«በአማራ ክልል በዚህ ሳምንት ከ27 በላይ የሚሆኑ ‘ሰላማዊ ሰዎች’ “በመንግሥት ኃይሎች” መገደላቸው ተነገረ» bbc

 

·       https://www.bbc.com/amharic/articles/cley9eeyxv0o

6 ሰአት በፊት

·    «በአማራ ክልል በዚህ ሳምንት 27 በላይ የሚሆኑሰላማዊ ሰዎች’ “በመንግሥት ኃይሎችመገደላቸው ተነገረ»

 May be an image of 1 person and textMay be an image of fire

 

«በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች በቀናት ልዩነትየመንግሥት ኃይሎችቤት ለቤትና መንገድ ላይሰላማዊ ሰዎችንመግደላቸውን የዐይን እማኞችና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ጥቃቶቹ ሰኞ ሰኔ 17 እና ረቡዕ ሰኔ 19 2016 / መፈጸማቸው የተነገረ ሲሆን፤ በጥቃቶቹም 27 በላይ ንጹሃን ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል።

በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በር ወረዳ ከደብረ ሲና ከተማ ወጣ ብላ በምትገኝ ሾላ ሜዳ በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ ሰኔ 19 በመንግሥት ኃይሎች ደርሷል በተባለ ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች መገደላቸውን እና አራት የሚሆኑ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በከተማዋአጋም በር መገንጠያበተባለ ሰፈር ጥቃቱ 1130 አካባቢ እንደተፈጸመ ለቢቢሲ የተናገሩ አንድ ከጥቃቱ የተረፉ እማኝ፤ በጥቃቱ በአብዛኛው ማዳበሪያ ለመውሰድ ከተለያዩ ቀበሌዎች የመጡ አርሶ አደሮች እንደተገደሉ ገልጸዋል።

ከዘጠኝ እስከ 12 የሚሆኑ ወታደሮችቀጥታ መጥተው ሱቅ ላይ የተኩስ እሩምታ ጀመሩያሉት የዐይን እማኙ፤ እሳቸውን ጨምሮ ማዳበሪያ ለመጫን በመጠባበቅ ላይ የነበሩ አርሶ አደሮች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የመንግሥት ኃይሎችማሙሽ በተባለ ሻይ ቤትሻይ ቡናእያሉ ነበር የተባሉ ስምንት የሚሆኑ ሰዎችን ቤቱ ውስጥ ገብተው እንደገደሏቸው ተናግረዋል።

ማዳበሪያ ለመጫን እዛው አካባቢ ላይ ነበርን። ስምንት ሰዎች የወደቁት እዛው ሻይ ቤት ነውያሉት እማኙ፤ እሳቸውና ጥቂት ሰዎች በጓዳ ዘለው ማምለጣቸውን ገልጸዋል።

ድንገት መጥተው ጨርሰውን ሄዱሲሉ ጥቃቱን የገለጹ ሌላ የዐይን እማኝ እሳቸውም ጥቃቱ የተፈጸመበት ቤት ውስጥ እንደነበሩ ተናግረዋል።

እኔ ምን እንዳዩ እንጃ። ማታ ነው፤ ሰዓት እላፊ እንኳ መጥተው አያውቁም ነበር። 1200 ላይ መጥተው አጋም በር መገንጠያ የምትባል መስመር አለች፤ እዛ ላይ ተኩስ ጀመሩ። አንድ አምስት ስድስት ሰዎች መንገድ ላይ ጣሉ [ገደሉ] ከዚህ የተረፉትን ደግሞ ሻይ ቤት እየገቡ በተቀመጡበት እርፍርፍ ነው ያደረጓቸውሲሉ ጥቃቱን ገልጸዋል።

እርሳቸው ከነበሩበት ሻይ ቤት ብቻ 11 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን የተናገሩት እማኙ፤ ሦስት ከሚሆኑ ሰዎች ጋር በጓዳ በር አምልጠው ሕይወታቸውን መታደግ ቢችሉም፤ 20ዎቹ እድሜ ላይ ይገኛል ያሉት ወንድማቸው መንገድ ላይ ተገድሎ እንዳገኙት ተናግረዋል።

በጥቃቱ ከአያቶቹ ጋር የሚኖር 14 ዓመት ታዳጊ ልጃቸው ቤታቸው አጠገብ ከሚገኝ መንገድ ላይ መገደሉን የተናገሩ አንድ አባት፤ በደብረ ሲና ሀዘን መቀመጣቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የተኩስ ድምጽ መስማታቸውን የተናገሩ አንድ የአካባቢው ነዋሪ እሳቸው የሚያውቁት 11 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጠው፤ ቁስለኞች ሾላ ሜዳ እና ደብረ ብርሃን ሆስፒታል መግባታቸውን ተናግረዋል።

11 ሟቾችን ስም ዝርዝር መሰብሰብ እንደቻሉ የተናገሩ ሌላ እማኝ፤ በማግስቱ ሰኔ 20 አራት ተጨማሪ አስከሬን ተገኝቷል ሲሉ የሟቾቹ ቁጥር 15 ነው ብለዋል።

“. . . አብዲላቅ፣ ማኔ አምባ፣ አራጨለንቆ፣ ወይን ውሃ፣ ሸንኮርጌ፣ እንዶዴ፣ ዶቃይት፣ ድብ አምባ ቀበሌዎች ትናንት [ሰኔ 20] ወደ ስምንት ደብር ቀብረን ነበርብለዋል።

