በግንቦት 7 አይመሃኝ፤ ራሱ የችግሩ ጠላላ ከኦህዴድ ውስጥ ነው።

ጮፍራራው ዕብለት።
„ወርቅ እና ብዙ ቀይ እንቁ ይገኛል፤
የውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።“
መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፲፭

ከሥርጉተ©ሥላሴ
 20.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


  • ·       መነሻ።

Ethiopia: ጥቃትና ግጭት የቀሰቀሱ ቡድን አባላት ተይዘዋል ተባለ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ፤

እንደምን ያለ ዝልብ መረጃ ነው እኒህ የኦሮሞ ሊሂቅ የሚሰጡት። ምኑ እና ምኑን ነው የሚያገናኙት። ረግረግ።
  • ·       ባጠቃላይ፤
እጅግ የሚገረሙ የለበጣ ሰብዕዊ መብት ረገጣዎችን እኛ አይደለነም እመኑን ነው ሳርቅጠሉ ላይ ሶኬት ማይክ ሰክተው የሚነግሩን። የሰኔ 16ቱ የሲቃ ድባባ፤ የቆሞስ ስመኛው በቀለ ራሱን አጠፋ ድራማ፤ ለቀበር የወጣው ህዝብ አንግልት እና እገዳ፤ የመስቀል አደባባይ የካሜራዎች ቀድመው መነሳት እና ሂደቶቹ፤ የሰሜን አሜሪካ ጉዞ ጋር የነበረው ግጥምጥሞሽ፤ የ አቶ ተስፋዬ ጌታቸው ህልፈት፤ ከዛ መልስ የተፈጠረው የተደሞ ሰሞናት ጭጭ ረጭ ያለው የመፈንቅለ መንፈስ ሙከራ የኩዴታ ምልክቶች ሆነው ነገር ግን „የቀን ጅቦት፤ በገንዘብ የተገዙ፤ ቦዘኔዎች፤ የጥፋት ሃይሎች ያሳደነዷቸው“ ጭፍርር ያለ ዕብለት ይደመጣል። አሁንም የሶሞናቱ ጉዳይም እንዲሁ።

ምንጩ አንድ ነው። ግን ያ አንድ ነገር ወገን ሆነና እና እንዴት ከችሎት ጋር ይገናኝ። እንዴት ሚዛናዊ ፍትህ ያግኝ? የአቤል ጩኸት የፍትህ ያለህ ይላል።
የሰኔ 16 የተከሳሾች የቀጠሮ መራዘም ጉዳይ ምንጩ ይኸው ነው። ምንአልባትም ዋና ወንጀለኞች ቦታ እስኪይዙ ድረስ ሊሆን ይችላል። „ሌባን ሌባ ቢሰርቀው ምን ይበጀው ነበር“ እንደሚበላው ጉዞው ሁሉ የኩሸት ነው።

ሲያልፍ ደግሞ ሁሉም መጸሐፍ ጸሐፊ ሆኖ ከወንጀሉ ነፃ ነኝ ይመጣል። ልክ አሁን አቶ ታማራት ላይኔ ሰቆጣ ላይ የወርቅ ከባ ተጎናጽፈው እንደ ተከበሩት ማለት ነው።

ትናንትም ደፍሮ እኔ ነኝ ማለት ሳይቻል በጅምላ ይቅርታ ጠይቀናል መባል ችግሩ ይህ ነው። ወቃሽም ነቃሽም ፍርድ እና ተፈራጅ ሳይኖር በጀምላ ለ27 ዓመቱ ጥፋት እኛ ሁላችን ተጠያቂዎች ነበርን በቃ አታንሱት ተባለ እና በዛ ታለፈ። እንደ ቅንጅቱ መራራ ሰንብት። አሁን የዛ ቅጥያ ነው። ከ5 ዓመት በኋዋላም ይህ መሰል ትርኢት ይፈጸማል። የራስን ወገን አጋልጦ ላለመስጠት የሚደረግ መሽኮርመም ነው።

