በሴት የፖለቲካ ሊሂቃን የነበረው ተስፋዬ ወደ መቃብር እያሰኘው ነው።
እንኳን ደህና መጡልኝ
በሴት የፖለቲካ ሊሂቃን የነበረው ተስፋዬ ወደ
መቃብር እያሰኘው ነው።
„የሞቱ ዝንቦች የተቀመመውን የዘይት ሽቱ ያገሙታል፤
እንዲሁም
ትንሽ ስንፍና ክብርን ያጠፋል።“
መጽሐፈ
መክብብ ፲ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08.05.2019
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
እውን ይህ ጽናት በምን ሁኔታ ተጠለፈ?
ድምጽ አልባዋ የአማራ እናትም ልጇ
ከቁም ነገር ደርሶ ማዬት ህልሟ ነበር።
"ቃል የእምነት ዕዳ" መሆኑ አክትሞ
የዘመን መጫኛ ሆነ ለዛውም ለሚዛን?
የአማራ እናትም ኢትዮጵያዊት ናት!
የመከራ ማጫ!
· እፍታ።
ህም! የት መጠጊያ ማግኘት እንደሚቻል አይታወቅም። ውሉ የጠፋበት ዘመን እንደዚህ ገጥሞ አያውቅም።
በድምጽ ውስጤ እንዲህም ገልጨዋለሁኝ፡፤
የእናትነት መክሊት ግማዱ በአብይወለማ ሌጋሲ።
( ከሥርጉተ ሥላሴ 08.05.2019)
የኢትዮጵያ ሴቶች የበይ ተመልካች ሆነው የኖሩበት የጨለማ ዘመን ወደ ተሻለ ደረጃ መሸጋገሩን፤
የመንፈስ የበላይነት ለማቀዳጀት መታለሙን የመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ/ም የጠ/ሚር አብይ አህመድ የሹመት ንግግር ተስፋ ሰጪ ከሆንኩባቸው
መሳጭ አመክንዮ አንኳሩ ነበር። የኢትዮጵያ እናቶችም እንደገና የተወለድን ያህል ተሰማን ያሉበት የመጀመሪያ ጊዜም ነበር።
ከዚህ በመቀጠል ሁለት አንስቶች በፌድሬሽን እና በተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሹመት መከተልን
ስናይ ተስፋችን አፋፋው። የወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና የወ/ሮ ሙፍርያት ካሚል።
ሳይዘገይም የሴት ሚ/ራትን ቁጥር ከፍ ለማድረግ የመጀመሪያው የካቤኔ አደረጃጀት ተስፋ ቀለበ።
ከመስከረሙ የኢህዴግ ጉባኤ ማግስት ሁለተኛው አዲስ ካቢኔ ሲዋቀር
ደግሞ የካቢኔው ግማሹ አምሳ በመቶ 50% ሴቶች መሆናቸው፤ የጠ/ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ሴት መሆናቸው፤ የምርጫ ኮሚሽን ሰብሳቢ እና
አማካሪ ሴት መሆናቸው፤ የፕሬስ ሰክሬታርያት ሴት መሆን /ባይሰነብትም/ የመከለካያ ሚነስተሯ ለመጀመሪያ
ጊዜ ሴት መሆን /ባይዘልቅም/ የኢትዮጵያ
ፕሬዚዳንት ሴት መሆን ወሸኔ ማለፊያ ተብሎ የዓለም ሚዲያ መነጋገርያ ርእሰ ጉዳይ ሆነ።
እኔም ብዙ ነገር ሰርቸበታለሁኝ። ቀደመን በሴቶች ላይ ጤነኛ መንፈስ እናውቅ ስለነበር ያ ቀለም ይፈድሳል ብለን አለጠረጠርነም አብሶ እኔ። ለካስ አማራ ከሆነ በሴት/ በፆታዊ ጉዳይም የክት እና ዘወትር ፍልስፍና ያለው የልቅና ጥበብ ቀይ መስመር ነበረበት። ግን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ስንት ዓይነት ሰው ናቸው? ? ? ! ! ! እዮር ሆይ እባክህን ሚስጢሩን ግለጥልን?
