#ትውልዱ።

 

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
እንዴት አደራችሁ ማህበረ ቅንነት? #ሰውኛነት በብዙ #መታገስን ይጠይቃል። ዕውነት ለመናገር በብዙ እንደምትታገሱኝም አውቃለሁኝ። እዬጎዳኋችሁ መሆኑን አውቃለሁኝ። ብዙ ጊዜ #በተጎዱ አመክንዮወች ዙሪያ ስለምሰራ። ለዚህም ነው አልፎ አልፎ ፎቶዬን እምለጥፈው። ስለሚጨንቀኝ። ሁልጊዜ መርዶ፤ በዕንባ እና ጭንቀት ላይ አተኩሮ መሥራት ለውድ ቤተሰቦቼ ከባድ እንደሚሆን አውቃለሁኝ። በደንብ ነው እምረዳው። 
 
ነገር ግን ትውልድን እንሰብ ካልን የትውልድን ተስፋ #የሚያጫጩ ገጠመኞችን ሁሉ መጋፈጥ ግድ ይለናል። በዛ ዙሪያም የወረት ሳይሆን በተከታታይ ልንተጋ ይገባል። #ዩንቨርስቲወች አደራ ማውጣት አለባቸው። ይህ መብታቸው ሳይሆን #ግዴታቸውም ነው። በአደራ የተሰጡ ልጆችን አደራ #አለማውጣት ኃላፊነት እና ተጠያቂነት ከሚሰማው የአንድ አገር መንግሥት የሚጠበቅ ባለመሆኑ ነው ሙግቱ። አንድ ወላጅ በብዙ ፈተና ውስጥ ሆኖ ወልዶ፤ አሳድጎ #አስብልልኝ ብሎ ልጅን ያህል የመኖር ተስፋ፦ አደራ ሲሰጥ አደራን መወጣት ግድ ነበር።
 
ያ አደራ ሲታመም ለምን ብሎ መጠዬቅ ደግሞ የእኛ ጉዳይ ነው። ለዚህም ነው ምላሽ እስኪገኝ ድረስ ጥያቄዬን ሳላቋርጥ ሳቀርብ የቆዬሁት። እርግጥ ነው አድካሚ ሊሆን ይችላል። እናንተን ውድ ቤተሰቦቼንም መጉዳቴን አውቃለሁኝ። ካልተደከመ #ማስበል አይገኝም።
 
የእኔ ልጅ ቢሆን?
የእኔ እህት ብትሆን?
የእኔ ታናሽ ወንድም ቢሆን?
 
የእኔ ታናሽ እህት ብትሆን ብሎ ማሰብ ይገባል። የሚገርማችሁ ለቤተሰቡ ሩህሩህ የሆነ ሰብዕና በዚህ አገራዊ፤ ብሄራዊ ጉዳይ ግን ቸለልታ ሳይ ህመሙ የፈፃሚው ብቻ ሳይሆን ሰውኛነት የነጠፈው በሌሎችም ላይ እንደ አለ አስባለሁኝ። ጭራሽ ምንም የማይመስላቸው ሰወች ይገጥሟችኋል። 
 
በውነቱ ሰው ለሆነ ሁሉ ጉዳዩ እረፍት የሚሰጥ አይደለም። ሰሞኑንም #ከ100 የማያንሱ ተጓዦች ታፍነዋል። መከረኛ የኢትዮጵያ ሹፌሮችም ኑሮ ቀራንዮ ላይ ነው። ቤተሰቦቻቸውን በገንዘብ #እንዲገዙ የተጠዬቁ ቤተሰቦች #ለልመና መንገድ ላይ ወጥተዋል የሚባል መረጃ አድምጫለሁኝ። 
 
ይህም ደግሞ ሳይፈቀድ እንደ #ታሰሩም ሰምቻለሁኝ። መረጃው ምን ያህል ትክክል ነው የሚለውን አንባቢ ያጣራ።
ይህ መከራ መቼ ይሆን ይቆማል ግን የሁሉም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ሊሆን ይገባል። ጉዳዩን #ቢሸሽም ጊዜ ራዲዮሎጂ ነውና ጊዜ ይገልጠዋል። ጉዳዩን ማድመጥ የማይፈልጉ #ሽሽት ላይ ያሉ ወገኖችም ቢሆኑ ዕውነት እና ፋክት ጊዜያቸውን ጠብቀው እራሳቸውን እንደሚያስከብሩ ሊረዱ ይገባል። ዶር ገዱ አንዳርጋቸው የልጆቻቸው መታገት አልነበረም ተርኒግ ፖይንታቸው። ለዚህም ነበር የሞገትኳቸው። ግርባው ብአዴን በሙሉ መንፈሱ ተነክሮበት ስለነበር። ትግሉ ድርጅቱን የማዳን እንጂ በትምህርት ላይ የተፈፀመ የማሳቀቅ ጆኖሳይድ አድርጎ በፍጹም አልተመለከተውም ነበር ቲም ገዱ። 
 