ወያኔ ሃርነት ትግራይ በአውራ ፓርቲነት ሲገድል ገዳዩም፤ መርምሪውም፤ ዳኛውም፤ አቃቢ ህጉም፤ ራሱም ህገ መንግሥቱም በራሱ አምሳል የተቀረጸ ስለሆነ እራሱን በራሱ ለማጥፋት፤ ለመክስ ፍርድም ለመስጠት ተቸገረ። አሁን ያለውም የኦህዴድ ችግር ይኸው ነው። ህግ መንግሥቱንም አትንኩት የሚሉት ለዚህ ነው።

ለውጡን ፈልገዋል ሥርልጣኑ ከ ወያኔ ወደ ኦሮሞ እንዲሸገገር፤ ኦነጋውያን ግን ለውጡ ከተገኜ በኋዋላ ያን ዲታ  የአብይ መንፈስ የኢህዴግ ሃብት እንዲሆን በህብረት አልፈለጉትም፤ እሱን በመሰለ አቀራረብ በመፍንቅለ መንግሥት የራሳቸውን መንፈስ ማስቀመጥ ይሻሉ። እንጂ ጠ/ ሚሩ ኦሮሞ ናቸው፤ ምክትል ጠ/ ሚሩ ኦሮሞ ናቸው፤ ፕሬዚዳንቱ ኦሮሞ ናቸው፤ ሌላው ቀርቶ በመንግሥት መሥርያ ቤቶች ያሉ ሚኒስተሮች የሌላ ብሄረሰብ አባል ቢሆን ጉዝጓዙ ምክትሉ ኦሮሞ ነው። አዲስ ላይም እንሱው ናቸው። የአዲሱ ሹመት ሂደት ድልድል እንዲህ ነው የተዋቀረው። 
እኛም አቅም ያለው ኦህዴድ እሱ ነው አትንኩት ድርሽ አትበሉበት ባዮች ነን። ምክንያቱም አማራ ተቀብሮ ነው የኖረው አሁንም በዛ እንዲቀጥል ነው ስትራቴጁ፤ ትጋርዮች ደግሞ የሚበቃቸውን ያህል ይዘዋል ስለዚህ የለውጡ ሞተር ካለበት ይሰከን ብለን በህሊና ፈረምን። 

ገራሚው ነገር ኦህዴዶች ሁሉም የኦነግ ዓርማ ስለምን ከተሰቀለበት ወረደ ነው የሚሉት፤ በሌላ በኩል በሰንደቅዓለማ መከራከረ የማይረባ ተራ ነገር ነውም ባይ ናቸው። ሉ ዕላዊነት ማለት ምን ማለት ስለመሆኑም?

 የኢህአዴግ የግንባሩ አባል የሆነው ኦህዴድ የኮምንኬሽኑ ሃላፊ ዶር ነገሬ ሌንጮ ሳይቀሩ የ ኦነግ አርማ ስለምን ተነሳ ባይ ናቸው። የኦነግን ጅረቶች የማሰባሰብ ዓላማው ትጋቱ ለዚህ መስል ከሆነ?

 መንፈሱ አቅም እና ጉልበት እንዲያገኝ እና ዓላማ እና ግቡን እንዲያስፈጽም እንጂ ሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶች ኦፌኮን ሆነ ኦህዴድ፤ ኦዴግን፤ ኦነግን እንደ አንድ ተፎካካሪ ተወዳድረው አሸናፊ ሆነው የመውጣት ህልም የላቸውም። ለዚህ እኮ ነው ኦቦ ሌንጮ ለታ ለጥ ብለው እዬተዝናኑ በተያዘላቸው ሆቴል የሚዘባነኑት ቱክ የለ ምን የለ። አልተመዘገቡም ነበር እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ይህቺ የመስከረም ጉባኤ እዬተጠበቀች ... ያው ሙሉ መረጃ አላቸው። 

ዶር ነገዎ ዲማ፤ ዶር ሌንጮ ባቲ፤ ኦቦ ሌንጮ ለታ፤ ዶር መራራ ጉዲና፤ ኦቦ በቀለ ገርባ፤ አቶ ጃዋር መሃመድ፤ ፕ/ ህዝቃኤል ጋቢሳ፤ ጄ/ ከማል ገልቹ፤ አቶ ዳውድ ኢብሳ፤ ኦቦ አዲሱ ረጋሳ ሁሎችም የሚፈልጉት የጠ/ ሚኒስተርነቱን ቦታ ነው፤ ሌላም አገር ያልገቡ አሉ፤ ከኢትዮጵያ ጋር መቀጠሉ ግድ ከሆነ። ከዛ  በማንኛውም ዘርፍ የ150 ዓመት ህልም ይቀጥላል። 

