ወንዝ፤ ገባሪ ወንዝ፤
የገባሪ ገባሪ ወንዝ፤
የገባሪ ገባሪ ገባሪ ወንዝ።
„የጠቢብ
ሰው የአፉ ቃል ሞገስ ናት።
የሰነፍ
ከንፈሮች ግን ራሱን ይውጡታል።“
መጽሐፈ
መክብብ ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፲፪
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09.05.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።
አልኳችሁ
ዛሬ ቪንቲ በስጭት ብላ፤ ወጅብ ስትለቅብን ነበር የዋለችው።
እናላችሁ እኔ እህታችሁ፤ ምኔ ሞኝ?! ዋናውን ሰቅሰቅ
ጠበቅ አድርጌ ከርችሜ ቁጭ።
ግን እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁን አዱኛዎቼ።
እናንተን አያሳጣኝ ፈጣሪዬ። አሜን!
ቄንጠኛውን ወግ በድምጥ ከፈለጋችሁ ቅኖቹ ...
አንድ
አገር አንድ መንግሥት
ያስፈልገዋል። ያ መንግሥት ግን የውጭጭ ያልሆነ፤ የእጣ እጣ ያልሆነ፤ የአድርሽኝ ያልሆነ ወይንም የሽሙጥ ያልሆነ ወይንም
የደርሶ መልስ ያልሆነ ወይንም ባጣ ቆዬኝ
ያልሆነ፤ በራሱ ውስጥ የሰከነ።
የጸና፣ ለህግ ተገዢ፤ ሚዛናዊ እና ተጠያቂነትን የሚቀበል።
ዘመኑ
የዬሀገሩ መንግሥታት አብዛኙቹ የፖለቲካ ድርጅት አላቸው። በህሊና በሠለጠኑት በውድድር፤ በፉክክር፤ በፍቅር፤ በመቻቻል በምርጫ
ተወዳድሮ ያሸነፈ በትረ መንግሥቱን ይይዛል።
እንደኛ
ያልሆነ ማለት ነው። ያው በዚህ ስሌት ሲኬድ እኛ በዚህ ዘርፍ ደረጃችን እንቁላል
ነው። ፍላጎቱን እንጂ መሆኑን ስላልሰጠን። በቃ ማለት ብቻ፤ ማለት አሁንም ማለት፤ ትናንትም ማለት፤ ዛሬም ማለት፤ ነገም
ማለት፤ ተዚያ ወዲያም ማለት … የማለት ስንቅ፤ የማለት ጥሪት፤ በማለት ተባዝተን የተቀናነስን።
የእኛ ነገር መቼም
ሲሂዱ ማደር ነው። የፖለቲካ ድርጅቱም መንግሥቱም በአንድ ወንዝ ነው። ያው ዝንቅቅን ስለሆነ በዛው ልለስነው ጉዳዬን።
ዛሬ ይህንም
ያጣን ይመስለኛል። አገር እሆናለሁ የሚለውን መንፈስን ራዕይ አሽኮኮ አድርጎ ለውሳኔም፤ ለቁርጥም ሳይበቃ የወለሌ ገበታ ላይ ይገኛል
የተስፋ ፏፏቴው ዘመነኛው አሻጋሪ መንግሥታችን።
ፉክክር ላይ ማን
እኔን እረቶኝ፤ እጬጌ ነኝ እያለ ሲፎካክር የባጀው ቄቡም፤ አውራውም፤ ጊደሩም፤ ወይፈኑም፤ ቅጥቅጡም፤ ማንን አምኖ እንደሆነ አይታወቅም የመንፈስ ትጥቁን ፈቶ ለሽ
ብሎ እንቅልፉን ደልቶት እንደሚያስነካው የተጠለለበት የኢትዮጵያ አዬር ይወቅለት።
አዲስ ሃሳብ፤ አዲስ
ዕሳቤ፤ አዲስ ፈጠራ ብሎ ነገር የለም፤ ያው የኩሬ ውሃ። ግራጫ በግርጫ ተደባብሎ እንሆ ስቀቀን አጤ ሆነ። … መቼም አንድ
አካል ዕድሜውን ሁሉ ሲደራጅ፤ በለስ ቢቀናኝ አገርን አምራለሁኝ፤ አንድ ቀን የማሸነፍ ዕድሉን ባገኝ ብሎ የምኞትን ስንቅ ሰንቆ
ግን በመንፈስ ሳይሰናዳ የከራረመው ባለግርጫ ሁሉ አሁን ተያይዞ የወለሌ ገበታ ብቻ ሆነ። የሚያፈናጥጥ
ፍለጋ ሩጫ ብቻ … ድድድድድድድ፤ መሃከነ!
