"ሳናውቅህ ስናውቅህ" ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድን በአማክንዮ ይሞግታል።
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎጌ በሰላም መጡልኝ።
"ሳናውቅህ ስናውቅህ "
„ፃድቅ ሲጣል
ዘሩም እህል ሲለምን አላዬሁም።“
(መዝሙረ ዳዊት
ምዕራፍ 36 ቁጥር 25።)
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
28.01.2020
" ሳናውቅህ ስናውቅህ " በጣም ከባድ አመክንዮ ነው። ስለ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ
ነው። አውቀናቸዋል የሚሉትም ቢሆኑ የሚያውቋቸው አይመስለኝም። በቻ በቅኔው ጎጃም ቅኔ እንዲህ ቅኔውን አሳምሮ ይዘረፈዋል። የቀረብኝ ዘመን ይቆጨኛል። ፌስ ቡክ ሳልሳተፍ። ትልቅ የትምህር ተቋም ነው። የመኖር ዩንቨርስቲ። ሥልጡን።
ዛሬ የርህርህና ተጋድሎ እለት ነበር። ሰው ሆነው ስለመፈጠራቸው የሚያውቁ ብፁዓን ዘሩን ለማጥፋት በተዘመተበት የአማራ ህዝብ ላይ የራሄል ዕንባን ያመሳጠሩ ህዝባዊ ሰልፎች በተለያዩ ከተሞች ተደርገዋል። ጠንከር ብሎም በቀጣይ ጊዜያቶች እንደሚቀጥሉ ተስፋዬ ፅኑ ነው።
ርህርህና በታገደበት የአብይዝም የመቃብር ሥፍራ ዘመን እንዲህ እርህርህናዊ ፀጋን ተጎናፅፈው፤ ሞትን ፈቅደው በጥዋቱ ለእዮር ያመለከቱ ወገኖቼን አመሰግናለሁ። ሰው ነኝ ማለት የሚገልፀው ተግባሩ ነውና። ብዙ መሳጭ ትምህርቶች ነበሩ። ብዙም ገሳጭ መምህር መልዕክቶችን
አንብቤያለሁ።
1. "ጉዳዩ ሌላ ነው። ዕውነቱን ህዝብ ያውቀዋል" ይላል የሰማዕት የአማራ ሊሂቃንን የዶር አንባቸው መኮነን እና የብጄ አሳምነው ፅጌን ፎቶ ጎን ለጎን ያደረገው ፖስተር። ይህ „የተሻለ ጊዜ መጥቷል ገዳዩ ብጄ አሳምነው ጽጌ ነው“ ለሚሉ የአብይዝም ካድሬዎች ዱላዊ መልዕክት ነው።
2. የጠሚር አብይ አህመድን ፎቶ በሁለት ተሰርቶ አንዱ በክብር ሌላው ተዘቅዝቆ ደግሞ „ሳናውቅህ ስናውቅህ " ይላል። ሰብዕናን የማንበብ፣ የመተርጎም፣ የማመሳጠር ልዕልና በልቅና። ሁላችንም ህሊናችን እንመረምር ዘንድ ይሞግታል።
3. አንዲት እህት የያዙት ፎቶ መሳጭ ነበር። " የመሪዎች ዝምታ ልጆቻቸው አውሮፓ ስለሚማሩ" ነው ይላል። ይህ የራሄልን እንባ ያመሳጥራል። ለዘመን ሊኳንዳ ቤት ክፈች ስለምተባለው የአማራ እናት መከራንም ያነባል።
4. "ሴትን አግቶ አሥመራ መዝናናት ዋጋ ያስከፍላል።" የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እና የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የዋንጫ ልዕልናም ታዳሚ በአርምሞ ቤተኛ ሆኗል። ከዚህ ላይ ሌላም ድንቅ ሚስጢር ወለል አድርጎ ይገልፃል። እፅፍበታለሁ።
5. " ነፃነታችን ከማንም አንጠብቅም " መረር ያለ መልዕክትም ዕለቱ አስተናግዷል።
6. በነብይ ብርጋዴር ጄኒራል አሳምነው ፅጌ ፎቶ " አንተ ብትኖር እኮ ከአርባ ጉጉ እስከ ደንቢደሎ አንሞትም ነበር" ይህ እንግዲህ የሻብያ፣ የኦነግ እና የህወኃት የሚስጢር ቁጥር ኮድ የከፈተ አንጎል አመክንዮዊ ነው። አንድ አባት በቆብ ያሰሩት ፖስተር ነው። ለዚህ ነው እኔ ጉዳዩ ከተረኝነት በላይ ነው የምለው።
7. ሌላው " ዬ54 ቀን ዝምታ ብልፅግና ወይንስ ብልግና?" ይህ የምርጫ ቦርድ ለብልጽግና የሰጠውን ዕውቅናውን ይመርምረው የሚል መልዕክት ይመስላል።
8. የኦነግ መንግሥት የተሞገተበት ቁልፍ አመክንዮ። "አማራን እያሳደዱ ወንጀለኞችን የሚሸከም መንግሥት አይወክለንም።" እኔ በግሌ መንግሥትም መሪም አለኝ አልልም።
ለኦነግ ተላልፎ የተሰጠው የትግል ዘመኔ እራሱ ያርመጠምጠኛል።
9. "እህቶቻችን የውሸት ትርክት ማወራረጃ አይሆኑም" የአቶ ተስፋዬን ገብረ እባብን ባይረስ የተሸከሙትን በሙሉ ከጠቅላይ ሚኒስተር አብይ ጀምሮ ያሉትን አፍቅሮተ አኖሌዎችን የገሰፀ የህዝብ ልዕልናዊ ድምጽ ነው።
10.
