ልጥፎች

ጋሞዎቹ ደሞቼ የፍቅራዊነት መርሆ ወንጌልም/ ቁራዕንም ናቸው።

ምስል
ብልህነት እንደ ጅረት ደግነቱ፤  የውስጥነት አብነቱ ከእትብቱ። „የእግዚአብሄር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦---- የሰው ልጅ ሆይ የወይን ግንድ በዱር ዛፎች መካከል ያለ የወይንሐረግ ፣ ከዛፍ ሁሉ ይልቅ ብልጫው ምንድር ነው?“ ከሥርጉተ©ሥላሴ  21.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት አላችሁልኝ? ደህና ናችሁ ወይ። ከሰሞናቱ የህፃናት፤ የእናቶች መከራ ጋር ሰውነቴን እዝሎት ስነበት፤ ምግብም በወጉ ሳልወስድ መዳህኒት እወስድ ስለነበር ተጎዳሁኝ፤ ከሁሉ ግን እንቅልፍ አልቦሽ መሆኔ ሰውኔትን አደከመው። እናላችሁ እንቅልፍ አጥቶ የሰነባበተው አካሌ ከአቅሜ በላይ ሆኖ ዲሞ ወጣ እና የማለዳ ተለምዶዬን ከውኜ ገደም ስል ከጥዋቱ ሦስት ሰዓት (09.00) እንደኛው አቆጣጠር አስከ ምሽቱ 1.00 ሰዓት (ከ19 ሰዓት) የት እንደወደቀኩኝ ሳለውቀው ተኛሁኝ። የሬቻም እልቂት መልዕክቴን ለተባባሩት መንግሥታት ልኬ ቤት መጥቼ ልክ እንደ ዛሬው እንዲህ ሆኜ ነበር። አድካሚ ሰሞን ነበር ያን ጊዜም። አድካሚነቱ በመንፈስ ነበር፤ ተስፋ ሲዝል፤ ራዕይ ሲጠወልግ፤ ያመናችሁት ባመናችሁበት ተገኘም አልተገኘም ከእንባ ጎን የመቆም አቅሙ በታመነው ልክ አለመሆን ራስን ይፈትናል። እኔ „ለማውያን ነኝ“ ስል ሰዋዊነት እና ተፈጥሯዊነት ነፍሱን የገዛው መንፈስ ነው በሚል ነበር። የሆነ ሆኖ ውስጤ መወስን ባቀታው ወጀብ ሲንገለታ ነው የሰነባባተው፤ መታመንን ለመስጠት ቅንነት አስፈላጊ ቢሆነም፤ ቅንነት ተቀባዩ ዋጋውን መመዘን ሲሳነው ስስጥን ያዝላል። ሰላም የአንድ አካል፤ ፍቅር የአንድ ወገን ቅንነትም የአንድዮሽ አይደሉምና። ፍቅር ስትሰጥ ተቀባዩ ለመስጠት መፍቀድ ብቻ ሳይሆን በዛ ውስጥ መገኘት ግድ ይለዋል። ብ

ዕውነት አንቀላፋ በጃዋር ቀያፋ።

ምስል
ውሎሽ? „ሁለት ዓይነት ሚዛን በእግዚአብሄር          ዘንድ አጸያፊ ነው“                 መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፳፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 20.29.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                   የስቃይ በረከት የዕንባ ዋናተኛ                   የፍትህ ውሏዋ የት ይሆን መገኛ?                   የጃዋር መ ጋ ኛ ለሽብር አይተኛ።                   ለጃዋር እርካታ የሚሊዮን ዋይታ፤              ለጃዋር ልቅና በመዲናዋ ላይ ንጹሃን ይሰዋ!                   ለጃዋር መታበይ አጀብ ነው ሁካታ ¡                   ለጃዋር ጭካኔ የመንግሥት ትርክታ!                    ለጃዋር ግነቱ ሚዲያ ክርፋቱ፤                    ለጆዋር ቅልቅል የሜጫ ቱማታ።                   ለጆዋር ምርቃና የእልቂት ሀተታ፤                   ለጃዋር ሠራዊት ፋክሊቲው ይዘጋ፤                   ይገዛ ይከመር፤ የሰጋት አለንጋ¡                  ለጆዋር ገረፍታ ጭብጫባ ሲቧካ፤                  ለጆዋር ዕውቅና ያዋጣል ብዥታ።                   ለጃዋር ንግሥና ህግጋት ይመታ¡                   ለጃዋር ዲስኩሩ ሚሊዮን ይምታታ!                   ለጃዋር ንግሥና የግራኝ ትዝታ!                   ለጃዋር ድንፋታ የእልቂት ሽውታ!                     ከጃዋር ሞቅታ የበቀል ገበታ፤            

በግንቦት 7 አይመሃኝ፤ ራሱ የችግሩ ጠላላ ከኦህዴድ ውስጥ ነው።

ምስል
ጮፍራራው ዕብለት። „ወርቅ እና ብዙ ቀይ እንቁ ይገኛል፤ የውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፲፭ ከሥርጉተ©ሥላሴ  20.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·        መነ ሻ። https://www.youtube.com/watch?v=FH6ngTrfYX4 Ethiopia: ጥቃትና ግጭት የቀሰቀሱ ቡድን አባላት ተይዘዋል ተባለ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ፤ እንደምን ያለ ዝልብ መረጃ ነው እኒህ የኦሮሞ ሊሂቅ የሚሰጡት። ምኑ እና ምኑን ነው የሚያገናኙት። ረግረግ። ·        ባጠ ቃላይ፤ እጅግ የሚገረሙ የለበጣ ሰብዕዊ መብት ረገጣዎችን እኛ አይደለነም እመኑን ነው ሳርቅጠሉ ላይ ሶኬት ማይክ ሰክተው የሚነግሩን። የሰኔ 16ቱ የሲቃ ድባባ፤ የቆሞስ ስመኛው በቀለ ራሱን አጠፋ ድራማ፤ ለቀበር የወጣው ህዝብ አንግልት እና እገዳ፤ የመስቀል አደባባይ የካሜራዎች ቀድመው መነሳት እና ሂደቶቹ፤ የሰሜን አሜሪካ ጉዞ ጋር የነበረው ግጥምጥሞሽ፤ የ አቶ ተስፋዬ ጌታቸው ህልፈት፤ ከዛ መልስ የተፈጠረው የተደሞ ሰሞናት ጭጭ ረጭ ያለው የመፈንቅለ መንፈስ ሙከራ የኩዴታ ምልክቶች ሆነው ነገር ግን „የቀን ጅቦት፤ በገንዘብ የተገዙ፤ ቦዘኔዎች፤ የጥፋት ሃይሎች ያሳደነዷቸው“ ጭፍርር ያለ ዕብለት ይደመጣል። አሁንም የሶሞናቱ ጉዳይም እንዲሁ። ምንጩ አንድ ነው። ግን ያ አንድ ነገር ወገን ሆነና እና እንዴት ከችሎት ጋር ይገናኝ። እንዴት ሚዛናዊ ፍትህ ያግኝ? የአቤል ጩኸት የፍትህ ያለህ ይላል። የሰኔ 16 የተከሳሾች የቀጠሮ መራዘም ጉዳይ ምንጩ ይኸው ነው። ምንአልባትም ዋና ወንጀለኞች ቦታ እስኪይዙ ድረስ ሊሆን ይችላል። „ሌባን ሌባ ቢሰርቀው ምን ይበጀው ነበር“ እንደሚበላው ጉዞው