ውጭ አገር የሚኖሩ እኔም አቅም አለኝ ባዮችም ቦታውን በእግር በፈረስ የሚፈልጉት አብይን እስከ ምርጫው ድረስ እንጂ ከዚያ ወዲያ አያስፈልገንም የሚሉ በዓለም አቅፍ ሚዲያ መግለጫ የሰጡ በእልህ እና በቁጭት የተናገሩ ሊሂቃንም አሉ እስኪገርመኝ ድረስ። 

ለነገሩ በዚህ ሰሞናት መቼም ልብ የለውም እንጂ የግንቦት 7 ብቸኛ ታማኞቹ እዬከዱት ስለመሆኑ ልብ ሊለው ይገባል። እንግዲህ በዚህ ውስጥ የዶር ለማ መገርሳ የጸና የኦሮሞነት መንፈስ ወደዬትኛው አቅጣጫ እንደ ሆነ ወፊቱ ትመርምረው የቤት ሥራውን ለእሷ ልስጠው።

ለዚህም ነው ቀደም ባሉት ሰሞናት ለውጡ ሊቀለበስ ይችላል ሲሉ ዶር ነግዎ ዲማ የተናገሩት። ይተዋወቃሉ። እኔም አስቀድሜ ይህንኑ ጽፌበታለሁ ሌቦች ተፈቱ ተብሎ ቡራ ከረዩ ሲባል። በሌላ በኩል ግን በአንድ አጀንዳ መስማማት አይችሉም። ሁሉችም ገዢ፤ ንጉሥ መሆን ነው የሚፈልጉት። 

በዚህ ማሃል ለእነሱ የሹመት ምርቃን ሲባል የኦሮሞ እናት ለእርድ ልጆቿን በዬዘመኑ ታቀርባለች ነገ። ዛሬ አንድ ላይ ናቸው በህውከቱም ተባባሪዎች ናቸው። ነገ ግን 6ወራት አይሞላም ቢገነጠሉ ብትንትናቸው ሲወጣ። ሌላ ሰውም ቢያሰቀምጡ ዶር አብይ አህመድ ቢለቁላቸው ማለቴ ዶር ለማ መገርሳ ይሁኑ ኦቦ አዲሱ ረጋሳ ወይንም ወ/ሮ አዳነች አበቤ?

ታስታውሱ እንደሆነ ዶር አብይ አህመድ ለእጩ ጠ/ ሚር ሲወዳደሩ የዲያስፖራውም የአገር ውስጡም ፖለቲካ በጫና ብዛት እንዲሰናከል በአንድ ላይ ተግተው ነበር። አሁን ደግሞ አገር ቤት በገቡ ማግስት ከሁለት ተከፍሏል። ነገ ደግሞ ከ6 ይሆናል። 

የትውልድ ብክነት ብቻ ሳይሆን በ2030 ኢትዮጵያ ትከስማለች ትንቢት ይፈጸም ዘንድ። ለነገሩ ለኦሮሞ ሊሂቃን ጉዳያቸው አይደለም። የሰብዕዊ መብት ተሟጋቾችም አይደሉም። ቢሆኑማ ቢያንስ የወ/ሮ ታዱሉን ዕንባ ማድመጥ በፈቀዱ ነበር።

ለራሳቸው ብቻ በተኮረኮደ ጥብቆ ፖለቲካ የታሰሩ ናቸው። „ትልቅ ነን ገዳን ለዓለም አውርሰናል፤ ጉድፌቻ፤ ሞጋሳ ፈጣሪዎች ነን“ ይሉናል፤ በመሆን ውስጥ ግን የሉም። በደርግ ጊዜ አርባጉጉ አካባቢ የነበረውን አሰቃቂ ግድያ በታሪክም አልሰማሁትም። መንገድ ላይ ፈንጅ በመቅረብ ስንት የራስ ወገን አልቋል። በወያኔ ዘመን ደግሞ በመንግሥት ተጋሪነት፤ ባለድርሻነት ያሻቸውን አደርገዋል ኦነጋውያን። ነገም አማራ በመስዋዕትነቱ ያመጣውን ለውጥ ዘብ ካልቆምለት መጪው ዘመን መራራ ይሆናል። አሁን አቅሙን አይተውታል እና። 