ማግሥት የሚታሰብ ከሆነ በትውልዱ ላይ የሚደርሱ ሁለገብ ፈተናወች ላይ #የወል ጉዳያችን ሊሆን ይገባል። አገር ካለ ሰው አገርነት የለውም እና። ችግርን በተከታታይ ካልተሰራበት መፍትሄው ጋር መገናኜት አይቻልም። ተጽፎ እንኳን ሼር የሚያደርግ የሚያነብም የለም። ይህ ደግሞ ግድፈቱን ለሚፈጽመው ማንኛውም ኃይል ተጨማሪ አቅም ይመግበዋል። እንዲያውም እኔ ነኝ እምሳቀቀው። አበዛሁ ይሆን ብዬ። አንዳንድ ጊዜ ጥፍት እምለውም ለዚህ ነው። 
 
እኛ የወገኖቻችን ጉዳት ቸል ባልን ቁጥር፤ የተጎጂ ቤተሰቦች የበለጠ #ይጎዱብናል። አጽናኝ አልባ ሲሆኑ። የ7ዓመታት የገነገነ ችግር እፍ ተብሎ የሚራገፍ አይሆንም። በበዛ ትዕግሥት፤ በበዛ ብልህነት፤ በበዛ ትህትና፤ በበዛ ትጋት የትውልድ ተስፋ ቀጣይነት ላይ ጠንክሮ እና በርትቶ መሥራት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። በተለይ ቅንጣት ሹመት እና ሽልማት፤ ቅንጣት ሥልጣን እና መወድስ የማንፈልግ ሰብዕናወች ጥረታችን መቀጠል ይኖርብናል። #እስክንጠራ
 
አሁን ወ/ት አስምራ ሹምዬ ከቃለ ምልልስ በኋላ ነው ድብዛዋ የጠፋው። በዚህ አመክንዮ ብቻ የሰባዕዊ መብት ተቋማት ሊተጉ ይገባ ነበር። ግን አስተዋሽ አልተገኜም። አሁንም የእናት ብርቱካን እጣ ፈንታ ከዛ ጋር በቅርበት የተዋህደ ነው። አስምራ በምን ሁኔታ ትሆን? 17 የሚለው እራሱ ሊስተካከል ይገባል። 18 መባል ይኖርበታል የታገቱት። መተከልም የተገደሉት ተገድለው የተረፋት ተሰውረዋል። የእነሱም ሁኔታ አስታዋሽ የለውም። ትጋቱም #የወረት እና የራስን ተልዕኮ የማስፈፀሚያ ብቻ መሆኑም ሌላው አሳዛኝ ክስተት ነው። 
 
ከውስጥ ሆኖ ማዬት እና መመርመር ይገባል። የእኔ ጉዳይ ብሎም። በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ ያለ ማህበረሰብ #ተጋድሎውን ለሌላ ዓላማ ማዋል በሰማይም በምድርም ወንጀል ይሆናል። ይህን መገበር ለግል ዝና እና ለሌላ ተልዕኮ ማስፈጸሚያነት ማዋልም ወንጀሉን ከሚፈጽሙት፤ ከሚያስፈጽሙት በላይ #አረመኔያዊነትም ነው። 
 
ተከታታይነት ያለው ተግባር አድካሚ ቢሆንም መድፈር ያስፈልጋል። እኔን ታግሳችሁ ለምታነቡኝ ወገኖቼ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ጫና አብዝቼ ከሆነ ደግሞ ይቅርታ እጠይቃለሁኝ። ያው ጭንቀትን መጋራት ባህላችን በመሆኑም ጭምር ነው። በመኖራችን ውስጥ ብዙ ተነግረው የማያልቁ ፈተናወችን እያስተናገድንም ነው በዚህ የምንሳተፈው። 
 
የሆነ ሆኖ ቁጥር አንድ ተጠያቂው #ግርባው #ብአዴን ነው። ያን ገራገር ቅን እና ደግ ህዝብ ክብር፤ ግርማ ሞገስ ያስደፈረም፤ ፈተና ላይም የጣለ እራሱ የአማራ ክልል መስተዳድር ነው። #ኦሮማራ ለአማራ ህዝብ የተፈቀደለት #የቀራንዮ መከራ ነው። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
25/03/2025
ጊዜ #ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?