በዚህ በያዝነው ዓመት የዓለም ዐቀፉ የሴቶች ቀን በእኛ ራዲዮን በራዲዮ ሎራም ሳይቀር አንድ አጀንዳ ሆኖ በድንቅነት ውይይት ተካሂዶበት ነበር።
ይህ መንፈስ ውስጡን ለማዬት፤ ውስጡን ለመጎርጎር ብዙም ሳንፈቅድ የመጀመሪያውን አውንታዊ ጉዳዮች
በቅንነት ተቀብለን አስተናገደን። እርግጥ ነው የጠ/ሚር አብይ አህመድ የምደባ መርህ ሦስት ነገሮች ላይ
ያተኮረ መሆኑን እኔ አሳምሬ ተረድቻለሁኝ።
ቢሆንም ግን ያን ጊዜ የሚነሱ አሉታዊ ሙግቶችን በተግባር ለመፈተሽ ጊዜ ሰጠሁት። ተደሞ
ያሻው ስለነበር። እንዲህ ዛሬ ዛሬ ሰባራ ቅል ሆኖ ማዋርዛትን
ሊያስነካው… / የኢንጂነር ወ/ሮ አይሻ መሃመድ ዲሞሽን በህሊናዬ በቂ ቦታ ያገኜ ነበር/
· የአብይወለማ ቀልብ።
የአብይወለማ ቀልብ የሚያርፈው
ከዞግ እና ከሰፈር ቅርርብ ጋር በጽኑ የተቆራኘ ሲሆን የቀድሞ ትውቅቅን ቅርበትን ከሰብዕና ግንባታው ጠቀሜታ አንጻር ሁኔታም አስልቶ
የሚከውን ስለመሆኑ ከውጥኑ እኔ አሳምሮ ይገባኛል።
ግን ቀድሜ እማስባቸው ጉዳዮች አሉታዊ ሳይሆን አዎንታዊ ስለሆነ በዛ ላይ ነበር
አቅሜን እማፈሰው። ቅን መሆን አይጎዳም። አዎንታዊ መሆንም ቢጠቅም እንጂ አያከስርም።
የሴቶች የፖለቲካ ሊሂቃን ወደ ፊት መምጣት እናትነትን ዕውቅና
መስጠት ብቻ ሳይሆን እናታዊነት ያለውን እምቅ አቅም ሁሉ ወደ ሥራ ሲተረጎም የብዙ ችግሮች መፍቻ ቁልፍ አድርጌ ነው እኔ በግሌ
እምመለከተው። አሁን የሚታዬው ደግሞ እናታዊነትም በርግጫ እና በፍጥጫ እዬተጠደፈ መሆኑን እያስታዋልኩ ነው።
አንዲት ሴት ወለደችም አልወለደችም፤ አገባችም አላገባችም፤ አግብታ ፈታችም የሃይማኖት አማኝ
ሆናችም አልሆነችም፤ ድንግል መነኩሴ ብትሆንም፤ ተማራችም አልተማራችም፤ ከተማ ኖረችም ገጠር እናትነት የሚሰጠው ገጸ በረከት ግን ስትፈጠር ከእዮር የተሰጣት፤ ማንም የማይቀማት እና የማይነጥቃት ልዩ መክሊቷ
ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት አሁን ይፋ እዬሆነ ያለው የካቢኔው አወቃቀር እና መንፈሱ በጥቅሉ ሲታይ
ፈንጅ ተቀብሮበታል። ያ ፈንጁ ደግሞ ከህወሃትም በከፋ ሁነታ ጸረ አማራ የሆነ ፖሊሲ አራማጅ
መሆኑን በጉልህ እያስተዋልነው።
ለውጡን ያመጠው ያ ማህበረሰብ ሆኖ ግን የበቀል ጽዋ በገፍ እንዲጨልጥ እዬተደረገ ያለውም ይህው ማህበረሰብ ስለመሆኑ
ተርጓሚ አያስፈልግም።
ግርባው ብአዴን እና የአማራ ሊሂቃን ያልገባቸው ፍሬ ነገር ይህ ነው። እጅግ መራራ እና ጎምዛዛ
አደገኛ ሁኔታ ላይ ያለው የአማራ ማህበረሰብ ነው። ሌሎች ማህበረሰቦች ዘግይተው ነው ፍዳውን የሚጋፈጡት። ጥግ ሲያጡ፤ አጋዥ
አይዟችሁ ባይ ሲሳባቸው ወይ ተንበርካኪ ሆነው ይዝለቃሉ ወይንም ደግሞ ተውጠው እንደሚሆን ይሆናሉ።
አሁን ዋናውን ግንድ ቅርንጫፎችን መላምሎ ግንዱን መገርሰስ ነው የአብይወለማ ቁልጭ ያለው ተልዕኮው።
ግንዱ ደግሞ አማራነት እና በዛ ውስጥ የዘለቀው ኢትዮጵያዊነት ነው። ተከታዩ አፋር ይሆናል ብዬ አስባለሁኝ። እርግጥ ነው ሌላ የማዳዳጫ
ቀመር ለሂደቱ አይጣፋም …
· እናትነት እና ግማዱ በዘመነ አብይወለማ።
ከሁሉ በላይ እናትነትን የአብይወለማ ሌጋሲ መፈናነፈኛ ነስቶ፤ ወጥሮ ይዞ እዬፈተነው ነው። ይህ
መቼም ስታስቡት እንደ መርግ የሚጫን ጉድ ነው። ውሃ ያዘለ ተራራ።
ለካስ ከድምጽ አልባዋ ኢትዮጵያዊ እናት አማራ በጥርስ ተይዛ ኗሯል።
