ስለምን መነጣጠል? መከራን የመድፈር፤ የመቀበል። መከራን ፈቅዶ የመሸከም፤ በመከራ ሐሴት አግኝቶ መከራን ስለማስተዳደር ለፈቀዱ ቀንበጥ ወጣቶች ልዩነት መፍጠር መታመም ነው። ድዌ ነው። በሽታ ነው። ወጣቶቹ ምን አበሳጫቸው? ስለምን ይህን እርምጃ ለመውሰድ ተገደዱ?
ስለምን መነጣጠል?
መከራን የመድፈር፤ የመቀበል። መከራን ፈቅዶ የመሸከም፤ በመከራ ሐሴት አግኝቶ መከራን ስለማስተዳደር ለፈቀዱ ቀንበጥ ወጣቶች ልዩነት መፍጠር መታመም ነው። ድዌ ነው። በሽታ ነው። ወጣቶቹ ምን አበሳጫቸው? ስለምን ይህን እርምጃ ለመውሰድ ተገደዱ? ይህን አገር እመራለሁ የሚለው ማህበረ እህዲድወኦነግ ሊመረምረው ይገባል። በቀል ዘርግቶ ህዝብ አዳምን እያስጨነቀ መከፋቱን የበለጠ ባያቆሳስለው ስል ላሳስብ እወዳለሁኝ።
እነኝህ ሦስት ወጣቶችም ሆኑ ሌሎችም በስቃይ ላይ የሚገኙ ወጣቶች የዘመን ሚስጢር ናቸው። ሁሉም ምን እያደረገ እንደሆን የሚመዝን የችሎት ተግባር ነው የፈፀሙት። በዚህ ጉዳይ ላይ ተራ የኮፒ ራይት ትርምስ መፍጠር ሳይሆን ሰክኖ እራስን መመርመር፤ እራስን ማድመጥ፤ እራስን ቡርሽ ገዝቶ ማረም ይገባል። እንጂ በሰፈር በአጥቢያ ተተልትሎ ማሰብ አይገባም። ከፍ እና ዝቅ ማድረግም አይገባም። አንድ ሰው ለአመነበት ተልዕኮ ህይወቱን ከመስጠት በላይ ምን ያድርግላችሁ? ጀግና ከሆኑ ሁሉም ጀግና፤ ሰማዕት ከሆኑም ሁሉም ሰማዕት። እንደ ዘራዕይ ደረስ፤ እንደ አብርኃም ደቦጭ፤ እንደ ሞገስ አስገዶም ። አታበላልጡ። ከፍ ዝቅ አታድርጉ። አትነጣጥሉ። አትለያዩ። በአፈፃፀሙም አትሻሙ። ወጣቶቹ ህሊናቸው የፈቀደውን ወስነው ፈጽመዋል።
ሌላው ትግሉንም አታነጣጥሉት ይህ ከሀምሌ ፭ ጀምሮ የህሊና ማህበራዊ ብቃት ክንውን የደረሰበት የእድገት ደረጃ በሂደቱ ከሀ እስከ ፐ በጽናት ቁመው የመሩ ያታገሉ ብቻ ሳይሆን የህዝባዊ ተሳትፎም አጠቃላይ ውጤት ነው። የአንድ አገር ልጅነት ርዕሰ መዲና፤ መንበረ መንግሥት መቀመጫ አለኝ የሚለው ሊኖረው ይገባል። ድንቅነሽ ባዕት ሊኖርት ይገባል። የዘመናት መስዋዕትነት የወል ማዕዶት አናት ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ፤ የአፍሪካ፤ የዓለም የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ መናህሪያ አዲስ አበባ ናት። አዲስ የተሸከመችውን በርደን ብቻዋን ልትቋቋመው ትችላለችን? ይህም አይደለም ኢትዮጵያን የአህጉራችን ሊቃናት ሊጨንቃቸው ሊጠባቸው የሚገባ ጉዳይ ነው። ለዚህም ነው እኔ ፓን አፍሪካ ሙብመንት ያስፈልጋል በዛ ላይ ሥሩ እያልኩ የተበተነውን ባልደራስ አሳስብ የነበረው።
የእነኝህ ወጣቶች ክንውንም ከዚህ አንፃር በስፋት እና በጥሞና ሊመረመር ይገባዋል ባይ ነኝ። ጠቅላይ ሚር አብይም የበቀል ሰይፋቸውን ከመምዘዝ የምግብ ጠረጴዛው ሳይቀር እንደ አድህኖ ስዕል አቡነ ዘበሰማያት ይባልበት የነበረውን ዘመን ደፍተው ከሰው ባሩድ እና ሮበት ጋር ተወዳጅተው የቁልቁሊት ከሚገሰግሱ ጥሞና ወስደው አቅማቸውን ቢፈትሹ መልካም ነው። አሁንም ሌላ ቀውስ ውስጥ ተዘፍቀው ከሚያጣጥሩ። ኃይል የህዝብ ፈቃድ ሲኖርበት እንጂ ከሌለበት ከባህር የወጣ አሳ ይሆናል። የሳቸው ድሪምላይክ ግስጋሴ ለብዙኃኑ እንቆቆ ከሆነ ላም እረኛ ምን አለን ቢያዳምጡ ጥሩ ነው።
በሌላው በኩል ግን እነኝህ ታይተው የማይጠገቡ ወጣቶች እራሳቸውን የማገዱበትን ሁኔታ ልጄ፤ ወንድሜ ቢሆን ብሎ ማሰብ ይገባል። በእነሱ ጉዳይ ትርፍ ነገር መነጋገር አያስፈልግም። አቁሳይ ስለሆነ። ተጨማሪ በደል ስለሆነ። የሰውነት ደረጃንም ዝቅ ስለሚያደርግ። በጥሞና ሰክኖ ሁሉንም ነገር በስክነት መመዘን ይገባል ባይ ነኝ።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
18/04/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