Zenebe Kassie እሙኃይ እንኳን ደስ አለወት። እናት ዓለም በረከተወት ይድረሰኝ። አሜን። እሙኃዮዋን እናቴን ያስታወሰኝ እለት ነበር።

 

እሙኃይ እንኳን ደስ አለወት። እናት ዓለም በረከተወት ይድረሰኝ። አሜን። እሙኃዮዋን እናቴን ያስታወሰኝ እለት ነበር። እንደአከላተምኳት ፈቃዷን ሳልፈጽም መራራ ስንብት ሆነ። 
 

 
ይህ መከራ የመጨረሻ ይሆን ዘንድ ምኞቴ ነው።
ከውስጤ ስለ እናቶቼ አስባለሁ። አንገላትተናችኋል። አሰቃይተናችኋል። ሃዘን ስጦታ አቅርብነልቻኋል።
ይቺ አገር ኢትዮጵያን ብለን ግን እራሳችን ረስተን ወጣትነታችን፤ ሐሴታችን ሁሉን ሰጥተን አሁንም እዛ ረግረግ ውስጥ መሆናችን ሳስበው ምጡ ምጥ ብቻ አይደለም። በሽታ ይገዛል።
የሆነ ሆኖ ከእሱ አብራክ የተፈጠሩ ልጆቹ፤ እሱንብላ አብራ እምትከላተመው የትዳር አጋሩም ያሳዝኑኛል። እንኳን ደስ አላቸው። ብቻ ለመኖር ለወሰነው ቢያንስ ይህን አቃለናል ብዬ አስባለሁ።
ለዘኔ ከእህት።
"ላም እረኛ ምን አለን" እባክህ አዳምጥ። በጥዋቱ ጽፌልህ ነበር አልሰማህኝም።
1) በምግብ ሊበክሉህ ስለሚችሉ ብርቱ ጥንቃቄ አድርግ።
2) ቅንነትህን በቅጡ አስተዳድረው። ፖለቲከኛ ቅንነቱ ብቻ ለድል አያበቃውም። ጥበብ ያስፈልገዋል።
3) ገራገርነትህንም እንዲሁ ማኔጅ አድርገው። ዓላማን በራስ እጅ ለማበጀት መወሰን ጎዳናህ ይሁን።
4) ለአንተ ሲሉ 12993 ተማሪወች ቤተሰቦቻቸው ወደ 64 ሺህ ከተስፋ ውጪ መሆናቸው ግቡን እና ስኬቱን አጥናው። ለቀጣዩ እርምጃ ስለሚረዳህ።
5) የህዝባችን መሰዋት በሚቀንሱ በሚያመጣጥኑ መንገዶችብቻ ጥናት ውሰድ። ብዙውን በርደን ውጭ ያለው ይፈጽም። እናንተ ቋያ ውስጥ ናችሁ እና።
7) ለጥሞና አላማህም። ቆራጥ ነህ። ብቻህን ለአጅም ጊዜ የገደምክ ቆራጥ ወጣት ነህ። አገር ተደፈረችሲባል ነው የወጣህው። ያን ጊዜም ጽፌ ነበር። እዛው ሁን ብዬ። በቀለኛ ሥርዓት ስለሆነ ይቀሙናል በሚል። አሁንም #ጥሞና ውሰድ። እራስህን አድምጥ። የኃይል አሰላለፋን አጥና። ስልት፤ ጥበብ፤ ወቅት፤ ሁኔታ በዘፈቀደ አይገኙም። ጊዜ ሰጥቶ ሲመረመር የሚገኝ ብልህነት ነው።
ጀግንነት እራሱ ጊዜ ሁኔታ ጥበብ እና ስልት ይጠይቃሉ። ዘመኑ በዝልኙ የሚነበብ አይደለም። አዬሩ በቁመናው ብቻ የሚተረጎም አይደለም። ማዬትም፤ መመልከትም ማስተዋል አይሆንም።
ማዬት እና መመልከትን ወደ ማስተዋል ስታሳድገው ነው ፍልስፍና ሆኖ ፋክትን አምጦ ዬሚወልደው። አቅጣጫህንም የሚቀይሰው። የእኔ ለምትለው ዓላማ ቀያሽ መሃንዲሱ አንተው ሁንለት። ጥገኛ አታድርገው። ለዚህ ደግሞ ማዬትን፤ መመልከትንወደ ምርም ማስተዋል፤ አትኩሮት ማሳደግ ሲቻል ነው።
