መቼነው ወደ እኛ የምትመጪው እትጌ ትግራይ?

ይብላኝልሽ ትግራይ።
„አቤቱ በአንተ ታመኛለሁና ጠብቀኝ።“
(መዝመሩ ዳዊት ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፩ )

ከሥርጉተ © ሥላሴ 
09.07.2018
(ከጭምቷ ሲወዘርላንድ)


  • ·        መነሻ።

Must Watch !!! Amazing Story on JTV Min Addis


  • ·        ብታ

አሁን እርሰ ጉዳይ ትግራይ ስትሆን የሚከፋችሁ ልትኖሩ ትችላላችሁ፤ ግን የግድ ነው። እኔም ፈልጌው፤ ወድጄው አይደለም። ለነገሩ እነሱም  በአንድም በሌላም የትግራይ ህዝብ ማለት የኛ ድርጅት ማለት ነው ይላሉ። አመክንዮውም የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሠረቱም የትግራይ ልጆች ነው። ያገዟቸው፤ ያበረታቶቸው እርሱ ህዝቡ ነው። ስንቅና ትጥቅ የሆናቸው እነሱው ናቸው። ሌሎች ተፎካካሪ ነን ባዮችም በትግራይ ሥም የተደራጁትም ያው የትግራይ ልጆች ናቸው። 

ስለዚህ ከዚህ ዕውነት ውጪ ሊሆን አይቻልም። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ብለህ ከትግራይ ውጪ ሰማይ ላይ የተነሳፈፈ መንፈስ ነው ማለት አይቻልም።

እኔ እንዲያውም አጋጣሚው ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ጀምሮ ትግራይን የመርሳት ሁኔታ ይፈጠራል ስል ጭራሽ የተባባሩት ድምጽ ሆነው ነው ያረፉት ተፎካካሪ ነን የሚሉትም መደመሩ ከጭካኔ እና ከአረመኔያዊነት ጋር ሆኗል። ያም መብት ስለሆነ ምንም ባልልም ትግራይን አታንሱ ስለሚለው ግን መነሻውም መድረሻውም መናህሪያውም ይሄው መሬት ስለሆነ ግድ ይላል።

 እርግጥ ነው በመልካም ነገሮች መትጋት ቢያስፍልግም፤ መልካም ነገሮች አረም እንዲያበቅሉ ያለው ሴራ ድር ብቻ ሳይሆን የወገንን ሰቆቃ እንዲህ እያዩ በዝምታ እለፈኝ ማለት ግን እጅግ ከባድ ነው። በዛ ላይ አሁንም ሰቆቃው እንዲቀጥል ያለው ሁኔታም ቢያንስ በመንፈስ መሰናዶ ያስፈልገዋል። በ አዲስ አባባው የድጋፍ ስለፍም እግሩን ያጣ ወንድም አለን። ሁለት ነፍሳትም አጸደ አርያም ላይ ናቸው። ከ150 ያለነሱ ቆስለዋል። በ እነድ ወር ብቻ ስንት ሞት፤ ስንት መሰደድ፤ ስንት ዕንባ ተደመጠ እግዚኦ! ስላንቺ ትግራይ ሆይ!

ሁሉም ነገር ሰው መሆን ይፈተናል የአርበኛ ከፍያለው ተፈራን ሰቆቃ ላደመጠ ሰው ለሆነ፤ ህሊና ላለው፤ ጤነኛ ሰብዕና ለኖረው፤ ዕብድ ላልሆነ ለማንኛውም ፍጡር ልርሳህ አልይህ ቢባል የማይሆን ነው።
… ዋ! ኢትዮጵያ እናቶች ስንቱን መከራ ቻላችሁት። አባቱን እህቱን አጥቶ እናቱም ሞት አፋፍ ላይ አልጋ ላይ ናቸው። ይሄ ነው እንግዲህ የዚያ ጠንቀኛ የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ሌጋሲ … ይቀጥልልን ባዮች … የእነ ማህበረ ተጋሩ የመርዝ ደቦ።