ገባሪ ወንዞች።
ገባሪ ወንዞች ከነመፈጠራቸው የተረሱ፤ የላችሁም የተባሉ፤ ግን በአጋፋሪነት ይባል፤
በአጃቢነት ከፖለቲካ እውቅና ውጪ ሲጠብቁ፤ ሲጠበቁ አንድሽ፤ ሁለትሽ፤ ሦስትሽ እያሉ ያልፋልን ሲቆጥሩ 27ኛው ላይ ደርሰው ሰሞኑን የግንባሩ
መግለጫ ላይ ሱማሌ ቀንቶት ተመልከተናል፤
ነገረ አቶ አህመድ
ሸዴ ግንባሩን በእጮኝነት ይሁን በጭን ረድነት አይታወቅም ጌጤ ተብለዋል። እንዳሉ እኮ አይቆጠሩም? ለምኑ ብለው 27 ዓመት ሙሉ በገባሪነት፤
የበይ ተመልካች ሆነው ሲከነዱ እንደባጁ አሁንም አንድዬው ይመልስው።
ረስቼው ቅልጥም የሆነ ቅጥልም ተሰጥቷቸዋል „አዳጊ
ክልሎች“ ተብለው። በሺሕ ዘመናት ውስጥ አልነበራችሁም፤ አልተፈጠራችሁም፤ አካል አምሳል
አልነበራችሁም፤ አሁን ነው በደደቢት ቆሌ እኛ በእጃችን ጠፍጥፈንም፤ አንቦልቡለንም አበጀናችሁ
ነው የአቤቱ ኦነግ እና የአቤቶ ህወሃት ሰነድ የሚላቸው። አፍ ባለው መቃብር ውስጥ ተከዝነው የኖሩ መከረኞች።
… አዬ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ፤ አቶ ሌንጮ ለታም ስንቱን ደባ በጆንያ፤ በቦንዳ፤ በጎታራ
ከዝነው ኦርኬሰተር መድበው ሲያወዛውዟቸው ባጁ?
የሚገርመው አሁንም
የቤተ መንግሥቱ መጠሐፍ ገላጭ አቶ ሌንጮ ለታ ናቸው … የቀራቸውን ሂሳብ እያወራረዱ፤ የተቀዳደችውን እየጣጠፉ፤
እያሾሩት ነው አሉ … አሻጋሪውን መንፈስ፤ ... ወፊቱ ነው የነገረችኝ … እሳቸውን አልባ ጉባኤ፤ ፓናል ዴስከሽን፤ ምህዳን፤ ምክክር፤ ውሳኔ
ቅዳሴ፤ ወረብ እና ማህሌት አላበደም የሚኒልክ ቤተ መንግሥት … ስለምን? ሰው ጠፍቶ፤ ሊቅም ተፈጥሞ …
የገባሪ ገባሪ ወንዞች።
አልኳችሁ እንዲያው ከምን እንደተፈጠሩ ግርም ይሉኛል። የገባሪ ገባሪ ወንዞች ነገር።
የሊቀ ሊቃውንት ብጡልነት አሻም በለው ትቢያ አሰኛቸው። በቀደመው
ዘመን ትንሽ ይሻላል ይባል ይሆን አይሁን ኬሚሴን ያላዬ እንበልና አሁን ያም ደረጃ ተቀንቶበት እዳሪ ተጥለዋል
አሉ። የቅርቦቹ፤ የጥጎቹ፤ ቤተኞቹ ሌሎች ሆነዋል አሉ … አሉ ነው ዘንድሮ … የድንገቴ ሱናሜ በላይ በላያችን …
ለነገሩ እኛም
እያዬን ነው፤ መቼስ አይን አያይም፤ ጆሮም አይሰማም አይባል … እሚገርመው በሬሳ ሃሳብ የኖረው ነፍስ አሁን ነፍስ ያላቸው
ዓራት ዓይናማ እንቡጦች ዘመናቸውም ነው እነሱ ብቅ ሲሉ ከእነሱ ጋር ፉክክር ደግሞ ይዘዋል። የሚገርም እኮ ነው። የረሱትን፤
ሲያሳጭዱት፤ ዘሩን አብረው ሲያስፈልሱት፤ አካሉን ሲወግሩት ለኖሩት ህዝብ እኛ እንበልጣለንም አለበት፤ ኧረ ራሳቸውን ችለው መቆም ቢችሉ በስንት ጣሙ፤ ያው አንሱስ አንድ ዕዳ አይደሉ፤ ሌላው ቀርቶ፤ ዛሬ እኮ
የህዝብ ማህበራዊ ንቃተ ህሊናው ነው አጀንዳ ቀራጭ የሆነው አነሱ ደግሞ አሮጌ ሪሞርኬ ምስጋን ይንሳው ….
