ወደቅን? ምን እንደ ገጠመን? ፈልገውን አያውቁም፤ አንዳንድ ጊዜ የሚገርሙ ገለጣዎችን ሳዳምጥ ጥያቄ ስጠይቃቸው አይመልሱም። ከዚህም ያለፉ ጉዳዮችም አሉ በዝምታ የማላፋቸው። አንድ ወንድሜ ድንጋይ ተሸክመው አንድ ሁኑለት ለ አማራው እያሉ ሲማጠኗቸው አይቻለሁኝ። የወንድ ልጅ ዕናባው በሆዱንም የጣሰ ጉዳይ አይቻለሁኝ፤ ሲማጠኑ አልቅሰዋል። እኔም አብሬ አልቅሻለሁኝ። 
  • ·       ዲስ ልጅ።

ብዙ ጊዜ እማዘወትራቸው ጹሑፎች አሉኝ። ተቃርኖ ያሉባቸው ናቸው። መዳባቸው የጠፋብኝ ናቸው። ውስጥን ለማግኘት ብዙ እጥራለሁኝ። ሃሳብ አቅራቢው ከሦስት ወገን የለም። ከተፎካካሪው፤ ከለውጡ፤ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ። ብቻ ቋሚ ፍላጎቱን ለማግኘት የሞገተኝ ጹሁፍ ነበር ወደ ሁለት ዓመት ይሆነኛል የተከታተልኩት። እንዲህ ዓይነት ጹሁፎች ብዙ ጊዜ ውስጣቸውን አግኝተው ለመቀጠል ይሁን፤ አጥተው መክነውም ሊቀሩ ይችላሉ፤ አሁን የሰዓሊ አምሳሉ ጹሑፎች የት ልመድባቸው ብዬ የምቸገርበት ነበር።

ከአዲሱ ለውጥ ጋር በተያያዘ ሁኔታ መንፈሱ የለም። ብቻ ወደ ሁለት ዓምት የተከታተልኩት ጹሑፍ የዝንባሌውን ጉዳይ ለሁለት ሦስት ወገኖቼ አራተኛ መንገድ እንዳለም ነግሬያቸው ነበር „ሽዌኛ“ የሚል። አሁን "የሽዋ ፓርቲ" የሚጠይቅ ሆኖ ወጥቷል ያ ጉልበቴን ምጥምጥ አድርጎ የበላው መንፈስ ውስጡን የሃይል አሰላለፉን ለማወቅ የሞገተኝ ጹሁፍ ነበር። እስኪ በቃው አሽቶኛል። 

ይህ መንፈስ ሲቀጥል ደግሞ አስኳሉ ወደ ብሄርተኝነት የሚወስድ መንገድ ጠራጊም ይመስለኛል። ማነው ብዙ? የትኛው ብሄር ብሄረሰብ ነው ባለ አቅም? በሌላ ጹሁፍ እኔ ሥራዬ ብዬ ስለምከታታለው አሁን ጎልቶ ወጥቷል። የአንድ ጸሐፊ መደበኛ ታዳሚ ካልተሆነ ሃሳቡን ማያያዝ አይቻልም በቀላሉ። ስለዚህ ለሌሎች የሚከሰተው ዘግይቶ ሊሆን ይችላል።  ቀን የሚጠብቅ ጉዳይ ነው ….

ይህ እንግዲህ ይህ ለውጥ ያመጣው ትርፍ፤ ያነጠረው የሃሳብ ማዕከል ሲሆን፤ ጠለል ብሎ ወለል ብሎ እዬታዬ ነው። ሃሳቡን እኔ አልቃወመውም፤ ማህበራት አሉ የጎንደር የጎጃም የሚል አሁን ማህበራት ሳይሆን የክ/ አገራዊ ፖለቲካ ፓርቲ ነው ጥያቄው። ያው ትግራይ ላይ ያለው ወያኔ ሃርነት ትግራይ እንዳለው ማለት ነው። መንፈሱ ጉልበታም አቅምም አለን የሚል ነው፤ አገር የመምራት ጸጋው ከእኛ ዘንድ ነውም ይላል።

 አብን ስለምን ሽዋ መጣ የሚል ተቃውሞም አለው መንፈሱ። የሽዋ ፓርቲ ሽዋ ላይ ያሉትን ሽወኛዎች ብቻ ሳይሆን ሌላ ቦታ ያሉትንም ጎንደርም፤ ጎጃምም፤ ወሎም፤ ወለጋም፤ ሐረርም፤ ሲዳማማም ውጪ አገር ያሉትንም ማሰባበሰብ ይኖርበታል። በነገራችን ላይ ዋልድባ ገዳም ታሪክን ማንበቡ ይጠቅማል። ስለዚህ መሄድም እንዳለ ማሰቡ ቢታሰብ መልካም ነው፤ ለምን መጣችሁብን ከማለት። 

የሆነ ሆኖ እዮባዊነትን ከሰነቅን በራሱ ጊዜ እዬጠራ የሚሄድ አምከንዮ ይኖራል። "የቂጣም ይሁን የልጅም ይሁን" እንደሚባለው …  መልክ የጎረፈው ሁሉ እዬያዘ ይሄዳል …. ይህ ጎርፋማ ጉማማዊ ጎማማዊ ዘመን … ጥሞናን ብንሰንቀው ወይ ፈርሰን እንሰነባበታልን፤ ወይ ደግሞ ቀጥልን እንገነባባለን።
  • ·       ህልመኝነቴ እስተምን? 

ክብረቶቼ ቅኖች፤ ///// ይህን የመጀመሪያውን ሃሳብ ስለ መደበኛ እና ስለ ሽምቅ ውጊያ በህዝብ አኗኗር ላይ ያለውን ጠንቅ በ2013/2014 ስጽፍ አልሜው ነበር። ዛሬም ይደገም እስኪ … ዓለም እንድትሰራ እንድትፈላስፍ የሚናፍቀኝ ነገር
1.       ስጥን የሚያነብ መሳሪያ፤
2.       ክፉ ሃሳብን የሚያጸዳ ማሽን፤
3.       ወይንም እንደ ባትሪ ቅኝት ቻርጅ የሚደረገበት ብልሃት። ቅንነት ማጣት ከሁሉም የከፋ ጋኔላዊ በሽታ ነው - ለእኔ።
  • ·       ርኩዝ።

Ethiopia አቶ ጀዋር 43 ሰወች ተገድለዋል ያሉት ሀሰት እንደሆነ ኮማንደር ክፍሌ አሰፋ ተናገሩ

Published on Sep 20, 2018 አቶ ጃዋር መሃመድ 43 ሰዎች ተገድለውብናል አለ

የኦሮሞ ልዩ ፖሊስ ሀላፊ አላማዮ ኢጂጉ ለምን ቶሎ አልደረሰም ሲባል "የመሬቱ አቀማመጥ ስለማይመች ነው"
ሲል ተሳልቋ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠው መግለጫ

የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት መግለጫ

የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት መግለጫ


Ethiopia || የኦሮሚያ ፓርቲዎች ስለ / ዕጣፋንታ የሰጡት አስደንጋጭ መግለጫ


የቅኖች ማህበር ይለምልም!
የኔዎቹ ውዶቼ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።