በጣም የሚገርመኝ

 በጣም የሚገርመኝ ልዕልት ዓለማችን #ጨካኞችን እና #ጭካኔን የምትሸከምበት #ደንደሷ ከብረት ቁርጥራጭ የተሠራ መሆኑ ነው። ዓለማችን ጨካኞችን እና ጭካኔን #ሃራም ብትል፦ ምድራችን የደስታ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊውን እና ገኃዱን ዓለም የሚያገናኘውን ሰማያዊ #ሐሴት የሰው ልጆች ሁሉ፤ የነፍስ ያላቸው ሁሉ የትርታቸው መተንፈሻ የመኖራቸው #እልልታ በሆነ ነበር። ለእኔ በደስታ እና በሐሴት መካከል ልዩነት አለ። ደስታ ጊዜያዊ፤ ሰው ሠራሽ እና #ምድራዊ#ሐሤት ግን #ሰማያዊ እና #ዝልቅ፦ መንፈሳዊውን እና ገኃዳዊ ዓለምን የሚያውህድ #የወርቅ #ድልድይ ነው። ብንታደል #ጨካኞች እና #ጭካኔ ቢመንኑልን። ቢወገዱልንም።
ሥርጉትሻ2025/03/23

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?