መቀመጫ ብሎ ነገር #ለመቀጣጫ? ለኢትዮጵያዊነት #መቅጫም። የእንብርት #እጥፋት። ጀግኖች የእምየዋ ልጆች ይነሱ እና ያድምጡ።
የእንብርት #እጥፋት። ጀግኖች የእምየዋ ልጆች ይነሱ እና ያድምጡ።
(መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲)

#ምዕራፍ ፲፱።
የዓለም #ጠይማን የነፃነት ቀንዲልን ድል አድዋን ካለ ርዕሰ ከተማ?
ያን ጥልቅ ምጥቅ ልቅና ኢትዮጵያዊ #ፍልስፍናን ካለ ርዕሰ መዲና?
የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ትውፊት፣ ወግ ልማድ፣ ባህል #ዊዝደም ያለ ርዕሰ ከተማ?
ኢትዮጵያ በልጆቿ ባሳደገቻቸው ውስጦቿ #ስትከዳ። እጅግ አሳዛኝ ገጠመኝ።
ውዶች ክብሮች ናፍቆቶች በጽሞና እሰቡት #እንብርት አልባ የእግዚአብሄር ፍጥረታትን?
የሰውን ልጅ ብቻ ሳይሆን አንዲት ጊደር #እንብርት የሌላት ስትሆን። ጽንስ በምን ይጸነሳል?
ለዛውም ለአፍታ - ታይተን፣ ለአፍታ - ብን ትን ለምንለው የህይወት #መስመር?
በኢትዮጵያ ላይ?
በእናት ላይ?
በአናት ላይ?
በውስጥነት ላይ?
አገር እና መንፈሱ ለማንም ለድርድር አይቀርብም።
አገር መንፈሷ በተደራጄ ጊዜዊ አቅም ወደ መቃብር አይላክም።
መማር ምንድን ነው? አዋቂነትስ????
አገር የሁለመና ትርታ - ትንፋሽ - ንጹህ አየር ነው። መተንፈሻ መቀማት የሞት ዓዋጅ ነው።
አሳዛኝ፣ ጨቋኝ መንፈስን ለመጫን መደራጀት ያውም አገርን አገርን በብላሽ ለመሸለም?
ከ2011 ዓም መስከረም 5 ጀምሮ አዲስ አበባ በኦሮምያ ሥር ናት፣ ሰላማዊ ሰልፍ ጠያቂወች ኦሮምያ ክልልን ነው መጠየቅ ያለባችሁ ይሁን ማሳወቅም ስል ሰሚ የለም። አልነበረም።
አሁን ያን የውስጥ ስምምነት በህጋዊ ዕውቅና ለማረጋገጥ ነበር የኮሚሽኑ አደረጃጀት ማለት ነው።
ኮሚሽኑን ያመኑ፣ የተማመኑ፣ አብረው ለመስራት የፈቀዱ ሁሉ፣ ይሆናል ብለው አቅም ጉልበት ያፈሰሱ ሁሉ ይህን የራስ #እንደራሴነት ንደት ሲያደምጡ ምን ይሉ ይሆን?
ታላቋ አገር ኢትዮጵያ፣
ረቂቁ መንፈሳዊቷ ኢትዮጵያዊነት፣
ከአንድ ዞግ ፖለቲካ ሥር ትንፋሽ ስትለምን እንዴት ያማል?
ተው - ያሉ፣ የመከሩ - የዘከሩ - ብልሆች "ኢትዮጵያዊነት ሱሴን፣ ስንኖር ኢትዮጵያ ስንሞት ኢትዮጵያ" እንደ አብዛኞቻችን ያላጣደፋቸው፤ ርጉወች፣ ጭምቶች በጣት የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊ - ሊቃውንታት ነብያትም ንደት ላይ ያለውን ዛሬን ምን ይሉታል፣ እኛንስ ምን ይሉን ይሆን? -------
በናታቸው ጉዳይ የቀደሙ ጠንቃቆች ከጸጸት የነጹ ይሆናሉ። እኛስ??? አማኞች፣ ተስፈኞች ከምኑ እንመደብ? ከየትስ - እንግባ?
የአፍሪካ መሪወች እሚሳሱላት ኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና አልባ ስትሆን ምን - ይበሉን?
እቴጌ ግብጽስ የልቧ ሲደርስ እንዲህ ኢትዮጵያዊ መንፈስ በዚህ ልክ መዲናውን ሲያጣ ምን ይሉ ይሆን?
ምንድን ነው #መቀመጫ ብሎ ነገር? እኔ መቀጣጫ እለዋለሁኝ። የአገራዊ ኮሚሽኑ ርዕሰ መዲና፣ ዋና ከተማ ከማለት የመቀጣጫ ቅጣት ሰየመለት። እግዚኦ! ነው።
አዲስ አበባ የኢትዮጵያ #ዋና ከተማ ማለት እንዴት ይሳናል? እንደምንስ - ያቅታል? ቅንነት የተለሞጠበት የሴራ ዳንቴል ነው #የመቀመጫ ድራማ። መቀጣጫ፣ ኢትዮጵያዊነትን #መቅጫም።
በአንድ ሥርዓት ውስጥ ከሁሉ የሚከፋው ብትን አፈር ለዜጋው መንሳት ነው። ኩርዶች ችግራቸው ይህ ነው። ኮተት እያለ ወደ እኛ ይህ ከርቤ ዘመን እየመጣ ነው።
ኢትዮጵያን የመፈተን፣ ኢትዮጵያዊነትን የማንገላታት ሌጋሲ ነገን - አያነጋም፣ ለዛሬም ጤና አይሰጥም።
ትርፍ ነገር፣ አፍ እላፊ ነገር አያስፈልግም። በተሰጠን ልክ ኢትዮጵያዊነት ያሳደገን ልጆቹ በዲስፕሊን መሞገት ያስፈልገናል። ለዚህ የተደረሰው በእኛ ጥረት ነው። እንጂ በማህበረ ኦነግ ስልት እና ጥበብ አልነበረም።
ምንም እንኳን አለሎው ነጥሮ ለእኛ ተደራሽ ቢሆንም። ነገ ሌላ ቀን ነው። ተስፋ ስላለ ከበቀል የነፃ፤ ሰውኛነትን ያስቀደመ ውስጣዊነት ዕድል ሲያገኝ ይህ ጥቁር፤ ጠራጠሮ ፍላጎት ይከስማል። ተስፋችን አምላካችን። ተስፋችን አላኃችን ነውና። ስለሆነም ነገን የሚያስከብር የሃሳብ ሙግት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
የኢትዮጵያ ውርስ ቅርስነት የሁላችን እንጂ አገራዊ ምክክሩ ለአንድ ዞግ እጅ መንሻ በፍጹም ሊያደርገው አይገባም። መብትም የለውምና። የውሳኔ ሃሳብ ይላል። ይሄ ቧልት ነው። አገራዊ መንፈስን የሚንድ። ዩጎዝላቢያን #መናፈቅም ነው።
"ከንቱ የከንቱ ከንቱ፣ ሁሉም ነገር ከንቱ።"
ቸር አስበን፣ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selasdie.
16/08/026.
ፍቅር ሲያልቅ፣ #ትዕግሥት ይሰደዳል።
ትዕግሥት ሲያልቅ #ፍቅር ይሰደዳል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