 አርሲ ሦስት አውራጃ ነው የነበራት። ጭላሉ፤ ጢቾ እና አርባጉጉ። ከአሰላ ጋር የሚያገናኝ ጢቾ ሆነ አርባጉጉ የረባ መንገድ አልነበረም። አውቶብስ እራሱ ከሮቤ አሰላ አልነበረም።  

 በቢሮ መኪና ነበር ለስብሰባ የምንሄደው።ይህን የመሰለ ሰቆቃ ያለበት ህዝብ ያ የሰለጠን ገዳን አበረከትን፤ ጉድፊቻን የተቀበል ስለሚባለው አጋጣሚው ሲገኝ ከቃል ያለፈ ህሊናን የለወጠ፤ በመንፈስ የታመቀውን ጥላቻ እና እራሰን አሳንሶ የማዬት ችግር ጋር ሊፋቱ ባስቻለ ነበር።

ከባህርዳር የድጋፍ ሰልፍ ማግስት አንድ የኦነግ ክንፍ ኢትዮጵያ ሲገባ አውሮፕላን ሲወርድ ቃለ ምልልስ ሲደረግለት አርማውን ለብሶ ነበር። አርማ ስለለበስከው ሳይሆን ያ የባከነው ትውልድ ዳግም እንደይባከን የመፍትሄ አካልነት ነበር የሚያስፈልገው። ያ በዬዘመኑ የጎዳህውን ማህበረሰብ ዝቅ ብለህ ለማገልገል መትጋት ነበር ቁም ነገሩ። ዘመን የማያስትምር ከሆነ ሽበቱም የሆድ ካለሆነ ተበጥብጦ አይጋት ነገር። 

የሞት ፉክክር፤ የፋሽስትነት ፉክክር፤ የአረመኔነት ፉከክር ተጀምሮ እስኪጨረስ የኦነግ ዓላማ ነው። ጭካኔያቸውም ልክ የለውም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሴራ ምንጭ የኮንፊደንስ ማነስም ጉዳይ ነው። የአቶ ጀዋር ከዚህ የሚለዬው ከሚገባው በላይ የተንጠራራ ስለሆነ ፍጹማዊ አንባገነን እና ፋሽታዊነት ስሜት ያደረበት ነው። የልሎቹ ደግሞ ፉክክር ተኮር ነው። ሁሉንም አንድ ላይ ጠቅልለው ነው የሚታመሱት።

አሁን ዶር ዲማ ነገዎ ሰማያዊ ፓርቲን „የአማራ ድርጅት“ ሲሉ ዘልፈውታል። ከዛ ቆፈናቸው አልወጡም ማለት። በዚህ ዕድሜ እና በዚህ የተመክሮ ዘመን የአንድን ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ መስፈርት እንዲህ አንጋለው ማዬት አለመታደል ነው። ከመነሻቸው ላይ እንደ ኩሬ እውሃ እዛው ላይ መታቆር። ዘመኑ ሄዶ አርጅተዋል አስተሳሰባቸው ግን አንዲት ስንዝር ፈቅ አላለም።
  
ኦቦ በቀለ ገርባ የ150 ዓመት ትግላችን ለድል በቃ አሉን። ያው እዛው ላይ ነው ያሉት ማለት ነው። እራሱ ብጥስ ቅንጥስ ያለው አረማመዳቸው ይመጣብኛል።  ዶር መራራ ጉዲኒ በበኩላቸው ኦህዴድ የታሪኩን ፈተና ማለፍ አይችለውም ባይ ናቸው።

አንድ አውሮፓ ያሚኖሩ ቅን የኦሮሞ አክቲቢስት በገበታ ሚዲያ ከአማራ አክቲቢስት ጋር ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ኦማራን ሃሳብ ያፈለቁ ናቸው፤ ጉዳይን ሲያማክራቸው ለእነ አቦ ሌንጮ ለታ ገና ያላታሸ ነው ግርድፍ ነው እንዳሏቸው ገልጸዋል፤ አሁን ቃለ ምልልሱ ተሰርዟል። ያው በዬሁኔታው ፍንጪ ይሰጣል። መቼውም የሚታረቅ ነገር አይደለም።

