ይህ ቤተ - ሰለሞን #የድውያን #ማገገሚያ #ጣቢያ የለውም።

 

ይህ ቤተ - ሰለሞን #የድውያን #ማገገሚያ #ጣቢያ የለውም።
 
"ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ።"
 May be an image of 1 person and babyMay be an image of 1 person, child and braids
 
በውነቱ ለዛሬ የሚሆነኝን ፈፅሜ ነበር። ነገር ግን መዳኛ የሌላቸው ነፍሳት እዬመጡ ቤቱን ያውኩታል። እዚህ እኮ ጎንድ ተክለኃይማኖት #መጠመቂያም የለም ወፈፍ ለሚያደርጋቸው። የአማኑኤል #ማገገሚያ ጣቢያ የለም። 
 
ቢያውቁት ቢረዱት የሃሳብ አቅም ያለው በትህትና፤ በአክብሮት በጥሞና የሚያነብበት፤ የሚያዳምጥበት፤ ሃሳቡን አቅርቦ የሚሞግትበት ነው። የውቂ ደብልቂ፤ የቅጽበተኞች መጋለቢያ አይደለም ቤቱ። ይህን ያሰኜው ሌላ ቦታ መፈለግ ነው ያለበት። ኢትዮጵያን #የተፀዬፈ ሰብዕና ይህ ቤት ልኩ አይደለም። 
 
ከዘለለው ጋር የማልዘል፤ ከጎረፈው ጋር የማልጎርፍ መሆኔ ይታወቃል። #መልካምነት#ቸርነት ሲነሱ ያንገፈግፋቸዋል። ኢትዮጵያ ስትነሳ ደማቸው #ይንተከተካል። ጎርፍ አምጥቶ ደለል የሠረባት ሁሉ እዬመጣ ልቤን ያወልቃል። እንዲያውም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማም እንደ ጠላት ያዩታል። #ይድከሙ - አይችሉም። #ይኳትኑ - #ነኩተው ይቀራሉ።
 
የአረብ ስፕሪንግ ተነሳ ኢንፖርት ኤክስፖርት ህግ ይግዛው፤ ፓኪሳትን ቤተ -:መንግሥት ንቅናቄው መጣ እኛም እንቀላቀለው የተነሱበትን የማያውቁ፦ ሰው በገነባው አቅም ተንጠላጥለው እንደ #ፌንጣ እዬዘለሉ ባጉም ባጉም። "ከበሮ በሰው እጅ" ሆኖ የፖለቲካ ድርጅቱም ተመሰረተ ጨዋታው ፈረሰ ቅሉ ተሰበረ አሟራው በረረ ሆኖ አዬን። ስንት አቅም የፈሰሰበት። 
 
አቅልም አደብም ጠፍቶ በምኞት ሰረገላ የፋንታዚ ልዑል ተሁኖ መከራን ማበራከት። አዬ የአማራ ህዝብ ቻል የተባለው ገመና እኮ ወዘተረፈ ነው። ኩፍትርትር ያለች ብጣቂ ወረቀት ልሳንም አንደበትም ሁና ታላቁን የአማራ ህዝብ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ከግብ አያደርስም። ማህበራዊ መሠረቱን ያጣው ሁሉ መተመሜያው የአማራ ፖለቲካ። ገቢው የአማራ ፖለቲካ። አጀቡ የአማራ ፖለቲካ። 
 
#ዝምታችን ቢከበር ምን አለ። ዝም እምለው በምክንያት እንጂ ሙግቱ ጠፍቶኝ አይደለም። በአማራ የተጋድሎ ንቅናቄ እኔ እማውቀው የዘለቀው ሳይለካለክ አቶ #አቻምዬለህ ታምሩን ብቻ ነው። ዛሬ እሱ ተገፍቶ በላይ የተዶለው ሁሉ አራጊ ፈጣሪ ሆኖ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል አያለሁ። በአማራ ጉዳይ ጥናታዊ ፁሁፍ ያቀረቡት ሁለት ፀሐፍት አቶ #አቻምዬለህ ታምሩ እና ፕሮፌሰር #ሃብታሙ ተገኜን ሲወርፋም አዳምጣለሁ። ልክን አለማወቅ። 
 