…" ጦር አዝምታ፣ መርታ፣ ድል ያደረገች፣ ሐገርን ነፃ ያወጣች የነገዋን የአማራ ወጣት ጣይቱን መልሱልን" ሊቅነት በጥበባዊ ጥሞና የተመሰጠረበት ብጡል አመክንዮ።
11.
"በአገራችን ታሪክ ውስጥ ተማሪዎችን የሚያግት፣ አሸባሪም ሆነ፣ ተማሪዎችን የሚያሳግት መሪ አላዬነም" በብልፅግና ሃኒ ሙን አሥመራ ለሚገኙት የኖቤል ተሸላሚ የህሊና መግሪያ።
12.
"በሴራ ፖለቲካ የታሰሩ ወንድሞቻችን በአስቸኳይ ይፈቱ" የቀውስ አደራጁን የኦነግ መንግሥት በአመክንዮ የሞገተ እድምታ።
13.
"የኦሮምያ ክልል እስከ መቼ የንፁኃንን ደም ይጠጣል? አባ ገዳዎች ሥራችሁ ምንድን ነው?" ሥራቸው እኔ እንደማስበው ዴሞግራፊን ማሳካት ነው። ሞጋሳን ማቀላጠፍ፤ ገብሮን በካቴና መጠርንፍ። የሆነ ሆኖ የኦሮሙማ ተልዕኮ ህዝባችን ገብቶታል። የተደማሪ አክቲቢስቶችንም መንፈስ ቀጥቷል መልዕክቱ።
14.
"የዩንቨርስቲ ሴት ተማሪዎች ሲታገዱ ግድ የማይሰጣቸው ሴት ሚኒስተሮች፣ እራሳቸውን እንጂ ሴቶችን አይወክሉም" ይህ መዶሻ „ጀግኒት“ በሚል መርኾ ሲያላግጡ የቆዩትን የአብይዝም የዕንባ ማህበርተኞች አንስቶችን በሙሉ ይመለከታል። ቀዳማይ እመቤት ዝናሽ ታያቸውንም።
15.
"ከህወሃት ሎሌነት ወደ ኦህዴድ ሎሌነት" ቃሬዛ ላይ ለሚገኘው ግርባው ኢህአዴግ የበታችነት ጊዜንውን ህዝብ ማወቁን ያውጃል። ካድሬዎችንም ይገስፃል። እንዲህ ሞቅ ሲል ብቅ ብለው አለን የሚሉትን አለዝዘኝ ዕብን
አክቲቢስቶችንም ይቀጣል። ሞት ላይ ቆመው የጫጉላ ጊዜ ላይ ይጨፍራሉና።
16.
