"ከበላይ አካል #የመጣ " በትዕዛዝ ፍላጎትን ማሳካት ከሆነ ስለምን #ኮሚሽን ተቋቋመ???

"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
#እኮ……… እኮ።
እንዲህ በሥርዓት ውስጥ ያላለፈን አጀንዳ በትዕዛዝ ከመፈጸም ይልቅ
እነ ብልፄው #በዓዋጅ የምትፈልጉትን መፈጸም ይቻል ነበር እኮ? ይህ ሁሉ ወጪ ከሚወጣ?
#ስድስት ዓመት? አይጣልን ያቀላል ሰው።
ከዚህ ለዚህ ፓርላማው #ሺህ አመት ይንገሡልን ብሎ ቢያጸድቅም ይቻላል። የኤርትራ የመንግሥት አያያዝ እንዲህ
#ከምክክሩ እንወጣለን" ስለሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ጉዳይ።
" አይጥ ወልዳ ወልዳ ከጅራቱ ስትደርስ" ዓይነት ነው። መገኜታችሁ #የተገባ ጉዳይ ነበር። እስከ ፍፃሜ መዝለቅም
#የተገባ ነው። ልቅ ሐረግ ነው የሚሆነው። መቋጧ የለሽ።
በስማ በለው ምን ተባለ ከማለት ባለው ዕድል ተጠቃሚ መሆን አትራፊ ነው። ምንጊዜም። ስለ እናት ጉዳይ አጀንዳ
የሁሉም #ልጆቿ ሊሆን ይገባል። እራስን ባይታዋር ማድረግ አይገባም። መሳተፍ ይገባል።
ፖለቲካ ከሰውነት በታች እንጂ በላይ አይደለምና። መተያዬቱ "ነገር በዓይን ይገባል" ይላሉ ባለቅኔወች ጎንደሮች።
ስለሆነም በተለይ #እናት ፓርቲ ምክክሩን ጥሎ እንዳይወጣ በአጽህኖት፤ በትህትናም ላሳስበው እሻለሁኝ። ኩርፊያ፤
ቁጣ፤ ቅያሜ በእናት ጉዳይ የተገባ አይደለም። "ዙሮ ዙሮ ከቤት።"
መገኜት፤ ማየት፤ ማድመጥ፤ ሃሳብን በቅጡ አደራጅቶ ማቅረብ፤ ጥቂቱ ለብዙኃን ውሳኔ ተገዥነትን መፈጸም
ይገባል። የዴሞክራሲ አስተምኽሮ ይህ ነው። ተጫኝ ሃሳብ ምክክሩ ካጠቃው ሳይለንት ዲስክርምኔሽን ይጋበዛል።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተሥላሴ።
Sergute©Selassie.
13/08/026.
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
See less
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