ቅንነታችን የእኛን ብወደውም ጊዜ እና ትውልድ ከማባከን ሌላ ትርፍ የለውም። አክቲቢስት መስፍን ፈይሳ የሚቃጠልበት ምን አለበት በሆዳችሁ ብትይዙት እያለ ነው። ያው ነው እኮ መንገዱ ገና ሲጀምሩት ጠረኑ ይታወቃል። በዚህም በዚያም ብሎ „ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም“ ነው።

አሁን አቶ ጃዋር መሃመድን የፈለገ ካባ ብታለብሰው የእስልምና መንግሥት በኢትዮጵያ ከመመስረት ዓላማው ንቅንቅ አይልም። ሁሎችም እንዲሁ ናቸው። እኔ ከአውሮፓው ህብረት ጉባኤ ወዲህ ተለወጡብኝ እላለሁ ዶር መራራ ጉዲና፤ ነገር ግን ይህን እኛ ሳናውቀው ኖረን እንጂ ከልጅነት እስከ እወቅት ኦሮሞ ገብ ሥልጣን እስኪመጣ ድርስ የጠበቁት ጉዳይ ነው፤ ለዚህ ነው ኦቦ በቀለ ገርባ „ስትራቴጂዋ ትግል ስናደርግ ቆይተን ያሉት።“

  ሌላው ቀርቶ ዶር መራራ ጉዲና ህዝብ ንቅንቅ ብሎ አንቦ ወጥቶ ሲቀበላቸው „ተቀላለቅሏል የትኛው የእኛ ደጋፊ መሆኑን ማወቅ አልቻልነም“ ብለው ነበር። ይህ ማለት ኦሮሞ አንድ በሆነ መንፈስ አንዲቀጥል አይፈልጉም ማለት ነው ሊሂቃኑ። በሳቸው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ለመገኘት የግድ ኦሮሞ መሆን አያስፈልግም፤ መሪ ናቸው እንደ መሪ ሁሉም ወጥቶ ቢቀበላቸው ክብር ነበር። እኔ የእናንተ ሳልሆን ደስታው ደስታችሁ ሊሆን አይገባም ዓይነት። 

እነሱ የተከተረ ፍላጎት እና ዓላማ ነው ያላቸው። ይህን ይዘው እኮ ነው ብሄራዊ መሪ መሆን ያቃታቸው።  የሁሉም መንፈሱ ግን ኦነጋውያነት ነው። ውስጣቸውን ምን እንደሚፈልጉ ራሱ የሚያውቁት አይመስለኝም፤ ማለቴ በተለያዬ ድርጅት መሆን አያስፈልጋቸውም ነበር - አገር ለመገንጠል ከሆነ፤ ስለምን ያታልሉ።

 ሌላው እህቴ እና በስልክ በጋራ የሳቅንበት 30 ሺህ ነፍስ ከእስር ተፈቶ ቃለ ምልልስ ሲደርግላቸው "መኪናዬ እስካሁን አልተፈታችም" ያሉት ቁሳዊነት ነው። ለእኔ የስኳር በሽተኛ ስለሆኑ ዘነዘናቸው ነፍሳቸው ብቻ ነው የሚስፈልገኝ እንጂ ቆርቆሯቸው አይደለም። እሳቸው ደግሞ ከነፍሳቸውም፤ ከ30ሺህ ወገን መለቀቅም በላይ አንድ ቆርቆሮ ጉዳያቸው ነው። መሪነት እንዲህ ይገለጣል?

