ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ እግዚአብሄር አቦይ ስብኃት ነጋን፤ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን፤ ሻለቃ ዳዊትን እንዲጠራላቸው ተማፀኑ። #የአብቹ ላንቃ መልዕክት ልኳል።

 

ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ እግዚአብሄር አቦይ ስብኃት ነጋን፤ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን፤ ሻለቃ ዳዊትን እንዲጠራላቸው ተማፀኑ። #የአብቹ ላንቃ መልዕክት ልኳል።
 May be an image of 1 person and text
 
ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በህይወት እያለ ይህን ይሰማ ዘንድ ፈቃዱ ስለሆነ ፈጣሪ ይመስገን።
 
እኔ በአብይዝም እና ህህዋቲዝም ጦርነት ካወገዙት በጣት ከሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊ ዜጎች አንዷ ነበርኩኝ። ሰቢዕዊ ቀውሱን ብቻ ነበር እምዘግበው። እንዲያውም ደስታችሁን በልክ ያዙት ምክንያቱም ሌላ ደስታ ስታገኙ መደርደሪያ እንዳይጠባችሁ፤ ከዚህም ሌላ ደስታችሁን ስትነጠቁ የሥነ ልቦና ህመም ተጠቂ እንዳትሆኑ፤ ይህም ብቻ ሳይሆን ደስታ ሲበዛ ፈጣሪ ይከፋ እና ምርቃት ያነሳል በማለት ስሞግትም ነበር የመቀሌ ተያዘ ርችት ጊዜ። አቶ ሻንቆ የሚባሉ ጥሩ ወዳጄ በጣም ይከፋብኝ ይሞግቱኝም ነበር። ዛሬ ያለውን ነገር ሁል በዝርዝር አስቀድሜ ጽፌዋለሁ ልቦና ላላቸው ወገኖቼ። አቅምም አላባከንኩም። 
 
ህወሃት ቤተ መንግሥቱን ፈቅዶ ከለቀ ጀምሮም በህወሃት ላይ አንዳችም ነገር አልፃፍኩም። የከፋኝ አማራ ክልል እና አፋር ክልል ላይ የፈፀመው በደል ነበር፤ እንጂ የአብይዝም ካድሬወች ውሃ በቀጠነ ህወሃትን ሲያብጠለጥሉት አቅም አላባከንኩም ፈቅዶ መንበረ ሥልጣንን ከማስከበር ሌላ ምን ይምጣላችሁ በማለት ነበር የሞገትኩት። ለዛውም ለእኔ ስለ ህወሃት ሆነ፤ ስለ ሻብያ ቀስቃሽም፤ ፕሮፖጋንዲስትም አያስፈልገኝም። በጦርነት ቀጠና ውስጥ ስለአደኩ ሁሉን በደል አውቀዋለሁና።
 
የሆነ ሆኖ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አዲሱን ዓዋጅ አውጃዋል። ለሰማዩም ዳኛ ውሰድልኝ ብለዋል። የአብይዝም እና ህወሃቲዝም ጦርነት ሆድዕቃው ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው እና እያዬን ነው። እያዳመጥን ነው።
 
#የኢትዮጵያ ፌድርሽን ምክር ቤት፤
#የኢትዮጵያ ፓርላማ፦
#የኢትዮጵያ ካቢኔ፤
#የጠቅላይ ሚር ቢሮ አማካሪና አገልጋዮች፤
#የኢትዮጵያ መንግሥት የዜና ኮምኒካሽን አውታር፤
#የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚር ራዕይና መዳረሻ
#የኢትዮጵያ የደህንነት ተቋማት ዕሳቤ እና እርምጃ ሊቀ መኳሳቸው አክቲቢስት ስዩም ተሾመ ነው። ሁሉም ነገርፍሬም ወርኩ፤ ሃርድ እና ሶፍት ዌሩ የተደራጀበት ሚስጢር ላዕላይ እና ታህታይ መዋቅሩ መንፈሱ ያለው እዚህው ነው። ስለሆነም አደብ ገዝቼ አዳምጠዋለሁ። ከአንድም ሁለት ጊዜ "#የአብቹ" #ላንቃ
 