እናት የሆኑ ሦስት ሊሂቃን አንዷ የፌድሬሽን አፈ ጉባኤ ናቸው። ሁለተኛዋ በፌድራል ደረጃ ያሉ የገቢዎች ሚ/ር ናቸው። ሦስተኛዋ ደግሞ ለጊዜው የፍትህ እናት የምንላቸው የፌድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ናቸው። ህሊና
ሲመረምር የጠ/ሚር አብይ አህመድ ሌጋሲ እናትነት ሳይቀር ለጸረ አማራ ፖሊሲ እያስገደደው እንደሆነ እያስተዋለነው።
የኢትዮጵያ የነበራት አንጡራ ጥሪቷ አናትነት ነው
ይህም
ተቀንቶበት ብክል እዬሆነ አረም እዬበቀለበት ነው። እናትን ሳይቀር ከአንድ ማህበረሰብ ከሆነ መንፈስን ለመግደል፤ ለማፍለስ፤ ለማሸማቀቅ፤
ተግቶ እዬተሰራበት ነው። ይህ ነገር በውነቱ የዓለም የሴቶች ድርጅቶች ሁሉ ከልባቸው ሆነው ሊከታተሉት የሚገባ ጉዳይ
ነው።
እኔ በወ/ሮ አዳነች አቤቤ ላይ እንዲህ የዘገጠ ነገር ይፈጸማል ብዬ አላስብም ነበር። በጣም
ተስፋ አድርጌባቸው የነበሩ ሴት ነበሩ። ሚ/ር ሲሆንም በጣም ደስ ብሎኝም ነበር። ነገር ግን እሳቸው አሁንም የአደማ ከተማ ከንቲባ ስለመሆናቸው እያሳዩን ነው። እኔ እንዴት እንቅልፍ
ወስዷቸው እንደሚያደር ሁሉ ሳስበው ይጨንቀኛል።
ሰላም ሲጠፋ እንደሚያሳስበን ፍትህ ሲዛባ እንደሚቆረቁረን ግብር ሲዛባም ሊያሳስብን ይገባል-ወ/ሮ አዳነች
February 3, 2019
የገቢ ሚ/ሯ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በሥልጣናቸው የሚያሳድዱት ማህበረሰብ„መብቴን እጠይቃለሁ ግዴታዬን
እውጣለሁም“ የሚለውን ለመጫን ግን በአማራ ክልል ነበር ሙሉ ወርድ ቀሚስ ለብሰው ተገኝተው ግዴታውን አሸክመውታል። ከሁሉም ክልሎች
የበለጠውን ቀረጥም የሚጫንበት ይህ ህዝብ ነው። በዳስ ልጆቹ የሚማሩ፤ ከጠመኔ አቅም እንኳን የማይሟላለትም ይኸው ክልል ነው።
ግዴታውን ይወጣል አማራ ግን በዬለም ፖሊሲ ተነድፎ ደግሞ ጸረ እሱነቱም ይመነጠራል። ከዚህ ጋር
በማዕካላዊ ጎንደር በያዝነው የ2011 ትምህርት ከ44 እስከ 55 ሺሕ የሚሆኑ ልጆች የትምህርት ዘመናቸው እንዲስተጓጎል ተደርጓል።
ልክ በዘመነ ኢህአፓ ጊዜ የእኛ በአንድ ዓመት እንደተጓተተው፤ ህወሃት ጎንደርን ሲይዝም የ12ኛ መልቀቂ ፈተና ችግር ገጥሞት እንደነበረው ዓይነት …
በዚህ በያዝነው ዓመት ለደረሰው ምስቅልቅል የአማራ ልጆች በዬዩንቨርስቲዎች የገጠማቸውን ፈተና
ጨምሮ ሌላ ሚኒስተር ሊሂቅ ተጠያቂ መሆናቸውም አይቀሬ ነው። የሰሞናቱ የጎበዝ ተማሪዎች የእስኮላርሽፕ በጠ/ሚር ግብዣ እና ዕውቅናም
ክልሉ መገለሉን አንድ ጹሑፍ አንብቤያለሁኝ።
ምን ዓይነት ጸላዬ ሰናይ እንደ ተከመበረበት ያ ቤተ መንግሥት ልብ እና ኩላሊት መርማሪው
አንድዬ ይፈታትሸው። ማዕቱን ከቻለውም ይቀጥልበት። ሌላ አቅም የለም ግን ጸሎት ብዙ ነገር ያደርጋል። ግፉም ልክም መጠንም ስለሌለው።
እናት መሆን ያልቻሉ የኢትዮጵያ ሴት ሊሂቃን በጉልህ የወጡትን ለዛሬው እነሆ …
· አንደኛ የፌድሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም።
ከራያ፣ አላማጣ እና ወልቃይት ጋር በተያያዘ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ማብራሪያ
Published on Oct 24,
2018
ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለምን ትከሰሳለች ? ሰፊ ትንተና (በአማራና በትግራይ ..)