ቀድሞውንም ከምንጣፉ
ጀምሮ ያው የመቀሌው ሥርዕዎ ንጉሥ በተነፈሰ፤ ባስነጠሰው ቁጥር ጭንቅ ነበር፤ የሰጣቸውን ብጥቅጣቂ ቀጣጥለው፤ ጣጥፈው ለጥ
ብለው ሲያደግድጉ 27 ዓመት ሙሉ ባጅተው አሁን ለይቶላቸው አደማ ላይ ጥፈት ቤታችን ከፍተን
አጀንዳችሁን ለማሳካት የትኛዋ ወፍ ቀድማን ብለዋል … አሉ ነው መቼስ የዘንድሮ የወግ ሱናሜ ... እኛም አይቅናችሁም አይሳካላችሁም ብለን ማህተማችን ገጭ! .. . ማን ጌታ ሲኖርብን፤ ስንት እብድ የዘራው አዝመራ ገመና ተሸክመው እኮ
ነው፤ የሰው ቤት ተደራቢ ለፈረቃኛ ረድ እንሆናልን የሚሉት … "ጉዲ ሰዲ" አሉ …
የገባሪ ገባሪ ገባሪ ወንዞች …
የገባሪ ገባሪ ገባሪ ወንዞች ያው የመቀሌው ሥርዕዎ መንግሥት በሚቆርጥላቸው ማህያ
ሳምሶናይታቸውን ተሸከመው፤ ኪሳቸውን ቡጢ አሳክለው አፈፍ አፈፍ ሲሉ የባጁ ሲሆኑ፤ አሁን ከሆነ ግን ጥግ የለሽ ኦፋዎች ሁነው ቀርተዋል … አሳዳጊ አልባ፤
ግን እንሱ የዋዛ!
ተተኪውንም በረድፍ አሰልፈው ተዲያስፖራ እስተ ጦቢያ ቀይ ምንጣፍ አዝርግተው፤ ኮለል ያለውን በትሃ ጠጅም አቀማጥለው፤ ሽንጡን
አሰናድተው ቤት ለአንግዳ ብለው እነሱ እግሬን አውጭኝ ብለው ሹልክ ሲሉ፤ እግረኛው ደግሞ ተተክቶ ሎንግ ሊብ! ሎንግ ሊብ!
እያለ ይገኛል … ባለተራው የሚኒሊክ ቤተ መንግሥት ቤተኛው።
ወንዙም፤ ገባሪውም፤
የገባሪ ገባሪውም፤ የገባሪ ገባሪ
ገባሪው ዘሃ እና ዝናን ሲያስማሙ አገር ልትፈነዳ ነው። ፍንድት ልትል። አቅጣጫ የጠፋው ህልውናዋም
ቃሬዛ ላይ ነው። አምዬዋ ልትፈነዳ ተሰናድታ ወንዙ ምን ቢያዝላት ጥሩ ነው ትላላችሁ ውዶቼ? ስጋት … ስጋ አላልኩም ስጋት … ነው እያዘዘላት ያለው? ሰጋቱ ለሷ፤ ለተመቸው ቅምጥል ደግሞ ድግሥ … በድግስ በሺ ነው … ግብረ ሰላም፤ በግብረ ሰላም፤ አይዋ ወለድ በዛ
ይዳንሳል፤ አይዋ ዘራፊ በዛ ይሞለቅቃል፤ አይዋ ድህነት ሚሊዮኑን በራህብ ሰቅዞ ዋይታ ያውጃል ግን ወንዙ ለሹ ብሎ ፈሰስስስስ ነጋ
ጠባ ግብር …. ነጋ ጠባ ድግስስስስስስስ … ፈሰስ አሉ ዘመንተኞች… ባለፈረቃ … ባለጨረቃ።
በዚህ ላይ ደግሞ
አዲስ አበባ ላይ መናፈሻ መዝናኛ አሰኝቷቸው እሱን ሲንቆለባብሱ ኢትዮጵያዊው ህልውና እብስ ልትል ነፍሱ ግቢ
ነፍስ ውጪ ነፍስ አፋፍ ላይ … ። ለመከራው
ማስተገሻ መዳህኒት እንኳን የለም አሉ።
ህም! እጬጌው ሰኔል በሰልፍ፤ አጤው ቹቻም በተርታ፤ አይዋ ድንጋይም በሽቅድድም በመደዴ
ተሰልፈው ይጠባበቃሉ አሉ፤ እኔ እቀድም እኔ እቀድም … ያው ወፊቱ ነው ሹክ ያለችኝ …
የሚገርመው በድለቂያው
ብዛት የህልውና ህመሙ ከህመም አልተቆጠረም፤ ለነገሩ መዳህኒት ቢታዘዝለትስ ዶላሩ ሰማይ ደጅ ሆኖ የለ? መደህኒት የሰማዩ ነውና
እሱ አንድዬ የኢትዮጵያን ህልውና አዲስ ኦርጅናል ነፍስ ከዋናው ከእዮር
ከሚጨበጥ ከሚዳሰስ እውናዊ ተስፋ ጋር ይላክለት … አሜን በሉ! ይደረግላት በሉ! ይሰካላት በሉ …
„በሰነፎች መካካል ከሚጮኽ ከገዢዎችው
ጮኽት
ይልቅ የጠቢባን ቃል በጸጥታ ትሰማለች።“
መጽሐፈ መክብብ ፱ ቁጥር ፲፯
ተስንብት በፊት ሌላም እንጎቻ አለች ...
የሽብር ቀን ለማኝ (ልብ ወለድ)
ክብረቶቼ አብረን
በመንፈስ ቅንነት ስለቆዬን ተባረኩልኝ።
ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