ለነገሩ የቢሮ አደረጃጃታቸው አገር ለመምራት ለዛው ዝብርቅርቁ የወጣ መሆኑ ለመሪነት ፖለቲካ የሚከብድ ይመስለኛል። ቢሯቸው የተዘረከረከ ነው በስንተኛው ዘመን ላይ እንዳሉ ራሱ ግምት ያስገባል።

ምን አልባት ለዶር መራራ ጉዲና የማይመቸው እስላማዊነት ሊሆን ይችላል። ከዚህ ባለፈ ደግሞ ሸዋዊነት የአንቦ ዋርካውም ጉዳይ አለ።  ወለጋ በሚመለከት የደንቢ ዶሎው ጉባኤ ምስክር ነው፤ ለምን መጣህ አብይ ከዚህ ነበር። ደንቢሻ የደንቢ ንጉሥ ብቻ ነው የምትፈልገው። ይህንም ጽፌበታለሁኝ። አርሲና ባሌ ደግሞ ሌልኛም ነው። 
  
የጃዋር ክንፍ በድል ካጠናቀቀ ወዬልሽ ቤተሳይዳ ነው። እራሱ የእስልምና እምነት ተከታዩ ፍዳውን ያያታል። የእስልምና ተከታይ ተዋናይ፤ የጥበብ ቤተኛ ማዬት በፍጥነት ይከስማል፤ አብሶ በሴቶች ነፃነት ዙሪያ የገዘፉ ፈተናዎች ይመጣሉ።

ጭካኔው ደግሞ እኛ እንደምናስበውም አይደለም። ቦኮ ሃራም እኮ ሲጀምረው እንዲህ ነው። እና ... አቤቶ የኢትዮጵያ መንግሥት ሱማሌ ላይ አልሸባብን አጋዬሁ እያለ የራሱን ገመና ተሸክሞ ይፈካክራል፤ ራሱን እያፈረሰ ህዝብ እያስጨፈጨፈ በግንቦት 7 ማመካኘት ያው ጉዞው ወደዛው መሆኑን የታወቀ ነው፤ የተገባ አይደለም። ጠናና ምልከታም ነው። 

ቀጣዩ ነገር ከአቅሙ በላይ ለሆነው ጉዳይ ሁሉ ኦህዴድ ሃይላዊ እርምጃ ወሳጅ ሆኖ ወደ ፍጹም አንባገነናዊነት ያመራ እና አብይ እና ፍቅራዊ ስብከት የግድግዳ ላይ ጌጥ ብቻ ሆነው ይቀራሉ። አብይና ይቅርታም መራራ ስንብት ልክ እንደ ቅንጀት ያደርጋሉ። በግርግር ወያኔ ሃርነት ትግራይ ስለቴ ሰመረ ይሆንለታል። በሌላ በኩል ለጃዋርያን ደግሞ ጉሮ ወሸባያ ነው ... 

„ቁልጭ ያለው ነገር አዲስ አባባ በቀለበት ውስጥ ነበረች ብንፈልግ አሁንም ማን ከልካይ አለኝ፤ ያለኝ ሥልጣን ይበቃኛል የጦር አዝማችነቱ ማለቱ ነው አቶ ጃዋር እሱን ዙፋን ደፍተህ እሱን ብትነኩት ዋ ተብለህ፤ በዚህ በቅደመ ሁኔታ አስረህ እና ታስረህ እንዴት ስለ ፍቅር ስለሰላም ስለ አብሮነት ይሰበካል። 

  • ·       ንጩ የቦከሃርም ንድፈሃሳብ ይህ ነው። ኦህዴዶች ድፈሩት።
ለነገሩ ጠ/ ሚር አብይ አህመድን ስለማስቀጠላችሁ ራሱ አይታወቅም። ብቻ ምረጡ ወይ አቶ ጀዋር መሃመድን እና የቡድኑን አባላት አቦ በቀለ ገርባን፤ ፕ/ ህዝቃኤል ገቢሳ ለእኔ እንኳን ስታሊንን ነው የሚመስሉኝ ወይ ደግሞ ጠ/ ሚር አብይ አህመድን።

ከዛ የለዬለት የሃይል አሰላለፍ ይኖራል። ብአዴን ላይ በአቶ ንጉሱ ጥላሁን የሚመራ አንድ ቡድን አለ፤ ኦህዴድ ደግሞ በኦቦ አዲሱ ረጋሳ የሚመራ ሌላ ቡድን አለ። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ላይም ቢሆን በአቦይ ስብሃት ነጋ እና በአቶ አባይ ወልዱ የሚመራ ቡድን አለ። በዚህ ላይ ቲም ቦኮሃርም ሲታከልበት ….  