Published on Jan 30,
2019
·
ሁለተኛ ወ/ሮ
ማእዛ አሸናፊ የፌድራሉ ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት
የዳኝነት ስርዓቱን እና የፍርድ ቤቶችን መዋቅር ለማሻሻል እየተሰራ ነው
Published on Apr 20,
2019
Shukshukta (ሹክሹክታ) - የመአዛ አሸናፊና የደመቀ መኮንን ፉክቻ | Meaza Ashenafi | Demeke Mekonnen | ADP
Published on May 7,
2019
· ሦስተኛ የ ገቢዎች ሚር ሚ/ር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ።
Ethiopia -የገቢዎች ሚኒስተር በአንድ ወገን ተይዟል- ክፍል 2
Published on Apr 5,
2019
asrat tv
· ቀሪ ሴት የፖለቲካ ሊሂቃን።
ሌሎቹ ምግባራቸው፤ ተግባራቸው እንዲህ በይፋ ሲወጣ ደግሞ የሚፈተሹ ይሆናሉ። ሲጠቃለል ለወ/ሮ
ማዕዛ አሸናፊ፤ ለወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፤ ለ/ወሮ አዳነች አቤቤ አንገታቸው ላይ አንድ የአላርም ቃጭል የሚያስፈልግ
ይመሰለኛል። የኢትዮጵያ
አብያዊ እናት እንጂ የዬክልላቸው ከንቲባ አለመሆናቸውን የሚያስታውሳቸው።
· ስውሩ ገማና።
ተሸፍነው በተመሰጠረው የለውጥ ሂደት ውስጥ ያለው እውነታዊ አመክንዮ አማራን በመንፈስም፤ በአካልም፤
በሥነ - ልቦናም ማፍለስ ነው። ይህን ልብ ያለው ሸብ አድርጎ ተጋድሎውን በጠነከረ፤ በጥበብ በተቃኜ ሁኔታ መቀጠል ይገባል።
ስለዚህ እናትነትን ሳይቀር እዬተፈታተነ የሚገኘው የአብይወለማ መንፈስ ቢያንስ እናትነት ጸጋችን ቢተውልን በትህትና አሳስበዋለሁኝ። በዬትም ሁኔታ የተመዱ አንስቶች እንደ ጸጋቸው ይሰሩ ዘንድ ባይጫናቸው መልካም ነው። በስተቀር ሴት የሚለው ቁጥር ብቻ ሆኖ ይቀራል።
እኔ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ጠ/ሚር እንደሚጡ ከምጓጓበት መሰረታዊ ጉዳይ በድፍረትም ለሴቶች
አናባቢ ቫዋላችን ናቸው ብዬ በ2017 የጻፍኩት ነገር ስንት አብይ
ጠ/ሚር እንዳለን አሁን ከሆነ እያስተዋልኩኝ ነው። ውስጤ ደግሞ ያዝናል።
እኔ የዛሬውን ቃል አባይ መንፈስ በዚህ መልክ ቀምሬው ነበር። „ጅሎቹ“
አብይ ለእኛም ለሴቶች አናባቢ። ክፍል ሦስት።
ጠ/ሚር አብይ አህመድን አውቃቸዋለሁኝ፤ አምናቸዋለሁኝ የሚሉትም የፖለቲካ ሊሂቃንም ቢሆኑ አለማዋቀቸውን ቢያውቁ ጥሩ ይመሰለኛል። እኛ ያወቅነው ትናጋን ብቻ እንጂ ህሊናን፤ መንፈሱን፤ ልቡን፤ ኩላሊቱን አልነበረም። አቅምም
የለንም። ሳናዋቃቸው ያወቁን መሪ ግን የመጀመሪያው እሳቸው ናቸው። ሳናውቃቸው አሳማረው ውስጣችን ማወቃቸው ደግሞ አሳምረው አሰለፈው ነድተውናል።
እዬራዊ ጸጋችን እናትነትን ለሰረዙ አንስት ሁሉ ይቅርታ የለውም!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