"#የአብቹ" ላንቃ የገለፀልን።
 
1) "ህወሃት እንኳን ትጥቅ ሊፈታ አስታጥቀነዋል።" ጋዜጠኛ ሲሳይ አንተን ያዬ ሰው። ምን ትል ይሆን?
2) "የአልጀርሱ ስምምነት ሊጣስ ይችላል።"
3) "ብአዴን ነፈስም አካልም የለለህ ጥምልምል ነህ።" የሚሸኜው፤ የሚሰወረው፤ የሚታሰረው ቀጣይ ሂደት ይጠበቅ ግርባው ብአዴን ዲያስፖራን ሊያስተባብር ዲሲ እንደሚገኝም አንከር ዘግቧል። ሲመለሱ ድግሱ ……
4) #ፐፐ! "ጌች ነፍሱ አለንልህ።" ፍቅሩ ደርቷል። ይጨርስላችሁ። ተገኝቶ ነው? ከልቤ ነው።
5) "የአማራ ኮምኒኬሽን ቢሮ ካቴና ጠብቅ ወይንም ትከላለህ ከምትለቀልቀው ድርሰትህ ጋር።"
6) "ቲም ህውሃትን የመሩ እነ አቶ አባይ ፀሐዬ ሻብያ ኤርትራ ወስዶ አናዞ ቢዲዮ ቀርፆ፤ ገድሎ ኢትዮጵያ አምጥቶ ሬሳቸውን በመጣሉ በዛን ጊዜ ነው በአብይዝም እና ኢሳያሲዝም መሃል ንፋስ የገባው፤" ተጋሩ "በላህው በላህው አብዩ አንጀቴን በላህው" እንዲሉ ይመስላል።
7) "የቦሌው የፋኖ ጥቃት አብይዝም የሰቲት ሁመራ በር ሲዘጋ ሻብያ ያደራጀው እና የመራው ኦፕሬሽን ነው።"
የራያ የህወሃቲዝም ጥቃትም የሻብያ እና የህወሃት የአዲስ ፍቅር የጫጉላ ሽርሽር ነው።
9) በጋዜጠኛ መሳይ የሚዲያ ተስትፎ ያለው ቆምጫጫ ሁነትንም የቀደምውን በምልሰት አይተን ታማኝነቱን እንጠረጥር ዘንድ ልዩ ጥሪ ቀርቧል። አንተስ ስዩሜ ኦሮማራ ላይ ምን ስትለን ነበር? ለግርባው ብአዴን አንተ ወይንስ እኛ ማነው ቀራቢ፤ ማንስ ነው አራጊ ፈጣሪ የነበረው? ይህ ብቻ አልነበረም የሌት ተቀን እምትባትትበት በህወሃት ብቻ አልነበረንም?
እኔ ሙግት ስለአቆምኩ እንጂ ስለፖለቲካ ድርጅት አደረጃጀት አመራር የተሰጠውም ሃሳብ ኮሳሳነት አብራራው ነበር። በሌሊኛው የስዩሜ ቪዲዮ ብቸኛው የፖለቲካ ድርጅት ብልጽግና ነው ይለናል። በውራጅ አባላት ደንብ አልቦሽ ፕሮግራም አልቦሽ መሪ ዕቅድ አልቦሽ የተደራጀውን። ምርጫ ቦርድ ዕውቅና ሲሰጠው የጨነገፈ ብዬ ማብራሪያ ሰጥቼበታለሁ። ምን ለማለት ነው በሚታወቅ አመክንዮ ብቻ መግለጫ ቢሰጥ እንደማለት።ዕውነት እንናገር ካልን የፖለቲካ ድርጅትን ፎርማት አስተካክሎ የተደራጀው ኢዜማ ነው። የፖለቲካ አቋሙም መብቱ ነው።
 
የሆነ ሆኖ ሰሞኑን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ምስላቸው የሰለቸው ስክሪን እፎይ ሲል ስዩሜ ደግሞ ቀጣዩ ጉዞ ትናንትን ቃኙቶ ዛሬን ነገን አመላክቶ። ደሬም ተነስታለች። የቀረ የለም ከ10 ያላነሱ የፖለቲካ ሰወች ሰብዕናቸውን እንዳሻው አድርጎታል። በልቶታል። እኔ እሱን እያዳመጥኩኝ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ነበር የሚታዩኝ።
 
የቻላችሁ ቅዱት። የቻላችሁ በጥሞና አዳምጡት። የቻላችሁ ስከኑበት። የቻላችሁ አደብ ሸምቱበት። የቻላችሁ አቅል አቅኑበት።
የእኔ ክብሮች ዘለግ ያሉ ሃሳቦችን ስለአቀረብኩኝ ደህና ሰንብቱልኝ። አሜን። ቸር ያሰማን። ቸር እንሁን። ቅንነትን እንመገብ።
«ስዩም ስለ ህወሓት ወረራ ያበጠውን አፈነዳው | የቦሌውን ጥቃት ዋና አቀናባሪ ታወቀ | መንግስት ያፈነው ከባድ ምስጢር ወጣ»
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
18/04/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።