በሌላ በኩል ማንም ሳይረዳው፤ ከጎኑም ማንም ሳይቆም አቶ #ተክሌ የሻው ስለ አማራ ህዝብ መከፋት፤ መገፋት ማንም #ባላሰበት ሰዓት "#ሞረሽ" የሚል የአማራ ድርጅት አቋቁሞ ሞገዱንም፤ ቋያውንም፤ እሳቱንም ዕጣ ነፍሱን ተንገበገበ። ዛሬ እሱንም ሲያብጠለጥሉት አዳምጣለሁ።
 
የአማራ እናት እንዲህ ዓይነት የተግለበለበ፤ አፋ እሳት የሚተፋ፤ ከራሱ ጋር የተጣላ፦ አደበ ቢስ ፍጡር አምጣ አትወልድም። በሥም መጥቶ መሞገት ያባት ነው። #በእንጉቻችሪት#በእንቁራሪት#በእንሽላሊት ሥም እተመጣ አገር አይብቃኝ። #አማርኛ ቋንቋን እንኳን አስተካክለው መፃፍ እኮ አይችሉም። አይደለም ሌላ። 
 
አሁን ደግሞ እኔ ቀርቻቸው ነበር እኔን መጥተው ሊያውኩ ይሻሉ። እዛ በጎፈንድ ሚ የሚያስተዳድሩትን ይጠይቁ። እኔ ማንም አለቃ፤ #ማንም መሪ፤ ማንም አዛዥ፤ ማንም አስተዳዳሪ የለኝም። የተሰደድኩት #ለነፃነቴ ነው። እኔ ሙግት ከጀመርኩ የተኮፈሰውን ሁሉ እርቃኑን አስቀረዋለሁኝ። ዝምታዬ ልጆችን፤ የትዳር አጋርን በማሰብ ነው። ዝምታዬ ይከበር። 
 
የእናንተን አቅለቢስ፤ የእናንተን አደበቢስ፤ የተደራጀ ሃሳብ ሊመራው የማይፈቅደውን፦ ለአማራ መከራ በሦስት እጥፍ በፎክክር ወገኔ ያለቀበት ምክንያት ምን እንደ ሆን ጠንቅቄ አውቃለሁ። ዝምታዬ ይከበር። ሙሉ 15 ጩኽናል ካለ ቆራጣ ምስጋና። አሁን ደክሞኛል።
 
አይደለም አማራ ቅኑ የአፋር ህዝብ ያለምንም እገዛ ሙሉ #አምስት ወር ብቻውን የተዋጋበት ምክንያት ጠንቅቄ እረዳለሁ። ልምዴ፤ ተመክሮዬ ይህን መርምሮ ጭብጡን ማወቅ ካልቻለ ለምን እደክማለሁ። የማንም አጃቢ - አንጋች አይደለሁም። አለቃ የለኝም።
 
 እስከዛሬ የሰው ሰብዕና ስገነባ፤ ስተጋ ኑሬም አዬሁት እስከዚህች ዕለት። ሁሉም የራሱን ልዕልና ግንባታ ላይ ነው። ለቀዳማዊ #እመቤትነትም ስውር ፍልሚያ እንዳለ እያስተዋል ነው። ያ ሁሉ የደም እና የዕንባ ጎርፍ ተጠቅጥቆ። ዝምታዬ ይከበር። 
 
እኔ ፕሮፖጋንዲስት አይደለሁም። የማንም የምንም። ምን እንዳለኝ ጠንቅቄ የማውቅ። የመብት እና የግዴታዬን ጣሪያ እና ግድግዳ ጠንቅቄ የማውቅ ነኝ። መስዕዋትነቱም ብድር አያስኬድም። ተርፎ ይናኛል። ስኬቴም የጨመተ ነው። 
 
ኢትዮጵያ እንደ #ባላንጣ እንዴት ትታይ? ለምን? አትሰቡት።
 
ማህበረ ቅንነት ኑሩልኝ። መልካም ቀን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
28/06/024
ዝምታዬ ይከበር።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።