በአካባቢው ለለቅሶ መጥተዋል የተባሉ ሦስት የፋኖ ታጣቂዎችን ተከትለው ሳይመጡ አልቀረም የተባሉትየመንግሥት ኃይሎች ስለ ታጣቂዎቹ መረጃ በመፈለግ ግድያውን ፈጽመዋልብለዋል።

ጥቃት አድራሾቹመከላከያ ሰራዊትለመሆናቸው በለበሱት የደንብ ልብስና በአካባቢው በቅርብ ርቀት ሲና በተባለ ስፍራ ካምፕ በመመስረታቸው እንዳረጋገጡ ገልጸዋል።

በሌላ ተመሳሳይ ጥቃት በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ይልማና ዴንሳ ወረዳ አዴት ከተማ በሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ ሰኔ 17 2016 .. ንጹሃን ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በጥቃቱ 11 ንጹሃን ሰዎች በመንግሥት ኃይሎች መገደላቸውን የተናገሩት ነዋሪዎች፤ ድርጊቱን ከበቀል ጋር አያይዘውታል።

በእለቱ የፋኖ ታጣቂዎች እና የመንግሥት ኃይሎች ለሰዓታት የዘለቀከባድ ውጊያማድረጋቸውን ተከትሎ ከሰዓት 900 አካባቢ ጥቃቱ መፈጸሙን የተናገሩት ነዋሪዎች፤ አንድ ሴትና 10 ወንዶች እንደተገደሉ ገልጸዋል።

ግድያው የፋኖ ታጣቂዎች ከተማዋን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ 02 ቀበሌ እርሻ ሰብል በተባለ ሰፈር መንገድ ላይ እና ቤት ለቤት መፈጸሙን የጠቆሙት ነዋሪዎች፤ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁበሚል ግድያው ተፈጽሟል ብለዋል።

ፋኖ ከተማውን ተቆጣጥሮ ውሎ በወጣበት ሰዓት ብዙ ኃይል ስለተመታባቸው በዛ ብስጭት ያገኙትን ሁሉ ነበር እየመቱ የነበረውሲሉ ስለ ግድያው የተናገሩ አንድ የአዴት ከተማ ነዋሪ፤ በጉልበት ስራ ተሰማርተው የነበሩ ሰዎችን ጨምሮ 11 ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል።

ሁለት ልጆች ናቸው ውጭ ላይ [መንገድ ላይ] የተመቱት እንጂ ሌላውን ከቤት እያወጡ ነው የገደሉትሲሉ ስለ ጥቃቱ የተናገሩ ሌላ ነዋሪ፤ 18 ዓመት ያልሞላውን ታዳጊ ጨምሮ ሟቾቹ አብዛኞቹ ወጣቶች ናቸው ብለዋል።

11 ሰዎች ግድያ በተፈጸመ በማግስቱ ሰኔ 18 ደግሞ ከከተማው መውጫ ባለ ርብርብ በተባለ አካባቢ ተጨማሪ አራት ሰዎች ተገድለዋል በማለት የሟቾቹ ቁጥር ከፍ እንደሚል የጠቆሙ ሌላ ነዋሪ፤ ከሟቾቹ ውስጥ አባትና ልጅ እንደሚገኙበት ገልጸዋል።

የሟቾቹ ቀብር ያኑ ቀንና በማግስቱቀለሞ ገብርኤልበተባለ ቤተ-ክርስቲያን መፈጸሙን የተናገሩት ነዋሪዎች፤ ግድያውን ተከትሎ ከክልሉ ዋና ከተማ ባሕር ዳር 43 . ርቀት ላይ የምትገኘው አዴት ከተማበሀዘን ተውጣለችብለዋል።

“[ከተማው] በጣም በሀዘን ተውጧል። የእያንዳንዱን ሰው ፊት ስታይው ለቅሶ፤ እንባ ነው። ትናንት ለቅሶ ነበረ፤ ማነው የእነዚህ ልጆች ቤተሰብ ብለሽ መለየት አትችይም [ነበር]” ሲሉ ማሕበረሰቡ በከባድ ሀዘን ውስጥ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ግድያውን ተከትሎ በአዴት ከተማ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ገደብን ጨምሮ የንግድ ተቋማትም ዝግ እንደሆኑ የተናገሩ አንድ ነዋሪ፤ ከዚህ በፊትም እንደዚህ አይነት ጥቃቶች ደርሰው እንደሚያውቁ ጠቁመዋል።

ሆቴሎች ዝግ ናቸው፤ ማንኛውም የስራ እንቅስቃሴ የለም፤ የመኪና መንገድ ዝግ ነው፤ ባጃጅ ሳይቀር ዝግ ነው [የለም]” ሲሉ በከተማዋ ውጥረት እንዳለ የጠቆሙት አንድ ነዋሪ፤ በቤተ-ክርስቲያን ከማክሰኞ እለት ጀምሮ ለሰባት ቀናት የጸሎትና የፍትሃት መርሃ ግብር ታውጇልሲሉ ሌላ ነዋሪ ተናግረዋል።

ቢቢሲ ግድያዎቹን አስመልክቶ የክልሉን የመንግሥት ባለስልጣናት ለማናገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

በአማራ ክልል በሰኔ ወር መጀመሪያ ቀናት በምዕራብ ጎጃም እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖችበመንግሥት ኃይሎችተፈጽሟል በተባለ ጥቃት 20 በላይ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል።

ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ በጀመረው የክልሉየትጥቅ ግጭትየፋኖን እና የመንግሥት ኃይሎችን ውጊያ ተከትሎሰላማዊ ሰዎችየጥቃት ሰለባ እንደሚሆኑ ተሟጋች ድርጅቶች በተደጋጋሚ አስታውቀዋል።»

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።