"የህወሃት የበላይነት በኦነግ የበላይነት እንዲተካ አንፈልግም" ይህን ያደረገው ግርባው ብአዴን ለሌንጮወዲማ ጭፍጨፋ አሳልፎ የአማራን ህዝብ የሰጠበትን ይሁዳዊነት ተፈተሽ እያለውም ነው።
ተሳትፎው ዕድሜ፣ ፆታ፣ የዕውቀት ደረጃ ልዩነት አልነበረውም። ሰው መሆንን የተረጎሙ፣ ያመሳጠሩ፣ ሩህሩሃን ተሳትፈውበታል። ፍፁም ሰላማዊ እና ውስጥነትን የሰነቀ ነበር። ሁሎችንም ከክፉ ነገር ጠብቆ በሰላም ወደዬቤታቸው ፈጣሪ ይመልስ። አሜን።
በሰልፉ ላይ አዛውንት፣ ነገ የደረቀባቸው ወጣቶች፣ ማህፀናቸው ደም የሚያለቅስ እናቶች፣ እንባ የሚያዘንቡ አባቶች፣ ወጣት ተማሪዎች፣ የደብረ ብርሃን ሆስፒታል ሠራተኞች፣ ልጆች ሳይቀር ተሳትፈዋል። ሴቶች በብዛት ተገኝተዋል። ሰልፉን በመምራት እና በማስተባበር የጎላ
ድርሻቸውን ተወጥተዋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ ተውለብልቧል። መቅድመ ወልድያ በጥዋት ጀምረው በጊዜ ክሽን አድርገው ጉባኤያቸውን ከውነዋል። የተሳተፋት ወልድያ፣ ዳንግላ፣ ደብረማርቆስ፣ ሽዋሮቢት፣ ደብረብርሃን ወረታ፣ መራዊ፣ ዱርቤቴ፣ ወረታ፣ ቡሬ፣ ደጀን፣ ሰማዕቱ ባህርዳር፣ ደጀን፣ ፍኖተ ሰላም፣ ራያቆቦ፣ ፈረስ ቤት ደጋ ዳሞት፣ የቀሩ ካሉ ጨምሩበት
· ስጋቴ።
ስጋቴ ግን አሁን ሰለፉን ያሰተባበሩትን ወገኖች ቀን ተጠብቆ
ደግሞ ሳቢያ ተፈልጎ እንዳይለቀሙ ይጨንቀኛል። ኦነግ በባህሪው ቂመኛ ነው። በቀለኛ ነው። ብቻ ተኝቶ ከመሞት እዬተነፈሱ መሞት
የተገባ ስለሆነ የማግሥት የአማራ ህዝብ እጣ ፈንታ፤ ብቸኝነት፤ አይዞህ ባይ ማጣት ከጨለማ የገዘፈ ነው። አማራ ለጫጉላ ጊዜ
የሚሆን አቅም ስሌለው አቅሙን ቆጥቦ ማስተዳደር ይገባዋል።
አማራ ቅን ህዝብ ነው። ደግ ህዝብ ነው። እሩህርህ ህዝብ
ነው። እኛ ለእያንዳንዱ ታጋይ ሆነ ተቋም በነፍስ ወከፍ ደግፈናል፤ እራሳችን ማግድናል እኛን የሚማግድ ዘመን እንዲህ አይኑን
አፍጦ ሲመጣ ግን ሁሉም ዝምታን ይመርጣል።
ወጣሁ የሚለውም የአማራ ህዝብ ጥቃት ብሎ ለመናገር ልሳኑ ዝግ ነው። የታሰሩት የታገቱት የአማራ ልጆች ናቸው። የሚጨፈጨፉት
የአማራ ልጆች ናቸው። የሚንገላታው የአማራ መንፈስ ሥነ - ልቦና ነው። ግን እዬታዬ ነው „ሰው ነኝ“ የሚለው ሁሉ አድራሻው የለም።
ሌላው ብዙ ሰው ስለምን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝም አለ
የሚል አለ። በአህጉርም፤ በሉላዊ ክፍት የሥራ ቦታ የሚመደቡት እኮ የኦነግ ካድሬዎች ናቸው። ስለዚህ ጭካኔው ይፋ እንዳይወጣ ያዳፍኑታል። ለዚህ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድም ዋና መደበኛ
ሥራቸው ነው።
ይህን እያዬ የአማራ ጋዜጠኛ፤ የአማራ አክቲቢስት፤
የአማራ ጸሐፍት፤ የአማራ ሊሂቃን የለዬለት ተጋድሎ ከማድረግ ይልቅ ከኦነግ ሥር ተለጥፎ ሲልፈሰፈስ ይታያል። መጥኔ።
አማራነቴን እወደዋለሁ!
የፈተናው ብዛት ፅናቴን ያፀናዋል። ህሊናዬንም በርህርህና ያንፀዋል።
የፈተናው ብዛት ፅናቴን ያፀናዋል። ህሊናዬንም በርህርህና ያንፀዋል።
የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ቀን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