#ማዬት እና #መመልከት

 #ማዬት እና #መመልከት እንደ አፈፃፀማቸው ስኬታቸው ይለያያል። ከውስጥ ማዬት እና ከላይ ማዬት አንድ አይደሉም። ማዬት ማስተዋልን ሲያጎናፀፍ #አትኩሮት ይወለዳል። አትኩሮት ጥሞናን ሲጠጣ ዬፍልስፍና ጎዳና ይጠርጋል። ጥናቱ ወደ ፍትኃዊነት ዝንባሌ ያመጣል። መመልከት ከማዬት ጋር በአንድ #ትርጉም ይካተታሉ። መመልከቱ ግልብም ጥልቅም ከሆነ ግብረ ምላሹ በመልከት ውስጥ እንኳን ይለያያል። መመልከትም ማዬትም የዓይን ብቻ አይደሉም። የህሊናም ናቸው። የህሊናም ብቻ አይደሉም #የ12 አካላት ናቸው። ሳዬው ልቤ ተሰነጠቀ፤ ነዘረኝ፤ መላ ሰውነቴን ወረረኝ የሚባለውም ለዚህ ነው። በምንሳተፍባቸው መስኮች ሁሉ መላ አካላት ዓይነ ህሊና አላቸው እያልኩ ነው። ለሰጠው። ይህ ሁሉ #ተስቶ ነው መግለብለቡም ፦ግንፍል ግንፍሉም፦ አፍሶ መልቀም፤ ለቅሞ ማፍሰስ የሆነው።
ሥርጉትሻ2024/06/28

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።