የመፈንቅለ መንግሥቱ መሰረታዊ ጉዳይ ያለው ከዚህ ጭብጥ በዚህ ሊንክ ውስጥ ነው። ምን ዳር ዳር ሻታ ያዞራችሁዋል? 
ከጃዋር መሀመድ ጋር የተደረገ ቆይታ በናሁ ቲቪ ብቻ!
Interview with Jawar Mohammed only on Nahoo TV!
ጀዋር መሐመድ ዛሬ . ውስጥ ስለተፈጠረው ግጭት የሰጠው መግለጫ
Ethiopia: የኦፌኮ ምክትል ልቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ OMN ጋር ያደረጉት ቆይታ

·      ወንጀል ማሽሞንሞን ህግ ተላላፊነት ነው።

አይሽሞንሞን ኢ - ሰብዕው ወንጀል። ቆቅ ሊለኝ ነው እኔ መግለጫው፤ ቃለ ምልልሱ። በቃ ፌክ ብቻ። „በገነዘብ የተገዙ የጥፋት ሃይሎች" የፈጠሩት ሳይሆን የመፈንቅለ መንግሥት ሂደት ነው … ከሆነ ሀጂ ጀዋርን ታስቀምጥላችሁ ወይንም እሱ የፈቀደውን፤ በስተቀር ደግሞ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች።

አዲስ አባባ ላይ ድላቸውን አክብረው የሄዱት ሁሉ የመንፈስ ቦንብ በዬአካባቢያቸው ያፈነዱ ዘንድ ተሰናድተው ነው ወደ ቀያቸው የተመለሱት፤ ሐዲዱን ፈጣሪው ኦህዴድ ነው። ታሪኩ ይሄው ነው።

በዚህ ውስጥ ግንቦት 7 የለበትም። ካለ ሃጢያቱ አይወነጀልም። ይህን ያህል አገር የማፍረስ ተልዕኮም ግንቦት 7 የለውም። ከቀስተ ደመና እስካሁን ያለው ታጋድሎ ፕ/ ብርሃኑ ነጋን ማንገሥ ብቻ ነው። አማራ ያልሆነ ካቢኔ መገንባት። 

ከዚህ በመለስ ሌላ ተልዕኮ የለውም። ፓሊሲ የለውም ግንቦት 7። ስለ ሉዕላዊነት ቢጠዬቅ መልስ የለውም። ስለ ኢኮኖሚ ቢጠዬቅ መልስ ማፊ ነው፤ ቀድሞ ነገር በራሱ ሃሳብ ውስጥ ኑሮ የማያውቅ ድርጅት ቢኖር ግንቦት 7 ነው። አንድም የዘለቀ ድርድር እኮ ኑሮት የማያውቀው ለዚህ ነው።

„ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ“ ነው አሁን የሆነው። ባለቤቶቹ እራሳቸው ኦህዴዶች ናቸው። ኦህዴድ ራሱን ያጥራ። 

አንድ ነገር ግን አዲስ አበባ በኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ ላይ የኦነግ አርማ ካልተውለበለ እያለ የሞገተ ድርጅት ስለምን ጅማ ላይ በሚያካሄደው ጉባዔ ላይ በውስጡ የከተመውን በእንቁላሌ ሸማ ሸምኖት የኖረውን አላደረገውም ኦህዴድ። ማንን ለማታለል ነው? 

ደግሞስ ያ ሁሉ ዲፕሎማት እያለ አገር የፈረስ ይመስል ያደረገውን ጅማ ላይ ቢያደርገው ምንስ ሲገደው ነውና? ማንስ ነኪ ኖሮት? ጄኒራል ጃዋር ከሆነ ትእዛዙ በሪሞት ኮንትሮል ነው ...  

ግን ቀጣዩ የኦህዴድ ሊቀመንር አቶ ጃዋር የፈረመላቸው እና የኮንፒተር ሽልማት ያበረከተላቸው ዶር ለማ መገርሳ? ኦቦ አዲሱ ረጋሳ? ወይንስ በሃሳቡ የሰረዛቸው፤ ፈጽሞ ዓይናቸውን ለማዬት የማይፈቅደው ዶር አብይ አህመድ?

