ዕውነት አንቀላፋ በጃዋር ቀያፋ።
ውሎሽ?
„ሁለት ዓይነት ሚዛን በእግዚአብሄር
ዘንድ አጸያፊ ነው“
መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፳፫
ከሥርጉተ©ሥላሴ
20.29.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
የስቃይ በረከት የዕንባ ዋናተኛ
የፍትህ ውሏዋ የት ይሆን መገኛ?
የጃዋር መጋኛ ለሽብር አይተኛ።
ለጃዋር እርካታ የሚሊዮን ዋይታ፤
ለጃዋር ልቅና በመዲናዋ ላይ ንጹሃን ይሰዋ!
ለጃዋር መታበይ አጀብ ነው ሁካታ¡
ለጃዋር ጭካኔ የመንግሥት ትርክታ!
ለጃዋር ግነቱ ሚዲያ ክርፋቱ፤
ለጆዋር ቅልቅል የሜጫ ቱማታ።
ለጆዋር ምርቃና የእልቂት ሀተታ፤
ለጃዋር ሠራዊት ፋክሊቲው ይዘጋ፤
ይገዛ ይከመር፤ የሰጋት አለንጋ¡
ለጆዋር ገረፍታ ጭብጫባ ሲቧካ፤
ለጆዋር ዕውቅና ያዋጣል ብዥታ።
ለጃዋር ንግሥና ህግጋት ይመታ¡
ለጃዋር ዲስኩሩ ሚሊዮን ይምታታ!
ለጃዋር ንግሥና የግራኝ ትዝታ!
ለጃዋር ድንፋታ የእልቂት ሽውታ!
ከጃዋር ሞቅታ የበቀል ገበታ፤
ለጃዋር አብሮነት የዕንባ ስጦታ፤
ለጃዋር ልዕልና እምዬ ትደፋ!
አገርም ይፋታ።
ለጃዋር ቅዥቱ ሁሉም ያረግርጉ፤
ለጃዋር ብልጭታ ብአህዴን ኦህዴድ ሁሉም ያደግድጉ።
ለጃዋር ከፍታ አብሮነት ተዳፋ
ዕውነት አንቀላፋ በጃዋር ቀያፋ።
- · ለግራጫማ ሰብዕና ግማሽ ሰውነት የተጻፈ። 20.09.2018
ነፃነት ለድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ ህፃናት!
እግዚአብሄርን ባገኘው አቶ ጆዋር መሃመድን ስለምን እንደ ፈጠረው እጠይቀው ነበር። ይህ የዘወትር ምኞቴ ነው።
„ሁለት ዓይነት ሚዛን በእግዚአብሄር ዘንድ አጸያፊ ነው“
መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፳፫
የኔዎቹ እንበርታ እንጸልይ!
በቃችሁ ይበለን የምናምነው አምላካችን። አሜን!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