ሰማዩ ተከፍቶ ምድር ጭንጫ ሆኖ
አለት ተሰንጥቆ ግርዶሽ ተቀርድዶ
የእናት ማህጸን በምሾ ተጎርዶ
መንፈስ ሰማያትን በአቤቱታ ደርቶ
እዬር ያዘዘለት ቁጣውን ሲልከው
አንችን ያዬ ትግራይ የልጆሽ ዘቦ።
መንፈስሽ ተሰዶ ርቆ ርቆ ርቆ
ከውስጣችን ደርቆ ደርቆ ደርቆ
የትናት ላይበቃ ዛሬን እንዲህ ፍቆ
ምህረት ለመቀበል ጀርበሽ ተፈልቅቆ
ልመናው ደመነ ምድር ዕንባ ጎርሶ።
ግራጫ መክኖብሽ ፈጣሪ ቢቆጣ
የህጣናት ዕጣ ለነገ መላጣ፤
የዘመን ሆምጣጣ የሰዎች ጋሬጣ
ወዮ! አንቺ ትግራይ የፊትሽ ፈንጣጣ፤
ቢጨንቀኝ ቢጠበኝ እኔ ያለሁኝ ተዚህ አልሆንሽ ዘብአደር
መቀነስ መቀነስ መቀነስ አይሆንሽም ገበር
ይህንን ጭካኔ የተኛሽው አቅፈሽ
በቃኝን የፈራሽ አንቺ ማተበኛ
ዛሬማ ዛሬማ የሆንሽው ዛሬኛ!!
  • ·        ስጤ

አሁን የትግራይ ልጆች ምን አቅም? ምንስ ሞራል አላቸው ጭካኔ ቀረብን ብለው የሚታመሱት? የሚሰማው እኮ እጅግ ሰው ሆኖ መፈጠረን የሚፈትን ነው። እኔ እነሱን ብሆን ቀና ብዬ ለመሄድ ሁሉ አያስችለኝም። ይሄ ሁሉ ግፍ በሌሎች ኢትዮጵውያን ላይ ደርሶ እነ አቶ አብርሃም ደስታ አካኪ ዘራፍ ይላሉ፤ ሎቱ ስብሃት! ደም የለመደባቸው የጫካ ሰዎች ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉበት ምክንያት ጭካኔ በሽታ ስለሆነ ታመው ነው። ሱስም አለባቸው። የዚህን አረመኔያው በሽታ ውርስ እና ቅርሴ ይሁንልኝ ብሎ መሬት አይብቃኝ ማለት ደግሞ ከዋኖቹ በሽተኞች በላይ ድውይነት ነው።

ጭካኔን፣ አረመኔነትን፣ ሰው መግደልን፤ ሰው ማሰቃዬትን፤ ሰውን ማሳደድን፤ ሰውን መበደልን፤ ሰውን መጨረስ የበሽተኞች የህሊና ቢሶች የእንሰሶች ነው። የሰው ልጅ ሰው ሆነ በሰው ላይ እጁን ያነሳ እለት ከሰውኛ ተፈጥሮው ወጥቷለኝ። የሚያሳዝነው ያ አልበቃ ብሎ አሁንም መንገዱ በዚህ መንገድ ከልሆነ በማለት የምህረትን እና የይቅርታውን ሰማያዊ የአብይ ካቢኔ ህግ ተጻሮ መቆም የትውልድ እርግማንነት ነው።

አሁን ይህን ቅዱስ ፍጡር ያዬ ሰው እህሉስ፤ እንቅልፉስ ሥራውስ እንዴት ሊከውን ይችላል? ይሄ እንግዲህ መንግሥት አለ በሚባልበት፤ የሰባዕዊ ኮሚሽን አለ በሚባልበት፤ የዕንባ ጠባቂ አቋቁመናል በሚ/ር መስሪያ ቤት ደረጃ በሚባልበት፤ በአፍሪካ ማዕከላዊ መዲና አዲስ አበባ ላይ ነው ይሄ የሚሆነው። ራያ ወልቃይት ጠገዴንማ እንዴት እና እንዴት እንደ ሆኑ ከዚህ ናሙና ሲወሰድ ከዚህም የከፋ፤ ከዚህም የከረፋ፤ ከዚህም የሚጎፈንን ገመና አለ። 

በባዶ ስድስት ደምቃ እና ከብራ የሰው እርድን ተሸክማ ዛሬ መሽቶ ይነጋላታል፤ አምርታ የደም ምርት ትመገባለች፤ ልጆቿ ነጭ ለብሰው ተኮፈሰው በዬአደባባዩ ይንጎባለላሉ፤ ተዋናይ፤ ጋዜጠኛ፤ አደራዳሪ ወዘተ…  ግን ሰው እዬደረቀባት፤ በሰው ቋንጣ እና በደረቀ ደማቸው ውስጥ ዘመንኖ መኖር ለዛሬ ሊሆን ይችላል። ነገ ግን ትውልዱ በተለያዬ ሁኔታ የሚቀጣበት የሰማይ ቁጣ አይቀሬ ይሆናል።