በግርባው በብአዴን በኩልም አቶ ጃዋር መሃመድ የፈረመላቸው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ወይንስ መሟያው ዶር ገዱ አንዳርጋቸው? እሱ እኮ ነው እዬመራው ያለው።

መቀሌ በራሱ መንፈስ ነው፤ ብአዴን ግርባው ግን በአቶ ጃዋር መንፈስ ውስጥ ነው። ለዚህ ነው የተፈቀደላቸው አቶ ንጉሱ ጥላሁን እንዲገኙ የተደረጉት አርሲኛ … ኬኛ! እራሱ ዶር አብይ አህመድ በዙሪያቸው ምን እዬተካሄደ እንደሆነ ልብ አላሉትም። የሚገርመው ይኸው ነው።

አንድም ቀን አቶ ንጉሡ ጥላሁን ዶር አብይ አህመድ በሚገኙበት ቦታ ላይ ተገኝተው አያውቁም። ይጸዬፉታል። እኔ አይቼ አላውቅም ለቅሶ ቤት እንኳን አብሮ ለመሄድ አይፈቅዱትም፤ ድጋፍ ሰልፉ ላይም አላዬኋዋቸውም። ለቅጽበት ባርዳር ላይ ለትውውቅ ሲሄዱ እንደ ማስተዋቅ አድርጓቸው ብቅ ብለው ነበር የትውውቁ ጊዜ። ስለምን? ኦነጋውያን ይከፉባቸዋል እነ የቦኮሃራም … ቀሳፊ መናፍስት ቢልኩስ?

ሌላው ደግሞ ገራሚው ነገር አዲስ አባባ ላይ የጥላቻ ቦንብ ታጥቆ እንዲሄድ የተደረገው ዬዞን ተወካዮች አሁን ደግሞ አቶ ጀዋርን መንፈስ ቀሪዎቹ ጅማ ላይ እንዲገናኙ ተደርጓል። እሱ ባገኛት ደቂቃ ሁሉ መርዙን ይረጫል። አማራ መሬት እንዲሄድ የተደረገው እኮ ውርስ ጃዋርውያን ለማሳከት ብቻ ነው። 

አማራ በአብይ መንፈስ ላይ ሸፍቶ የግራኝ መሃመድን ሌጋሲ እንዲደግፍ ነው፤ ከዛ ያገኛታል አማራ … 

የአቶ ንጉሡ ጥላሁን ዕውነት ይህ ነው። አቶ ንጉሱ ጥላሁን ኮስትርነታቸው ለጭቃ እሾሕነት እያዋሉት ነው። አማራ ወዮልህ ነው እሳቸው ወደፊት ከመጡ?

አማራ መሬት ላይ አመጽ እንዲነሳ ነው አሁን ቤተክርስትያን እንድትደፈር የተደረገው። አመጽ እርቧቸዋል።

ይህን ሴራ በመረዳት መሳሪያ ባለመሆን አደብ ገዝቶ የቦኮሃራም ግርፎች ነጥረው ይወጡ ዘንድ በጸሎት መትጋት አለበት - አማራ። ከዚህ ላይ „ደምጻችን ይሰማ“ የለበትም፤ ፖለቲካዊ ጥያቄም የለውም። አማራ ግን ደሙን ከፍሎ ላመጣው ለውጥ ዘብ መቆም ግድ ይለዋል። በስተቀር ግን ዘመነ ጉዲት ነው የሚሆነው። ተራፊ የለም በጃዋር ያን፤ በህዝቅኤላውያን ... ጦሮ ...

„ለውጡ ይዞት የመጣው ሰላም ብቻ ሳይሆን ፈተናም ነው“ ባይ ናቸው አቶ ንጉሡ ጥላሁን እሳቸው አንድ ውሃ ያዘለ ተራራ እና ፈተና መሆናቸውን እኔ ብነግራቸውስ? የጃውራውያን ህልመኛ ናቸው እኮ አቶ ንጉሡ ጥላሁን። ይህን መቼም አይክዱትም፤   

ፍትህ ለነፃነት!

የኔዎቹ ኑሩልኝ።


መልካም የማስተዋል ጊዜ።  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።