6) እሙኃይን በጥልቀት እሰብ። ቤታቸውን እይ። ኑሯቸውን እይ። መከፋታቸውን ጊዜ ወስደህ አጥና። አንተን ስለፈጠሩ፤ አንተን ስላስገኙ እስከ መቼ እንዲህ ኩርምት ድቅቅ ብለው የመከራ ጉም ስንቃቸው ይሁን? የረባ ድንኳን፦ የረባ ልብስ፤ የረባ የጎን ማረፊያ ሳይኖራቸው በመቁጠሪያ ዘመናቸው ምን አደረጉ? ሲሆን ሲሆን የመነኮሳት ህልም እዬሩሳሌም ነው ያን እሰብላቸው። ማካካስ ባይቻልም።
መኖራቸውን እንደገና አደራጅተህ #እንዲስቁ ተጎንብሰህ እንዲመርቁህ እራሱን አስችለህ እንደፕሮጀክት ውሰደው። እባክህ ህይወታቸው እያለች እሰብላቸው።
እኔየበሞቴ ልዕልቴን ከሞት ብትመለስልኝ እክሳት ነበር። ግን አመለጠኝ።እናት እያለች አይታወቅህም። እምታውቀው ስታጣ ነው። ዘኔ አዲስ ማንነት ነው። አውቀዋለሁ የምትለው ሁሉ ቋንቋ ሳይቀር ይጠፋህል። አንተ እራስህ ትጠፋለህ። አንተን ለማግኜት አራት አምስት ዓመት አይበቃህም።
የማይቻል ነገር ነው። ከባድ እጅግ ከባድ። መርግ እጅግ መርግ። ምንም እምታስታውሰው ዬለም። መኖርን ትጠላዋለህ። ለምን መሰለህ? እናት እናልጅ ቱዊንስ ናቸው። ስለዚህ ግማሹ አካል እና መንፈስ መቃብር ውስጥ፤ ግማሹ ቁሞ ሲሄድ ሊታረቅ የማይችል ፈተና ይሆናል።
እኔ መጽናናት ያልቻልኩበት ሚስጢር ምንድን ነው ብዬ ሳስብ ያገኜሁት ፍሬ ነገር ይህ ነው። ከጠቀመህ ብዬ ነው የፃፍኩልህ። ለእሙኃይ ጊዜ ስጥ። በአጭሩ እድሜህ ተንከራተኃል። ለምታምንበት ወቅት ለሚሰጥህ ዓላማ እራስህን አስገዝተህ ደክመኃል። ለዚህ ትመሰገናለህ። ማድመጥ ግን ይቀርኃል። አድምጥ።
#ላም እረኛ ምን አለ መርምር። ከአንተ በብዙ በዕድል እና በአጋጣሚ ሊመዘኑ ወይንም ሊለኩ በማይችሉ የፈቃድ ስጦታ ተመክሮ ያላቸውን ሂደቶች በማድመጥ ተጠቅምባቸው።
ችግሩ በነፃ የሚገኙ ስለሆነ ለኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ፋይዳ አይመጣጠናቸውም። እንጂ ከዚህ ግማሽ ገጽ ብጽፍ ገቢ ነው። ምክር ሲሆን ደግሞ ፕሮፌሽንም ነው። ምን ለማለት ነው አቅም የወንዝ ዳር አሽዋ አይደለም። በቅጡ ምራው። አስተዳድረው።
ዘኔ ይህ ፁሁፍ በአንተ ዙሪያ የመጨረሻዬ ነው። የእሙኃይን ነገር አደራ። እሳቸው ሁለመናቸውንሰጡህ? አንተስ?????
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ውዶቼእንዴት አደራችሁ? እንደምን አረፈዳችሁ? ለምታደርጉልኝ ትብብር እና ለምትሰጡኝ ቅንነት ኑሩልኝን አበረክታለሁ።
መሸቢያ ጊዜ። ደህና ሁኑልኝ። አሜን
ቸር ያሰማን። ቸር እንሁን። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
05/06/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።