ይህን የምህረት እና የይቅርታ ዘመን እቴጌዋ የ27 ዓመቷ መነን በሱባኤ ጥቁር ለብሳ፤ ድንጋይ ተሸክማ መቀበል ያለባት ትግራይ ነበረች። ሁሉም ሰው አይበድልም። ሁሉ ሰው ጨካኝ አይሆንም ግን በድርጅት ደረጃ ይህን ያህል የመከራ ዶፍ 27 ዓመት የተስተናገደው በማህጸኗ ፍሬ ነው። ቅጣቱን ለማሰቀረት ቀረብን ብሎ ደረት ነፍቶ በመፏለል ሳይሆን፤ በተሰበረ ልቦና እራስን ዝቅ አድርጎ ወደ ፈጣሪ አቤት በማለት በሚሆን መሆን ብቻ ነው። አሁን የኢህአዴግ መከራ ተዚህ ላይ ነው።

በዘረፋው፤ በቅንዝረኛው፤ በወረራው፤ በደም፤ በጭካኔ፤ በአረመኔነት የተበከለው የማተበኛው የትግራይ ህዝብ ቀጣዩ ዕጣ ፈንታ ከምድር ቁጣ ይልቅ እኔን የሚያሳስበኝ ደጋግሜ እንደጻፍኩት የሰማዩ ቁጣ ነው። ይህ ግፍ እኮ ምድሪቱን ነዲድ ሊያደርግ ይችላል። ይህ ግፍ አኮ ምድሪቱን የተባይ መሬት ሊያደርጋት ይችላል። ይህ መስቃ እኮ ምድሪቱን ምድረበዳ ሊያደርጋት ይችላል።

ማን ከዚህ ጭካኔ፤ ከዚህ አረመኔነት ጋር አብሮ መኖርን ሊያስብ፤ ሊያልም ይችላል ብሎ ማሰብ ይገባል በጥሞና? ትእግስት ስያልቅ ፍቅር ይሰደዳል እና። ይህም ሆኖ የአሁኑ ፉከራ እና ቀረርቶ የታዘዘውን የእዮር ስይፍ ወደ አፎቱ እንዲመለስ የሚያደርግ አይደለም። የወልዮሽ የጥሞና ጊዜን መቀበል ካልተቻለ ንጹሃንን ጨምሮ የሚያጋይ መከራ ይመጣል። የዚያን ጊዜ ወዮ ነው። አሁንም ብጥብጥን፤ ግጭትን፤ ህውከትን፤ ፍልስትን ደምን ማቀድ ሰውኛ ነው ለማለት አያስችልም። ሁሉም አንቅሮ የተፋ ዕለት ቁጥቋጦ አይገኝም። ሰው የሚችለውን ያህል ብቻ ነው እና የሚችለው። ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።

  • ·        ህ አርበኛ …

እግሩ ተቆርጦ ሁለቱ፤ ያም አልበቃ ብሎ ደግሞ እንደገና ተዘቅዝቆ ተገርፏል ቀንና ሌሊት … አሁን የትግራይ ልጅ ይህን እዬሰማህ ቆመህ መሄድ ይቻልሃልን? ሌላ ህይወት … የሥልጣን ዘመን፤ የፉክክር ዘምን ታልማለህን? እራሱ በተፎካካሪ ፓርቲነት በትግራይ ሥም የተደራጁት ምንስ አቅም ይኖራቸዋል ተፎካካሪ ሆኖ አንደበትን ከፍቶ ለመናገር? ከረባቱ ገበርዲኑ ጥርጥሩ ሁሉም ከሰውነት በውነት ይጠጋልን? እህሉስ ከጉሮሮ መውረድ ይችላልን? እንዴት ይቻላል? 

ሰው ጠልተህ ሰው ነኝ ማለት እንዴተስ ይቻልሃል? ከቂም ጎርሰህ እዬዋጥክ እንዴት ስለማግስት ትውልድ ቢያንስ ስለ ራስህ የእትብት ብትን አፈር ማሰብ ይቻልሃልን? የሰው እኮ ግፍ አለው። የሥጋ እኮ ግፍ አለው። ልጅም አያወጣም ነገንም አያበረክትም። ነገ ከመምጣቱ በፊት ይሞታል። መራራ ነው ግን አይቀሬ ነው …

ጋዜጠኛ … ባለሥልጣን … ባለ ማዕረግ … ታዋቂ … ተዋናይ የሚባለው ሁሉ እትብተኛው ሁሉ እኔ እንጃ እንዴት አንገቱን ቀና አድርጎ በዛች መከረኛ ምድር መኖርን እንደሚያልም?

የኢትዮጵያ ህዝብ እኮ በቁሙ የጸደቀ ህዝብ ነው። እነዚህን አረመኔዎን ብቻ ሳይሆን ጭካኔ እንዲቀጥል የተሰለፉትን የአራዊት ማህበርተኞችን አክሎ ተሸክሞ ይኖራል። እንዴት ዓይነት ቻይ ህዝብ ነው  የኢትዮጵያ ህዝብ። የሰው እርድ የለመደበትም ግዳዩን ይጥላል አሁንም።

አዬ የአላዛሯ ኢትዮጵያ ዘመን ስንቱን ተሸከምክ? አዬ ኢትዮጵያዊ ሰው ሆይ! ስንቱን ፍዳ ተሸክመህ 27 ዓመት ሙሉ ማቀቅክ? አብሮ መብላት፤ አብሮ መኖር፤ አብሮ መጋባት፤ አብሮ አንድ ደብር ማስቀደስ፤ አብሮ አንድ መስጊድ ድዋ ማድረግ? ይከብዳል። እውነት ይከብዳል።
ቢያንስ አሁን ባለቀ ሰዓት በደል ፈጻሚዎች ይቅርታ አድርጉልን መድፈር ተሳናቸው?
  • ·        የቸርነት አንበል።

በቅድሚያ እንዴት ሰነበትክ የቸርነት አንበል አቶ ዮሴፍ ገብሬ የተከስክበትን የመልካምንት ወንጀልም አዳምጫለሁኝ። አቅመ ቢሶች በዬቦታው፤ በዬሁኔታው፤ በዬዘመኑ ተግባራቸው ይሄው ነው። ማድረቅ፤ መንቀል፤ መንደል፤ ማሳደድ፤ ማጥቆር፤ ማክስል ነው የተፈጠሩበት። እንዳንተ ስለልተፈጠሩ አንተን መሆን ቀርቶ መምሰል አይቻላቸውም። ምክንያቱም አንተ ስትወለድ የቸርነትን መልዕክት ይዘህ ነው። አንተ የቸርነት መልእከተኛ ነህ። መልካሙ ነገር ተስፋ ሳትቆርጥ መቀጠልህ ነው። ስለሆነም ጽናትህን አጠንከረህ በመልካም ተግባርህ መቀጠልህ አስደስቶኛል። መልካም ሰው ነህ። ኑርልን!

ሌላው የቸርነት አንበል ታናሼ አቶ ጆሲ ገብሬ ይህን ቪዲዮ ለማዬት በውነቱ አቅም አልነበረኝም። በጸሎት እርዳታ ነው ሙሉውን ጨርሼ ማድመጥ ያቻልኩት። አርበኛ አቶ ክፍያለው ተፈራ ትህትናው እኮ እራሱ እንኳንስ ይህን ሁሉ መከራ እና ፍዳ ቀርቶ አንዲት ጨንገርም የሚያሳርፍ አልነበረም። የሚገርም ንጽህና አይቸበታለሁኝ። ስብዕናው ወደ ሞራላዊነት የሚጠጋ ነው። 

እንዲህ ዓይነት ፍጡሮች ከጭካኔ ጋር የማይተባባሩ ናቸው። በማዬት ብቻ ወደ ጭካኔ ብጥብጥ የሚያመራ ሰብዕና እንደሌለው ይታወቃል። ምን ይባላል ፈጣሪ አምላክ መኖርን ፈቅዶለታል እና ለሚሊዮኖች የጽናት ተቋም ሆኖ እንደ ዋርካ ስፍቶ፤ ከግቡ ደርሶ፤ ወልዶ፤ ከብዶ፤ ዘሩን ተክቶ፤ ለማዬት ያብቃን።

አንተ ደግሞ የሠራኸው ተግባር የልብ ነው። ፍጥነትህ በራሱ መንፈስ ነው። ይህን ያዩ ቅዱሳን ደግሞ ቋሚ የሆኑ ሁኔታዎቹን ያመቻቹለታል ብዬ አስባለሁኝ። መኖር ማለት እኮ አገልጋይነትን መፍቅድ ማለት ነው።

እናትዬ ብሩክ ቅዱስ ሁን፤ እጅግ መራራ መከራ ስለነበር መቻልን ማስቻል ባልችልም ግን ቢያንስ ማዳመጤ መከራውን የመጋራት ያህል ስለሆነ ራሴን ተቆጣጠሬ አዳምጨዋለሁኝ። በሌላ በኩል የሲዊዝ የመልካምንት ባልደረባ ኢትዮጵያዊ ወገኖቼም ክብር ለእናንተ ይሁን። ዝቅ ብዬ አመሰግናችሁ አለሁኝ። ተባረኩ። የምታደርጉትን የደግነት፤ የጽድቅ መንገድ ሁሉ በዚህ በጆሲ እከታተላለሁኝ ቅዱሶች ሁሉ ኑሩልኝ።

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
የኔዎቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ።

ማለፊያ ጊዜ።  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።